ሕዝቅኤል 22 – NASV & CCB

New Amharic Standard Version

ሕዝቅኤል 22:1-31

የኢየሩሳሌም ኀጢአት

1የእግዚአብሔር ቃል እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፤

2“የሰው ልጅ ሆይ፤ አትፈርድባትምን? ደም በምታፈስሰው በዚህች ከተማ ላይ አትፈርድባትምን? ጸያፍ ተግባሯን ፊት ለፊት ንገራት፤ 3እንዲህም በላት፤ ‘ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ በመካከልሽ ደምን በማፍሰስና ጣዖታትን በመሥራት ራስሽን የምታረክሺ፣ ፍርድንም በራስሽ ላይ የምታፈጥኚ ከተማ ሆይ፤ 4ባፈሰስሽው ደም በድለሻል፤ በሠራሽውም ጣዖት ረክሰሻል፤ ከዚህም የተነሣ ቀንሽን አቅርበሻል፤ ዕድሜሽንም አሳጥረሻል። ስለዚህ ለአሕዛብ መዘባበቻ፣ ለአገሩም ሁሉ መሣለቂያ አደርግሻለሁ። 5አንቺ የተዋረድሽና ሽብር የሞላብሽ ሆይ፤ በቅርብም በሩቅም ያሉ ይሣለቁብሻል።

6“ ‘እነሆ በመካከልሽ ያለ እያንዳንዱ የእስራኤል መስፍን ደም ለማፍሰስ ሥልጣኑን ይጠቀማል። 7አባቶችና እናቶች በውስጥሽ ተዋረዱ፤ መጻተኞች ተጨቈኑ፤ ድኻ አደጎችና መበለቶች ተንገላቱ። 8ንዋያተ ቅድሳቴን አቃለልሽ፤ ሰንበታቴንም አረከስሽ። 9ደምን ለማፍሰስ ወሬ የሚያቀብሉ በውስጥሽ አሉ፤ በኰረብታ ቤተ ጣዖት የተሠዋውን የሚበሉና ዝሙትን የሚፈጽሙ ሰዎች በመካከልሽ ይገኛሉ። 10የአባታቸውን መኝታ የሚደፍሩ ሰዎች በውስጥሽ አሉ፤ በሥርዐቱ መሠረት ንጹሕ ባልሆኑበት በወር አበባቸው ጊዜ ሴቶችን በማስገደድ የሚደፍሩ በመካከልሽ ይገኛሉ። 11በውስጥሽ አንዱ የባልንጀራውን ሚስት ያባልጋል፤ ሌላውም የልጁን ሚስት ያስነውራል፤ ሌላው ደግሞ የገዛ እኅቱ የሆነችውን የአባቱን ልጅ ይደፍራል። 12በመካከልሽ ያሉ ሰዎች ደም ለማፍሰስ ጕቦ ይቀበላሉ፤ አንቺም ዐራጣና ከፍተኛ ወለድ22፥12 ወይም ዐራጣና ወለድ በመውሰድ ከባልንጀራሽ የማይገባ ትርፍ ዘረፍሽ፤ እኔንም ረስተሻል፤ ይላል ጌታ እግዚአብሔር

13“ ‘ያለ አግባብ ባገኘሽው ጥቅምና በመካከልሽ ባፈሰስሽው ደም ላይ እጄን አጨበጭባለሁ። 14እኔ ልቀጣሽ በምነሣበት ጊዜ፣ በልበ ሙሉነት መቆም ትችያለሽን? ወይስ እጅሽ ሊበረታ ይችላልን? እኔ እግዚአብሔር ተናግሬአለሁ፤ አደርገዋለሁም። 15በሕዝቦች መካከል እበትንሻለሁ፤ በየአገሩም እዘራሻለሁ፤ ከርኩሰትሽም አጠራሻለሁ። 16በሕዝቦች ዘንድ በምትረክሺበት ጊዜ፣22፥16 ወይም ርስትሽን ለአንቺ በሰጠሁሽ ጊዜ እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቂያለሽ።’ ”

17የእግዚአብሔርም ቃል እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፤ 18“የሰው ልጅ ሆይ፤ የእስራኤል ቤት የብረት ዝቃጭ ሆነብኝ፤ ሁሉም በከውር ውስጥ ቀልጦ እንደሚቀር መዳብ፣ ቈርቈሮ፣ ብረትና እርሳስ ናቸው፤ እነዚህ ከብር የሚወጡ ዝቃጭ ናቸው። 19ስለዚህ ልዑል እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ ‘ሁላችሁም የብረት ዝቃጭ ስለ ሆናችሁ ወደ ኢየሩሳሌም እሰበስባችኋለሁ። 20ሰው ብርንና መዳብን፣ ብረትንና እርሳስን እንዲሁም ቈርቈሮን ለማቅለጥ በከውር ውስጥ አስገብቶ እሳት እንደሚያነድድበት፣ እኔም እንደዚሁ በቍጣዬና በመዓቴ ወደ ከተማዪቱ እሰበስባችኋለሁ፤ በዚያም አቀልጣችኋለሁ። 21ሰብስቤአችሁ የቍጣዬን እሳት በእስትንፋሴ አነድድባችኋለሁ፤ እናንተም በዚያ ውስጥ ቀልጣችሁ ትቀራላችሁ፤ እኔ እግዚአብሔር ቍጣዬን በላያችሁ እንዳፈሰስሁ ታውቃላችሁ። 22ብር በከውር ውስጥ እንደሚቀልጥ፣ እናንተም በከተማዋ ውስጥ ትቀልጣላችሁ፤ በዚያን ጊዜ እኔ እግዚአብሔር ቍጣዬን በላያችሁ እንዳፈሰስሁ ታውቃላችሁ።’ ”

23የእግዚአብሔርም ቃል እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፤ 24“የሰው ልጅ ሆይ፤ ምድሪቱን፣ ‘አንቺ ያልነጻሽ በቍጣም ቀን ዝናብ ያላገኘሽ22፥24 ከሰብዐ ሊቃናት ጋር ተመሳሳይ ሲሆን ዕብራይስጡ ግን ያልነጻሽ ወይም ያልዘነበብሽ ይለዋል። ምድር ነሽ’ በላት። 25መሳፍንቷ22፥25 ከሰብዐ ሊቃናት ጋር ተመሳሳይ ሲሆን ዕብራይስጡ ግን ነቢያት ይለዋል እያገሣ ግዳዩን እንደሚቦጫጭቅ አንበሳ በውስጧ ያሤራሉ፤ ሕዝቡን ይበላሉ፤ ንብረትንና የከበሩ ነገሮችን ይነጥቃሉ፤ ብዙዎችንም ሴቶች መበለት ያደርጋሉ። 26ካህናቷ በሕጌ ላይ ያምፃሉ፤ ንዋያተ ቅድሳቴን ያረክሳሉ፤ የተቀደሰውን ከረከሰው አይለዩም፤ በጐደፈውና በንጹሑ መካከል ልዩነት እንደሌለ ያስተምራሉ፤ ሰንበታቴን ከማክበር ዘወር ብለዋል፤ በዚህም በመካከላቸው ተንቄአለሁ። 27በውስጧ የሚገኙ መኳንንቷ ግዳይ እንደሚቦጫጭቁ ተኵላዎች ናቸው፤ በግፍ ትርፍ ለመሰብሰብ ደም ያፈስሳሉ፤ ሕይወትም ያጠፋሉ። 28ነቢያቷም በሐሰት ራእይና በውሸት ሟርት ይህን ሁሉ ድርጊት ያድበሰብሱላቸዋል፤ እግዚአብሔርም ሳይናገር፣ ‘ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል’ ይላሉ። 29በምድሪቱ የሚኖረው ሕዝብ ይቀማል፤ ይዘርፋል፤ ፍትሕ በማጕደልም ድኻውንና ችግረኛውን ይጨቍናል፤ መጻተኛውንም ይበድላል።

30“ምድሪቱን እንዳላጠፋት ቅጥሩን የሚጠግን፣ በፈረሰውም በኩል በፊቴ የሚቆምላት ሰው ከመካከላቸው ፈለግሁ፤ ነገር ግን አንድም አላገኘሁም። 31ስለዚህ መዓቴን አፈስስባቸዋለሁ፤ በጽኑ ቍጣዬም አነድዳቸዋለሁ፤ ያደረጉትንም በራሳቸው ላይ እመልሳለሁ፤ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።”

Chinese Contemporary Bible (Simplified)

以西结书 22:1-31

耶路撒冷的罪恶

1耶和华对我说: 2“人子啊,你要审判耶路撒冷这杀人流血的城。你要审判她,使她知道自己一切可憎的行为。 3你要向她宣告主耶和华的话,说,‘唉,你这杀人流血、制造偶像玷污自己的城啊,你的末日到了。 4你既犯罪杀人、制造偶像玷污自己、自招审判,我要使你成为列国列邦侮辱和讥讽的对象。 5你这声名狼藉、混乱不堪的城将要受到远近各国的耻笑。

6“‘看啊,在你城中的以色列首领各逞权势,杀人流血。 7他们轻慢父母,压迫寄居者,欺负孤儿寡妇。 8他们藐视我的圣物,亵渎我的安息日。 9在你这城中,有人好诽谤、杀人流血,有人在山上吃祭物,有人淫乱, 10有人与继母通奸,羞辱父亲,有人奸污经期不洁的妇女, 11有人与邻居的妻子干出可憎之事,有人玷污自己的儿媳妇,有人奸污自己的同父姊妹。 12在你这城中,他们受贿杀人,放债取利,压榨邻居,早把我忘了。这是主耶和华说的。

13“‘我见你谋财害命,就击掌叹息。 14在我惩罚你的日子,你还有勇气和力量吗?我耶和华言出必行, 15我要把你驱散到列国,分散到列邦,我要除掉你的污秽。 16你必在列国面前受凌辱,你便知道我是耶和华。’”

17耶和华对我说: 18“人子啊,在我看来,以色列人已经变成了渣滓。他们是炉中的铜、锡、铁、铅,都是银渣滓。 19所以主耶和华说,‘你们既是渣滓,我要把你们聚集在耶路撒冷城。 20我要在烈怒中把你们聚集在城里熔化,就像人把银、铜、铁、铅、锡聚在高温的炉中熔化一样。 21我要聚集你们,把我的怒火倒在你们身上,熔化你们。 22你们要在城中熔化,就像银在炼炉中熔化。你们就知道我耶和华已将我的烈怒倾倒在你们身上。’”

23耶和华对我说: 24“人子啊,你要对以色列说,‘在我发怒的日子,将没有雨水滋润你这不洁之地。 25你的首领图谋恶事,好像咆哮着撕碎猎物的狮子,他们草菅人命,抢夺财宝,使多人变成寡妇。 26你的祭司强解我的律法,亵渎我的圣物。他们圣俗不分,也不教导人分辨洁净的和污秽的。他们藐视我的安息日,亵渎我。 27你的首领好像撕碎猎物的豺狼,杀人流血,谋取不义之财。 28你的先知对他们说虚假的异象和占卜,像用白灰刷墙一样掩盖他们的罪恶,说,耶和华这样说,其实耶和华没有说。 29你的居民强取豪夺,欺压贫困的,虐待寄居的,无法无天。 30我想在他们中间寻找一位重修城墙的人,站在我面前为这地方堵住缺口,免得我毁灭这里。可是,我一个也找不到。 31因此,我要向他们倾倒我的烈怒,用怒火灭尽他们,照他们的所作所为报应他们。这是主耶和华说的。’”