1 ዜና መዋዕል 1 – New Amharic Standard Version NASV

New Amharic Standard Version

1 ዜና መዋዕል 1:1-54

ከአዳም እስከ አብርሃም ያለው የትውልድ ሐረግ እስከ ኖኀ ልጆች

1አዳም፣ ሴት፣ ሄኖስ፣

2ቃይናን፣ መላልኤል፣ ያሬድ፣

3ሄኖክ፣ ማቱሳላ፣ ላሜሕ፣ ኖኅ።

4የኖኅ ወንዶች ልጆች1፥4 የሰብዓ ሊቃናት ትርጕም ከዚህ ጋር ይስማማል፤ ዕብራይስጡ ግን፣ የኖኀ ወንዶች ልጆች የሚለውን አይጨምርም።፤ ሴም፣ ካም፣ ያፌት።

ያፌታውያን

1፥5-7 ተጓ ምብ – ዘፍ 10፥2-5

5የያፌት ወንዶች ልጆች፤1፥5 ወንዶች ልጆች ማለት ዘር ወይም ሕዝብ ማለት ነው፤ እንዲሁም ቍ6-10፤ 17 እና 20

ጋሜር፣ ማጎግ፣ ማዴ፣ ያዋን፣ ቶቤል፣ ሞሳሕ፣ ቴራስ።

6የጋሜር ወንዶች ልጆች፤

አስከናዝ፣ ሪፋት፣ ቴርጋማ።

7የያዋን ወንዶች ልጆች፤

ኤሊሳ፣ ተርሴስ፣ ኪቲም፣ ሮድኢ።

ካማውያን

1፥8-16 ተጓ ምብ – ዘፍ 10፥6-20

8የካም ወንዶች ልጆች፤

ኵሽ፣ ምጽራይም፣1፥8 ግብፅ ናት፤ እንዲሁም ቍ11 ፉጥ፣ ከነዓን።

9የኵሽ ወንዶች ልጆች፤

ሳባ፣ ኤውላጥ፣ ሰብታ፣ ራዕማ፣ ሰብቃታ።

የራዕማ ወንዶች ልጆች፤

ሳባ፣ ድዳን።

10ኵሽ ናምሩድን ወለደ፤

እርሱም በምድር ላይ የመጀመሪያው ኀያል ጦረኛ ሆነ።

11ምጽራይም የሉዲማውያን፣ የዐናማውያን፣ የላህባማውያን፣ የነፍተሂማውያን፣ 12የፈትሩሲማውያን፣ የፍልስጥኤማውያን ቅድመ አባቶች የሆኑት የከስሉሂ ማውያንና የከፍቶሪማውያን ነገዶች አባት1፥12 አባት ማለት ቅድመ አያት ወይም እንጅላት ወይም መሠረት ማለት ነው፤ እንዲሁም ቍ16 ነው።

13ከነዓን የበኵር ልጁ የሆነው የሲዶን እንዲሁም የኬጢያውያን፣ 14የኢያቡሳውያን፣ የአሞራውያን፣ የጌርጌሳውያን፣ 15የኤዊያውያን፣ የዐርካውያን፣ የሲኒውያን፣ 16የአራዴዎያውያን፣ የሰማርያውያን፣ የአማቲያውያን አባት ነው።

ሴማውያን

1፥17-23 ተጓ ምብ – ዘፍ 10፥21-3111፥10-27

17የሴም ወንዶች ልጆች፤

ኤላም፣ አሦር፣ አርፋክስድ፣ ሉድ፣ አራም።

የአራም ወንዶች ልጆች፤1፥17 ወይም፣ የሲዶናውያን አለቃ

ዑፅ፣ ሁል፣ ጌቴር፣ ሞሳሕ።

18አርፋክስድ ሳላን ወለደ፤

ሳላም ዔቦርን ወለደ።

19ዔቦር ሁለት ወንዶች ልጆች ወለደ፤

በዘመኑ ምድር ስለ ተከፈለች፣ የአንደኛው ስም ፋሌቅ1፥19 ፋሌቅ ማለት መከፈል ማለት ነው ተብሎ ተጠራ፤ ወንድሙም ዮቅጣን ተባለ።

20ዮቅጣንም፣

አልሞዳድን፣ ሣሌፍን፣ ሐስረሞትን፣ ያራሕን፣ 21ሀዶራምን፣ አውዛልን፣ ደቅላን፣ 22ዖባልን፣1፥22 አንዳንድ የዕብራይስጥ ቅጆችና የሱርስቱ ትርጕም (እንዲሁም ዘፍ 10፥28 ይመ) ከዚህ ጋር ይስማማል፤ ብዙ የዕብራይስጥ ቅጆች ግን፣ ዒባል ይላሉ። አቢማኤልን፣ ሳባን፣ 23ኦፊርን፣ ኤውላጥን፣ ዮባብን ወለደ፤ እነዚህ ሁሉ የዮቅጣን ወንዶች ልጆች ናቸው።

24ሴም፣ አርፋክስድ1፥24 ዕብራይስጡ ከዚህ ጋር ይስማማል፤ አንዳንድ የሰብዓ ሊቃናት ቅጆች ግን፣ አርፋክስድ፣ ቃይንም ይላሉ (የዘፍ 11፥10 ማብ ይመ)።፣ ሳላ፣

25ዔቦር፣ ፋሌቅ፣ ራግው፣

26ሴሮሕ፣ ናኮር፣ ታራ፣

27እንዲሁም በኋላ አብርሃም የተባለው አብራም።

የአብርሃም ቤተ ሰብ

28የአብርሃም ወንዶች ልጆች፤ ይስሐቅ፣ እስማኤል።

የአጋር ዘሮች

1፥29-31 ተጓ ምብ – ዘፍ 25፥12-16

29የእነዚህ ዘሮች የሚከተሉት ናቸው፤

የእስማኤል በኵር ልጅ ነባዮት፣ ቄዳር፣ ነብዳኤል፣ መብሳም፣ 30ማስማዕ፣ ዱማ፣ ማሣ፣ ኩዳን፣ ቴማን፣ 31ኢጡር፣ ናፌስ፣ ቄድማ፤

እነዚህ የእስማኤል ወንዶች ልጆች ናቸው።

የኬጡራ ዘሮች

1፥32-33 ተጓ ምብ – ዘፍ 25፥1-4

32የአብርሃም ቁባት ኬጡራ የወለደቻቸው ወንዶች ልጆች ዘምራን፣ ዮቅሳን፣ ሜዳን፣ ምድያም፣ የስቦቅና፣ ስዌሕ ናቸው።

የዮቅሳን ወንዶች ልጆች፤

ሳባ፣ ድዳን።

33የምድያም ወንዶች ልጆች፤

ጌፌር፣ ዔፌር፣ ሄኖኅ፣ አቢዳዕ፣ ኤልዳዓ፤

እነዚህ ሁሉ የኬጡራ ዘሮች ናቸው።

የሣራ ዘሮች

1፥35-37 ተጓ ምብ – ዘፍ 36፥10-14

34አብርሃም ይስሐቅን ወለደ።

የይስሐቅ ወንዶች ልጆች፤

ዔሳው፣ እስራኤል።

የዔሳው ወንዶች ልጆች

35የዔሳው ወንዶች ልጆች፤

ኤልፋዝ፣ ራጉኤል፣ የዑስ፣ የዕላም፣ ቆሬ።

36የኤልፋዝ ወንዶች ልጆች፤

ቴማን፣ ኦማር፣ ስፎ1፥36 ብዙ የዕብራይስጥ ቅጆች፣ አንዳንድ የሰብዓ ሊቃናት ትርጕሞችና የሱርስቱ ቅጅ (እንዲሁም ዘፍ 36፥11 ይመ) ከዚህ ጋር ይስማማሉ፤ አያሌ የዕብራይስጥ ቅጆች ግን፣ ጾፊ ይላሉ፣ ጎቶም፣

ቄኔዝ፣ ቲምናዕ፣ አማሌቅ።

37የራጉኤል ወንዶች ልጆች፤

ናሖት፣ ዛራ፣ ሣማ፣ ሚዛህ።

በኤዶም የሚኖሩ የሴይር ሰዎች

1፥38-42 ተጓ ምብ – ዘፍ 36፥20-28

38የሴይር ወንዶች ልጆች፤

ሎጣን፣ ሦባል፣ ጽብዖን፣ ዓና፣ ዲሶን፣ ኤጽር፣ ዲሳን።

39የሎጣን ወንዶች ልጆች፤

ሖሪ፣ ሄማም፤ ቲሞናዕ የሎጣን እኅት ነበረች።

40የሦባል ወንዶች ልጆች፤

ዓልዋን፣ ማኔሐት፣ ዔባል፣ ስፎ፣ አውናም።

የጽብዖን ወንዶች ልጆች፤

አያ፣ ዓና።

41የዓና ወንድ ልጅ፤

ዲሶን።

የዲሶን ወንዶች ልጆች፤

ሔምዳን1፥41 ብዙ የዕብራይስጥና አንዳንድ የሰብዓ ሊቃናት ትርጕሞች (እንዲሁም ዘፍ 36፥26) ከዚህ ጋር ይስማማሉ፤ አያሌ የዕብራይስጥ ቅጆች ግን፣ ሐምራን ይላሉ።፣ ኤስባን፣ ይትራን፣ ክራን።

42የኤጽር ወንዶች ልጆች፤

ቢልሐን፣ ዛዕዋን፣ ዓቃን።

የዲሳን ወንዶች ልጆች፤

ዑፅ፣ አራን።

የኤዶምያስ ነገሥታት

1፥43-54 ተጓ ምብ – ዘፍ 36፥31-43

43በእስራኤል አንድም ንጉሥ ገና ሳይነግሥ1፥43 ወይም፣ እስራኤላዊ የሆነ ንጉሥ ገና በእነርሱ ላይ ከመንገሡ በፊት በኤዶም ምድር የነገሡ ነገሥታት እነዚህ ናቸው፤

የቢዖር ልጅ ባላቅ፤ ከተማዪቱም ዲንሃባ ትባል ነበር።

44ባላቅ ሲሞትም የባሶራ ሰው የሆነው የዛራ ልጅ ኢዮባብ በእግሩ ተተክቶ ነገሠ።

45ኢዮባብ ሲሞት የቴማን አገር ሰው የሆነው ሑሳም በእግሩ ተተክቶ ነገሠ።

46ሑሳም ሲሞት በሞዓብ ምድር ምድያምን ድል ያደረገው የባዳድ ልጅ በእግሩ ተተክቶ ነገሠ። የከተማዪቱም ስም ዓዊት ተባለ።

47ሃዳድም ሲሞት የመሥሬቃ ሰው የሆነው ሠምላ በእግሩ ተተክቶ ነገሠ።

48ሠምላም ሲሞት በወንዙ1፥48 ምናልባት ኤፍራጥስን ነው። አጠገብ ያለችው የረሚቦት ሰው የሆነው ሳኡል በእግሩ ተተክቶ ነገሠ።

49ሳኡልም ሲሞት የዓክቦር ልጅ የሆነው በኣልሐናንም በእግሩ ተተክቶ ነገሠ።

50በኣልሐናን ሲሞት ሀዳድ በእግሩ ተተክቶ ነገሠ። ከተማውም ፋዑ ትባል ነበር፤ ሚስቱ መሄጣብኤል ትባላለች፤ እርሷም የሜዛሃብ ልጅ የመጥሬድ ልጅ ነበረች። 51ሀዳድም ሞተ።

ዋና ዋናዎቹ የኤዶም ሕዝብ አለቆች እነዚህ ነበሩ፤

ቲምናዕ፣ ዓልዋ፣ የቴት፣ 52አህሊባማ፣ ኤላ፣ ፊኖን፣ 53ቄኔዝ፣ ቴማን፣ ሚብሳር፣ 54መግዲኤል፣ ዒራም።

እነዚህ የኤዶም አለቆች ነበሩ።