1 ዜና መዋዕል 11 – NASV & CCB

New Amharic Standard Version

1 ዜና መዋዕል 11:1-47

ዳዊት በእስራኤል ላይ ነገሠ

11፥1-3 ተጓ ምብ – 2ሳሙ 5፥1-3

1እስራኤል ሁሉ በኬብሮን ወደ ዳዊት መጥተው እንዲህ አሉት፤ “እነሆ፤ እኛ የገዛ ሥጋህና ደምህ ነን፤ 2በቀደመው ዘመን ሳኦል ንጉሥ ሆኖ ሳለ እስራኤልን ወደ ጦርነት የምትመራ አንተ ነበርህ፤ እግዚአብሔር አምላክህም፣ ‘ሕዝቤን እስራኤልን የምትጠብቅ አንተ ነህ፤ ንጉሣቸውም ትሆናለህ’ ብሎሃል”።

3የእስራኤል ሽማግሌዎች ሁሉ ንጉሥ ዳዊት ወዳለበት ወደ ኬብሮን መጡ፤ ዳዊትም በኬብሮን በእግዚአብሔር ፊት ከእነርሱ ጋር ቃል ኪዳን ገባ። እግዚአብሔር በሳሙኤል አማካይነት በሰጠው ተስፋ መሠረት ዳዊትን ቀብተው በእስራኤል ላይ አነገሡት።

ዳዊት ኢየሩሳሌምን ድል አደረገ

11፥4-9 ተጓ ምብ – 2ሳሙ 5፥6-10

4ዳዊትና እስራኤላውያን ሁሉ ኢያቡስ ወደምትባለው ወደ ኢየሩሳሌም ሄዱ። በዚያም የሚኖሩ ኢያቡሳውያን 5ዳዊትን፣ “ወደዚህ ፈጽሞ አትገባም” አሉት፤ ዳዊት ግን የጽዮንን ምሽግ ያዘ፤ እርሷም የዳዊት ከተማ ናት።

6ዳዊትም፣ “ኢያቡሳውያንን ቀድሞ የሚወጋ ሰው የሰራዊቱ አዛዥ ይሆናል” አለ፤ ስለዚህ የጽሩያ ልጅ ኢዮአብ በመጀመሪያ ወጣ፤ እርሱም አዛዥ ለመሆን በቃ።

7ከዚያም ዳዊት መኖሪያውን በዐምባዪቱ ውስጥ አደረገ፤ ከዚህም የተነሣ የዳዊት ከተማ ተባለች። 8ዳዊትም ከሚሎ ጀምሮ የከተማዪቱን ዙሪያ ቅጥር ሠራ፤ ኢዮአብ ደግሞ የቀረውን የከተማዪቱን ክፍል መልሶ ሠራ። 9እግዚአብሔር ጸባኦት ከእርሱ ጋር ስለ ነበር፣ ዳዊት በየጊዜው እየበረታ ሄደ።

የዳዊት ኀያላን ሰዎች

11፥10-41 ተጓ ምብ – 2ሳሙ 23፥8-39

10የዳዊት ኀያላን ሰዎች አለቆች እነዚህ ናቸው፤ እነርሱም እግዚአብሔር በሰጠው ተስፋ መሠረት መንግሥቱ በምድሪቱ ሁሉ ትሰፋ ዘንድ ከሌሎቹ እስራኤላውያን ጋር ሆነው ለመንግሥቱ ብርቱ ድጋፍ ሰጡ። 11የዳዊት ኀያላን ሰዎች ስም ዝርዝር ይህ ነው፤

ሐክሞናዊው ያሾብዓም የጦር መኮንኖቹ አለቃ11፥11 ሠላሳ ወይም እንደ አንዳንድ የሰብዓ ሊቃናት ትርጕሞች፣ ሦስት (እንዲሁም 2ሳሙ 23፥8 ይመ) ይላሉ ነበረ፤ እርሱም ጦሩን አንሥቶ በአንድ ጊዜ ሦስት መቶ ሰው ገደለ።

12ከእርሱም ቀጥሎ ከሦስቱ ኀያላን አንዱ የሆነው የአሆሃዊው የዱዲ ልጅ አልዓዛር ነው፤ 13እርሱም ፍልስጥኤማውያን ለጦርነት በተሰበሰቡ ጊዜ በፈስደሚም ከዳዊት ጋር አብሮ ነበረ፤ ገብስ በሞላበት የዕርሻ ቦታ ወታደሮቹ ከፍልስጥኤማውያን ፊት ሸሹ፤ 14ይሁን እንጂ በዕርሻው መካከል ቦታ ይዘው ስለ ነበረ ፍልስጥኤማውያንን ገደሉ፤ እግዚአብሔርም ታላቅ ድል ሰጣቸው።

15ከፍልስጥኤማውያን ሰራዊት ጥቂቱ በራፋይም ሸለቆ ሰፍሮ ሳለ፣ ከሠላሳዎቹ አለቆች ሦስቱ ዳዊትን ለመገናኘት በዓዶላም ዋሻ አጠገብ ወደሚገኘው ወደ ዐለቱ ወረዱ። 16በዚያን ጊዜ ዳዊት በምሽጉ ውስጥ ነበረ፤ የፍልስጥኤማውያን ሰራዊት ደግሞ በቤተ ልሔም ነበረ። 17ዳዊትም ውሃ ፈልጎ ነበርና፣ “ከቤተ ልሔም በር አቅራቢያ ከሚገኘው ጕድጓድ የምጠጣው ውሃ ማን ባመጣልኝ!” አለ። 18በዚህ ጊዜ ሦስቱ የፍልስጥኤማውያንን ሰራዊት ጥሰው በማለፍ በቤተ ልሔም በር አጠገብ ከሚገኘው ጕድጓድ ውሃ ቀድተው ለዳዊት አመጡለት፤ እርሱ ግን ሊጠጣው ስላልፈለገ በእግዚአብሔር ፊት አፈሰሰው። 19ከዚያም፣ “ይህን ከማድረግ እግዚአብሔር ይጠብቀኝ፤ ይህ በሕይወታቸው ቈርጠው የሄዱትን የእነዚህን ሰዎች ደም እንደ መጠጣት አይደለምን?” አለ። ይህን ለማምጣት በሕይወታቸው ቈርጠው ስለ ነበር፣ ዳዊት ሊጠጣው አልፈለገም።

ሦስቱ ኀያላን ሰዎች የሠሩት ይህን ነበር።

20የኢዮአብ ወንድም አቢሳ የሦስቱ አለቃ ነበረ። እርሱም ጦሩን አንሥቶ ሦስት መቶ ሰዎች ገደለ፤ ከዚህም የተነሣ እንደ ሦስቱ ሁሉ ዝነኛ ሆነ። 21ከሦስቱ አንዱ ሆኖ ባይቈጠርም እንኳ፣ ዕጥፍ ክብር አገኘ፤ አዛዣቸውም ሆነ።

22ከቀብስኤል የመጣውና ታላቅ ጀብዱ የሠራው የዮዳሄ ልጅ በናያስ ብርቱ ተዋጊ ነበረ። እርሱም እጅግ የታወቁ ሁለት የሞአብ ሰዎችን ገደለ። እንዲያውም አንድ ጊዜ በረዶ ምድርን በሸፈነበት ቀን ወደ አንድ ጕድጓድ ወርዶ አንበሳ ገደለ። 23ደግሞም ቁመቱ አምስት ክንድ11፥23 2.3 ሜትር ያህል ነው። የሆነ አንድ ግብፃዊ ገደለ፤ ግብፃዊው የሸማኔ መጠቅለያ የመሰለ ጦር በእጁ ቢይዝም፣ በናያስ ግን ቈመጥ ይዞ ገጠመው፤ ከግብፃዊው እጅ ጦሩን ነጥቆ በገዛ ጦሩ ገደለው። 24የዮዳሄ ልጅ በናያስ የፈጸመው ጀብዱ ይህ ነበር፤ እርሱም እንደ ሦስቱ ኀያላን ዝነኛ ሆነ። 25ከሠላሳዎቹም ይልቅ የበለጠ ክብር ተጐናጸፈ፤ ይሁን እንጂ ከሦስቱ አንዱ አልነበረም፤ ዳዊትም የክብር ዘቡ አዣዥ አደረገው።

26ኀያላኑም እነዚህ ነበሩ፤

የኢዮአብ ወንድም አሣሄል፣

የቤተ ልሔሙ የዱዲ ልጅ ኤልያናን፣

27ሃሮራዊው ሳሞት፣

ፊሎናዊው ሴሌድ፣

28የቴቍሔ ሰው የሆነው የዒስካ ልጅ፣

ዒራስ፣ የዓናቶቱ ሰው አቢዔዜር፣

29ኩሳታዊው ሴቤካይ፣

አሆሃዊው ዔላይ፣

30ነጦፋዊው ማህራይ፣

የነጦፋዊው የበዓና ልጅ ሔሌድ፣

31ከብንያም ወገን የጊብዓ ሰው የሆነው የሪባይ ልጅ ኤታይ፣

ጲርዓቶናዊው በናያስ፣

32የገዓስ ሸለቆዎች ሰው የሆነው ኡሪ፣

ዐረባዊው አቢኤል፣

33ባሕሩማዊው ዓዝሞት፣

ሰዓልቦናዊው ኤሊያሕባ፣

34የጊዞናዊው የአሳን ልጆች፣

የሃራራዊው የሻጌ ልጅ ዮናታን፣

35የሃራራዊው የሳኮር ልጅ አሒአም፣

የኡር ልጅ ኤሊፋል፣

36ምኬራታዊው ኦፌር፣

ፍሎናዊው አኪያ፣

37ቀርሜሎሳዊው ሐጽሮ፣

የኤዝባይ ልጅ ነዕራይ፤

38የናታን ወንድም ኢዮኤል፣

የሃግሪ ልጅ ሚብሐር፣

39አሞናዊው ጼሌቅ፣

የጽሩያ ልጅ የኢዮአብ ጋሻ ጃግሬ ቤሮታዊው ነሃራይ፣

40ይትራዊው ዒራስ፣

ይትራዊው ጋሬብ፣

41ኬጢያዊው ኦርዮ፣

የአሕላይ ልጅ ዛባድ፣

42የሮቤላዊው የሺዛ ልጅ ዓዲና፤ እርሱም የሮቤላውያንና አብረውት ለነበሩት የሠላሳ ሰዎች አለቃ ነበረ።

43የማዕካ ልጅ ሐናን፣

ሚትናዊው ኢዮሣፍጥ፣

44አስታሮታዊው ዖዝያ፣

የአሮዔራዊው የኮታም ልጆች ሻማና ይዒኤል፣

45የሺምሪ ልጅ ይዲኤል፣

ወንድሙም ቴዳዊው ዮሐ፣

46መሐዋዊው ኤሊኤል፣

የኤልነዓም ልጆች ይሪባይና ዮሻውያ፣

ሞዓባዊው ይትማ፣

47ኤሊኤል፣ ዖቤድና ምጾባዊው የዕሢኤል።

Chinese Contemporary Bible (Simplified)

历代志上 11:1-47

大卫做以色列人的王

1以色列人都聚集到希伯仑来见大卫,对他说:“我们是你的骨肉同胞。 2从前,即使扫罗做王的时候,率领以色列人出征打仗的仍是你。你的上帝耶和华也曾应许让你做祂以色列子民的牧者和首领。” 3以色列的长老都到希伯仑大卫王,大卫与他们在耶和华面前立约,他们膏立大卫以色列的王,这应验了耶和华借撒母耳所说的话。 4大卫以色列众人来到耶路撒冷,即耶布斯。那时耶布斯人住在那里。 5耶布斯人对大卫说:“你攻不进来。”可是,大卫攻取了锡安的堡垒,即后来的大卫城。 6大卫说:“谁先攻打耶布斯人,谁就做元帅。”洗鲁雅的儿子约押首先进攻,于是就做了元帅。 7大卫占据了堡垒,因此那堡垒就叫大卫城。 8大卫又从米罗开始,在四围修建城墙,其余的部分由约押修建。 9大卫日渐强盛,因为万军之耶和华与他同在。

大卫的勇士

10以下是大卫手下众勇士的统领,他们和以色列百姓竭力拥护大卫做王,正如耶和华对以色列的应许。 11大卫的勇士有哈革摩尼雅朔班,他是三勇士之首,曾在一次交战中挥矛刺死了三百人。 12其次是亚合朵多的儿子以利亚撒,他是三勇士之一。 13他曾在巴斯·达闵大卫一起抵抗非利士人。那里有一块大麦田,以色列人战败逃跑, 14他们却坚守阵地,奋勇杀敌。耶和华使以色列人大获全胜。 15一次,三十位勇士中有三位到亚杜兰洞附近的磐石那里见大卫,当时非利士的军队驻扎在利乏音谷。 16那时大卫留守在堡垒里,非利士人的驻军在伯利恒17大卫渴了,说:“真想有人打一些伯利恒城门旁的井水给我喝!” 18那三位勇士就冲过非利士人的营地,到伯利恒城门旁的井打水,带回来给大卫大卫却不肯喝,他把水浇奠在耶和华面前, 19说:“我的上帝啊!这三人冒死去打水,这些水就像是他们的血,我决不能喝。”因此,大卫不肯喝。这是三勇士的事迹。

20约押的兄弟亚比筛是这三个勇士的统领,他曾挥矛刺死三百人,在三勇士中出了名, 21最有声望,因此做了他们的统领,只是不及前三位勇士。

22甲薛耶何耶大的儿子比拿雅是位勇士,做过非凡的事。他曾杀死摩押的两个勇猛战士,也曾在下雪天跳进坑中杀死一头狮子, 23还曾杀死一个两米多高的埃及巨人。当时埃及人拿着织布机轴般粗的长矛,比拿雅只拿着棍子迎战,他夺了对方的长矛,用那矛刺死了对方。 24这是耶何耶大的儿子比拿雅的事迹,他在这三个勇士中出了名, 25比那三十个勇士更有声望,只是不及前三位勇士。大卫派他做护卫长。

26其他勇士有约押的兄弟亚撒黑伯利恒朵多的儿子伊勒哈难27哈律沙玛比伦希利斯28提哥亚益吉的儿子以拉亚拿突亚比以谢29户沙西比该亚合以莱30尼陀法玛哈莱尼陀法巴拿的儿子希立31便雅悯支派基比亚利拜的儿子以太比拉顿比拿雅32迦实溪户莱亚拉巴亚比33巴路米押斯玛弗沙本以利雅哈巴34基孙哈深的众子、哈拉沙基的儿子约拿单35哈拉沙甲的儿子亚希暗吾珥的儿子以利法勒36米基拉希弗比伦亚希雅37迦密希斯罗伊斯拜的儿子拿莱38拿单的兄弟约珥哈基利的儿子弥伯哈39亚扪洗勒、为洗鲁雅的儿子约押拿兵器的比录拿哈莱40以帖以拉以帖迦立41乌利亚亚莱的儿子撒拔42示撒的儿子亚第拿——吕便支派中率领三十人的首领、 43玛迦的儿子哈难弥特尼约沙法44亚施他拉乌西亚亚罗珥何坦的儿子沙玛耶利45提洗申利的儿子耶叠和他的兄弟约哈46玛哈未以利业伊利拿安的儿子耶利拜约沙未雅摩押伊特玛47以利业俄备得米琐巴雅西业