2 ዜና መዋዕል 23 – NASV & CCBT

New Amharic Standard Version

2 ዜና መዋዕል 23:1-21

1በሰባተኛው ዓመት ዮዳሄ በረታ፤ የመቶ አለቆች ከሆኑት ከይሮሐም ልጅ ከዓዛርያስ፣ ከይሆሐናን ልጅ ከይስማኤል፣ ከዖቤድ ልጅ ከዓዛርያስ፣ ከዓዳያ ልጅ ከማዕሤያ፣ ከዝክሪ ልጅ ከኤሊሳፋጥ ጋር ቃል ኪዳን አደረገ። 2እነርሱም ወደ መላው ይሁዳ ሄደው፣ ሌዋውያንንና የእስራኤል ቤት አለቆችን ከየከተማው ሁሉ ሰበሰቡ። ወደ ኢየሩሳሌም በመጡ ጊዜም፣ 3ጉባኤው ሁሉ በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ውስጥ ከንጉሡ ጋር ቃል ኪዳን አደረጉ።

ዮዳሄም እንዲህ አላቸው፤ “እግዚአብሔር ለዳዊት ዘር በሰጠው ተስፋ መሠረት እነሆ፤ የንጉሡ ልጅ ይነግሣል። 4እንግዲህ እናንተ የምታደርጉት ይህ ነው፤ በሰንበት ዕለት ተረኛ ከሆናችሁት ከእናንተ ከካህናቱና ከሌዋውያኑ አንድ ሦስተኛው በሮቹን ጠብቁ፤ 5አንድ ሦስተኛው ቤተ መንግሥቱን፣ አንድ ሦስተኛው ‘የመሠረት ቅጽር በር’ የተባለውን ጠብቁ፤ የቀሩት ሰዎች በሙሉ በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ አደባባይ ይሁኑ። 6ተረኛ ከሆኑት ካህናትና ሌዋውያን በቀር ማንም ሰው ወደ እግዚአብሔር ቤተ መቅደስ አይግባ፤ እነርሱ የተቀደሱ ስለሆኑ ይግቡ፤ የቀሩት ሰዎች በሙሉ ግን፣ ወደ ቤተ መቅደሱ እንዳይገቡ እግዚአብሔር ያዘዘውን ይጠብቁ23፥6 ወይም አይግባ የሚለውን የእግዚአብሔር ትእዛዝ ይጠብቁ7ሌዋውያኑም የጦር መሣሪያቸውን በእጃቸው ይዘው በንጉሡ ዙሪያ ይቁሙ፤ ወደ ቤተ መቅደሱ የሚገባ ማንኛውም ሰው ይገደል፤ ንጉሡ በሚሄድበትም ቦታ ሁሉ አብረውት ይሁኑ።”

8ሌዋውያኑና ይሁዳ ሁሉ ልክ ካህኑ ዮዳሄ እንዳዘዘው አደረጉ፤ ካህኑ ዮዳሄ ከጥበቃ ክፍሎች የትኛውንም አላሰናበተም ነበርና፣ እያንዳንዱ በሰንበት ቀን በሥራ ላይ የሚሰማሩትንና ከሥራ የሚወጡትን የራሱን ሰዎች ወሰደ፤ 9ከዚያም በቤተ መቅደሱ የነበሩትን የንጉሥ ዳዊት ጦሮች፣ ታላላቅና ታናናሽ ጋሻዎች ለመቶ አለቆቹ ሰጣቸው። 10ሰዎቹም ሁሉ እያንዳንዳቸው መሣሪያቸውን በእጃቸው እንደ ያዙ ከቤተ መቅደሱ ደቡብ አንሥቶ እስከ ሰሜን ድረስ በመሠዊያውና በቤተ መቅደሱ አጠገብ በንጉሡ ዙሪያ እንዲቆሙ አደረገ።

11ዮዳሄና ወንዶች ልጆቹ የንጉሡን ልጅ አምጥተው ዘውድ ጫኑለት፤ የኪዳኑንም መጽሐፍ ሰጥተውት አነገሡት፤ ቀብተውትም፣ “ንጉሡ ለዘላለም ይኑር!” እያሉ ጮኹ።

12ጎቶልያም የሚሯሯጠውንና ደስታውን ለንጉሡ የሚገልጠውን ሕዝብ ሁካታ ስትሰማ፣ ሕዝቡ ወዳለበት ወደ እግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ሄደች። 13ንጉሡ በመግቢያው ላይ ባለው በዐምዱ አጠገብ ቆሞ አየች፣ የጦር መኮንኖችና መለከት ነፊዎችም በንጉሡ አጠገቡ ነበሩ፤ የምድሪቱ ሕዝብ ሁሉ ይደሰቱ፣ መለከትም ይነፉ ነበር፤ መዘምራንም በዜማ ዕቃ ታጅበው የበዓሉን ዝማሬ ይመሩ ነበር፤ ጎቶልያም ልብሷን ቀድዳ፣ “ይህ ዐመፅ ነው! ይህ ዐመፅ ነው!” ብላ ጮኸች።

14ካህኑ ዮዳሄም የወታደር አዛዥ ወደ ሆኑት ወደ መቶ አለቆቹ፣ “በሰልፉ መካከል አውጥታችሁ አምጧት23፥14 ወይም ከቅጥሩ ውስጥ አውጥታችሁ አምጧት፤ የሚከተላት ካለም በሰይፍ ግደሉት” ሲል ላከባቸው። ካህኑም፣ “በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ አትግደሏት” ብሎ ነበርና። 15እርሷም በቤተ መንግሥቱ ግቢ የፈረስ መግቢያ በር ወደ ተባለው ቦታ እንደ ደረሰች ያዟት፤ በዚያም ገደሏት።

16ዮዳሄም ራሱ፣ ሕዝቡና ንጉሡ የእግዚአብሔር ሕዝብ እንደሚሆኑ ቃል ኪዳን ገባ23፥16 ወይም በእግዚአብሔር በሕዝቡና በንጉሡ መካከል የተደረገው ቃል ኪዳን (2ነገ 11፥17)17ከዚህ በኋላ ሕዝቡ በሙሉ ሄዶ የበኣልን ቤተ ጣዖት አፈረሰው፤ መሠዊያዎቹንና ጣዖታቱን አደቀቀ፤ የበኣልን ካህን ማታንንም በመሠዊያዎቹ ፊት ለፊት ገደሉት። 18ዮዳሄ በሙሴ ሕግ እንደ ተጻፈውና ዳዊትም እንዳዘዘው፣ በደስታና በመዝሙር የሚቃጠለውን የእግዚአብሔርን መሥዋዕት እንዲያቀርቡ ዳዊት ለመደባቸው ካህናትና ሌዋውያን የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ ኀላፊነት ሰጣቸው። 19እንዲሁም በማንኛውም ነገር የረከሰ ሰው እንዳይገባ፣ በቤተ መቅደሱ ቅጥር በሮች ላይ ጠባቆች አቆመ። 20የመቶ አለቆቹን፣ መኳንንቱን፣ የሕዝቡን ገዦችና የአገሩን ሕዝብ ሁሉ ይዞ ንጉሡን ከላይ ከቤተ መቅደሱ ወደ ታች አመጣው። በላይኛውም መግቢያ በኩል ወደ ቤተ መንግሥቱ ገብተው ንጉሡን በመንግሥቱ ዙፋን ላይ አስቀመጡት። 21መላውም የአገሩ ሕዝብ ተደሰተ፤ ጎቶልያ ስለ ተገደለችም ከተማዪቱ ሰላም አግኝታ ነበር።

Chinese Contemporary Bible (Traditional)

歷代志下 23:1-21

耶何耶大立約阿施為猶大王

1第七年,耶何耶大發憤圖強,召來一些百夫長與他們立約。他們是耶羅罕的兒子亞撒利雅約哈難的兒子以實瑪利俄備得的兒子亞撒利雅亞大雅的兒子瑪西雅,以及細基利的兒子以利法2他們走遍猶大各城,把利未人和以色列的各族長召集到耶路撒冷3全體會眾到上帝的殿中與王立約。耶何耶大對他們說:「王的兒子當做王!這是耶和華對大衛子孫的應許。 4你們要這樣做,三分之一在安息日值班的祭司和利未人要把守各門, 5三分之一要把守王宮,三分之一要把守基址門,所有民眾要留在耶和華殿的院子裡。 6只有祭司和供職的利未人可以進耶和華的殿,因為他們是聖潔的。其他人一律不准進殿。所有的人都要遵守耶和華的吩咐。 7利未人要手持兵器護衛在王周圍。凡擅自進殿的,一律處死。無論王去哪裡,你們都要緊隨左右。」

8於是,利未人和所有猶大人遵照耶何耶大祭司的命令而行,各自帶來在安息日值班和休班的屬下,因為耶何耶大祭司沒有讓他們休班。 9耶何耶大祭司把上帝殿中大衛王的矛槍和大小盾牌交給百夫長。 10耶何耶大安排眾民手持兵器,從殿右到殿左,在祭壇和殿周圍護衛王, 11然後他們領王子出來,給他戴上王冠,把律法書交給他。耶何耶大及其眾子膏立王子為王。眾人高呼:「願王萬歲!」

亞她利雅被處死

12亞她利雅聽到人們奔走稱頌王的聲音,便走進耶和華的殿,眾人都聚集在那裡。 13她看見王站在門口的柱旁,百夫長和吹號的人侍立在王左右,眾民都歡呼吹號,歌樂手用各種樂器帶領眾人唱歌頌揚,便撕裂衣服,喊道:「反了!反了!」 14耶何耶大祭司認為不可在耶和華的殿裡處死亞她利雅,便命令帶兵的百夫長出來,對他們說:「把她帶出去。要用刀殺死所有跟隨她的人。」 15他們抓住她,把她帶到馬匹進出王宮的入口,在那裡殺了她。

耶何耶大的改革

16耶何耶大讓民眾和王與他一起立約,要做耶和華的子民。 17於是,民眾出去拆毀了巴力廟,砸碎祭壇和偶像,在壇前殺了巴力的祭司瑪坦18耶何耶大大衛的吩咐讓利未祭司負責耶和華殿裡的事務。大衛曾吩咐利未祭司在耶和華的殿中司職,照摩西的律法向耶和華獻燔祭,歡呼歌唱。 19耶何耶大還派門衛把守耶和華殿的各門,禁止一切不潔淨的人入內。 20他率領百夫長、貴族、首領和全體民眾護送王從耶和華的殿裡下來,經上門進入王宮,擁立王登上王位。 21民眾都歡喜快樂,城裡安定,因為亞她利雅已死在刀下。