但以理书 4 – CCB & NASV

Chinese Contemporary Bible (Simplified)

但以理书 4:1-37

尼布甲尼撒的第二个梦

1尼布甲尼撒王传谕天下各族、各邦、各语种的人:“愿你们大享平安! 2我乐意向你们述说至高的上帝对我所行的神迹奇事。

3“祂的神迹何其伟大!

祂的奇事何其可畏!

祂的国度永远长存,

祂的统治直到万代。

4“我尼布甲尼撒安居在家,在宫中享受荣华。 5但我做了一个梦,令我害怕。我躺在床上的时候,脑中出现的情景和异象使我恐惧。 6我便召巴比伦所有的智者来为我解梦。 7术士、巫师、占星家和占卜者都来了,我将梦告诉他们,他们却不能给我解梦。 8最后但以理来到我面前,他又名伯提沙撒——取自我神明的名,他有圣洁神明的灵。我将梦告诉他,说, 9‘术士的首领伯提沙撒啊,我知道你有圣洁神明的灵,任何奥秘都难不倒你。请你为我解释我梦中所见的异象。

10“‘以下是我躺在床上时脑中出现的异象:我看见大地中央有棵非常高大的树。 11这树长得苍劲有力,高可参天,从地极都能看见。 12它的叶子美丽,果实累累,可作众生的食物。野兽在它的荫下躺卧,飞鸟在它的枝头栖息,一切生灵都从它那里得到食物。

13“‘我躺在床上时脑中出现了异象,我看见一位圣洁的守望者从天而降。 14他大声说,砍倒那棵树,削掉它的枝子,剥光它的叶子,抛散它的果子,使野兽逃离树下,飞鸟离开枝头。 15但把树丕留在地里,用铁环和铜环箍住他留在野地的青草中,让他被天上的露水浸湿,与野兽一起吃草。 16要改变他的人心,给他一个兽心,达七年之久。 17这是守望者的命令,是圣者的决定,要让众生知道至高者主宰世上万国,祂要把国赐给谁就赐给谁,即使是最卑微的人。’

18“这就是我尼布甲尼撒王所做的梦。伯提沙撒啊,你要为我解梦,因为我国中所有的智者都不能为我解梦。但是你能,因为你有圣洁神明的灵。”

但以理解梦

19但以理,又名伯提沙撒,一时非常惊讶,惶恐不安。王说:“伯提沙撒啊,不要因为这梦和梦的意思而惶恐不安。”伯提沙撒回答说:“我主啊,愿这梦发生在恨你的人身上,梦的意思应验在你的仇敌身上。 20你梦见的树苍劲有力,高可参天,从地极都能看见。 21它的叶子美丽,果实累累,可作众生的食物。野兽住在它的荫下,飞鸟宿在它的枝头。 22王啊,这苍劲有力的树就是你,你的威名高达穹苍,你的权柄延至地极。 23王看见圣洁的守望者从天而降,说,‘将这树砍倒、毁灭,但把树丕用铁环和铜环箍住留在野地的青草中,让他被天上的露水浸湿,与野兽一起吃草,达七年之久。’

24“王啊,以下是梦的意思,是至高者裁定要临到我主我王的事: 25你必从人群中被赶走,与野兽同住,像牛一样吃草,被天上的露水浸湿,达七年之久,直到你知道至高者主宰世上万国,祂要把国赐给谁就赐给谁。 26守望者命令留下树丕,表示等到你承认上天掌权后,你将重掌国权。 27王啊,请接受我的劝谏,你要秉公行义,以断绝罪恶;怜悯穷人,以除掉罪过。这样,你的国运也许可以延续。”

梦兆应验

28这一切事果然发生在尼布甲尼撒王身上。 29十二个月后,他在巴比伦王宫的屋顶散步时, 30说:“这宏伟的巴比伦岂不是我用大能建立为京都,以显我的威严和荣耀吗?” 31话未说完,天上就有声音说:“尼布甲尼撒王啊,你听着,你已失去王权。 32你必从人群中被赶走,与野兽同住,像牛一样吃草,达七年之久,直到你知道至高者主宰世上万国,祂要把国赐给谁就赐给谁。” 33这话立刻应验在尼布甲尼撒身上。他从人群中被赶走,像牛一样吃草,身体被天上的露水浸湿,直到他的头发长如鹰毛,指甲长如鸟爪。

34“七年后,我尼布甲尼撒举目望天,恢复了神智,便称颂至高者,赞美、尊崇永活者。

“祂的统治永无穷尽,

祂的国度直到万代。

35世人都微不足道,

祂在天军和世人中独行其道,

无人能拦阻祂的手,

或质问祂的作为。

36“那时,我恢复了神智,也恢复了我的威严和荣耀,重现我国度的辉煌。我的谋士和大臣都来朝见我,我重掌国权,势力比以前更大。 37现在我尼布甲尼撒颂赞、尊崇、敬奉天上的王,因为祂的作为公正,祂行事公平,能够贬抑行为骄傲的人。”

New Amharic Standard Version

ዳንኤል 4:1-37

ናቡከደነፆር በሕልሙ ዛፍ አየ

1ከንጉሥ ናቡከደነፆር፣

በምድር ሁሉ ለሚኖሩ ሕዝቦች፣ መንግሥታትና ልዩ ልዩ ቋንቋዎችን ለሚናገሩ ሰዎች ሁሉ፤

ሰላም ይብዛላችሁ!

2ልዑል አምላክ ያደረገልኝን ታምራዊ ምልክቶችንና ድንቅ ሥራዎች ስነግራችሁ እጅግ ደስ እያለኝ ነው።

3ምልክቱ እንዴት ታላቅ ነው!

ድንቁስ እንዴት ብርቱ ነው!

መንግሥቱ የዘላለም መንግሥት ነው፤

ግዛቱም ከትውልድ እስከ ትውልድ ይኖራል።

4እኔ ናቡከደነፆር በቤቴ ደልቶኝ በቤተ መንግሥቴም ተመችቶኝ እኖር ነበር። 5አንድ ያስፈራኝ ሕልም አየሁ፤ በዐልጋዬ ላይ ተኝቼ ሳለሁ፣ ወደ አእምሮዬ የመጡት ምስሎችና ራእዮች አስደነገጡኝ። 6ስለዚህ የባቢሎን ጠቢባን ሁሉ ወደ እኔ መጥተው ሕልሜን እንዲተረጕሙልኝ አዘዝሁ። 7ጠንቋዮቹ፣ አስማተኞቹ፣ ኮከብ ቈጣሪዎቹና4፥7 ወይም ከለዳውያን መተተኞቹ በመጡ ጊዜ ሕልሙን ነገርኋቸው፤ ነገር ግን ሊተረጕሙልኝ አልቻሉም። 8በመጨረሻም በአምላኬ ስም ብልጣሶር ተብሎ የተጠራውና የቅዱሳን አማልክት መንፈስ ያለበት ዳንኤል ገብቶ በፊቴ ቆመ፤ ሕልሜንም ነገርሁት።

9እኔም እንዲህ አልሁት፤ “የጠቢባን አለቃ ብልጣሶር ሆይ፤ የቅዱሳን አማልክት መንፈስ በአንተ ውስጥ እንዳለ ዐውቃለሁ፤ ምንም ዐይነት ምስጢር አያስቸግርህም፤ ያየሁት ሕልም እነሆ፤ ተርጕምልኝ። 10በዐልጋዬ ላይ ተኝቼ ሳለሁ ያየሁት ራእይ ይህ ነው፦ እነሆ በፊቴ በምድር መካከል ቁመቱ እጅግ ረዥም የሆነ ዛፍ ቆሞ ተመለከትሁ። 11ዛፉም እጅግ አደገ፤ ጠነከረም፤ ጫፉም ሰማይ ደረሰ፤ እስከ ምድር ዳርቻ ድረስም ይታይ ነበር። 12ቅጠሎቹ ያማሩ፣ ፍሬዎቹ የተንዠረገጉ ነበሩ፤ በላዩም ለሁሉ የሚሆን ምግብ ነበረበት። የምድር አራዊት ከጥላው በታች ያርፉ ነበር፤ በቅርንጫፎቹም ላይ የሰማይ ወፎች ይኖሩ ነበር፤ ፍጥረትም ሁሉ ከእርሱ ይመገብ ነበር።

13“በዐልጋዬ ላይ ተኝቼ ሳለሁ ባየሁት ራእይ አንድ ቅዱስ መልእክተኛ4፥13 ወይም ጕበኛ፤ እንዲሁም 17 እና 23 ከሰማይ ሲወርድ አየሁ። 14እርሱም ድምፁን ከፍ አድርጎ እንዲህ አለ፤ ‘ዛፉን ቍረጡ፤ ቅርንጫፎቹን ጨፍጭፉ፤ ቅጠሎቹን አራግፉ፤ ፍሬውንም በትኑ፤ ከሥሩ ያሉት እንስሶች፣ በቅርንጫፎቹም ላይ ያሉት ወፎች ይሽሹ። 15ነገር ግን ጕቶውና ሥሩ በሜዳው ሣር ላይ በብረትና በናስ ታስሮ በመሬት ውስጥ ይቈይ።

“ ‘በሰማይ ጠል ይረስርስ፤ በጥሻም ውስጥ ከአራዊት ጋር ይኑር። 16አእምሮው ከሰው አእምሮ ይለወጥ፤ የእንስሳም አእምሮ ይሰጠው፤ ሰባት ዓመትም ይለፍበት።

17“ ‘ውሳኔው በመልእክተኞች ተገልጿል፤ ፍርዱም በቅዱሳኑ ተነግሯል፤ ይኸውም፣ ልዑል በሰዎች መንግሥታት ሁሉ ላይ እንደሚገዛና እነዚህንም መንግሥታት ለወደደው እንደሚሰጥ፣ ከሰዎችም የተናቁትን በላያቸው እንደሚሾም፣ ሕያዋን ሁሉ ያውቁ ዘንድ ነው።’

18“እኔ ናቡከደነፆር ያየሁት ሕልም ይህ ነው፤ አሁንም ብልጣሶር ሆይ፤ በመንግሥቴ ካሉ ጠቢባን ሁሉ አንዳቸውም ሊተረጕሙልኝ ስላልቻሉ፣ ምን ማለት እንደ ሆነ ንገረኝ። አንተ የአማልክት መንፈስ በውስጥህ ስላለ ልትተረጕምልኝ ትችላለህ።”

ዳንኤል ሕልሙን ተረጐመ

19ከዚያም ብልጣሶር የተባለው ዳንኤል ለጥቂት ጊዜ በጣም ታወከ፤ ሐሳቡም አስደነገጠው። ንጉሡም፣ “ብልጣሶር ሆይ፤ ሕልሙም ሆነ ትርጕሙ አያስደንግጥህ” አለው።

ብልጣሶርም እንዲህ ብሎ መለሰ፤ “ሕልሙ ለሚጠሉህ ይሁን፤ ትርጕሙም ለጠላቶችህ! 20እጅግ አድጎና ጠንክሮ ያየኸው ዛፍ፣ ጫፉም እስከ ሰማይ ደርሶ በምድር ሁሉ የሚታየው፣ 21ቅጠሎቹ የሚያምሩ፣ ፍሬውም ተንዠርግጎ ለሁሉ ምግብ የሆነው፣ የዱር አራዊት መጠለያ የሆነውና በቅርንጫፎቹ ላይ ለሰማይ ወፎች ጐጆ መሥሪያ ያለው፣ 22ንጉሥ ሆይ፤ ያ ዛፍ አንተ ነህ፤ ታላቅና ብርቱ ሆንህ፤ ታላቅነትህ አድጎ እስከ ሰማይ ደረሰ፤ ግዛትህም እስከ ምድር ዳርቻ ተንሰራፋ።

23“ንጉሥ ሆይ፤ አንተ፣ ‘ዛፉን ቍረጡ፣ አጥፉትም፤ በብረትና በናስ የታሰረውን ጕቶና ሥሩን በሜዳው ሣር ላይ በብረትና በናስ ታስሮ በመሬት ውስጥ ይቈይ፤ በሰማይ ጠል ይረስርስ፤ እንደ ዱር አራዊትም ይኑር፤ ሰባት ዓመትም ይለፍበት’ እያለ ከሰማይ የወረደውን ቅዱሱን መልእክተኛ አየህ።

24“ንጉሥ ሆይ፤ ትርጕሙ ይህ ነው፤ ልዑሉ በንጉሡ በጌታዬ ላይ ያወጣው ዐዋጅ ይህ ነው፤ 25ከሕዝብ ተለይተህ ትሰደዳለህ፤ ዱር አራዊትም ጋር ትኖራለህ። እንደ ከብት ሣር ትበላለህ፤ በሰማይ ጠልም ትረሰርሳለህ፤ ልዑሉ በሰዎች መንግሥታት ሁሉ ላይ እንደሚገዛና እነዚህንም መንግሥታት ለወደደው እንደሚሰጥ እስክታውቅ ድረስ ሰባት ዓመታት ያልፉብሃል። 26የዛፉ ጕቶ ከነሥሩ እንዲቀር መታዘዙ፣ ሥልጣን ከሰማይ መሆኑን ስታውቅ መንግሥትህ እንደሚመለስልህ ያመለክታል። 27ስለዚህ ንጉሥ ሆይ፤ ምክሬን ስማ፤ ኀጢአት መሥራትን ትተህ ትክክለኛ የሆነውን አድርግ፤ ክፋትን ትተህ ለተጨቈኑት ቸርነትን አድርግ፤ ምናልባት በሰላም የምትኖርበት ዘመን ይራዘምልህ ይሆናል።”

ሕልሙ ተፈጸመ

28ይህ ሁሉ በንጉሡ በናቡከደነፆር ላይ ደረሰ፤ 29ከዐሥራ ሁለት ወራት በኋላ፣ ንጉሡ በባቢሎን ቤተ መንግሥት ሰገነት ላይ ሲመላለስ ሳለ፣ 30“በብርቱ ኀይሌ፣ ለገናናው ክብሬ ንጉሣዊ መኖሪያ ትሆን ዘንድ ያሠራኋት ታላቂቷ ባቢሎን ይህች አይደለችምን?” አለ።

31ንግግሩን ገና ከአፉ ሳይጨርስ፣ እንዲህ የሚል ድምፅ ከሰማይ መጣ፤ “ንጉሥ ናቡከደነፆር ሆይ፤ ስለ አንተ የታወጀው ይህ ነው፤ መንግሥትህ ከአንተ ተወስዷል፤ 32ከሕዝብ መካከል ትሰደዳለህ፤ ከዱር አራዊት ጋርም ትኖራለህ፤ እንደ ከብት ሣር ትበላለህ፤ ልዑሉ በሰዎች መንግሥት ሁሉ ላይ ሙሉ ሥልጣን እንዳለውና እነዚህንም መንግሥታት ለወደደው እንደሚሰጥ እስክታውቅ ድረስ ሰባት ዓመት ያልፋል።”

33ወዲያውኑ በናቡከደነፆር ላይ የተነገረው ሁሉ ተፈጸመ፤ ከሕዝቡ መካከል ተሰደደ፤ እንደ ከብትም ሣር በላ። የራስ ጠጕሩ እንደ ንስር ላባና፣ ጥፍሮቹም እንደ ወፍ ጥፍሮች እስኪያድጉ ድረስ ሰውነቱ በሰማይ ጠል ረሰረሰ።

34ጊዜው ከተፈጸመ በኋላ፣ እኔ ናቡከደነፆር ዐይኖቼን ወደ ሰማይ አነሣሁ፤ አእምሮዬም ተመለሰልኝ፤ ልዑሉንም ባረክሁት፤ ለዘላለምም የሚኖረውን ወደስሁት፤ ክብርንም ሰጠሁት።

ግዛቱ የዘላለም ግዛት ነው፤

መንግሥቱም ከትውልድ እስከ ትውልድ ይኖራል።

35የምድር ሕዝቦች ሁሉ፣

እንደ ኢምንት ይቈጠራሉ፤

በሰማይ ኀይላት፣

በምድርም ሕዝቦች ላይ፣

የወደደውን ያደርጋል፤

እጁን መከልከል የሚችል የለም፤

“ምን ታደርጋለህ?” ብሎ የሚጠይቀውም የለም።

36አእምሮዬ እንደ ተመለሰልኝ፣ ወዲያው ለመንግሥቴ ክብር፣ ግርማዊነቴና ሞገሴ ተመለሱልኝ፤ አማካሪዎቼና መኳንንቴ ፈለጉኝ፤ ወደ ዙፋኔም ተመለስሁ፤ ከቀድሞውም የበለጠ ታላቅ ሆንሁ። 37የሰማይ አምላክ የሚያደርገው ሁሉ ትክክል፣ መንገዶቹም ሁሉ ጽድቅ ስለሆኑ፣ አሁንም እኔ ናቡከደነፆር እርሱን አወድሰዋለሁ፤ ከፍ ከፍ አደርገዋለሁ፤ አከብረዋለሁም፤ እርሱም በትዕቢት የሚመላለሱትን ማዋረድ ይችላል።