ሐዋርያት ሥራ 1 – NASV & CCBT

New Amharic Standard Version

ሐዋርያት ሥራ 1:1-26

ኢየሱስ ወደ ሰማይ ዐረገ

1ቴዎፍሎስ ሆይ፤ ኢየሱስ ለማድረግና ለማስተማር የጀመረውን ሁሉ ቀደም ባለው መጽሐፌ ጽፌልሃለሁ፤ 2ይኸውም እስከ ዐረገበት ቀን ድረስ ለመረጣቸው ሐዋርያት በመንፈስ ቅዱስ አማካይነት የሰጣቸው ትእዛዝ ነው። 3ከሕማማቱም በኋላ ራሱ ቀርቦ ሕያው መሆኑን፣ ለእነዚሁ በብዙ ማስረጃ እያረጋገጠላቸው አርባ ቀንም ዐልፎ ዐልፎ እየታያቸው ስለ እግዚአብሔር መንግሥት ነገራቸው። 4ከእነርሱም ጋር በማእድ ተቀምጦ ሳለ እንዲህ ሲል አዘዛቸው፤ “ከኢየሩሳሌም አትውጡ፤ ነገር ግን እኔ ስናገር የሰማችሁትን፣ አብ የሰጠውን ተስፋ ጠብቁ፤ 5ዮሐንስ በውሃ አጥምቆ ነበርና፣ እናንተ ግን ከጥቂት ቀን በኋላ በመንፈስ ቅዱስ ትጠመቃላችሁ።”

6እነርሱም ተሰብስበው ሳሉ፣ “ጌታ ሆይ፤ የእስራኤልን መንግሥት መልሰህ የምታቋቁምበት ጊዜው አሁን ነውን?” ብለው ጠየቁት።

7እርሱም እንዲህ አላቸው፤ “አብ በገዛ ሥልጣኑ የወሰነውን ጊዜ ወይም ወቅት ማወቁ ለእናንተ አልተሰጣችሁም፤ 8ነገር ግን መንፈስ ቅዱስ በእናንተ ላይ በሚወርድበት ጊዜ ኀይልን ትቀበላላችሁ፤ በኢየሩሳሌም፣ በይሁዳና በሰማርያ ሁሉ፣ እስከ ምድር ዳርቻ ድረስ ምስክሮቼ ትሆናላችሁ።”

9ይህን ካለ በኋላ እያዩት ወደ ላይ ዐረገ፤ ደመናም ከዐይናቸው ሰወረችው።

10እርሱም በሚሄድበት ጊዜ ትኵር ብለው ወደ ሰማይ ሲመለከቱ፣ እነሆ፤ ነጫጭ ልብስ የለበሱ ሁለት ሰዎች ድንገት አጠገባቸው ቆሙ፤ 11እንዲህም አሏቸው፤ “እናንት የገሊላ ሰዎች ሆይ፤ ወደ ሰማይ እየተመለከታችሁ እዚህ የቆማችሁት ለምንድን ነው? ይህ ከእናንተ ዘንድ ወደ ሰማይ ሲያርግ ያያችሁት ኢየሱስ፣ ልክ ወደ ሰማይ ሲወጣ እንዳያችሁት በዚሁ ሁኔታ ይመለሳል።”

ማትያስ በይሁዳ ምትክ ተመረጠ

12ከዚያም ደብረ ዘይት ከተባለው ተራራ ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ፤ ይህም ተራራ ከኢየሩሳሌም የሰንበት መንገድ ያህል1፥12 አንድ ሺሕ አንድ መቶ ሜትር ገደማ ነው። ይርቅ ነበር። 13ወደ ከተማዪቱም በገቡ ጊዜ ወደሚኖሩበት ሰገነት ወጡ፤ እነዚህም ጴጥሮስ፣ ዮሐንስ፣ ያዕቆብ፣ እንድርያስ፣ ፊልጶስ፣ ቶማስ፣ በርተሎሜዎስ፣ ማቴዎስ፣ የእልፍዮስ ልጅ ያዕቆብ፣ ቀናኢ የተባለው ስምዖንና የያዕቆብ ልጅ ይሁዳ ነበሩ። 14እነዚህ ሁሉ ከሴቶቹና ከኢየሱስ እናት ከማርያም ጋር እንዲሁም ከወንድሞቹ ጋር በአንድ ልብ ሆነው ያለ ማቋረጥ ተግተው ይጸልዩ ነበር።

15በእነዚያም ቀናት፣ ጴጥሮስ መቶ ሃያ በሚሆኑ ወንድሞች1፥15 ወይም አማኞች መካከል ቆሞ፣ 16እንዲህ አለ፤ “ወንድሞች ሆይ፤ ኢየሱስን ለያዙት ሰዎች መሪ ስለ ሆናቸው ስለ ይሁዳ፣ መንፈስ ቅዱስ አስቀድሞ በዳዊት አፍ የተናገረው የመጽሐፉ ቃል መፈጸም ስላለበት፣ 17እርሱ ከእኛ እንደ አንዱ ተቈጥሮ በዚህ አገልግሎት የመሳተፍ ዕድል አግኝቶ ነበር።”

18ይህ ሰው ስለ ክፉ ሥራው በተከፈለው ዋጋ መሬት ገዛ፤ በዚያም በግንባሩ ተደፍቶ ሰውነቱ እመካከሉ ላይ ፈነዳ፤ ሆድ ዕቃውም ተዘረገፈ። 19ይህም በኢየሩሳሌም በሚኖሩት ሁሉ ዘንድ ተሰማ፤ መሬቱም በቋንቋቸው “አኬልዳማ” ተብሎ ተጠራ፤ ትርጓሜውም “የደም መሬት” ማለት ነው።

20ጴጥሮስም በመቀጠል እንዲህ አለ፤

“በመዝሙር መጽሐፍ፣

‘መኖሪያው ባዶ ትሁን፤

የሚኖርባትም ሰው አይገኝ’ ደግሞም፣

‘ሹመቱን ሌላ ሰው ይውሰደው’

ተብሎ ተጽፏል። 21ስለዚህ ጌታ ኢየሱስ በመካከላችን በገባበትና በወጣበት ጊዜ ሁሉ፣ ከእኛ ጋር ከነበሩት መካከል አንድ ሰው መምረጥ ያስፈልጋል፤ 22ይኸውም፣ ከዮሐንስ ጥምቀት ጀምሮ ኢየሱስ ከእኛ ተለይቶ እስካረገበት ቀን ድረስ የነበረ መሆን አለበት፤ ምክንያቱም ከእነዚህ ሰዎች አንዱ ከእኛ ጋር የትንሣኤው ምስክር እንዲሆን ያስፈልጋል።”

23ስለዚህ ኢዮስጦስ የሚሉትን፣ በርስያን የተባለውን ዮሴፍንና ማትያስን ሁለቱን አቀረቡ፤ 24እንዲህም ብለው ጸለዩ፤ “ጌታ ሆይ፤ አንተ የሰውን ሁሉ ልብ ታውቃለህ፤ ከእነዚህ ከሁለቱ መካከል የመረጥኸውን ሰው አመልክተንና 25ይሁዳ ወደ ገዛ ራሱ ስፍራ ትቶት በሄደው በዚህ አገልግሎትና በሐዋርያዊነት ቦታ ላይ ሹመው።” 26ከዚያም ዕጣ ጣሉላቸው፤ ዕጣውም ለማትያስ ወጣ፤ እርሱም ከዐሥራ አንዱ ሐዋርያት ጋር ተቈጠረ።

Chinese Contemporary Bible (Traditional)

使徒行傳 1:1-26

應許聖靈降臨

1提阿非羅啊,在前一封信中,我從耶穌的生平和教導開始, 2一直談到祂藉著聖靈吩咐了自己選立的使徒,然後被接回天上。 3祂受難後用許多確鑿的證據證實自己活著,在四十天之內屢次向使徒顯現,與他們談論上帝的國。 4有一次,耶穌和他們在一起吃飯的時候,叮囑他們:「你們不要離開耶路撒冷,要在那裡等候我對你們說過的天父的應許。 5因為從前約翰用水給你們施洗,但再過幾天,你們要受聖靈的洗。」

6他們跟耶穌在一起的時候問祂:「主啊,你要在這時候復興以色列國嗎?」 7耶穌回答說:「天父照祂的權柄定下的時間、日期不是你們可以知道的。 8但聖靈降臨在你們身上後,你們必得到能力,在耶路撒冷猶太全境和撒瑪利亞,直到地極,作我的見證人。」

9耶穌說完這番話,就在他們眼前被提升天,被一朵雲彩接去,離開了他們的視線。 10祂上升時,他們都定睛望著天空,忽然有兩個身穿白衣的人站在他們身旁, 11說:「加利利人啊!你們為什麼站在這裡望著天空呢?這位離開你們被接到天上的耶穌,你們看見祂怎樣升天,將來祂還要怎樣回來。」

選立新使徒

12於是,他們從橄欖山回到耶路撒冷。橄欖山距離耶路撒冷不遠,約是安息日允許走的路程1·12 按猶太人的傳統,在安息日只能走約一公里遠。13他們進城後,來到樓上自己住的房間。當時有彼得約翰雅各安得烈腓力多馬巴多羅買馬太亞勒腓的兒子雅各、激進黨人西門雅各的兒子猶大14他們和耶穌的母親瑪麗亞、耶穌的弟弟們及幾個婦女在一起同心合意地恆切禱告。

15那時,約有一百二十人在聚會,彼得站起來說: 16「弟兄們,關於帶人抓耶穌的猶大,聖靈藉著大衛的口早已預言,這經文必須要應驗。 17這人原本是我們中間的一員,與我們同擔使徒的職分。」

18猶大用作惡得來的錢買了一塊田,他頭朝下栽倒在那裡,肚破腸流。 19這消息很快傳遍了耶路撒冷,當地人稱那塊田為「亞革大馬」,就是「血田」的意思。

20彼得繼續說:「詩篇上寫道,『願他的家園一片荒涼,無人居住』,又說,『願別人取代他的職位。』 21-22所以,我們必須另選一個人代替猶大,與我們一同為主耶穌的復活做見證。他必須是從主耶穌接受約翰的洗禮起一直到主升天,始終與我們在一起的人。」

23被提名的有別號巴撒巴又叫猶士都約瑟馬提亞兩個人。 24-25大家便禱告說:「主啊!你洞悉人的內心,求你指明這兩個人中你要揀選哪一個來擔負使徒的職分。猶大丟棄了這職分,去了他該去的地方。」 26然後,他們抽籤,抽中了馬提亞,就把他列入十一使徒中。