ማርቆስ 1 – NASV & CCBT

New Amharic Standard Version

ማርቆስ 1:1-45

የመጥምቁ ዮሐንስ ስብከት

1፥2-8 ተጓ ምብ – ማቴ 3፥1-11ሉቃ 3፥2-16

1የእግዚአብሔር ልጅ1፥1 አንዳንድ ቅጆች የእግዚአብሔር ልጅ የሚለው ሐረግ የላቸውም።፣ የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል መጀመሪያ።

2በነቢዩ በኢሳይያስ፣ እንዲህ ተብሎ ተጽፏል፤

“እነሆ፤ መንገድህን የሚያዘጋጅ መልእክተኛዬን

በፊትህ እልካለሁ፤

3‘የጌታን መንገድ አዘጋጁ፤

ጥርጊያውንም አስተካክሉ’

እያለ በበረሓ የሚጮኽ ድምፅ።” 4ስለዚህ መጥምቁ ዮሐንስ በበረሓ እያጠመቀና ለኀጢአት ስርየት የንስሓ ጥምቀት እየሰበከ መጣ። 5የይሁዳ አገር በሞላ፣ የኢየሩሳሌም ሰዎች በጠቅላላ ወደ እርሱ በመሄድ ኀጢአታቸውን እየተናዘዙ በዮርዳኖስ ወንዝ በእርሱ እጅ ተጠመቁ። 6ዮሐንስ የግመል ጠጕር ይለብስ፣ በወገቡ ጠፍር ይታጠቅ፣ አንበጣና የበረሓ ማርም ይበላ ነበር። 7ስብከቱም፣ “እኔ ጐንበስ ብዬ የጫማውን ማሰሪያ መፍታት ከማይገባኝ፣ ከእኔ የሚበልጥ ከእኔ በኋላ ይመጣል፤ 8እኔ በውሃ አጠምቃችኋለሁ፤ እርሱ ግን በመንፈስ ቅዱስ ያጠምቃችኋል” የሚል ነበር።

የኢየሱስ መጠመቅና መፈተን

1፥9-11 ተጓ ምብ – ማቴ 3፥13-17ሉቃ 3፥21-22

1፥1213 ተጓ ምብ – ማቴ 4፥1-11ሉቃ 4፥1-13

9በዚህ ጊዜ ኢየሱስ የገሊላ ከተማ ከሆነችው ከናዝሬት መጥቶ በዮርዳኖስ ወንዝ በዮሐንስ እጅ ተጠመቀ። 10ከውሃው በሚወጣበትም ጊዜ፣ ሰማያት ተከፍተው፣ መንፈስ ቅዱስ እንደ ርግብ በእርሱ ላይ ሲወርድ አየ፤ 11“የምወድድህ ልጄ አንተ ነህ፤ በአንተ ደስ ይለኛል” የሚል ድምፅ ከሰማይ ተሰማ።

12ወዲያውም መንፈስ ቅዱስ ወደ በረሓ መራው፤ 13በሰይጣንም እየተፈተነ አርባ ቀን በበረሓ ቈየ። ከአራዊት ጋር ነበር፤ መላእክትም አገለገሉት።

የመጀመሪያዎቹ ደቀ መዛሙርት መመረጥ

1፥16-20 ተጓ ምብ – ማቴ 4፥18-22ሉቃ 5፥2-11ዮሐ 1፥35-42

14ዮሐንስ እስር ቤት ከገባ በኋላ፣ ኢየሱስ የእግዚአብሔርን ወንጌል እየሰበከ ወደ ገሊላ ሄዶ፣ 15“ጊዜው ደርሷል፤ የእግዚአብሔር መንግሥት ቀርባለች፤ ንስሓ ግቡ፤ በወንጌልም እመኑ” እያለ ይሰብክ ነበር።

16ኢየሱስ በገሊላ ባሕር አጠገብ ሲያልፍ፣ ስምዖንና ወንድሙ እንድርያስ ዓሣ አጥማጆች ስለ ነበሩ፣ መረብ ወደ ባሕር ሲጥሉ አያቸው። 17ኢየሱስም፣ “ተከተሉኝ፤ ሰው አጥማጆች አደርጋችኋለሁ” አላቸው። 18እነርሱም ወዲያውኑ መረባቸውን ትተው ተከተሉት።

19ትንሽ ዕልፍ እንዳለ፣ የዘብዴዎስ ልጅ ያዕቆብና ወንድሙ ዮሐንስ በጀልባ ሆነው መረባቸውን ሲያበጃጁ አያቸውና፣ 20ወዲያውኑ ጠራቸው። እነርሱም አባታቸውን ከቅጥር ሠራተኞቹ ጋር በጀልባው ላይ ትተው ተከትለውት ሄዱ።

ኢየሱስ ርኩስ መንፈስ አስወጣ

1፥21-28 ተጓ ምብ – ሉቃ 4፥31-37

21ከዚያም ወደ ቅፍርናሆም ሄዱ፤ ኢየሱስም ወዲያው በሰንበት ቀን ወደ ምኵራብ ገብቶ ማስተማር ጀመረ። 22እንደ ጸሐፍት ሳይሆን፣ እንደ ባለ ሥልጣን በማስተማሩ ሕዝቡ በትምህርቱ ተገረሙ። 23በዚያን ጊዜ በምኵራባቸው ውስጥ የነበረ ርኩስ1፥23 ወይም ክፉ፤ እንዲሁም 26 እና 27 ይመ መንፈስ ያደረበት አንድ ሰው እንዲህ በማለት ጮኸ፤ 24“የናዝሬቱ ኢየሱስ ሆይ፤ ከእኛ ምን ትሻለህ? ልታጠፋን መጣህን? እኔ ማን እንደ ሆንህ ዐውቃለሁ፤ አንተ የእግዚአብሔር ቅዱስ ነህ!”

25ኢየሱስም፣ “ጸጥ በል፤ ከእርሱም ውጣ!” ብሎ ገሠጸው። 26ርኩሱም መንፈስ ሰውየውን በኀይል ካንፈራገጠው በኋላ እየጮኸ ወጣ።

27ሕዝቡ በሙሉ በመገረም፣ “ይህ ነገር ምንድን ነው? ሥልጣን ያለው አዲስ ትምህርት መሆኑ ነው! ርኩሳን መናፍስትን እንኳ ያዝዛል፤ እነርሱም ይታዘዙለታል!” እያሉ እርስ በርስ ተጠያየቁ። 28ወዲያውም ዝናው በገሊላ ዙሪያ ባሉ ስፍራዎች ሁሉ ተዳረሰ።

ኢየሱስ ብዙዎችን ፈወሰ

1፥29-31 ተጓ ምብ – ማቴ 8፥14-15ሉቃ 4፥3839

1፥32-34 ተጓ ምብ – ማቴ 8፥1617ሉቃ 4፥4041

29ወዲያው ከምኵራብ እንደ ወጡ፣ ከያዕቆብና ከዮሐንስ ጋር ወደ ስምዖንና ወደ እንድርያስ ቤት ገቡ። 30የስምዖን ዐማት በትኵሳት በሽታ ታማ ተኝታ ነበር፤ ስለ እርሷም ነገሩት፤ 31ስለዚህም እርሱ ወደ ተኛችበት በመሄድ እጇን ይዞ አስነሣት፤ ትኵሳቱም ተዋት፤ ተነሥታም ታገለግላቸው ጀመር።

32ጀንበር ከጠለቀች በኋላ፣ ምሽት ላይ የአካባቢው ሰዎች ሕመምተኞችንና በአጋንንት የተያዙትን ሁሉ ወደ እርሱ አመጡ።

33የከተማዋ ሕዝብ በሙሉ በቤቱ ደጅ ላይ ተሰብስቦ ነበር። 34እርሱም በተለያየ በሽታ የታመሙትን ብዙዎችን ፈወሰ፤ ብዙ አጋንንትም አወጣ፤ ነገር ግን አጋንንቱ የኢየሱስን ማንነት ያውቁ ስለ ነበር እንዲናገሩ አልፈቀደላቸውም።

ኢየሱስ በገለልተኛ ስፍራ ጸለየ

1፥35-38 ተጓ ምብ – ሉቃ 4፥4243

35ማለዳም ገና ጎሕ ሳይቀድ፣ ኢየሱስ ተነሥቶ ከቤት ወጣ፤ ወደ አንድ ገለልተኛ ስፍራም ሄዶ ይጸልይ ጀመር። 36ስምዖንና ባልደረቦቹም ተከትለው ይፈልጉት ጀመር፤ 37ባገኙትም ጊዜ፣ “ሰው ሁሉ ይፈልግሃል” አሉት።

38እርሱም፣ “ከዚህ ተነሥተን በአቅራቢያ ወዳሉት መንደሮች እንሂድ፤ እዚያም ልስበክ፤ የመጣሁት ለዚሁ ነውና” አላቸው። 39ስለዚህ ወደ ምኵራባቸው እየገባ በመስበክና አጋንንትን በማስወጣት በመላዋ ገሊላ ይዘዋወር ጀመር።

ኢየሱስ ለምጻሙን ሰው አነጻ

1፥40-44 ተጓ ምብ – ማቴ 8፥2-4ሉቃ 5፥12-14

40አንድ ለምጻም1፥40 ለምጽ የሚለው ቃል በግሪኩ አገላለጽ የተለያዩ የቈዳ በሽታዎችን ያመለክታል። ወደ እርሱ ቀርቦ ከፊቱ በመንበርከክ፣ “ብትፈቅድ እኮ ልታነጻኝ ትችላለህ” በማለት ለመነው።

41ኢየሱስም ለሰውየው በመራራት እጁን ዘርግቶ ዳሰሰውና፣ “እፈቅዳለሁ፣ ንጻ” አለው። 42እርሱም ወዲያው ከለምጹ ነጻ፤ ከበሽታውም ተፈወሰ።

43ኢየሱስም ሰውየውን አጥብቆ በማስጠንቀቅ እንዲህ ሲል አሰናበተው፤ 44“ለማንም አንድ ነገር እንኳ እንዳትናገር ተጠንቀቅ፤ ነገር ግን ምስክር እንዲሆናቸው ሄደህ ራስህን ለካህን አሳይ፤ ስለ መንጻትህም ሙሴ ያዘዘውን መሥዋዕት አቅርብ” አለው። 45ሰውየው ግን በሄደበት ሁሉ ነገሩን በሰፊው አወራ፤ ወሬውንም አሠራጨ። በዚህ ምክንያት ኢየሱስ ወደ ማንኛውም ከተማ በግልጽ መግባት አልተቻለውም፤ ከዚህም የተነሣ ከከተማ ውጭ በሚገኙ ሰዋራ ቦታዎች መኖር ጀመረ፤ ሰዎች ግን ከየአቅጣጫው እርሱ ወዳለበት መምጣት አላቋረጡም።

Chinese Contemporary Bible (Traditional)

馬可福音 1:1-45

施洗者約翰預備道路

1有關上帝的兒子耶穌基督的福音是這樣開始的。

2以賽亞先知書上說:

「看啊,

我要差遣我的使者在你前面為你預備道路。

3他在曠野大聲呼喊,

『預備主的道,

修直祂的路。』」

4果然,約翰出現了,他在曠野勸人悔改,接受洗禮,使罪得到赦免。 5猶太全境和耶路撒冷的居民都到約翰那裡承認他們的罪,在約旦河裡接受他的洗禮。

6約翰身穿駱駝毛的衣服,腰束皮帶,吃的是蝗蟲和野蜜。 7他傳道說:「在我之後,有一位能力比我更大的要來,我連彎腰替祂解鞋帶也不配。 8我是用水給你們施洗,但祂要用聖靈給你們施洗。」

耶穌受洗

9那時,耶穌從加利利拿撒勒約旦河接受約翰的洗禮。 10耶穌從水中一上來,就看見天開了,聖靈好像鴿子一樣降在祂身上, 11從天上有聲音說:「你是我的愛子,我甚喜悅你。」

耶穌受試探

12聖靈隨即催促祂到曠野。 13祂在曠野受撒旦的試探四十天。祂與野獸在一起,有天使服侍祂。

呼召四漁夫

14約翰被捕後,耶穌來到加利利宣講上帝的福音,說: 15「時候到了,上帝的國臨近了,你們要悔改,相信福音。」

16耶穌沿著加利利湖邊走,看見兩個漁夫——西門和他的弟弟安得烈正在湖上撒網捕魚。 17耶穌對他們說:「來跟從我!我要使你們成為得人的漁夫。」 18他們立刻拋下漁網,跟從了耶穌。

19耶穌往前走了不遠,又看見西庇太的兩個兒子雅各約翰正在船上補網, 20便立刻呼召他們。他們就辭別父親和船上的工人,跟從了耶穌。

傳道趕鬼

21他們到了迦百農,耶穌在安息日去會堂裡講道。 22那裡的人都很吃驚,因為祂教導他們時像個有權柄的人,不像律法教師。 23當時會堂裡有一個被污鬼附身的人喊道: 24拿撒勒的耶穌啊,我們和你有什麼關係?你是來毀滅我們嗎?我知道你是誰,你是上帝的聖者!」

25耶穌責備牠說:「住口,從他身上出來!」

26污鬼使那人抽搐了一陣,大叫一聲,就出來了。 27在場的人十分驚訝,彼此議論說:「這是怎麼回事?真是充滿權柄的新教導啊!竟然連污鬼都服從祂的命令。」 28於是,耶穌的名聲立刻傳遍了整個加利利

醫病趕鬼

29耶穌同雅各約翰離開會堂,來到西門安得烈家。 30當時西門的岳母正發燒,躺在床上,他們立刻把這事告訴耶穌。 31耶穌走到她的床邊,拉著她的手扶她起來,她的燒立刻退了,便起來服侍他們。

32日落之後,有人把病人和被鬼附身的人都帶來見耶穌。 33全城的人都聚在門前。 34耶穌醫好了許多患各種疾病的人,又趕出很多鬼。祂不准鬼說話,因為鬼認識祂。

在加利利傳道

35第二天清早,天還沒亮,耶穌就起來獨自走到曠野去禱告。 36西門和同伴們四處尋找耶穌, 37找到了,便對祂說:「大家都在找你呢!」

38耶穌卻回答說:「我們到附近的鄉鎮去吧,我也好在那裡傳道,因為我就是為這事來的。」

39於是,耶穌走遍加利利,在各會堂傳道,趕鬼。

治好痲瘋病人

40有一次,一個患痲瘋病的人來到耶穌面前,跪下央求:「只要你肯,一定能使我潔淨。」

41耶穌動了慈心,就伸手摸他,說:「我肯,你潔淨了吧!」 42那人的痲瘋病立即消失了,他就潔淨了。 43耶穌讓他回去並鄭重地叮囑: 44「不要把這事告訴別人,要去讓祭司察看你的身體,並照摩西的規定獻祭,向眾人證明你已經潔淨了。」

45但那人離開之後,卻到處傳揚這件事,以致耶穌無法再公開進城。祂只能待在城外的曠野,可是人們仍從各處來找祂。