ማቴዎስ 28 – NASV & CCBT

New Amharic Standard Version

ማቴዎስ 28:1-20

የኢየሱስ ከሙታን መነሣት

28፥1-8 ተጓ ምብ – ማር 16፥1-8ሉቃ 24፥1-10

1ሰንበት ካለፈ በኋላ፣ በሳምንቱ መጀመሪያ ቀን ጎሕ ሲቀድድ፣ ማርያም መግደላዊትና ሌላዋ ማርያም መቃብሩን ሊያዩ ሄዱ።

2በድንገት ታላቅ የምድር መናወጥ ሆነ፤ የጌታም መልአክ ከሰማይ ወርዶ ወደ መቃብሩ በመሄድ ድንጋዩን አንከባልሎ በላዩ ላይ ተቀመጠበት፤ 3መልኩ እንደ መብረቅ ብሩህ፣ ልብሱም እንደ በረዶ ነጭ ነበር። 4ጠባቂዎቹ መልአኩን ከመፍራት የተነሣ ተንቀጠቀጡ፤ እንደ በድንም ሆኑ።

5መልአኩም ሴቶቹን እንዲህ አላቸው፤ “አትፍሩ፤ የተሰቀለውን ኢየሱስን እንደምትፈልጉ ዐውቃለሁና፤ 6እርሱ በዚህ የለም፤ እንደ ተናገረው ተነሥቷል፤ ኑና ተኝቶበት የነበረውን ቦታ እዩ። 7አሁንም ፈጥናችሁ ሂዱና ለደቀ መዛሙርቱ፣ ‘ከሙታን ተነሥቷል፤ ቀድሟችሁ ወደ ገሊላ ይሄዳል፤ በዚያ ታዩታላችሁ’ ብላችሁ ንገሯቸው። እንግዲህ ነግሬአችኋለሁ!”

8ሴቶቹም በፍርሀትና በደስታ ተሞልተው ለደቀ መዛሙርቱ ለመንገር በፍጥነት እየሮጡ የመቃብሩን ስፍራ ትተው ሄዱ። 9ወዲያው ኢየሱስ አገኛቸውና፣ “ሰላም ለእናንተ ይሁን!” አላቸው። እነርሱም ወደ ኢየሱስ ቀርበው እግሩን ይዘው ሰገዱለት። 10ኢየሱስም፣ “አትፍሩ፤ ሂዱና ወደ ገሊላ እንዲሄዱ ለወንድሞቼ ንገሯቸው፤ በዚያ ያዩኛል” አላቸው።

የጠባቂዎች ምስክርነት

11ሴቶቹ በመንገድ ላይ ሳሉ፣ ከጠባቂዎቹ ጥቂቶቹ ወደ ከተማ በመሄድ የሆነውን ሁሉ ለካህናት አለቆች አወሩላቸው። 12የካህናት አለቆችም ከሽማግሌዎች ጋር ተሰብስበው ተማከሩ፤ ለወታደሮቹ በቂ ገንዘብ በመስጠት 13እንዲህ አሏቸው፤ “ ‘ተኝተን ሳለን ደቀ መዛሙርቱ በሌሊት መጥተው ሰረቁት’ በሉ፤ 14ይህ ወሬ በገዥው ዘንድ ቢሰማ እንኳ፣ እኛ እናስረዳዋለን፤ ምንም ክፉ ነገር እንዳይደርስባችሁ እናደርጋለን።” 15ወታደሮቹም ገንዘቡን ተቀብለው እንደ ታዘዙት አደረጉ። ይህም ታሪክ እስከ ዛሬ ድረስ በአይሁዶች ዘንድ በሰፊው እንደ ተሠራጨ ነው።

ታላቁ ተልእኮ

16ከዚያም ዐሥራ አንዱ ደቀ መዛሙርት በገሊላ ወዳለው ኢየሱስ ወዳመለከታቸው ተራራ ሄዱ። 17ባዩትም ጊዜ ሰገዱለት፤ ጥቂቶች ግን ተጠራጠሩ። 18ኢየሱስም ደቀ መዛሙርቱ ወዳሉበት ቀርቦ እንዲህ አላቸው፤ “ሥልጣን ሁሉ በሰማይና በምድር ተሰጥቶኛል፤ 19ስለዚህ ሂዱና ሕዝቦችን ሁሉ በአብ፣ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸው ደቀ መዛሙርት አድርጓቸው፤ 20ያዘዝኋችሁንም ሁሉ እንዲጠብቁ አስተምሯቸው፤ እኔም እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ነኝ።”

Chinese Contemporary Bible (Traditional)

馬太福音 28:1-20

耶穌復活

1安息日剛過,週日黎明時分,抹大拉瑪麗亞和另一位瑪麗亞一同到墳墓去察看。

2突然,大地劇烈地震動,上帝的天使從天而降,推開堵著墓穴的石頭,坐在上面。 3他的容貌如閃電,衣裳潔白如雪。 4看守墓穴的衛兵嚇得要死,渾身發抖。

5天使對那兩個女人說:「不要怕,我知道你們是在找那位被釘十字架的耶穌。 6祂不在這裡,正如祂所說的,祂已經復活了。你們來看,這是安放祂的地方。 7現在你們快回去,把這消息告訴祂的門徒,祂已經從死裡復活,先你們一步去了加利利,你們將在那裡見到祂。記住,我已經告訴你們了。」

8她們聽了又驚又喜,連忙離開墳墓,跑去告訴門徒。 9忽然,耶穌迎面而來,對她們說:「願你們平安!」她們就上前抱住祂的腳敬拜祂。

10耶穌對她們說:「不要害怕。去告訴我的弟兄,叫他們到加利利去,他們將在那裡見到我。」

行賄造謠

11她們還在趕路的時候,有些守墓的衛兵已經進城把整件事告訴祭司長。 12祭司長和長老聚集商議,決定用重金買通守墓的衛兵,又吩咐他們: 13「你們就說,『半夜裡我們熟睡的時候,耶穌的門徒把祂的屍體偷走了。』 14如果這件事傳到總督那裡,我們一定會替你們出面,保你們無事。」 15守衛收下錢,便依照吩咐去做。於是,這說法在猶太人中一直流傳到今天。

大使命

16十一個門徒趕到加利利,到了耶穌和他們約定的山上, 17看到耶穌就敬拜祂,但有些人仍然心存疑惑。 18耶穌上前對門徒說:

「天上地下所有的權柄都交給我了。 19所以,你們要去使萬民作我的門徒,奉父、子、聖靈的名給他們施洗, 20教導他們遵守我吩咐你們的一切。記住,我必常與你們同在,一直到世界的末了。」