ሮሜ 3 – NASV & CCBT

New Amharic Standard Version

ሮሜ 3:1-31

የእግዚአብሔር ታማኝነት

1ታዲያ አይሁዳዊ መሆን ጥቅሙ ምንድን ነው? መገረዝስ ምን ፋይዳ አለው? 2በየትኛውም መንገድ ጥቅሙ ብዙ ነው፤ ከሁሉ አስቀድሞ የእግዚአብሔር ቃል በዐደራ የተሰጠው ለእነርሱ ነው።

3አንዳንዶች እምነት ባይኖራቸውስ? የእነርሱ አለማመን የእግዚአብሔርን ታማኝነት ዋጋ ያሳጣዋልን? 4ፈጽሞ አይሆንም! ሰው ሁሉ ሐሰተኛ፣ እግዚአብሔር ግን እውነተኛ ይሁን፤ እንዲህ ተብሎ ተጽፏልና፤

“ከቃልህ የተነሣ እውነተኛ፣

በፍርድም ፊት ረቺ ትሆናለህ።”

5የእኛ ዐመፃ የእግዚአብሔርን ጽድቅ አጕልቶ የሚያሳይ ከሆነ፣ ምን ማለት እንችላለን? እንደ ሰው ለመከራከር ያህል እግዚአብሔር በእኛ ላይ ቍጣውን ማምጣቱ ትክክል አይደለም ሊባል ነውን? እንደ ሰው ሲታሰብ ማለቴ ነው። 6በርግጥ እንዲህ ሊሆን አይችልም፤ እንዲህ ቢሆንማ ኖሮ እግዚአብሔር በዓለም ላይ እንዴት ሊፈርድ ይችላል? 7“የእኔ ውሸተኛ መሆን የእግዚአብሔርን እውነተኛነት የሚያጐላ፣ ክብሩንም የሚጨምርለት ከሆነ፣ ኀጢአተኛ ተብዬ እስካሁን እንዴት ይፈረድብኛል?” በማለት ሊከራከር የሚችል ሰው ይኖር ይሆናል። 8ይህማ “በጎ እንዲመጣ ክፉ እንሥራ” ይላሉ በማለት አንዳንዶች እንደሚያስወሩብን ነው፤ በእነዚህ ሰዎች ላይ የሚደርሰው ፍርድ ትክክለኛ ነው።

ማንም ጻድቅ አይደለም

9እንግዲህ ምን እንላለን? እኛ ከእነርሱ እንበልጣለንን?3፥9 ወይም እንብሳለንን ከቶ አይደለም፤ አይሁድም ሆኑ አሕዛብ፣ ሁሉም ከኀጢአት በታች እንደ ሆኑ አስቀድመን ከስሰናቸዋል።

10እንዲህ ተብሎ እንደ ተጻፈ፤

“ጻድቅ ማንም የለም፤ አንድም እንኳ፤

11አስተዋይ የለም፤

እግዚአብሔርንም የሚሻ አንድም የለም።

12ሁሉም ተሳስተዋል፤

በአንድነት የማይጠቅሙ ሆነዋል፤

በጎ የሚያደርግ ማንም የለም፤

አንድም እንኳ።”

13“ጕረሯቸው የተከፈተ መቃብር ነው፤

አንደበታቸው ሽንገላን ያዘወትራል።”

“በከንፈሮቻቸው የእባብ መርዝ አለ።”

14“አፋቸው ርግማንና ምሬት ሞልቶበታል።”

15“እግራቸው ደም ለማፍሰስ ፈጣን ነው፤

16በመንገዳቸው ጥፋትና ጕስቍልና ይገኛል፤

17የሰላምንም መንገድ አያውቁም።”

18“በዐይናቸው ፊት የእግዚአብሔር ፍርሀት የለም።”

19እንግዲህ አፍ ሁሉ እንዲዘጋና ዓለም በሙሉ ለእግዚአብሔር መልስ እንዲሰጥ ሕግ የሚናገረው ሁሉ ከሕግ በታች ላሉት እንደ ሆነ፣ እናውቃለን፤ 20ስለዚህ ሕግን በመጠበቅ ማንም በእርሱ ፊት ጻድቅ ነው ሊባል አይችልም፤ ይልቁንም በሕግ አማካይነት ኀጢአትን እንገነዘባለን።

በእምነት የሚገኝ ጽድቅ

21አሁን ግን ሕግና ነቢያት የመሰከሩለት፣ ከሕግ ውጭ የሆነ፣ የእግዚአብሔር ጽድቅ ተገልጧል። 22ይህ የእግዚአብሔር ጽድቅ ኢየሱስ ክርስቶስን በማመን የሚገኝ ጽድቅ ነው። ልዩነት የለም፤ 23ምክንያቱም ሁሉም ኀጢአትን ሠርተዋል፤ የእግዚአብሔርም ክብር ጐድሏቸዋል፤ 24በኢየሱስ ክርስቶስ በሆነው ቤዛነት እንዲያው በጸጋው ጸድቀዋል፤ 25በደሙም በሆነው እምነት፣ እግዚአብሔር የማስተስረያ መሥዋዕት አድርጎ አቅርቦታል፤3፥25 ወይም እግዚአብሔር ቍጣውን በመተው ኀጢአትን ለማስወገድ ይህንም ያደረገው ቀድሞ የተፈጸመውን ኀጢአት ሳይቀጣ በትዕግሥት በማለፍ ጽድቁን ለማሳየት ነው፤ 26በአሁኑ ዘመን ይህን ያደረገው፣ ጽድቁን ይኸውም እርሱ ራሱ ጻድቅ ሆኖ፣ በኢየሱስ የሚያምነውን የሚያጸድቅ መሆኑን ለማሳየት ነው።

27ታዲያ ትምክሕት ወዴት ነው? እርሱማ ቀርቷል። በየትኛው ሕግ? በሥራ ሕግ ነውን? አይደለም፤ በእምነት ሕግ ነው እንጂ። 28ማንም ሰው ሕግን በመፈጸም ሳይሆን፣ በእምነት እንደሚጸድቅ እናረጋግጣለን። 29እግዚአብሔር የአይሁድ አምላክ ብቻ ነውን? የአሕዛብስ አምላክ አይደለምን? አዎን፤ የአሕዛብም አምላክ ነው፤ 30የተገረዘውን በእምነት፣ ያልተገረዘውንም በዚያው እምነት የሚያጸድቅ አንድ እግዚአብሔር ብቻ ነውና። 31ታዲያ እንዲህ ከሆነ ከእምነት የተነሣ ሕግን ዋጋ የሌለው እናደርግ ይሆን? ፈጽሞ አይደረግም፤ ሕጉን እናጸናለን እንጂ።

Chinese Contemporary Bible (Traditional)

羅馬書 3:1-31

1那麼,猶太人有什麼長處呢?割禮有什麼價值呢? 2其實益處非常多!首先,上帝的聖言託付給了猶太人。 3雖然有些人不相信,但那有什麼關係呢?難道上帝的信實可靠會因他們的不信而化為無有嗎? 4當然不會!縱然人人都撒謊,上帝仍然真實可靠。正如聖經上說:

「你的判語證明你是公義的;

你雖被人控告,卻終必得勝。」

5我姑且用人的觀點說:「如果我們的不義可以反襯出上帝的公義,我們該做何論?上帝向我們發怒是祂不公正嗎?」 6當然不是!若是這樣,上帝怎麼能審判這世界呢? 7你們又說:「如果我們的虛謊凸顯出上帝的真實,增加祂的榮耀,為什麼祂還要把我們當作罪人審判呢?」 8為什麼你們不乾脆說:「我們作惡吧,好成就善事」?有人毀謗我們,說我們傳這種道理。這些人受審判是罪有應得!

沒有義人

9那麼,我們猶太人比別人優越嗎?絕對不是!我們已經說過,無論是猶太人還是希臘人,所有的人都身陷罪中。 10正如聖經上說:

「沒有義人,一個也沒有,

11沒有人明白,沒有人尋求上帝。

12人人偏離正路,變得毫無價值。

沒有人行善,一個也沒有。

13他們的喉嚨是敞開的墳墓,

舌頭上盡是詭詐,

嘴唇有蛇的毒液,

14滿口咒詛,言語惡毒;

15殺人流血,腳步飛快;

16所到之處,大肆毀滅;

17平安之路,他們未曾知道;

18他們眼中毫無對上帝的畏懼。」

19我們知道律法所講的都是針對律法之下的人,好叫所有的人都無話可說,使全世界都伏在上帝的審判之下。 20因為無人能夠靠遵行律法而被上帝視為義人,律法的本意是要使人知罪。

因信稱義

21但如今,上帝的義在律法以外顯明出來,有律法和眾先知做見證。 22人只要信耶穌基督,就可以被上帝稱為義人,沒有一個人例外。 23因為世人都犯了罪,虧欠上帝的榮耀, 24但蒙上帝的恩典,靠著基督耶穌的救贖,世人被無條件地稱為義人。 25上帝使基督耶穌成為贖罪祭,以便人藉著相信耶穌的寶血可以得到赦免。這是為了顯明上帝的義,因為祂用忍耐的心寬容人過去的罪, 26好在現今顯明祂的義,使人知道祂是公義的,祂也稱信耶穌的為義人。

27既然如此,我們哪裡能誇口呢?當然沒有可誇的。靠什麼方法讓人不能誇口呢?靠遵守律法嗎?不是!是靠信主的方法。 28因為我們堅信人被稱為義人是藉著信,不是靠遵行律法。 29難道上帝只是猶太人的上帝嗎?祂不也是外族人的上帝嗎?祂當然也是外族人的上帝。 30因為上帝只有一位,祂本著信稱受割禮的人為義人,也本著信稱未受割禮的人為義人。 31這麼說來,我們是藉著信心廢掉上帝的律法嗎?當然不是!我們反倒是鞏固律法。