1 ዜና መዋዕል 3 – NASV & CCB

New Amharic Standard Version

1 ዜና መዋዕል 3:1-24

የዳዊት ወንዶች ልጆች

3፥1-4 ተጓ ምብ – 2ሳሙ 3፥2-5

3፥5-8 ተጓ ምብ – 2ሳሙ 5፥14-161ዜና 14፥4-7

1ዳዊት በኬብሮን ሳለ የወለዳቸው ወንዶች ልጆች እነዚህ ነበሩ፤

ከኢይዝራኤላዊቷ ከአኪናሆም የተወለደው የበኵር ልጁ አምኖን፣

ሁለተኛው፣ ከቀርሜሎሳዊቷ ከአቢግያ የተወለደው ዳንኤል፣

2ሦስተኛው ከጌሹር ንጉሥ ከተልማይ ልጅ ከመዓካ የተወለደው አቤሴሎም፣

አራተኛው የአጊት ልጅ አዶንያስ፣

3አምስተኛው የአቢጣል ልጅ ሰፋጥያስ፣

ስድስተኛው ከሚስቱ ከዔግላ የተወለደው ይትረኃም።

4እነዚህ ስድስቱ የተወለዱት ዳዊት በኬብሮን ሆኖ ሰባት ዓመት ተኩል በገዛበት ጊዜ ነበር።

ዳዊት በኢየሩሳሌም ሠላሳ ሦስት ዓመት ነገሠ፤ 5በዚያም የወለዳቸው ልጆች እነዚህ ነበሩ፤

ሳሙስ፣3፥5 ዕብራይስጡ፣ ሺማ ይላል፤ ሻሙአ ከሚለው ጋር አንድ ነው። ሶባብ፣ ናታን፣ ሰሎሞን፤ እነዚህ አራት ወንዶች ልጆች ከዓሚኤል ልጅ ከቤርሳቤህ የተወለዱ ናቸው።

6እንዲሁም ሌሎች ወንዶች ልጆች ነበሩት፤ ስማቸውም ኢያቤሐር፣ ኤሊሱዔ፣ ኤሊፋላት፣ 7ኖጋ፣ ናፌቅ፣ ያፍያ፣ 8ኤሊሳማ፣ ኤሊዳሄ፣ ኤሊፋላት ይባላል፤ በአጠቃላይ ዘጠኝ ነበሩ።

9ከቁባቶቹ ከወለዳቸው ወንዶች ልጆች ሌላ እነዚህ ሁሉ ልጆቹ ነበሩ፤ እነዚህም ትዕማር የምትባል እኅት ነበረቻቸው።

የይሁዳ ነገሥታት

10የሰሎሞን ልጅ ሮብዓም ነበረ፤

የሮብዓም ልጅ አቢያ፣

የአቢያ ልጅ አሳ፣

የአሳ ልጅ ኢዮሣፍጥ፣

11የኢዮሣፍጥ ልጅ ኢዮራም፣

የኢዮራም ልጅ አካዝያስ፣

የአካዝያስ ልጅ ኢዮአስ፣

12የኢዮአስ ልጅ አሜስያስ፣

የአሜስያስ ልጅ ዓዛርያስ፣

የዓዛርያስ ልጅ ኢዮአታም፣

13የኢዮአታም ልጅ አካዝ፣

የአካዝ ልጅ ሕዝቅያስ፣

የሕዝቅያስ ልጅ ምናሴ፣

14የምናሴ ልጅ አሞጽ፣

የአሞጽ ልጅ ኢዮስያስ።

15የኢዮስያስ ወንዶች ልጆች፤

በኵሩ ዮሐናን፣

ሁለተኛ ልጁ ኢዮአቄም፣

ሦስተኛ ልጁ ሴዴቅያስ፣

አራተኛ ልጁ ሰሎም።

16የኢዮአቄም ዘሮች፤

ልጁ ኢኮንያ፣

ልጁ ሴዴቅያስ።

ከምርኮ በኋላ የነበረው የነገሥታቱ የትውልድ ሐረግ

17የምርኮኛው የኢኮንያን ዘሮች፤

ልጁ ሰላትያል፣ 18መልኪራም፣ ፈዳያ፣ ሼናጻር፣ ይቃምያ፣ ሆሻማ፣ ነዳብያ።

19የፈዳያ ወንዶች ልጆች፤

ዘሩባቤል፣ ሰሜኢ።

የዘሩባቤል ወንዶች ልጆች፤

ሜሱላም፣ ሐናንያ፤ እኅታቸው ሰሎሚት ትባላለች። 20ሌሎችም አምስት ልጆች ነበሩ፤ እነርሱም ሐሹባ፣ ኦሄል፣ በራክያ፣ ሐሳድያ፣ ዮሻብሒሴድ።

21የሐናንያ ዘሮች፤

ፈላጥያ፣ የሻያ፤ እንዲሁም የረፋያ፣ የአርናን፣ የአብድዩና የሴኬንያ ወንዶች ልጆች።

22የሴኬንያ ዘሮች፤

ሸማያና ወንዶች ልጆቹ፤ ሐጡስ፣ ይግአል፣ ባሪያሕ፣ ነዓርያ፣ ሻፋጥ፤ በአጠቃላይ ስድስት ነበሩ።

23የነዓርያ ወንዶች ልጆች፤

ኤልዮዔናይ፣ ሕዝቅያስ፣ ዓዝሪቃም፤ በአጠቃላይ ሦስት ነበሩ።

24የኤልዩዔናይም ወንዶች ልጆች፤

ሆዳይዋ፣ ኤልያሴብ፣ ፌልያ፣ ዓቁብ፣ ዮሐናን፣ ደላያ፣ ዓናኒ፤ በአጠቃላይ ሰባት ናቸው።

Chinese Contemporary Bible (Simplified)

历代志上 3:1-24

大卫的子孙

1以下是大卫希伯仑生的儿子:长子暗嫩,由耶斯列亚希暖所生;次子但以利,由迦密亚比该所生; 2三子押沙龙,由基述达买的女儿玛迦所生;四子亚多尼雅,由哈及所生; 3五子示法提雅,由亚比她所生;六子以特念,由大卫的妻子以格拉所生。 4以上六人都是大卫希伯仑生的。大卫希伯仑做王七年零六个月,在耶路撒冷做王三十三年。 5大卫耶路撒冷生的儿子有示米亚朔罢拿单所罗门,这四个儿子的母亲是亚米利的女儿拔示芭6大卫的儿子还有益辖以利沙玛以利法列7挪迦尼斐雅非亚8以利沙玛以利雅大以利法列,共九人。 9这些都是大卫的儿子,不包括嫔妃生的儿子。大卫还有个女儿,名叫她玛

所罗门的后裔

10所罗门的儿子是罗波安罗波安的儿子是亚比雅亚比雅的儿子是亚撒亚撒的儿子是约沙法11约沙法的儿子是约兰约兰的儿子是亚哈谢亚哈谢的儿子是约阿施12约阿施的儿子是亚玛谢亚玛谢的儿子是亚撒利雅亚撒利雅的儿子是约坦13约坦的儿子是亚哈斯亚哈斯的儿子是希西迦希西迦的儿子是玛拿西14玛拿西的儿子是亚们亚们的儿子是约西亚15约西亚的儿子有长子约哈难、次子约雅敬、三子西底迦、四子沙龙16约雅敬的儿子是耶哥尼雅西底迦

耶哥尼雅的后裔

17被掳的耶哥尼雅的儿子是撒拉铁18玛基兰毗大雅示拿萨耶加米何沙玛尼达比雅19毗大雅的儿子是所罗巴伯示每所罗巴伯的儿子是米书兰哈拿尼雅,女儿是示罗密20他还有五个儿子:哈舒巴阿黑比利迦哈撒底于沙·希悉21哈拿尼雅的儿子是毗拉提耶筛亚耶筛亚利法雅利法雅亚珥南亚珥南俄巴底亚俄巴底亚示迦尼22示迦尼的儿子是示玛雅示玛雅的儿子是哈突以甲巴利亚尼利雅沙法23尼利雅的三个儿子是以利约乃希西迦亚斯利干24以利约乃的七个儿子是何大雅以利亚实毗莱雅阿谷约哈难第莱雅阿拿尼