民数记 28 – CCB & NASV

Chinese Contemporary Bible (Simplified)

民数记 28:1-31

日常献祭的条例

1耶和华对摩西说: 2“你告诉以色列人,要在规定的时间献上蒙我悦纳的馨香火祭,作为我的食物。 3以下是他们要献给耶和华的火祭。

“每天两只毫无残疾、一岁的公羊羔作燔祭, 4早晨和傍晚各献一只, 5同时献上素祭——一公斤细面粉调上一升油。 6这是在西奈山上规定的日常燔祭,是献给耶和华的馨香火祭。 7与每只羊羔一同献上的还有一升酒,要将酒洒在圣所作为献给耶和华的奠祭。 8傍晚献羊羔时,也要像早上一样同时献上素祭和奠祭,作蒙耶和华悦纳的馨香火祭。

安息日献的祭

9“安息日,要献两只毫无残疾、一岁的公羊羔,同时献上奠祭以及两公斤调油的细面粉作素祭。 10这是在日常燔祭和奠祭以外安息日所献的燔祭。

初一献的祭

11“在朔日,要给耶和华献燔祭——两头公牛犊、一只公绵羊和七只一岁的公羊羔,都要毫无残疾。 12同时要献上调了油的细面粉作素祭,每头公牛需献三公斤素祭,每只公绵羊需献两公斤素祭, 13每只公羊羔需献一公斤素祭。这馨香的燔祭是献给耶和华的火祭。 14献燔祭时要同时献上奠祭,每头公牛需献二升奠酒,每只公绵羊需献一点二升奠酒,每只羊羔需献一升奠酒。这是朔日要献的燔祭,一年之中月月如此。 15除了日常的燔祭和奠祭以外,还要把一只公山羊献给耶和华作赎罪祭。

逾越节献的祭

16“一月十四日是耶和华的逾越节, 17十五日开始节庆,你们要连续七天吃无酵饼。 18第一天要举行圣会,不可做日常工作。 19你们要把毫无残疾的两头公牛犊、一只公绵羊和七只一岁的公羊羔献给耶和华作燔祭; 20同时要献上调了油的细面粉作素祭,每头公牛需献三公斤素祭,每只公绵羊需献两公斤素祭, 21每只公羊羔需献一公斤素祭; 22同时还要献一只公山羊作赎罪祭,为你们赎罪。 23除了早晨献的日常燔祭以外,要献上这些祭物。 24接连七天,除了日常的燔祭和同献的奠祭以外,还要照上面的规定给耶和华献上馨香的火祭。 25第七天,你们要举行圣会,不可做日常工作。

七七收获节献的祭

26“七七收获节庄稼初熟之日,就是你们把新素祭献给耶和华的日子,不可工作,要举行圣会。 27你们要把两头公牛犊、一只公绵羊和七只一岁的公羊羔献给耶和华作馨香的燔祭。 28同时要献上调了油的细面粉作素祭,每头公牛需献三公斤素祭,每只公绵羊需献两公斤素祭, 29每只公羊羔需献一公斤素祭。 30此外,还要献上一只公山羊作赎罪祭,为你们赎罪。 31除了日常的燔祭和同献的素祭以外,还要献上奠祭。祭牲不可有残疾。

New Amharic Standard Version

ዘኍል 28:1-31

የየዕለቱ መሥዋዕት

1እግዚአብሔር (ያህዌ) ሙሴን እንዲህ አለው፤ 2“ይህን ትእዛዝ ለእስራኤላውያን እንዲህ ብለህ ስጣቸው፤ ‘ሽታው ደስ እንዲያሰኘኝ በእሳት የሚቀርብልኝን የምግብ ቍርባን የተወሰነውን ጊዜ ጠብቃችሁ አቅርቡልኝ።’ 3ደግሞም እንዲህ በላቸው፤ ‘በእሳት ለእግዚአብሔር (ያህዌ) የምታቀርቡት መሥዋዕት ይህ ነው፤ አንድ ዓመት የሆናቸውንና እንከን የሌለባቸውን ሁለት ተባዕት የበግ ጠቦቶች መደበኛ የሚቃጠል መሥዋዕት በማድረግ በየዕለቱ አቅርቡ። 4አንዱን ጠቦት ጧት ሌላውን ደግሞ ማታ አቅርቡ፤ 5ከዚህም ጋር ተወቅጦ በተጠለለ በሂን28፥5 አንድ ሊትር ያህል ነው። አንድ አራተኛ የወይራ ዘይት የተለወሰ የኢፍ28፥5 ሁለት ሊትር ያህል ነው። አንድ ዐሥረኛ ልም ዱቄት የእህል ቍርባን አዘጋጁ። 6ይህም ሽታው ደስ እንዲያሰኝ በእሳት ለእግዚአብሔር (ያህዌ) የሚቀርብ ምሥዋዕት ሲሆን፣ በሲና ተራራ የተደነገገ መደበኛ የሚቃጠል መሥዋዕት ነው። 7ከእያንዳንዱ ጠቦት ጋር አብሮት የሚቀርበውም የመጠጥ ቍርባን ፈልቶ የወጣለት የሂን አንድ አራተኛ መጠጥ ይሆናል፤ የመጠጡንም ቍርባን በተቀደሰው ቦታ ላይ ለእግዚአብሔር (ያህዌ) አፍስሱት። 8ሁለተኛውንም ጠቦት ጧት ባቀረባችሁት ዐይነት አድርጋችሁ ከእህል ቍርባኑና ከመጠጥ ቍርባኑ ጋር ማታ አቅርቡት፤ ይህም ሽታው እግዚአብሔርን (ያህዌ) ደስ የሚያሰኝ በእሳት የሚቀርብ መሥዋዕት ነው።

የሰንበት መሥዋዕት

9“ ‘በሰንበት ዕለት፣ አንድ ዓመት የሆናቸውንና እንከን የማይገኝባቸውን ሁለት ተባዕት የበግ ጠቦቶች መሥዋዕት ከመጠጥ ቍርባኑና በዘይት ከተለወሰ የኢፍ28፥9 አራት ተኩል ሊትር ያህል ነው። ሁለት ዐሥረኛ ልም ዱቄት ጋር አቅርቡ። 10ይህም ከመጠጥ ቍርባኑ ጋር በመደበኛነት ከሚቀርበው የሚቃጠል መሥዋዕት ሌላ በየሰንበቱ የሚቀርብ የሚቃጠል መሥዋዕት ነው።

የየወሩ መሥዋዕት

11“ ‘በየወሩ መባቻ እንከን የሌለባቸውን ሁለት ወይፈኖች፣ አንድ አውራ በግ፣ ዓመት የሆናቸውን ሰባት ተባዕት የበግ ጠቦቶችን የሚቃጠል መሥዋዕት አድርጋችሁ ለእግዚአብሔር (ያህዌ) አቅርቡ። 12ከእያንዳንዱ ወይፈን ጋር ለእህል ቍርባን የሚሆን በዘይት የተለወሰ የኢፍ28፥12 ስድስት ተኩል ሊትር ያህል ነው። ሦስት ዐሥረኛ ልም ዱቄት፣ ከአውራውም በግ ለእህል ቍርባን የሚሆን በዘይት የተለወሰ የኢፍ ሁለት ዐሥረኛ ልም ዱቄት ይቀርባል፤ 13እንደዚሁም ከእያንዳንዱ የበግ ጠቦት ጋር ለእህል ቍርባን የሚሆን በዘይት የተለወሰ የኢፍ አንድ ዐሥረኛ ልም ዱቄት አቅርቡ፤ ይህም ለሚቃጠል መሥዋዕት ሲሆን ሽታው ደስ የሚያሰኝና በእሳት ለእግዚአብሔር (ያህዌ) የሚቀርብ መሥዋዕት ነው። 14ከእያንዳንዱ ወይፈን ጋር ለመጠጥ ቍርባን የሚሆን የኢን28፥14 ሁለት ሊትር ያህል ነው። ግማሽ የወይን ጠጅ፣ ከአውራው በግ ጋር የኢን28፥14 አንድ ሊትር ያህል ነው። አንድ ሦስተኛ፣ ከእያንዳንዱም የበግ ጠቦት ጋር የኢን አንድ አራተኛ የወይን ጠጅ ይቅረብ፤ ይህም በየወሩ መባቻ ዓመቱን ሙሉ የሚቀርብ የሚቃጠል መሥዋዕት ነው። 15ከመጠጥ ቍርባኑ ጋር በመደበኛነት ከሚቀርበው የሚቃጠል መሥዋዕት ሌላ አንድ ተባዕት ፍየል የኀጢአት መሥዋዕት ሆኖ ለእግዚአብሔር (ያህዌ) ይቀርባል።

ፋሲካ

28፥16-25 ተጓ ምብ – ዘፀ 12፥14-20ዘሌ 23፥4-8ዘዳ 16፥1-8

16“ ‘የመጀመሪያው ወር በገባ በዐሥራ አራተኛው ቀን የእግዚአብሔር (ያህዌ) ፋሲካ በዓል ይከበራል። 17በዚሁ ወር በዐሥራ አምስተኛው ቀን በዓል ይሆናል፤ እስከ ሰባትም ቀን ድረስ ያለ እርሾ የተጋገረ ቂጣ ብሉ። 18በመጀመሪያው ቀን የተቀደሰ ጉባኤ አድርጉ፤ የዘወትር ተግባራችሁንም አትሥሩበት። 19እንከን የሌለባቸው ሁለት ወይፈኖች፣ አንድ አውራ በግና ዓመት የሆናቸው ሰባት ተባዕት የበግ ጠቦቶች በእሳት የሚቃጠል መሥዋዕት በማድረግ ለእግዚአብሔር (ያህዌ) አቅርቡ። 20ከእያንዳንዱም ወይፈን ጋር ለእህል ቍርባን የሚሆን በዘይት የተለወሰ የኢፍ ሦስት ዐሥረኛ ልም ዱቄት፣ ከአውራውም በግ ጋር የኢፍ ሁለት ዐሥረኛ ልም ዱቄት አቅርቡ፤ 21ከሰባቱም የበግ ጠቦቶች ከእያንዳንዳቸው ጋር የኢፍ አንድ ዐሥረኛ ልም ዱቄት አዘጋጁ። 22በተጨማሪም ማስተስረያ እንዲሆናችሁ አንድ ተባዕት ፍየል የኀጢአት መሥዋዕት አድርጋችሁ አቅርቡ። 23እነዚህንም ጧት ጧት በመደበኛነት ከሚቀርበው የሚቃጠል መሥዋዕት ጋር አቅርቧቸው። 24በዚህም ዐይነት ሽታው እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ ሆኖ በየዕለቱ ለሰባት ቀን በእሳት ለሚቀርብ መሥዋዕት የምግብ ቍርባን አዘጋጁ፤ ይህም ከመጠጥ ቍርባኑ ጋር በመደበኛነት ከሚቀርበው የሚቃጠል መሥዋዕት ጋር ሆኖ በተጨማሪ ይቀርባል። 25በሰባተኛው ቀን የተቀደሰ ጉባኤ አድርጉ፤ የዘወትር ተግባርም አትሥሩበት።

የሳምንቱ በዓል

28፥26-31 ተጓ ምብ – ዘሌ 23፥15-22ዘዳ 16፥9-12

26“ ‘በየሳምንቱ በሚደረገው በዓል፣ አዲስ የእህል ቍርባን ለእግዚአብሔር (ያህዌ) በምታቀርቡበት በፍሬ በኵራት ቀን የተቀደሰ ጉባኤ አድርጉ፤ የዘወትር ተግባርም አትሥሩበት። 27ሁለት ወይፈኖች፣ አንድ አውራ በግና ዓመት የሆናቸውን ሰባት ተባዕት የበግ ጠቦቶች ሽታው እግዚአብሔርን (ያህዌ) ደስ የሚያሰኝ አድርጋችሁ የሚቃጠል መሥዋዕት አቅርቡ። 28ከእያንዳንዱም ወይፈን ጋር ለእህል ቍርባን የሚሆን በዘይት የተለወሰ የኢፉ ሦስት ዐሥረኛ፣ ከአውራው በግ ጋር የኢፍ ሁለት ዐሥረኛ ልም ዱቄት ይቀርባል፤ 29ከሰባቱም የበግ ጠቦቶች ከእያንዳንዳቸው ጋር የኢፉ አንድ ዐሥረኛ ልም ዱቄት ይቅረብ። 30በተጨማሪም ማስተስረያ እንዲሆንላችሁ አንድ ተባዕት ፍየል አቅርቡ። 31ከእህል ቍርባኑ ጋር በመደበኛነት ከሚቀርበው የሚቃጠል መሥዋዕት በተጨማሪ፣ እነዚህን ከመጠጥ ቍርባናቸው ጋር አቅርቡ። እንስሳቱም እንከን የሌላቸው መሆናቸውን አረጋግጡ።