ሕዝቅኤል 21 – NASV & CCB

New Amharic Standard Version

ሕዝቅኤል 21:1-32

የቅጣት በትር የሆነችው ባቢሎን

1የእግዚአብሔር ቃል እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፤ 2“የሰው ልጅ ሆይ፤ ፊትህን ወደ ኢየሩሳሌም አዙር፤ በመቅደሱ ላይ ቃል ተናገር፤ በእስራኤል ምድር ላይ ትንቢት ተንብይ፤ 3እንዲህም በል፤ ‘እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ እኔ በአንቺ ላይ ተነሥቻለሁ፤ ሰይፌን ከሰገባው እመዝዛለሁ፤ ጻድቁንም፣ ክፉውንም ከአንተ ዘንድ አስወግዳለሁ። 4ጻድቁንም ክፉውንም ስለማስወግድ ሰይፌ ከደቡብ ጀምሮ እስከ ሰሜን ባለው ሕዝብ ሁሉ ላይ ከሰገባው ይመዘዛል። 5ሰይፌን ከሰገባው የመዘዝሁት እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ሕዝቡ ሁሉ ያውቃል፤ እርሱም ወደ ሰገባው አይመለስም።’

6“ስለዚህ የሰው ልጅ ሆይ፤ አቃስት፤ በተሰበረ ልብና በመረረ ሐዘን አቃስት፤ 7እነርሱም፣ ‘ለምን ታቃስታለህ?’ ቢሉህ፣ ‘ስለሚመጣው ክፉ ወሬ ነው፤ ልብ ሁሉ ይቀልጣል፤ እጅም ሁሉ ይዝላል፤ ነፍስ ሁሉ ይደክማል፤ ጕልበትም ሁሉ ውሃ ይሆናል’ በላቸው። እነሆ ይመጣል፤ ይፈጸማልም፤ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።”

8የእግዚአብሔር ቃል እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፤ 9“የሰው ልጅ ሆይ፤ ትንቢት ተናገር፤ እንዲህም በል፤ ‘ጌታ እንዲህ ይላል፤

“ ‘ሰይፍ! ሰይፍ!

የተሳለ የተወለወለም፤

10የተሳለው ሊገድል፣

የተወለወለውም እንደ መብረቅ ሊብረቀረቅ ነው!

“ ‘ታዲያ፣ እንዴት ደስ ሊለን ይችላል? ሰይፉ የልጄን በትረ መንግሥት እንደ ማንኛውም በትር ንቋል።

11“ ‘በእጁ እንዲያዝ፣

ሰይፉ ሊወለወል ተሰጥቷል፤

ገዳዩ በእጁ እንዲጨብጠው፣

ተስሏል፤ ተወልውሏል።

12የሰው ልጅ ሆይ፤ ይህ በሕዝቤ ላይ፣

በእስራኤልም መሳፍንት ሁሉ ላይ መጥቷልና፤

ጩኸት፣ ዋይታም አሰማ።

እነርሱ ከሕዝቤ ጋር በአንድ ላይ፣

ለሰይፍ ተጥለዋል፤

ስለዚህ ደረትህን ምታ።

13“ ‘ፈተና በርግጥ ይመጣል፤ ሰይፉ የናቀው በትረ መንግሥት ዘላቂነት ባይኖረውስ? ይላል ጌታ እግዚአብሔር።’

14“እንግዲህ፣ የሰው ልጅ ሆይ፤ ትንቢት ተናገር፤

በእጅህም አጨብጭብ፤

ሰይፉ ሁለት ጊዜ፣

ሦስት ጊዜም ይምታ፤

በእጅጉ የሚገድል፣

ለግድያ የሚሆን፣

በየአቅጣጫውም የሚከባቸው ሰይፍ ነው።

15ልብ ሁሉ ይቀልጥ ዘንድ፣

የሚወድቁትም እንዲበዙ፣

በበሮቻቸው ሁሉ፣

የግድያውን ሰይፍ21፥15 ከሰብዐ ሊቃናት ጋር ተመሳሳይ ሲሆን በዕብራይስጡ ግን የዚህ ቃል ትርጕም አይታወቅም። አኑሬአለሁ።

ወዮ! እንዲያብረቀርቅ ተወልውሏል፤

ለመግደልም ተመዝዟል።

16ሰይፍ ሆይ፤ በስለትህ አቅጣጫ ሁሉ፣

ወደ ቀኝም፣

ወደ ግራም ቍረጥ።

17እኔም በእጄ አጨበጭባለሁ፤

ቍጣዬም ይበርዳል፤

እኔ እግዚአብሔር ተናግሬአለሁ።”

18የእግዚአብሔር ቃል እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፤ 19“የሰው ልጅ ሆይ፤ የባቢሎን ንጉሥ ሰይፍ የሚመጣባቸውን የሁለት መንገዶች ካርታ ንደፍ፤ መንገዶቹም ከአንድ አገር የሚነሡ ናቸው፤ መንገዱ ወደ ከተማው በሚገነጠልበት ቦታ ላይ ምልክት አቁም። 20በአሞናውያን ከተማ በረባት ላይ ለሚመጣው ሰይፍ አንደኛውን መንገድ ምልክት አድርግ፤ በይሁዳና በተመሸገችው ከተማ በኢየሩሳሌም ላይ ለሚመጣውም ሰይፍ ሁለተኛውን መንገድ ምልክት አድርግ። 21የባቢሎን ንጉሥ በጥንቈላ ምሪት ለማግኘት በመንታ መንገድ ላይ በሁለቱ ጐዳናዎች መጋጠሚያ ላይ ይቆማል፤ ቀስቶቹን በመወዝወዝ ዕጣ ይጥላል፤ አማልክቱን ያማክራል፤ ጕበትንም ይመረምራል። 22የቅጥር መደርመሻ አምጥቶ እንዲያቆም፣ ለመግደል ትእዛዝ እንዲሰጥ፣ ፉከራ እንዲያሰማ፣ ቅጥር መደርመሻውን በከተሞች በር ላይ እንዲያደርግ፣ የዐፈር ድልድል እንዲያበጅና ምሽግ እንዲሠራ የኢየሩሳሌም ዕጣ በቀኝ እጁ ወጣ። 23ይህም ከእርሱ ጋር ቃል ኪዳን ለገቡት የተሳሳተ ምሪት ይመስላል፤ እርሱ ግን በደላቸውን ያሳስባቸዋል፤ ማርኮም ይዟቸው ይሄዳል።

24“ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘እናንተ በምታደርጉት ሁሉ ኀጢአታችሁን በመግለጽ፣ በግልጽም በማመፅ በደላችሁን ስላሳሰባችሁ፣ እንዲህም ስላደረጋችሁ በምርኮ ትወሰዳላችሁ።

25“ ‘አንተ የግፍ ጽዋህ የሞላ፣ የምትቀጣበት ቀን የደረሰ፣ ርኩስና ክፉ የእስራኤል መስፍን ሆይ፤ 26ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ጥምጥምህን አውልቅ፤ ዘውድህን ጣል፤ እንደ ከዚህ በፊቱ አይሆንም፤ ዝቅ ያለው ከፍ ይላል፤ ከፍ ያለውም ዝቅ ይላል። 27ባድማ! ባድማ! ባድማ አደርጋታለሁ፤ የሚገባው ባለ መብት እስከሚመጣ ድረስ እንደ ቀድሞው አትሆንም፤ ለእርሱም ደግሞ እሰጣታለሁ።” ’

28“አንተ የሰው ልጅ ሆይ! እንዲህ ብለህ ተናገር፤ ‘ስለ አሞናውያንና ስለ ስድባቸው ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤

“ ‘ሰይፍ! ሰይፍ!

ሊገድል የተመዘዘ፣

ሊያጠፋ የተጠረገ፣

እንደ መብረቅ ሊያብረቀርቅ የተወለወለ፤

29የታለመልህ የሐሰት ራእይ፣

የተነገረልህ የውሸት ሟርት ቢኖርም፣

የግፍ ጽዋቸው በሞላ፣

ቀናቸው በደረሰ፣

መታረድ በሚገባቸው ክፉዎች፣

ዐንገት ላይ ይሆናል።

30“ ‘ሰይፉን ወደ ሰገባው መልሰው፤

በተፈጠርህበት ምድር፣

በተወለድህበትም አገር፣

በዚያ እፈርድብሃለሁ።

31መዓቴን በላይህ አፈስሳለሁ፤

የቍጣዬንም እሳት አነድድብሃለሁ፣

በጥፋት ለተካኑ፣

ለጨካኞች ሰዎች አሳልፌ እሰጥሃለሁ።

32ለእሳት ማገዶ ትሆናለህ፣

ደምህ በምድርህ ይፈስሳል፣

ከእንግዲህ መታሰቢያ አይኖርህም፤

እኔ እግዚአብሔር ተናግሬአለሁና።’ ”

Chinese Contemporary Bible (Simplified)

以西结书 21:1-32

耶和华审判的刀

1耶和华对我说: 2“人子啊,你要面向耶路撒冷,说预言斥责以色列和圣所, 3告诉以色列,耶和华这样说,‘我要与你为敌,我要拔刀将你那里的义人和恶人一同消灭, 4从南到北不留一人, 5使世人都知道我耶和华已拔刀出鞘,不再收回。’ 6人子啊,你要在他们面前哀叹,要伤心欲绝地哀叹。 7如果有人问你为什么哀叹,你就说有噩耗传来,听见的人都胆战心惊、两手发软、精神萎靡、膝弱如水。灾难必很快发生。这是主耶和华说的。”

8耶和华对我说: 9“人子啊,你要说预言,告诉他们,耶和华这样说,

“‘有一把刀,

有一把刀磨快擦亮了,

10磨得锋利,为要杀戮,

擦得亮如闪电。

我们岂能因我儿的权杖而快乐?这刀鄙视一切权杖。 11这刀已交给人去擦亮,好握在手中,这刀已磨快擦亮,预备交给屠杀的人。 12人子啊,号啕大哭吧,因为这刀要攻击我的子民和所有以色列的首领,他们都要死于刀下。所以你要捶胸顿足。 13这刀必试验他们,这刀所鄙视的权杖若不复存在,怎么办呢?这是主耶和华说的。’

14“人子啊,你要拍掌对他们说预言,你要拿刀挥舞两三次,预示这刀要从四面八方大肆杀戮, 15使他们吓得肝胆俱裂,许多人倒在家门口。我已赐下这亮如闪电的刀,用来杀戮。 16刀啊,你要左砍右劈,大肆杀戮。 17我要拍掌,我的烈怒要平息。这是我耶和华说的。”

18耶和华对我说: 19“人子啊,你要为巴比伦王的刀画出两条进攻之路,两条路要从一个地方出发,要在通往城邑的路口设路标。 20一条路通往亚扪拉巴城,一条路通往犹大的坚城耶路撒冷21巴比伦王将站在两路的岔口,摇签求问他的神像,察看祭牲的肝。 22他右手拿到的是攻打耶路撒冷的签,于是,他用撞城锤来攻耶路撒冷的城门,厮杀吶喊,建垒筑台围攻城池。 23犹大人必认为这是虚假的征兆。他们曾向巴比伦王发誓效忠,但巴比伦王要使他们想起自己的罪,并掳走他们。

24“主耶和华说,‘因为你们的过犯昭然若揭,你们的罪恶表露无遗,因此,你们必遭掳掠。 25你这邪恶败坏的以色列首领啊!你的结局到了,审判你的日子来了。’ 26主耶和华说,‘取下你的头巾,摘下你的冠冕吧,时局转变了。要提拔卑微的,贬抑高贵的。 27毁灭,毁灭,我要毁灭这国,使它荡然无存,直到那应得的人来到后,这国才能得到重建,我要把这国交给他。’

28“人子啊,你要说有关亚扪人及其耻辱的预言,告诉他们,主耶和华说,‘有刀,有刀已出鞘,为要杀戮;它亮如闪电,要行毁灭。 29有关你们的异象和占卜是虚假的,你们将与其他恶人一同被杀,因为你们的结局到了,审判你们的日子来了。 30你们要收刀入鞘,我要在你们的家乡,在你们的出生之地审判你们, 31我要把烈怒倒在你们身上,将我的怒火喷在你们身上,把你们交在嗜杀成性的恶徒手中, 32你们必被当作柴焚烧,你们的血必流在自己的土地上,无人再记得你们。因为这是我耶和华说的。’”