ዘፀአት 39 – NASV & TNCV

New Amharic Standard Version

ዘፀአት 39:1-43

የካህናት አልባሳት

1ለመቅደሱ አገልግሎት ከሰማያዊ፣ ከሐምራዊና ከቀይ ማግ የተፈተሉ ልብሶችን ሠሩ፤ እንዲሁም እግዚአብሔር (ያህዌ) ሙሴን እንዳዘዘው ለአሮን የተቀደሱ ልብሶችን ሠሩ።

ኤፉድ

39፥2-7 ተጓ ምብ – ዘፀ 28፥6-14

2ኤፉዱን ከወርቅ፣ ከሰማያዊ፣ ከሐምራዊና ከቀይ ማግ፣ በቀጭኑ ከተፈተለ ሐር ሠሩት39፥2 በዚህ እንዲሁም በቍጥር 7፡8 እና 22 ላይ፣ ሥራ3ጥበበኛ ባለሙያ እንደሚሠራው በሰማያዊ፣ በሐምራዊ፣ በቀይ ማግና በቀጭን በፍታ ይሠራ ዘንድ ወርቁን በስሱ ቀጥቅጠው እንደ ክር ቈራረጡት። 4ለኤፉዱ ከሁለቱ ጐኖቹ ጋር ተያይዘው ያሉትን የትከሻ ንጣዮችን ሠሩ፤ ይኸውም ማያያዝ እንዲቻል ነው። 5በጥበብ የተፈተለው መታጠቂያ በተመሳሳይ መልክ ሆኖ እግዚአብሔር (ያህዌ) ሙሴን እንዳዘዘው፣ ከኤፉዱ ጋር አንድ ወጥ የሆነና ከወርቅ፣ ከሰማያዊ፣ ከሐምራዊና ከቀይ ማግ፣ በቀጭኑ ከተፈተለ ሐር የተሠራ ነበረ።

6የከበሩ መረግዶችን በወርቅ ፈርጦች በመክፈፍ፣ እንደ ማኅተም የእስራኤልን ልጆች ስሞች ቀረጹባቸው። 7ከዚያም እግዚአብሔር (ያህዌ) ሙሴን እንዳዘዘው በኤፉዱ የትከሻ ንጣዮች ላይ ለእስራኤል ልጆች እንደ መታሰቢያ ድንጋዮች አያያዟቸው።

የደረት ኪስ

39፥8-21 ተጓ ምብ – ዘፀ 28፥15-28

8የደረት ኪሱንም ጥበበኛ ባለሙያ እንደሚሠራው ሥራ በተመሳሳይ መንገድ ሠሩት፤ እንደ ኤፉዱም ከወርቅ፣ ከሰማያዊ፣ ከሐምራዊና ከቀይ ማግ በቀጭኑም ከተፈተለ በፍታ ሠሩት። 9ርዝመቱ አንድ ስንዝር ወርዱም አንድ ስንዝር39፥9 ወደ 22 ሳንቲ ሜትር ያህል ነው። ሲሆን፣ ጥንድ ድርብ ሆኖ ባለ አራት ማእዘን ነበረ። 10ከዚያም የከበሩ ድንጋዮችን በአራት ረድፍ በላዩ ላይ አደረጉበት፤ በመጀመሪያው ረድፍ ሰርድዮን፣ ቶጳዝዮንና የሚያብረቀርቅ ዕንነበር፤ 11በሁለተኛውም ረድፍ በሉር፣ ሰንፔርና39፥11 ወይም ላፒስ ላዙሊ አልማዝ፣ 12በሦስተኛውም ረድፍ ያክንት፣ ኬልቄዶንና አሜቴስጢኖስ፣ 13በአራተኛውም ረድፍ ቢረሌ፣ መረግድና ኢያስጲድ39፥13 ከእነዚህ የከበሩ ማዕድኖች መካከል አንዳንዶቹ ማንነታቸው አይታወቅም። ነበረ፤ በወርቅ ፈርጥ ላይ ተደርገው ነበር። 14ለእያንዳንዱ የእስራኤል ልጆች ስም አንዳንድ ሆኖ፣ በእያንዳንዱ ላይ እንደ ማኅተም ከዐሥራ ሁለቱ ነገዶች የአንዱ ስም የተቀረጸበት ዐሥራ ሁለት ድንጋዮች ነበሩ።

15ለደረት ኪሱም ልክ እንደ ገመድ ከንጹሕ ወርቅ የተጐነጐኑ ድሪዎችን አበጁለት። 16ሁለት የወርቅ ፈርጦችንና ሁለት የወርቅ ቀለበቶችን ሠርተው ቀለበቶቹን ከደረት ኪሱ ሁለት ጐኖች ጋር አያያዟቸው። 17ሁለቱን የወርቅ ድሪዎች በደረት ኪሱ ጐንና ጐን ካሉት ቀለበቶች ጋር አያያዟቸው፤ 18የድሪዎቹን ሌሎች ጫፎች ከፊት ካለው ከኤፉዱ የትከሻ ንጣዮች ጋር በማገናኘት ከሁለቱ የወርቅ ፈርጦች ጋር አያያዟቸው። 19ሁለት የወርቅ ቀለበቶችን ሠርተው ከኤፉዱ ቀጥሎ ካሉት ከሌሎቹ ሁለት የደረት ኪስ ጐኖች ጋር ከውስጠኛው ጠርዝ ላይ አያያዟቸው። 20ከዚያም ሁለት ተጨማሪ የወርቅ ቀለበቶችን ሠርተው ልክ ከኤፉዱ መታጠቂያ በላይ፣ ከመጋጠሚያው አጠገብ፣ ከኤፉዱ ፊት ለፊት ካሉት ከትከሻ ንጣዮች ጋር አያያዟቸው። 21እግዚአብሔር (ያህዌ) ሙሴን እንዳዘዘው የደረት ኪሱ ከኤፉዱ ተነጥሎ ለብቻው እንዳይንጠለጠል የደረት ኪሱን ቀለበቶች ከመታጠቂያው ጋር በማገናኘት፣ ከኤፉዱ ቀለበቶች ጋር በሰማያዊ ፈትል አሰሯቸው።

ሌሎች የካህናት አልባሳት

39፥22-31 ተጓ ምብ – ዘፀ 28፥31-43

22የኤፉዱን ቀሚስ በሸማኔ ሥራ ሙሉ በሙሉ ከሰማያዊ ጨርቅ ሠሩት፤ 23ይህም እንደ ክሳዱ ቅድ ከቀሚሱ መካከል ላይ ዐንገትጌ39፥23 በዕብራይስጡ የዚህ ቃል ትርጕም በትክክል አይታወቅም። ነበረው፤ እንዳይተረተርም በዐንገትጌው ዙሪያ ላይ ቅምቅማት ነበረው። 24በቀሚሱ ጠርዝ ዙሪያ ከሰማያዊ፣ ከሐምራዊና ከቀይ ማግ እንዲሁም በቀጭኑ ከተፈተለ በፍታ ላይ ሮማኖቹን አደረጉ። 25ከንጹሕ ወርቅም ሻኵራዎችን ሠሩ፤ እነዚህንም በሮማኖቹ መካከል በጠርዙ ዙሪያ አደረጉ። 26እግዚአብሔር (ያህዌ) ሙሴን እንዳዘዘው ለአገልግሎት ይለበሱ ዘንድ ሻኵራዎቹና ሮማኖቹ በቀሚሱ ጠርዝ ዙሪያ ላይ ተሰባጥረው ይገኙ ነበር።

27ለአሮንና ለወንዶች ልጆቹ የሸማኔ ሥራ የሆነውን ከቀጭን በፍታ ሸሚዞችን ሠሩ፤ 28እንዲሁም ከቀጭን በፍታ ጥምጥምን፣ የሐር ቆቦቹንና በቀጭኑ ከተፈተለም በፍታ ሱሪዎችን ሠሩ። 29መታጠቂያው እግዚአብሔር (ያህዌ) ሙሴን እንዳዘዘው በቀጭኑ ከተፈተለ በፍታና ከሰማያዊ፣ ከሐምራዊና ከቀይ ማግ፣ የጥልፍ ጠላፊ ሥራ ሆኖ የተሠራ ነበረ።

30ከንጹሕ ወርቅ የተቀደሰውን አክሊል ሰሌዳ ሠርተው፣ በማኅተም ላይ እንደ ተቀረጸ ጽሑፍ፣

“ቅዱስ ለእግዚአብሔር (ያህዌ)

የሚል ቀረጹበት፤ 31ከዚያም እግዚአብሔር (ያህዌ) ሙሴን እንዳዘዘው ከመጠምጠሚያው ጋር ለማያያዝ ሰማያዊ ፈትል አሰሩበት።

ሙሴ የማደሪያውን ድንኳን መቈጣጠሩ

39፥32-41 ተጓ ምብ – ዘፀ 35፥10-19

32በዚህ መሠረት የማደሪያው ድንኳን፣ የመገናኛው ድንኳን ሥራ በሙሉ ተጠናቀቀ። እስራኤላውያን ልክ እግዚአብሔር (ያህዌ) ሙሴን እንዳዘዘው ሁሉን ነገር ሠሩ። 33ከዚያም የማደሪያውን ድንኳን ወደ ሙሴ አመጡት፤

እነዚህም ድንኳንና ዕቃዎቹ ሁሉ፣ ማያያዣዎቹ፣ ክፈፎቹ፣ አግዳሚዎቹ፣ ምሰሶዎቹና መቆሚያዎቹ፤

34ቀይ ከተነከረ የአውራ በግ ቈዳ የተሠራ መደረቢያ፣ የለፋ የአቆስጣ ቈዳ39፥34 ይህ የባሕር አውሬ ነው። መደረቢያና መከለያ መጋረጃ፤

35የምስክሩ ታቦት፣ ከመሎጊያዎቹና ከስርየት መክደኛው ጋር፤

36ጠረጴዛው ከዕቃዎቹ ሁሉና ከገጸ ኅብስቱ ጋር፤

37ከንጹሕ ወርቅ የሆነው መቅረዝ ከተደረደሩት መብራቶችና ከዕቃዎቹ ሁሉ ጋር፣ የመብራቱም ዘይት፤

38የወርቅ መሠዊያው፣ ቅብዐ ዘይቱ፣ መልካም መዐዛ ያለው ዕጣን እንዲሁም የድንኳኑ መግቢያ መጋረጃ፤

39የናስ መሠዊያው ከናስ መጫሪያው፣ መሎጊያዎቹና ዕቃዎቹ ሁሉ ጋር፤

የመታጠቢያው ሳሕን ከነማስቀመጫው፤

40የአደባባዩ መጋረጃዎች ከምሰሶዎቹና ከመቆሚያዎቹ ጋር፣ የአደባባዩ መግቢያ መጋረጃ፤

ገመዶቹና የአደባባዩ ድንኳን ካስማዎች፤

የማደሪያው የመገናኛው ድንኳን ዕቃዎች ሁሉ፤

41በመቅደሱ ሲያገለግሉ የሚለበሱት የተፈተሉት ቀሚሶች፣ ለካህኑ ለአሮን የተቀደሱት ቀሚሶችና ወንዶች ልጆቹ ካህናት ሆነው ሲያገለግሉ የሚያደርጓቸው ቀሚሶች ናቸው።

42እስራኤላውያን ልክ እግዚአብሔር (ያህዌ) ሙሴን እንዳዘዘው ሥራውን ሁሉ አከናወኑ። 43ሙሴ ሥራውን አየ፤ ልክ እግዚአብሔር (ያህዌ) እንዳዘዘው መሥራታቸውንም ተመለከተ፤ ስለዚህ ባረካቸው።

Thai New Contemporary Bible

อพยพ 39:1-43

เครื่องแต่งกายปุโรหิต

1เขาใช้ด้ายสีน้ำเงิน ม่วง และแดงทอเครื่องแต่งกายเพื่อปฏิบัติหน้าที่ในสถานนมัสการและเครื่องแต่งกายบริสุทธิ์สำหรับอาโรนตามที่องค์พระผู้เป็นเจ้าทรงบัญชาโมเสส

เอโฟด

(อพย.28:6-14)

2พวกเขา39:2 หรือเขาเช่นเดียวกับข้อ 7,8 และ 22ทำเอโฟดโดยใช้ทองคำ ด้ายสีน้ำเงิน ม่วง และแดง และผ้าลินินเนื้อดี 3พวกเขาเอาทองมาตีแผ่จนบาง ตัดเป็นเส้นๆ เพื่อจะทอเข้าไปกับผ้าลินินเนื้อดี ด้ายสีน้ำเงิน ม่วง และแดง นี่เป็นผลงานของช่างฝีมือผู้ชำนาญ 4พวกเขาทำแถบสองชิ้นที่บ่าสำหรับเอโฟดไว้โยงมุมสำหรับผูกเข้าด้วยกัน 5ทำสายคาดเอวอย่างประณีตด้วยทองคำ ด้ายสีน้ำเงิน ม่วง และแดง และผ้าลินินเนื้อดีทอเข้าเป็นชิ้นเดียวกับเอโฟดตามที่องค์พระผู้เป็นเจ้าทรงบัญชาโมเสส

6พวกเขานำโกเมนสองชิ้นฝังบนเรือนทองและสลักชื่อบุตรชายทั้งหลายของอิสราเอลเหมือนกรรมวิธีสลักแหวนตรา 7แล้วพวกเขาติดเข้ากับแถบบ่าของเอโฟด เป็นหินอนุสรณ์ถึงประชากรอิสราเอลตามที่องค์พระผู้เป็นเจ้าทรงบัญชาโมเสส

ทับทรวง

(อพย.28:15-28)

8พวกเขาทำทับทรวงโดยช่างฝีมือผู้ชำนาญโดยใช้ทองคำ ด้ายสีน้ำเงิน ม่วง และแดง และผ้าลินินเนื้อดีเหมือนกับที่ใช้ทำเอโฟด 9เป็นผืนสี่เหลี่ยมจัตุรัสขนาดกว้างยาวด้านละหนึ่งคืบ39:9 คือ กว้างยาวด้านละประมาณ 22 เซนติเมตร พับเป็นสองทบ 10แล้วพวกเขาฝังอัญมณีสี่แถวเข้ากับทับทรวง แถวแรกได้แก่ ทับทิม บุษราคัม และนิล 11แถวที่สองได้แก่ พลอยขี้นกการเวก ไพฑูรย์ และมรกต 12แถวที่สามได้แก่ พลอยสีม่วง โมรา และเพทายม่วง 13แถวที่สี่ได้แก่ เพทาย โกเมน และมณีโชติ ทั้งหมดนี้ฝังไว้บนเรือนทอง 14อัญมณีสิบสองเม็ดนี้แต่ละเม็ดสลักชื่อบุตรชายแต่ละคนของอิสราเอลแทนทั้งสิบสองเผ่าเหมือนสลักตรา

15พวกเขายังได้ทำสร้อยเกลียวทองคำบริสุทธิ์ลักษณะคล้ายเชือกสำหรับทับทรวง 16และทำเรือนทองสองเรือนกับห่วงทองคำสองห่วง ติดห่วงทองคำทั้งสองเข้ากับมุมทั้งสองของทับทรวง 17เขาคล้องสร้อยเกลียวทองสองสายเข้ากับห่วงที่มุมทับทรวง 18และติดปลายอีกด้านของสร้อยเกลียวเข้ากับเรือนทองทั้งสอง แล้วติดเข้ากับแถบบ่าทั้งสองของเอโฟดตรงด้านหน้า 19เขาทำห่วงทองคำสองห่วงติดกับอีกสองมุมของทับทรวงตรงขอบด้านในชิดกับเอโฟด 20และทำห่วงทองคำอีกสองห่วงติดที่ปลายล่างของแถบบ่าตรงด้านหน้าของเอโฟด ชิดกับตะเข็บเหนือสายคาดเอวของเอโฟด 21เขาผูกห่วงของทับทรวงเข้ากับห่วงของเอโฟดโดยใช้ด้ายถักสีน้ำเงินติดเข้ากับสายคาดเอว เพื่อไม่ให้ทับทรวงเลื่อนหลุดจากเอโฟด ตามที่องค์พระผู้เป็นเจ้าทรงบัญชาโมเสส

เครื่องแต่งกายของปุโรหิตชิ้นอื่นๆ

(อพย.28:31-43)

22พวกเขาทอเสื้อคลุมเข้าชุดกับเอโฟดด้วยผ้าสีน้ำเงินทั้งตัว 23มีช่องตรงกลางเป็นคอเสื้อ39:23 ในภาษาฮีบรูคำนี้มีความหมายไม่ชัดเจนสำหรับสวมหัว มีแถบทอขลิบริมเพื่อไม่ให้ขาดลุ่ย 24แล้วทำผลทับทิมด้วยด้ายสีน้ำเงิน ม่วง และแดง และผ้าลินินเนื้อดีไว้รอบชายเสื้อคลุม 25และเขาทำลูกพรวนทองคำบริสุทธิ์ติดสลับกับผลทับทิมรอบชายเสื้อคลุม 26เสื้อคลุมที่ชายล่างติดผลทับทิมสลับลูกพรวนนี้ สำหรับอาโรนใช้สวมเวลาปฏิบัติหน้าที่ ตามที่องค์พระผู้เป็นเจ้าทรงบัญชาโมเสส

27เขาทอเสื้อตัวในด้วยผ้าลินินเนื้อดีสำหรับอาโรนและบรรดาบุตรชาย 28แถบคาดหน้าผาก ผ้าโพกศีรษะ และเครื่องแต่งกายชั้นใน ล้วนทำจากผ้าลินินเนื้อดีแบบเดียวกันนี้ 29สายคาดเอวทำด้วยผ้าลินินเนื้อดี ปักอย่างวิจิตรโดยใช้ด้ายสีน้ำเงิน ม่วง และแดงตามที่องค์พระผู้เป็นเจ้าทรงบัญชาโมเสส

30เขาทำแผ่นทองคำบริสุทธิ์สำหรับคาดหน้าผากสลักข้อความเหมือนสลักตราว่า “บริสุทธิ์แด่องค์พระผู้เป็นเจ้า” 31แล้วเขาใช้ด้ายสีน้ำเงินผูกแผ่นทองคำนี้ติดกับผ้าโพกศีรษะ ตามที่องค์พระผู้เป็นเจ้าทรงบัญชาโมเสส

โมเสสตรวจงานพลับพลา

(อพย.35:10-19)

32ดังนั้นงานทุกชิ้นสำหรับการสร้างพลับพลาหรือเต็นท์นัดพบก็สำเร็จสมบูรณ์ ชนอิสราเอลได้ทำทุกสิ่งตามที่องค์พระผู้เป็นเจ้าทรงบัญชาโมเสสไว้ทุกประการ 33พวกเขานำส่วนประกอบทั้งหมดมามอบแก่โมเสสดังนี้คือ พลับพลา อุปกรณ์ประกอบทุกอย่าง ตะขอ ไม้ฝาพลับพลา คานขวาง เสา ฐานรองรับ 34เครื่องคลุมพลับพลาที่ทำจากหนังแกะตัวผู้ย้อมสีแดงและที่ทำจากหนังพะยูน ม่านกั้นทางเข้า 35หีบพันธสัญญาพร้อมคานหาม และพระที่นั่งกรุณา 36โต๊ะพร้อมภาชนะทุกอย่างและขนมปังเบื้องพระพักตร์ 37คันประทีปทองคำบริสุทธิ์พร้อมตะเกียง เครื่องใช้ประกอบทุกอย่าง และน้ำมันสำหรับจุดประทีป 38แท่นทองคำ น้ำมันเจิม เครื่องหอม ม่านกั้นทางเข้าเต็นท์ 39แท่นทองสัมฤทธิ์พร้อมตะแกรงทองสัมฤทธิ์ และคานหาม และเครื่องใช้ทุกอย่าง อ่างชำระพร้อมฐานรอง 40ม่านกั้นลานพลับพลาพร้อมเสาและฐานรองรับ และม่านกั้นทางเข้าลานพลับพลา เชือก และหลักหมุด สำหรับลานพลับพลา เครื่องตบแต่งทั้งหมด สำหรับพลับพลาหรือเต็นท์นัดพบ 41ทั้งเครื่องแต่งกายบริสุทธิ์ที่ทอขึ้นสวมใส่เมื่อรับใช้ในสถานนมัสการสำหรับปุโรหิตอาโรนและบรรดาบุตรชายสวมขณะปฏิบัติหน้าที่ปุโรหิต

42ชนอิสราเอลทั้งปวงปฏิบัติตามทุกสิ่งที่องค์พระผู้เป็นเจ้าทรงบัญชาโมเสส 43โมเสสตรวจตราผลงานทั้งหมดและกล่าวอวยพรพวกเขา เพราะทุกสิ่งเรียบร้อยตามพระบัญชาขององค์พระผู้เป็นเจ้า