民数记 27 – CCB & NASV

Chinese Contemporary Bible (Simplified)

民数记 27:1-23

女儿的继承权

1西罗非哈约瑟之子玛拿西的玄孙、玛吉的曾孙、基列的孙子、希弗的儿子。他的女儿是玛拉挪阿曷拉密迦得撒。她们前来, 2站在会幕门口对摩西以利亚撒祭司、众首领和全体会众说: 3“我们的父亲死在旷野,他并没有跟可拉一伙一起反叛耶和华,而是因自己的罪而死,没有留下儿子。 4难道因为他没有儿子,他的名字就要从族中消失吗?请让我们在父亲的家族中分一份产业吧。” 5摩西就把她们的请求呈到耶和华面前。 6耶和华对摩西说: 7西罗非哈的女儿说得有理。你要从她们父亲的家族中分一份产业给她们,让她们继承父亲的产业。 8你要告诉以色列人,‘人死后如果没有儿子,就由女儿继承产业; 9如果没有女儿,就由其兄弟继承; 10如果没有兄弟,就由其父的兄弟继承; 11如果其父没有兄弟,就由其族中最近的亲属继承。’”这是耶和华吩咐摩西颁布给以色列人的律例。

约书亚接替摩西做首领

12耶和华对摩西说:“你上亚巴琳山去眺望我赐给以色列人的土地。 13看了以后,你就要像你哥哥亚伦一样去祖先那里了。 14因为会众在旷野反叛我的时候,你们二人没有按照我的指示取水,没有在他们面前尊我为圣。”耶和华指的是米利巴泉事件,发生在旷野的加低斯15摩西对耶和华说: 16“耶和华啊,你是赐人生命的上帝,求你立一个人做会众的首领, 17带领他们或进或退,免得你的会众像没有牧人的羊群。” 18耶和华对摩西说:“的儿子约书亚心里有圣灵,你把他召来,按手在他身上, 19让他站在以利亚撒祭司和全体会众面前,当着他们的面任命他做首领, 20把你的权柄赐给他,使以色列全体会众都听从他。 21遇到事情,他要去以利亚撒祭司那里,让祭司借着乌陵为他求问我。他和全体会众或进或出都要听从以利亚撒的指示。” 22摩西遵命而行,把约书亚召来,让他站在以利亚撒祭司和全体会众面前, 23然后照耶和华的吩咐按手在他的头上,任命他做首领。

New Amharic Standard Version

ዘኍል 27:1-23

የሰለጰዓድ ሴት ልጆች

1የምናሴ ልጅ፣ የማኪር ልጅ፣ የገለዓድ ልጅ፣ የአፌር ልጅ፣ የሰለጰዓድ ሴት ልጆች ከዮሴፍ ልጅ ከምናሴ ጐሣዎች ነበሩ፤ ስማቸውም ማህለህ፣ ኑዓ፣ ዔግላ፣ ሚልካና ቲርጻ ይባላል። እነርሱም፣ 2ወደ መገናኛው ድንኳን መግቢያ ቀረቡ፤ በሙሴ፣ በካህኑ በአልዓዛር፣ በመሪዎችና በመላው ማኅበርም ፊት ቆመው እንዲህ አሉ፤ 3“አባታችን በምድረ በዳ ሞተ፤ ተባብረው በእግዚአብሔር (ያህዌ) ላይ ካመፁት ከቆሬ ተከታዮች ጋር አልነበረም፤ የሞተው ግን በራሱ ኀጢአት ሲሆን፣ ወንዶች ልጆችም አልነበሩትም። 4ታዲያ አባታችን ወንድ ልጅ ባለመውለዱ ስሙ ከጐሣዎቹ ተለይቶ እንዴት ይጠፋል? ለእኛም በአባታችን ዘመዶች መካከል ርስት ስጡን።”

5ስለዚህ ሙሴ ጕዳያቸውን ወደ እግዚአብሔር (ያህዌ) አቀረበ፤ 6እግዚአብሔርም (ያህዌ) እንዲህ አለው፤ 7“የሰለጰዓድ ልጆች ጥያቄ ትክክል ነው፤ በርግጥ በአባታቸው ዘመዶች መካከል ድርሻቸውን ርስት አድርገህ ልትሰጣቸው ስለሚገባ የአባታቸውን ድርሻ ለእነርሱ አስተላልፍላቸው።

8“እስራኤላውያንን እንዲህ በላቸው፤ ‘አንድ ሰው ወንድ ልጅ ሳይተካ ቢሞት ውርሱን ለሴት ልጁ አስተላልፉ። 9ሴት ልጅ ከሌለችው ደግሞ ውርሱን ለወንድሞቹ ስጡ። 10ወንድሞች ከሌሉትም ውርሱን ለአባቱ ወንድሞች ስጡ። 11አባቱ፣ ወንድሞች ከሌሉት ውርሱን ከጐሣው መካከል ቅርብ ለሆነ ዘመዱ ይስጥ፤ እርሱም ይውረሰው። ይህም እግዚአብሔር (ያህዌ) ሙሴን ባዘዘው መሠረት ለእስራኤላውያን ሕጋዊ መመሪያ ይሆናቸዋል።’ ”

ኢያሱ በሙሴ እግር ተተካ

12ከዚያም እግዚአብሔር (ያህዌ) ሙሴን እንዲህ አለው፤ “በዓባሪም ሸንተረር ላይ ወዳለው ወደዚህ ተራራ ውጣና ለእስራኤላውያን የሰጠኋቸውን ምድር እይ። 13ካየኸውም በኋላ አንተም እንደ ወንድምህ እንደ አሮን ወደ ሕዝብህ ትሰበሰባለህ፤ 14ምክንያቱም ማኅብረ ሰቡ በጺን ምድረ በዳ ባለው ውሃ አጠገብ ባመፁ ጊዜ እኔን በሕዝቡ ፊት ቅዱስ አድርጋችሁ ለማክበር ሁለታችሁም ትእዛዜን ስላልጠበቃችሁ ነው።” ይህም በጺን ምድረ በዳ በቃዴስ የሚገኝ የመሪባ ውሃ ነው።

15ሙሴ እግዚአብሔርን (ያህዌ) እንዲህ አለው፤ 16“የሰብአዊ ፍጡር ሁሉ መንፈስ አምላክ (ኤሎሂም) የሆነ ጌታ እግዚአብሔር (ያህዌ) በዚህ ማኅበረ ሰብ ላይ ሰው ይሹም፤ 17እርሱም፣ የእግዚአብሔር (ያህዌ) ሕዝብ እረኛ እንደሌለው የበግ መንጋ እንዳይሆን በፊቱ የሚወጣና የሚገባ፣ መርቶ የሚያወጣውና የሚያገባው እንዲሆን ነው።”

18ስለዚህም እግዚአብሔር (ያህዌ) ሙሴን እንዲህ አለው፤ “መንፈስ ቅዱስ27፥18 ወይም መንፈስ ያደረበትን የነዌን ልጅ ኢያሱን ወስደህ እጅህን ጫንበት። 19በካህኑ በአልዓዛርና በመላው ማኅበር ፊት እንዲቆም አድርገው፤ በፊታቸውም ሹመው፤ 20መላው የእስራኤል ማኅበረ ሰብ እንዲታዘዝለትም ከሥልጣንህ ከፍለህ ስጠው። 21እርሱም በእግዚአብሔር (ያህዌ) ፊት ሆኖ በኡሪም በመጠየቅ ውሳኔ በሚያስገኝለት በካህኑ በአልዓዛር ፊት ይቆማል፤ እርሱም ሆነ መላው የእስራኤል ማኅበረ ሰብ በአልዓዛር ትእዛዝ ይወጣሉ፤ በእርሱም ቃል ይገባሉ።”

22ሙሴም እግዚአብሔር (ያህዌ) እንዳዘዘው አደረገ፤ ኢያሱንም ወስዶ በካህኑ በአልዓዛርና በመላው የእስራኤል ማኅበር ፊት አቆመው፤ 23ከዚያም እግዚአብሔር (ያህዌ) በሙሴ አማካይነት ባዘዘው መሠረት እጁን በራሱ ላይ ጭኖ ሾመው።