何西阿书 1 – CCB & NASV

Chinese Contemporary Bible (Simplified)

何西阿书 1:1-11

1乌西雅约坦亚哈斯希西迦犹大王,约阿施的儿子耶罗波安以色列王期间,耶和华将祂的话传给备利的儿子何西阿

何西阿娶妓女为妻

2耶和华首次向何西阿说话时,对他说:“你去娶一个妓女为妻,和她生养儿女,因为这片土地上的人极其淫乱,背弃了耶和华。” 3于是,何西阿娶了滴拉音的女儿歌蜜为妻,她怀孕为他生了一个儿子。 4耶和华对何西阿说:“给他取名叫耶斯列1:4 耶斯列”意思是“上帝撒种”。此处指上帝要像撒种一样驱散以色列人,但在1:11指上帝要赐福他们,就像撒种后获得了大丰收。,因为再过不久,我就要因耶户家在耶斯列的屠杀而惩罚他们,消灭以色列国。 5那时,我要在耶斯列平原折断以色列的弓。” 6后来,歌蜜又怀孕生了一个女儿。耶和华对何西阿说:“给她取名叫罗·路哈玛1:6 罗·路哈玛”意思是“不蒙怜悯”。,因为我将不再怜悯以色列家,也不再赦免他们的罪。 7但我要怜悯犹大家,使他们依靠他们的上帝耶和华得到拯救,而不是依靠战弓、刀剑、马匹、骑兵和战争。” 8罗·路哈玛断奶后,歌蜜又怀孕生了一个儿子。 9耶和华说:“给他取名叫罗·阿米1:9 罗·阿米”意思是“不是我的子民”。,因为以色列人不再是我的子民,我也不再是他们的上帝。

以色列的复兴

10“然而,以色列的人数必像海沙一样量不尽、数不完。从前我在什么地方对他们说‘你们不是我的子民’,将来也要在那里对他们说‘你们是永活上帝的儿女’。 11那时,犹大人和以色列人将被聚集起来,为自己选立一位首领,从流亡之地返回故乡,安居乐业。耶斯列的日子将是伟大的日子。

New Amharic Standard Version

ሆሴዕ 1:1-11

1በይሁዳ ነገሥታት በዖዝያን፣ በኢዮአታም፣ በአካዝና በሕዝቅያስ ዘመን እንዲሁም በእስራኤል ንጉሥ በዮአስ1፥1 በዕብራይስጥ ዮአስ የሚለው ቃል የኢዮአስ አማራጭ ትርጕም ነው ልጅ በኢዮርብዓም ዘመን ወደ ብኤሪ ልጅ ወደ ሆሴዕ የመጣው የእግዚአብሔር ቃል ይህ ነው፤

የሆሴዕ ሚስትና ልጆቹ

2እግዚአብሔር በሆሴዕ መናገር በጀመረ ጊዜ፣ እግዚአብሔር “ምድሪቱ ከእግዚአብሔር ተለይታ ታላቅ ምንዝርና እያደረገች ስለሆነ፣ ሄደህ አመንዝራ ሴት አግባ፤ የምንዝርና ልጆችንም ለራስህ ውሰድ” አለው። 3ስለዚህ እርሱ የዴቤላይምን ሴት ልጅ ጎሜርን አገባ፤ እርሷም ፀነሰች፤ ወንድ ልጅም ወለደችለት።

4እግዚአብሔርም ሆሴዕን እንዲህ አለው፤ “በኢይዝራኤል ስለ ተፈጸመው ግድያ የኢዩን ቤት በቅርቡ ስለምቀጣና የእስራኤልንም መንግሥት እንዲያከትም ስለማደርግ፣ ስሙን ኢይዝራኤል ብለህ ጥራው። 5በዚያም ቀን በኢይዝራኤል ሸለቆ፣ የእስራኤልን ቀስት እሰብራለሁ።”

6ጎሜር እንደ ገና ፀነሰች፤ ሴት ልጅም ወለደች፤ እግዚአብሔርም ሆሴዕን እንዲህ አለው፤ “ይቅር እላቸው ዘንድ ለእስራኤል ቤት ከእንግዲህ ስለማልራራላቸው፣ ስሟን ሎሩሃማ1፥6 ሎሩሃማ ማለት ያልተወደደች ማለት ነው ብለህ ጥራት። 7ነገር ግን ለይሁዳ ቤት እራራለሁ፤ በቀስት ወይም በሰይፍ ወይም በጦርነት ወይም በፈረሶችና በፈረሰኞች ሳይሆን በአምላካቸው በእግዚአብሔር አድናቸዋለሁ።”

8ጎሜር፣ ሎሩሃማን ጡት ካስጣለች በኋላ ሌላ ወንድ ልጅ ወለደች። 9እግዚአብሔርም እንዲህ አለው፤ “ሎዓሚ1፥9 ሎዓሚ ማለት ሕዝቤ አይደለም ማለት ነው ብለህ ጥራው፤ ምክንያቱም እናንተ ሕዝቤ አይደላችሁም፤ እኔም አምላካችሁ አይደለሁምና።

10“ይሁን እንጂ እስራኤላውያን ሊሰፈርና ሊቈጠር እንደማይችል እንደ ባሕር አሸዋ ይሆናሉ፤ ‘ሕዝቤ አይደላችሁም’ በተባሉበት ቦታ፣ ‘የሕያው አምላክ ልጆች’ ተብለው ይጠራሉ። 11የይሁዳ ሕዝብና የእስራኤል ሕዝብ እንደ ገና አንድ ይሆናሉ፤ አንድ መሪም ይሾማሉ፤ አንድ ሆነውም በምድሪቱ ይገንናሉ፤ የኢይዝራኤል ቀን ታላቅ ይሆናልና።