2 ዜና መዋዕል 22 – NASV & CCBT

New Amharic Standard Version

2 ዜና መዋዕል 22:1-12

የይሁዳ ንጉሥ አካዝያስ

22፥1-6 ተጓ ምብ – 2ነገ 8፥25-29

22፥7-9 ተጓ ምብ – 2ነገ 9፥21-29

1ከዐረቦች ጋር ወደ ሰፈር የመጡት ወራሪዎች፣ ታላላቅ ወንድሞቹን ሁሉ ገድለዋቸው ስለ ነበር፣ የኢየሩሳሌም ሕዝብ የኢዮሆራምን የመጨረሻ ልጅ አካዝያስን በአባቱ ምትክ አነገሡት። ስለዚህ የይሁዳ ንጉሥ የኢዮሆራም ልጅ አካዝያስ መግዛት ጀመረ። 2አካዝያስ በነገሠ ጊዜ ዕድሜው ሃያ ሁለት22፥2 አንዳንድ የሰብዓ ሊቃናትና የሱርስቱ ቅጆች (እንዲሁም 2ነገ 8፥26 ይመ) ከዚህ ጋር ይስማማሉ፤ ዕብራይስጡ ግን አርባ አራት ይላል። ዓመት ነበር፤ በኢየሩሳሌም ተቀምጦም አንድ ዓመት ገዛ። እናቱም ጎቶልያ የተባለች የዘንበሪ የልጅ ልጅ ነበረች።

3እናቱ ክፋትን እንዲያደርግ ትመክረው ስለ ነበር፣ እርሱም በአክዓብ ቤት መንገድ ሄደ። 4ከአባቱ ሞት በኋላ የአክዓብ ቤት አማካሪዎቹ በመሆን ወደ ጥፋት ስለ መሩት፣ የአክዓብ ቤት እንዳደረገው ሁሉ እርሱም በእግዚአብሔር ፊት ክፉ ነገር አደረገ። 5እንዲሁም የእስራኤል ንጉሥ የአክዓብ ልጅ ኢዮራም የሶርያን ንጉሥ አዛሄልን ለመውጋት ወደ ሬማት ገለዓድ በሄደ ጊዜ፣ የእነዚህኑ ሰዎች ምክር ተከትሎ ከኢዮራም ጋር አብሮት ሄደ፣ ሶርያውያንም ኢዮራምን አቈሰሉት።

6ስለዚህ ከሶርያ ንጉሥ ከአዛሄል ጋር ባደረገው ጦርነት ሬማት22፥6 ጥቂት የዕብራይስጥ ቅጆች የሰብዓ ሊቃናት፣ የቩልጌትና የሱርስቱ ትርጕም (2ነገ 8፥29) ከዚህ ጋር ይስማማሉ አብዛኞቹ የዕብራይስጥ ቅጆች ግን፣ አዛርያ ይላሉ። ላይ ከደረሰበት ቍስል ለመዳን ወደ ኢይዝራኤል ተመለሰ።

የአክዓብ ልጅ ኢዮራም በመቍሰሉም የይሁዳ ንጉሥ የኢዮሆራም ልጅ አካዝያስ ሊጠይቀው ወደ ኢይዝራኤል ወረደ።

7አካዝያስ ኢዮራምን ለመጠየቅ መሄዱን፣ እግዚአብሔር ለአካዝያስ መውደቅ ምክንያት አደረገው፤ አካዝያስ እንደ ደረሰም የናሜሲን ልጅ ኢዩን ለመቀበል ከኢዮራም ጋር ወጣ፤ ኢዩም የአክዓብን ቤት እንዲያጠፋ እግዚአብሔር የቀባው ሰው ነበር። 8ኢዩ በአክዓብ ቤት ላይ ፍርድ በሚፈጽምበት ጊዜ፣ አካዝያስን ያጅቡ የነበሩትን የይሁዳን መሳፍንትና የዘመዶቹን ወንዶች ልጆች አግኝቶ ገደላቸው። 9ከዚያም አካዝያስን ለመፈለግ ሄደ፤ የእርሱም ሰዎች አካዝያስን በሰማርያ ከተደበቀበት አግኝተው ያዙት፤ ወደ ኢዩም አምጥተው ገደሉት። “እግዚአብሔርን በፍጹም ልቡ የፈለገው የኢዮሣፍጥ ልጅ ነው” በማለት ቀበሩት። ስለዚህ ከአካዝያስ ቤት የመንግሥቱን ሥልጣን ይይዝ ዘንድ የሚችል ሰው አልነበረም።

ጎቶልያና ኢዮአስ

22፥10–23፥21 ተጓ ምብ – 2ነገ 11፥1-21

10የአካዝያስ እናት ጎቶልያ ልጇ መሞቱን ባየች ጊዜ፣ የይሁዳን ንጉሣውያን ቤተ ሰብ በሙሉ አጠፋች፤ 11የንጉሥ ኢዮሆራም ልጅ ዮሳቤት ግን፣ ከሚገደሉት መሳፍንት መካከል ኢዮአስን ደብቃ ወሰደችው፣ ከሞግዚቱም ጋር በእልፍኝ ሸሸገችው። የኢዮሆራም ልጅ የካህኑ የዮዳሄ ሚስት ዮሳቤት፣ የአካዝያስ እኅት በመሆኗ፣ ሕፃኑን የደበቀችው ጎቶልያ እንዳትገድለው ነበር። 12እርሱም ጎቶልያ ምድሪቱን በገዛችበት ጊዜ ሁሉ፣ በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ተደብቆ ስድስት ዓመት አብሯቸው ኖረ።

Chinese Contemporary Bible (Traditional)

歷代志下 22:1-12

猶大王亞哈謝

1耶路撒冷的居民擁立約蘭的小兒子亞哈謝22·1 亞哈謝」即21·17提到的「亞哈斯」。為王。因為約蘭的其他兒子都被那些與阿拉伯人同來攻營的匪徒殺了,於是猶大約蘭的兒子亞哈謝做了王。 2亞哈謝二十二歲22·2 參考七十士譯本、敘利亞譯本和列王紀下8·26。希伯來文是「四十二歲」。登基,在耶路撒冷執政一年。他母親叫亞她利雅,是暗利的孫女。 3他重蹈亞哈家的覆轍,因為他的母親唆使他作惡。 4他像亞哈家一樣做耶和華視為惡的事,因為他父親死後,亞哈家便唆使他作惡,使他走向滅亡。 5他照亞哈家的主意,與以色列亞哈的兒子約蘭一起去基列拉末征討亞蘭哈薛亞蘭人擊傷約蘭6約蘭便回到耶斯列療傷。猶大亞哈謝22·6 亞哈謝」希伯來文是「亞撒利雅」。前去探望他。

7亞哈謝去見約蘭,遇害身亡,這事出於上帝。原來他到那裡後便與約蘭去攻擊寧示的孫子耶戶耶戶是耶和華膏立去毀滅亞哈家的人。 8耶戶討伐亞哈家的時候,遇見猶大眾首領和亞哈謝的眾侄兒,他們都是服侍亞哈謝的,耶戶就把他們全部殺掉。 9然後耶戶搜捕亞哈謝,民眾找到躲在撒瑪利亞亞哈謝,把他押到耶戶那裡殺了。他們念他是全心尋求耶和華的約沙法的孫子,就把他埋葬了。這樣,亞哈謝家無人能保住王位。

亞她利雅篡權

10亞哈謝的母親亞她利雅見她兒子死了,便決定除掉猶大王室的後裔。 11約蘭王的女兒、亞哈謝的妹妹約示芭亞哈謝的兒子約阿施從將要被殺的王子中偷出來,將他和他的乳母藏在一間臥室裡躲避亞她利雅的殺害。約示芭耶何耶大祭司的妻子。 12約阿施和他們在上帝的殿裡藏了六年。那時亞她利雅篡位當政。