民数记 29 – CCB & NASV

Chinese Contemporary Bible (Simplified)

民数记 29:1-40

吹号节献的祭

1“七月一日,你们不可工作,要举行圣会,吹响号角。 2你们要把馨香的燔祭献给耶和华,即毫无残疾的公牛犊一头、公绵羊一只和一岁的公羊羔七只; 3同时要献上调了油的细面粉作素祭,每头公牛犊需献三公斤素祭,每只公绵羊需献两公斤素祭, 4每只公羊羔需献一公斤素祭; 5还要献上一只公山羊作赎罪祭,为你们赎罪。 6此外,要照常献上朔日和日常应献的燔祭、素祭和奠祭,给耶和华作馨香的火祭。

赎罪日献的祭

7“七月十日,你们要举行圣会,禁食,不可工作。 8你们要给耶和华献上馨香的燔祭,即毫无残疾的公牛犊一头、公绵羊一只和一岁的公羊羔七只; 9同时要献上调了油的细面粉作素祭,每头公牛犊需献三公斤素祭,每只公绵羊需献两公斤素祭, 10每只公羊羔需献一公斤素祭; 11还要献上一只公山羊作赎罪祭。此外,要照常献上赎罪祭和日常献的燔祭、素祭和奠祭。

住棚节献的祭

12“在七月十五日那一天,你们要举行圣会,不可工作,为耶和华守节期七天。 13你们要给耶和华献上馨香的燔祭,即毫无残疾的公牛犊十三头、公绵羊两只和一岁的公羊羔十四只; 14同时要献上调了油的细面粉作素祭,每头公牛犊需献三公斤素祭,每只公绵羊需献两公斤素祭, 15每只公羊羔需献一公斤素祭; 16还要献上一只公山羊作赎罪祭。此外,要照常献上日常的燔祭、素祭和奠祭。

17“节期的第二天,你们要献上毫无残疾的公牛犊十二头、公绵羊两只和一岁的公羊羔十四只; 18同时要把一定数量的素祭和奠祭与公牛犊、公绵羊和公羊羔一起献上。 19除了日常献的燔祭、素祭和奠祭以外,还要献上一只公山羊作赎罪祭。

20“节期的第三天,你们要献上毫无残疾的公牛十一头、公绵羊两只和一岁的公羊羔十四只; 21同时要把一定数量的素祭和奠祭与公牛、公绵羊和公羊羔一起献上。 22除了日常献的燔祭、素祭和奠祭以外,还要献上一只公山羊作赎罪祭。

23“节期的第四天,你们要献上毫无残疾的公牛十头、公绵羊两只和一岁的公羊羔十四只; 24同时要把一定数量的素祭和奠祭与公牛、公绵羊和公羊羔一起献上。 25除了日常献的燔祭、素祭和奠祭以外,还要献上一只公山羊作赎罪祭。

26“节期的第五天,你们要献上毫无残疾的公牛九头、公绵羊两只和一岁的公羊羔十四只; 27同时要把一定数量的素祭和奠祭与公牛、公绵羊和公羊羔一起献上。 28除了日常献的燔祭、素祭和奠祭以外,还要献上一只公山羊作赎罪祭。

29“节期的第六天,你们要献上毫无残疾的公牛八头、公绵羊两只和一岁的公羊羔十四只; 30同时要把一定数量的素祭和奠祭与公牛、公绵羊和公羊羔一起献上。 31除了日常献的燔祭、素祭和奠祭以外,还要献上一只公山羊作赎罪祭。

32“节期的第七天,你们要献上毫无残疾的公牛七头、公绵羊两只和一岁的公羊羔十四只; 33同时要把一定数量的素祭和奠祭与公牛、公绵羊和公羊羔一起献上。 34除了日常献的燔祭、素祭和奠祭以外,还要献上一只公山羊作为赎罪祭。

35“节期的第八天,你们不可工作,要举行庄严的聚会。 36你们要给耶和华献上馨香的燔祭,即毫无残疾的公牛一头、公绵羊一只和一岁的公羊羔七只; 37同时要把一定数量的素祭和奠祭与公牛、公绵羊和公羊羔一起献上。 38除了日常献的燔祭、素祭和奠祭以外,还要献上一只公山羊作赎罪祭。

39“这些是你们在节期内要献给耶和华的祭物,不包括你们许愿和自愿献的燔祭、素祭、奠祭和平安祭。”

40摩西把耶和华的一切吩咐传达给以色列人。

New Amharic Standard Version

ዘኍል 29:1-40

የመለከት በዓል

29፥1-6 ተጓ ምብ – ዘሌ 23፥23-25

1“ ‘በሰባተኛው ወር በመጀመሪያው ቀን የተቀደሰ ጉባኤ አድርጉ፤ የዘወትር ሥራም አትሥሩበት፤ ይህም የመለከት ድምፅ የምታሰሙበት ቀናችሁ ነው። 2እንከን የሌለባቸውን አንድ ወይፈን፣ አንድ አውራ በግና ዓመት የሆናቸው ሰባት ተባዕት የበግ ጠቦቶች ሽታው እግዚአብሔርን (ያህዌ) ደስ የሚያሰኝ የሚቃጠል መሥዋዕት አድርጋችሁ አቅርቡ። 3ከወይፈኑ ጋር ለእህል ቍርባን የሚሆን የኢፍ29፥3 ስድስት ተኩል ሊትር ያህል ነው። ሦስት ዐሥረኛ፣ ከአውራውም በግ ጋር የኢፍ ሁለት ዐሥረኛ፣29፥3 አራት ተኩል ሊትር ያህል ነው። በዘይት የተለወሰ ልም ዱቄት አቅርቡ፤ 4ከእያንዳንዱም ሰባት የበግ ጠቦት ጋር በዘይት የተለወሰ የኢፍ አንድ ዐሥረኛ29፥4 ሁለት ሊትር ያህል ነው። ልም ዱቄት አዘጋጁ። 5ማስተስረያ እንዲሆናችሁም አንድ ተባዕት ፍየል የኀጢአት መሥዋዕት በማድረግ በተጨማሪ አቅርቡ። 6እነዚህ እንግዲህ በተደነገገው መሠረት ከእህል ቍርባናቸውና ከመጠጥ ቍርባናቸው ጋር በየዕለቱና በየወሩ ከሚቀርቡት የሚቃጠሉ መሥዋዕቶች ሌላ ተጨማሪ ሆነው፣ ለእግዚአብሔር (ያህዌ) ሽታቸው ደስ የሚያሰኝ በእሳት የሚቀርቡ መሥዋዕቶች ናቸው።

የማስተስረያ ቀን

29፥7-11 ተጓ ምብ – ዘሌ 16፥2-3423፥26-32

7“ ‘በዚሁ በሰባተኛው ወር በዐሥረኛውም ቀን የተቀደሰ ጉባኤ አድርጉ፤ ራሳችሁን አዋርዱ፤29፥7 ወይም ጹሙ ሥራም አትሥሩ። 8ሁሉም እንከን የሌለባቸው አንድ ወይፈን፣ አንድ አውራ በግና ዓመት የሆናቸው ሰባት ተባዕት የበግ ጠቦቶች፣ ሽታው እግዚአብሔርን (ያህዌ) ደስ የሚያሰኝ የሚቃጠል መሥዋዕት አድርጋችሁ አቅርቡ። 9ከወይፈኑ ጋር ለእህል ቍርባን የሚሆን የኢፍ ሦስት ዐሥረኛ፣ ከአውራ በጉ ጋር የኢፍ ሁለት ዐሥረኛ በዘይት የተለወሰ ዱቄት አቅርቡ፤ 10ከሰባቱ የበግ ጠቦቶችም ከእያንዳንዳቸው ጋር በዘይት የተለወሰ የኢፍ አንድ ዐሥረኛ ልም ዱቄት አዘጋጁ። 11ማስተስረያ እንዲሆንም ለኀጢአት መሥዋዕት ከሚቀርበው እንዲሁም ከእህሉ ቍርባንና ከመጠጡ ቍርባን ጋር በመደበኛነት ቀርቦ ከሚቃጠለው መሥዋዕት ሌላ አንድ ተባዕት ፍየል የኀጢአት መሥዋዕት አድርጋችሁ በተጨማሪ አቅርቡ።

የዳስ በዓል

29፥12-39 ተጓ ምብ – ዘሌ 23፥33-43ዘዳ 16፥13-17

12“ ‘በሰባተኛው ወር በዐሥራ አምስተኛው ቀን የተቀደሰ ጉባኤ አድርጉ፤ የዘወትር ሥራ አትሥሩ፤ ለእግዚአብሔርም (ያህዌ) የሰባት ቀን በዓል አክብሩ። 13ሁሉም እንከን የሌለባቸው ዐሥራ ሦስት ወይፈኖች፣ ሁለት አውራ በጎችና ዓመት የሆናቸው ዐሥራ ሁለት ተባዕት የበግ ጠቦቶች የሚቃጠል መሥዋዕት በማድረግ ሽታው እግዚአብሔርን (ያህዌ) ደስ እንዲያሰኝ በእሳት አቅርቡ። 14ከዐሥራ ሦስቱ ወይፈኖች ከእያንዳንዳቸው ጋር የኢፍ ሦስት ዐሥረኛ፣ ከሁለቱ አውራ በጎችም ከእያንዳንዳቸው ጋር የኢፍ ሁለት ዐሥረኛ በዘይት የተለወሰ ልም ዱቄት የእህል ቍርባን አቅርቡ፤ 15እንዲሁም ከዐሥራ አራቱ ተባዕት የበግ ጠቦቶች ከእያንዳንዳቸው ጋር የኢፍ አንድ ዐሥረኛ በዘይት የተለወሰ ልም ዱቄት የእህል ቍርባን አቅርቡ። 16ከእህሉ ቍርባንና ከመጠጡ ቍርባን ጋር በመደበኛነት ከሚቀርበው የሚቃጠል መሥዋዕት ሌላ አንድ ተባዕት ፍየል የኀጢአት መሥዋዕት አድርጋችሁ በተጨማሪ አቅርቡ።

17“ ‘በሁለተኛው ቀን ሁሉም እንከን የሌለባቸው ዐሥራ ሁለት ወይፈኖች፣ ሁለት አውራ በጎችና ዓመት የሆናቸው ዐሥራ አራት ተባዕት የበግ ጠቦቶች አቅርቡ። 18ከወይፈኖቹ፣ ከአውራ በጎቹና ከበግ ጠቦቶቹ ጋር በተወሰነው ቍጥር መሠረት የእህል ቍርባናቸውንና የመጠጥ ቍርባናቸውን አብራችሁ አቅርቡ። 19ደግሞም ከእህሉ ቍርባንና ከመጠጡ ቍርባን ጋር በመደበኛነት ከሚቀርበው የሚቃጠል መሥዋዕት ሌላ አንድ አውራ ፍየል የኀጢአት መሥዋዕት አድርጋችሁ በተጨማሪ አቅርቡ።

20“ ‘በሦስተኛው ቀን ሁሉም እንከን የሌለባቸው ዐሥራ አንድ ወይፈኖች፣ ሁለት አውራ በጎችና ዓመት የሆናቸው ዐሥራ አራት ተባዕት የበግ ጠቦቶች አቅርቡ። 21ከወይፈኖቹ፣ ከአውራ በጎቹና ከበግ ጠቦቶቹ ጋር የእህል ቍርባናቸውንና የመጠጥ ቍርባናቸውን በተወሰነው ቍጥር መሠረት አብራችሁ አቅርቡ። 22ደግሞም ከእህሉ ቍርባንና ከመጠጡ ቍርባን ጋር በመደበኛነት ከሚቀርበው የሚቃጠል መሥዋዕት ሌላ አንድ ተባዕት ፍየል የኀጢአት መሥዋዕት አድርጋችሁ በተጨማሪ አቅርቡ።

23“ ‘በአራተኛው ቀን ሁሉም እንከን የሌለባቸው ዐሥር ወይፈኖች፣ ሁለት አውራ በጎችና ዓመት የሆናቸው ዐሥራ አራት ተባዕት የበግ ጠቦቶች አቅርቡ። 24ከወይፈኖቹ፣ ከአውራ በጎቹና ከጠቦቶቹ ጋር የእህል ቍርባናቸውንና የመጠጥ ቍርባናቸውን በተደነገገው ቍጥር መሠረት አቅርቡ። 25ደግሞም ከእህሉ ቍርባንና ከመጠጡ ቍርባን ጋር በመደበኛነት ከሚቀርበው የሚቃጠል መሥዋዕት ሌላ አንድ ተባዕት ፍየል የኀጢአት መሥዋዕት አድርጋችሁ በተጨማሪ አቅርቡ።

26“ ‘በአምስተኛው ቀን ሁሉም እንከን የሌለባቸው ዘጠኝ ወይፈኖች፣ ሁለት አውራ በጎችና ዓመት የሆናቸው ዐሥራ አራት ተባዕት የበግ ጠቦቶች አቅርቡ። 27ከወይፈኖቹ፣ ከአውራ በጎቹና ከጠቦቶቹ ጋር የእህል ቍርባናቸውንና የመጠጥ ቍርባናቸውን በተወሰነው ቍጥር መሠረት አቅርቡ። 28ደግሞም ከእህሉ ቍርባንና ከመጠጡ ቍርባን ጋር በመደበኛነት ከሚቀርበው የሚቃጠል መሥዋዕት ሌላ አንድ ተባዕት ፍየል የኀጢአት መሥዋዕት አድርጋችሁ በተጨማሪ አቅርቡ።

29“ ‘በስድስተኛው ቀን ሁሉም እንከን የሌለባቸው ስምንት ወይፈኖች፣ ሁለት አውራ በጎችና ዓመት የሆናቸው ዐሥራ አራት ተባዕት የበግ ጠቦቶች አቅርቡ። 30ከወይፈኖቹ፣ ከአውራ በጎቹና ከበግ ጠቦቶቹ ጋር የእህል ቍርባናቸውንና የመጠጥ ቍርባናቸውን በተወሰነው ቍጥር መሠረት አቅርቡ። 31ደግሞም ከእህሉ ቍርባንና ከመጠጡ ቍርባን ጋር በመደበኛነት ከሚቀርበው የሚቃጠል መሥዋዕት ሌላ አንድ ተባዕት ፍየል የኀጢአት መሥዋዕት አድርጋችሁ በተጨማሪ አቅርቡ።

32“ ‘በሰባተኛው ቀን ሁሉም እንከን የሌለባቸው ሰባት ወይፈኖች፣ ሁለት አውራ በጎችና ዓመት የሆናቸው ዐሥራ አራት ተባዕት የበግ ጠቦቶች አቅርቡ። 33ከወይፈኖቹ፣ ከአውራ በጎቹና ከበግ ጠቦቶቹ ጋር የእህል ቍርባናቸውንና የመጠጥ ቍርባናቸውን በተወሰነው ቍጥር መሠረት አቅርቡ። 34ደግሞም ከእህሉ ቍርባንና ከመጠጡ ቍርባን ጋር በመደበኛነት ከሚቀርበው የሚቃጠል መሥዋዕት ሌላ አንድ ተባዕት ፍየል የኀጢአት መሥዋዕት አድርጋችሁ በተጨማሪ አቅርቡ።

35“ ‘በስምንተኛው ቀን የተቀደሰ ጉባኤ አድርጉ፤ የዘወትር ሥራም አትሥሩ። 36ሁሉም እንከን የሌለባቸው አንድ ወይፈን፣ አንድ አውራ በግና ዓመት የሆናቸው ሰባት ተባዕት የበግ ጠቦቶች የሚቃጠል መሥዋዕት በማድረግ ሽታው እግዚአብሔርን (ያህዌ) ደስ የሚያሰኝ ቍርባን በእሳት አቅርቡ። 37ከወይፈኑ፣ ከአውራ በጉና ከበግ ጠቦቶቹ ጋር የእህል ቍርባናቸውንና የመጠጥ ቍርባናቸውን በተወሰነው ቍጥር መሠረት አቅርቡ። 38ደግሞም ከእህሉ ቍርባንና ከመጠጡ ቍርባን ጋር በመደበኛነት ከሚቀርበው የሚቃጠል መሥዋዕት ሌላ አንድ ተባዕት ፍየል የኀጢአት መሥዋዕት አድርጋችሁ በተጨማሪ አቅርቡ።

39“ ‘በስእለትና በበጎ ፈቃድ ከምታቀርቧቸው ቍርባኖች በተጨማሪ፣ የሚቃጠሉ መሥዋዕቶቻችሁን፣ የእህል ቍርባኖቻችሁን፣ የመጠጥ ቍርባኖቻችሁንና የኅብረት መሥዋዕቶቻችሁን29፥39 በተለምዶ የደኅንነት መሥዋዕት ይባላል። በተወሰኑት በዓሎቻችሁ ላይ ለእግዚአብሔር (ለያህዌ) አቅርቡ።’ ”

40ሙሴም እግዚአብሔር (ያህዌ) ያዘዘውን ሁሉ ለእስራኤላውያን ነገራቸው።