ሕዝቅኤል 23 – NASV & CCB

New Amharic Standard Version

ሕዝቅኤል 23:1-49

ሁለቱ ዘማውያት እኅትማማቾች

1የእግዚአብሔር ቃል እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፤ 2“የሰው ልጅ ሆይ፤ ከአንድ እናት የተወለዱ ሁለት ሴቶች ልጆች ነበሩ፤ 3ገና በወጣትነታቸው ዘማውያት በመሆን በግብፅ ሳሉ አመነዘሩ፤ በዚያችም ምድር አጐጠጐጤአቸው ተዳበሰ፤ የድንግልናቸውም ጕያ በእጅ ተሻሸ። 4የታላቂቱ ስም ኦሖላ፣ የእኅቷም ኦሖሊባ ነበር፤ ሁለቱም የእኔ ሆኑ፤ ወንዶችና ሴቶች ልጆችም ወለዱ። ስማቸውም፣ ኦሖላ ሰማርያ ናት፤ ኦሖሊባም ኢየሩሳሌም።

5“ኦሖላ የእኔ ሆና ሳለ በእኔ ላይ አመነዘረች፤ ጦረኞች ከሆኑት ጎረቤቶቿ ከአሦራውያን ውሽሞቿ ጋር ሴሰነች፤ 6እነርሱም ሐምራዊ የለበሱ፣ ገዦችና አዛዦች፣ ሁሉም መልከ ቀና ጐበዛዝትና ፈጣን ፈረሰኞች ነበሩ። 7እርሷ በዝሙት ራሷን ምርጥ ለሆኑት አሦራውያን ሁሉ አሳልፋ ሰጠች፤ አብረዋት ባመነዘሩት ሰዎች ጣዖት ሁሉ ረከሰች። 8በግብፅ የጀመረችውን አመንዝራነቷን አልተወችም፤ በዚያ ወንዶች በወጣትነቷ ከእርሷ ጋር ተኙ፤ የድንግልናዋን ጡት አሻሹ፤ ፍትወታቸውን አፈሰሱባት።

9“ስለዚህ አብራቸው ላመነዘረች ለአሦራውያን ውሽሞቿ አሳልፌ ሰጠኋት። 10እነርሱም ዕርቃን አስቀሯት፤ ወንዶችና ሴቶች ልጆቿን ነጠቋት፤ እርሷንም በሰይፍ ገደሏት፤ በሴቶችም ዘንድ መተረቻ ሆና ቀረች፤ ፍርድም ተፈጸመባት።

11“እኅቷ ኦሖሊባ ይህን አይታ ነበር፤ ሆኖም በፍትወቷና በዘማዊነቷ ከእኅቷ የባሰች ብልሹ ሆነች። 12ደግሞም ገዦችና አዛዦች፣ ጌጠኛ ልብስ የለበሱ ጦረኞች፣ ፈጣን ፈረሰኞችና፣ ሁሉም መልከ ቀና ከሆኑት አሦራውያን ጐበዛዝት ጋር አመነዘረች። 13ይህችም እንደ ረከሰች አየሁ፤ ሁለቱም በአንድ መንገድ ሄዱ።

14“በአመንዝራነቷ እየባሰች ሄደች፤ በደማቅ ቀይ ቀለም በግድግዳ ላይ የተቀረጹ የከለዳውያንን23፥14 ወይም የባቢሎናውያን ወንዶች ምስል አየች፤ 15እነርሱም ወገባቸውን በቀበቶ የታጠቁና በራሳቸው ላይ ተንጠልጣይ ያለው ጥምጥም የጠመጠሙ ነበሩ፤ ሁሉም የከለዳውያን23፥15 ወይም የባቢሎናውያን፤ እንዲሁም በ16 ተወላጆችና የባቢሎን ሠረገላ አዛዦች ይመስሉ ነበር። 16ባየቻቸውም ጊዜ በፍትወት ተቃጠለች፤ ወደ ከላውዴዎን መልእክተኞች ላከችባቸው። 17ባቢሎናውያንም መጥተው ወደ ፍቅር መኝታዋ ገቡ፤ በፍትወታቸውም አረከሷት፤ እርሷም በእነርሱ ከረከሰች በኋላ ጠልታቸው ከእነርሱ ዘወር አለች። 18ግልሙትናዋን በአደባባይ በፈጸመችና ዕርቃን በገለጠች ጊዜ ከእኅቷ ዘወር እንዳልሁ፣ ጠልቻት ከእርሷም ዘወር አልሁ። 19እርሷ ግን በግብፅ ያመነዘረችበት የወጣትነት ዘመኗ ትዝ እያላት የባሰ ዘማዊት ሆነች። 20በዚያም አባለዘራቸው እንደ አህያ፣ የዘር ፍሰታቸውም እንደ ድንጕላ ፈረስ ዘር ፍሰት ከሆነ ውሽሞቿ ጋር አመነዘረች፤ 21በግብፅ ምድር ጕያሽን የታሸሽበትንና የወጣትነት ጡቶችሽን የተዳበስሽበትን23፥21 ከሱርስቱ ጋር (በተጨማሪ 3 ይመ) ተመሳሳይ ሲሆን ዕብራይስጡ ግን በወጣትነት ጡቶችሽ ምክንያት የተዳበስሽበትን ይላል የኰረዳነትሽን ብልግና ተመኘሽ።

22“ስለዚህ፣ ኦሖሊባ ሆይ፤ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ጠልተሻቸው ከእነርሱ ዘወር ያልሽውን ውሽሞችሽን በአንቺ ላይ አስነሣለሁ፤ እነርሱንም ከየአቅጣጫው አመጣብሻለሁ፤ 23እነርሱም ባቢሎናውያንና ከለዳውያን ሁሉ፣ የፋቁድ፣ የሱሔና የቆዓ ሰዎች፣ ከእነርሱም ጋር አሦራውያን ሁሉ ናቸው። እነዚህም መልከ ቀና ጐበዛዝት ሲሆኑ፣ ሁላቸውም በፈረስ ላይ የተቀመጡ ገዦችና አዛዦች፣ የሠረገላ አዛዦችና ከፍተኛ ባለ ሥልጣኖች ነበሩ። 24እነርሱም የጦር መሣሪያ23፥24 በዕብራይስጥ የዚህ ቃል ትርጕም አይታወቅም፣ ሠረገላና ጋሪ በመያዝ ብዙ ሕዝብ ሆነው ይመጡብሻል፤ ትላልቅና መለስተኛ ጋሻ በማንገብና የራስ ቍር በመድፋት በየአቅጣጫው ይሰለፉብሻል፤ እኔም ለፍርድ በእጃቸው አሳልፌ እሰጥሻለሁ፤ በሕጋቸውም መሠረት ይቀጡሻል። 25የቅናት ቍጣዬን በአንቺ ላይ አመጣለሁ፤ እነርሱም በአንቺ ላይ በቍጣ ይወጣሉ፤ አፍንጫሽንና ጆሮሽን ይቈርጣሉ፤ ከአንቺ ወገን የተረፉትም በሰይፍ ይወድቃሉ። ወንዶችና ሴቶች ልጆችሽን ይወስዱብሻል፤ የተረፉትንም እሳት ይበላቸዋል። 26ልብስሽን ይገፉሻል፤ ምርጥ ጌጣጌጥሽንም ይወስዱብሻል። 27በግብፅ የጀመርሽውን ብልግናና ሴሰኝነት ከአንቺ አስወግዳለሁ፤ አንቺም ዐይንሽን ወደ እነዚህ አታነሺም፤ ከእንግዲህ ግብፅን አታስቢም።

28“ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፤ እነሆ ተጸይፈሻቸው ከእነርሱ ዘወር ላልሽው ለጠላሻቸው አሳልፌ እሰጥሻለሁ። 29እነርሱም በጥላቻ ይቀርቡሻል፤ የለፋሽበትንም ሁሉ ይቀሙሻል፤ ከማሕፀን እንደ ወጣሽ ዕርቃንሽን ያስቀሩሻል፤ የሴሰኝነትሽ ኀፍረት ይገለጣል። ብልግናሽና ገደብ የለሽ ርኩሰትሽ፣ 30ይህን አምጥተውብሻል፤ ከአሕዛብ ጋር በማመንዘር በጣዖቶቻቸው ረክሰሻልና። 31በእኅትሽ መንገድ ስለ ሄድሽ የእርሷን ጽዋ በእጅሽ አስጨብጥሻለሁ።

32“ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤

“ሰፊና ጥልቅ የሆነውን ጽዋ፣

የእኅትሽን ጽዋ ትጠጪአለሽ፤

ብዙም ስለሚይዝ ስድብና ነቀፌታ

ትጠግቢአለሽ።

33በእኅትሽ በሰማርያ ጽዋ፣

በመፍረስና በጥፋት ጽዋ፣

በስካርና በሐዘን ትሞዪአለሽ።

34ትጠጪዋለሽ፤ ትጨልጪዋለሽም፤

ከዚያም ጽዋውን ትሰባብሪዋለሽ፤

ጡትሽንም ትቈራርጪአለሽ፤

እኔ ተናግሬአለሁ፤ ይላል ጌታ እግዚአብሔር

35“ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ረስተሽኛል፤ ወደ ኋላም ገሸሽ አድርገሽኛልና የብልግናሽንና የሴሰኝነትሽን ውጤት ትሸከሚአለሽ።”

36እግዚአብሔር እንዲህ አለኝ፤ “የሰው ልጅ ሆይ፤ በኦሖላና በኦሖሊባ ትፈርዳለህን? እንግዲያውስ ጸያፍ ተግባራቸውን ንገራቸው። 37አመንዝረዋል፤ እጃቸውም በደም ተበክሏልና። ከጣዖቶቻቸው ጋር አመነዘሩ፤ የወለዱልኝን ልጆቻቸውን እንኳ ለእነርሱ መብል ይሆኑ ዘንድ በእሳት ሠውተውላቸዋል።23፥37 ወይም የወለዱልኝን ልጆች እንኳ በእሳት ውስጥ አሳለፏቸው 38ደግሞም ይህን አደረጉብኝ፤ በዚያኑ ቀን ቤተ መቅደሴን አረከሱ፤ ሰንበታቴንም አቃለሉ። 39ልጆቻቸውን ለጣዖቶቻቸው በሠዉባት ዕለት ወደ መቅደሴ ገብተው አረከሷት፤ እንግዲህ በቤቴ ውስጥ ያደረጉት እንዲህ ያለውን ነው።

40“ከዚህም በላይ ወንዶች ከሩቅ እንዲመጡላቸው መልእክተኛ ላኩ፤ እነርሱም መጡ። አንቺም ገላሽን ታጥበሽ፣ ዐይንሽን ተኵለሽና በጌጣጌጥ ተውበሽ ጠበቅሻቸው። 41በተዋበ ዐልጋ ላይ ተቀመጥሽ፤ ዕጣኔንና ዘይቴን ያኖርሽበትንም ጠረጴዛ ከዐልጋው ፊት ለፊት አደረግሽ።

42“የሚፈነጥዙ ሰዎች ድምፅ በዙሪያዋ ነበር፤ ከሚያውኩ ሰዎች ጋር ከበረሓ የመጡ ሰካራሞች ነበሩ፤ በሴትየዋና በእኅቷም ላይ አንባር፣ በራሳቸውም ላይ የተዋበ አክሊል አደረጉላቸው። 43እኔም በአመንዝራነት ሰውነቷ ስላለቀው፣ ‘እርሷ ሕይወቷ ይኸው ስለሆነ እንደ ዝሙት ዐዳሪ ይጠቀሙባት’ አልሁ። 44እነርሱም ከእርሷ ጋር ተኙ፤ ሰው ከአመንዝራ ሴት ጋር እንደሚተኛ ከእነዚያ ባለጌ ሴቶች፣ ከኦሖላና ከኦሖሊባ ጋር ተኙ። 45ጻድቃን ግን ለአመንዝራና ለነፍሰ ገዳይ ሴቶች የሚገባቸውን ፍርድ ይፈርዱባቸዋል። አመንዝሮች ናቸውና፤ እጃቸውም በደም ተበክሏል።

46“ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ሕዝብን ቀስቅሰህ አምጣባቸው፤ ለሽብርና ለዝርፊያም አሳልፈህ ስጣቸው። 47ሕዝቡ በድንጋይ ይወግራቸዋል፤ በገዛ ሰይፋቸው ይቈራርጣቸዋል፤ ወንድና ሴት ልጆቻቸውን ይገድላል፤ ቤቶቻቸውንም ያቃጥላል።

48“ስለዚህ ሴቶች ሁሉ እንዲጠነቀቁና መጥፎ ፈለጋችሁን እንዳይከተሉ፣ ሴሰኝነትን ከምድሪቱ አጠፋለሁ። 49የሴሰኝነታችሁን ዋጋ ታገኛላችሁ፤ ጣዖት በማምለክ ለፈጸማችሁት ኀጢአት ቅጣት ትሸከማላችሁ፤ በዚያን ጊዜ እኔ ጌታ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቃላችሁ።”

Chinese Contemporary Bible (Simplified)

以西结书 23:1-49

两个淫妇的比喻

1耶和华对我说: 2“人子啊,有一对同胞姊妹, 3她们在埃及做娼妓,年轻时就淫乱,任人抚摸她们的胸,玩弄她们的乳。 4姐姐名叫阿荷拉,妹妹名叫阿荷利巴。后来她们都归属了我,并且生儿育女。阿荷拉撒玛利亚阿荷利巴耶路撒冷

5阿荷拉归属我后仍然淫乱,贪恋她的情人——亚述人。 6他们都是身穿紫衣的省长和总督,都是英俊的年轻骑士。 7她便与这些亚述的精英放纵情欲,拜他们的偶像,玷污自己。 8她没有放弃在埃及的淫荡行为,她年轻的时候就任人玩弄、发泄情欲。 9因此,我把她交在她所恋慕的亚述人手里。 10他们扒光她的衣服,夺去她的儿女,用刀杀了她。她受了报应,成了妇女口中的笑柄。

11“她妹妹阿荷利巴看见这一切,不但没有引以为戒,反而更加放荡淫乱。 12她贪恋亚述的省长和总督,那些衣着华丽、英俊的年轻骑士。 13我看见她玷污了自己,与姐姐的行径如出一辙。 14她还变本加厉地放荡淫乱,看见墙上用朱砂画着迦勒底人的像, 15腰间束带,头巾飘扬,都像是来自迦勒底巴比伦人的将领, 16便恋上了他们,差遣使者到他们那里。 17巴比伦人便来上她的床,放纵情欲玷污了她。之后,她便厌弃他们。 18她继续公开地淫乱,在众人面前赤身露体,我厌弃她,像厌弃她姐姐一样。 19她却更加淫乱,怀念自己年轻时在埃及为娼的日子, 20怎样与那些体壮精足、如驴似马的情人纵淫, 21渴望重温早年的淫行,任埃及人摸胸弄乳。

22“因此,主耶和华对阿荷利巴这样说,‘我要使那些被你离弃的情人从四面八方来攻击你。 23他们是巴比伦人,还有从比割书亚哥亚来的迦勒底人以及亚述人,都是骑马的省长和总督及年轻英俊的有名将领。 24他们率领大队人马,带着兵器、战车和军需车来攻击你。他们顶盔贯甲,手拿盾牌从四面八方进攻你。我要让他们惩罚你,他们会按自己的律例来审判你。 25我要借着他们向你倾倒我的义愤,他们要在愤怒中对付你,割去你的鼻子和耳朵,掳去你的儿女,城中剩下的人都要死于刀下,被火吞噬。 26他们要剥下你的衣服,夺去你的珠宝。 27我要借此制止你从埃及染上的淫乱和放荡,使你不再向往埃及28我要把你交在你所厌恶的人手中, 29他们必满怀仇恨地对付你,夺去你努力得来的一切,留下你赤身露体,使你淫荡的丑恶公布于众。 30因为你与各国苟合,被他们的偶像玷污,这些事必临到你身上。 31你既然步你姐姐的后尘,我要让你喝她喝的那杯。’

32“主耶和华说,

“‘你必喝你姐姐那又大又深的杯,

成为人们耻笑和辱骂的对象。

33你姐姐撒玛利亚的杯盛满了恐惧和凄凉。

你喝了后必酩酊大醉,

满心忧愁。

34你必一滴不剩把它喝光,

然后把杯摔成碎片,

抓破自己的胸脯。

这是主耶和华说的。’

35“主耶和华说,‘你既忘记我,把我抛在脑后,就要受自己放荡淫乱的报应。’”

36耶和华又对我说:“人子啊,你要审判阿荷拉阿荷利巴,指出她们的丑行。 37她们淫荡,手上沾满血腥,与偶像淫乱,把为我所生的儿女烧死献给偶像。 38同时,她们还在同一天玷污我的圣所,亵渎我的安息日, 39她们焚烧自己的儿女献祭给偶像,并在当天进入我的圣所,亵渎圣所。这就是她们在我圣所里的恶行。

40“她们甚至派使者请来远方的人,并且沐浴洗身,描眉画眼,佩戴首饰, 41坐在华丽的床上,面前的桌子上摆设着我的香料和膏油。 42她们屋里传出众人的安乐声,从旷野来的酒徒和粗汉把镯子戴在这对姊妹的手腕上,把华冠戴在她们的头上。 43我说,‘她们纵欲无度、年老色衰,这些人还与她们淫乱。 44他们与这对淫妇阿荷拉阿荷利巴淫乱,好像与娼妓淫乱一样。 45她们是双手沾满血腥的淫妇,必有义人按她们应得的报应审判她们。’

46“主耶和华说,‘我要使许多人起来攻击、抢掠她们,叫她们胆战心惊。 47这些人要用石头打死她们,用刀杀戮她们和她们的儿女,用火烧毁她们的房屋。 48这样,我便制止了这地方的淫乱,所有的妇女都引以为戒,不敢效法她们。 49她们淫乱,必得报应;她们拜偶像,必受惩罚。这样,你们就知道我是主耶和华。’”