1 ሳሙኤል 9 – NASV & TNCV

New Amharic Standard Version

1 ሳሙኤል 9:1-27

ሳሙኤል ሳኦልን ለንጉሥነት ቀባው

1ቂስ የተባለ አንድ ታዋቂ ብንያማዊ ሰው ነበረ፤ እርሱም የአቢኤል ልጅ፣ የጽሮር ልጅ፣ የብኮራት ልጅ፣ የብንያማዊው የአፌቅ ልጅ ነበር። 2ቂስም ከእስራኤል ልጆች መካከል በመልከ ቀናነቱ ተወዳዳሪ የማይገኝለት፣ ቁመቱም ከሌሎቹ ሁሉ ይልቅ ከትከሻው በላይ ዘለግ ያለ፣ ሳኦል የተባለ ወጣት ልጅ ነበረው።

3በዚያም ጊዜ የሳኦል አባት የቂስ አህዮች ጠፍተው ነበር፤ ቂስም ልጁን ሳኦልን፣ “ከአገልጋዮቹ መካከል አንዱን ይዘህ ሂድና አህዮቹን ፈልግ” አለው። 4ስለዚህ በኰረብታማው በኤፍሬም አገርና በሻሊሻ አካባቢ ባለው ስፍራ ሁሉ ተዘዋወረ፤ ሆኖም አህዮቹን አላገኙም። ወደ ሻዕሊምም ግዛት ዘልቀው ገቡ፤ አህዮቹ ግን በዚያም አልነበሩም። እንዲሁም በብንያም ግዛት በኩል ዐለፈ፤ ሆኖም አላገኟቸውም።

5ወደ ጹፍ ግዛት በደረሱ ጊዜ ሳኦል አብሮት የነበረውን አገልጋይ፣ “አባቴ ይህን ጊዜ ስለ አህዮቹ ማሰቡን ትቶ ስለ እኛ መጨነቅ ስለሚጀምር፣ ና እንመለስ” አለው።

6አገልጋዩ ግን፣ “እነሆ፤ በዚህች ከተማ አንድ የእግዚአብሔር ሰው አለ፤ እርሱም በጣም የተከበረ ነው፤ የሚናገረውም ሁሉ በትክክል ይፈጸማል፤ በየትኛው መንገድ መሄድ እንዳለብን ይነግረን ይሆናልና ወደዚያ እንሂድ” ሲል መለሰለት።

7ሳኦልም አገልጋዩን፣ “መሄዱን እንሂድ፤ ነገር ግን ለሰውየው ምን እንሰጠዋለን? በስልቻዎቻችን የያዝነው ስንቅ ዐልቋል። ለእግዚአብሔር ሰው የምናበረክተውም ስጦታ የለንም፤ ታዲያ ምን አለን?” አለው።

8አገልጋዩ፣ “እኔ የአንድ ሰቅል ጥሬ ብር ሩብ9፥8 ሦስት ግራም ያህል ነው። አለኝ፤ በየትኛው መንገድ መሄድ እንዳለብን ይነግረን ዘንድ ገንዘቡን ለእግዚአብሔር ሰው እሰጠዋለሁ” ሲል በድጋሚ መለሰለት። 9ቀደም ሲል በእስራኤል ዘንድ አንድ ሰው እግዚአብሔርን ለመጠየቅ ሲሄድ፣ “ኑ ወደ ባለ ራእዩ እንሂድ” ይል ነበር፤ ዛሬ ነቢይ የሚባለው በዚያ ጊዜ ባለ ራእይ ይባል ነበርና።

10ሳኦልም፣ “መልካም፤ ና እንሂድ” አለው። ስለዚህ የእግዚአብሔር ሰው ወዳለበት ከተማ ሄዱ።

11በከተማዪቱ መዳረሻ ያለውን ኰረብታ በመውጣት ላይ ሳሉ፣ ውሃ ለመቅዳት የሚወጡ ልጃገረዶችን አግኝተው፣ “ባለ ራእዩ እዚህ ነውን?” ሲሉ ጠየቁ።

12እነርሱም እንዲህ ሲሉ መለሱላቸው፤ “አዎን አለ፤ እነሆ፤ ከፊታችሁ ነው፤ ፈጠን በሉ፤ ሕዝቡ በማምለኪያው ኰረብታ ላይ መሥዋዕት ስለሚያቀርብ፣ ወደ ከተማችን ገና ዛሬ መምጣቱ ነው፤ 13ወደ ከተማዪቱም በገባችሁ ጊዜ፣ ለመብላት ወደ ማምለኪያው ኰረብታ ከመውጣቱ በፊት ታገኙታላችሁ። መሥዋዕቱን እርሱ መባረክ ስላለበት፣ እርሱ እስኪመጣ ድረስ ሕዝቡ መብላት አይጀምርም፤ ከዚያ በኋላ የተጋበዘው ሕዝብ ይበላል፤ አሁኑኑ ውጡ፤ ወዲያው ታገኙታላችሁ።”

14እነርሱም ወደ ከተማዪቱ ወጡ፤ ወደ ከተማዪቱም በመግባት ላይ ሳሉ፣ እነሆ፤ ሳሙኤል ወደ ማምለኪያው ኰረብታ ለመውጣት እነርሱ ወዳሉበት አቅጣጫ መጣ።

15ሳኦል ከመምጣቱ ከአንድ ቀን በፊት እግዚአብሔር ለሳሙኤል ይህን እንዲህ ሲል ገልጦለት ነበር፤ 16“ነገ በዚህ ጊዜ ከብንያም ምድር አንድ ሰው ወደ አንተ እልካለሁ፤ በሕዝቤ በእስራኤል ላይ መሪ እንዲሆን ቅባው፤ እርሱም ሕዝቤን ከፍልስጥኤማውያን እጅ ይታደጋል። እነሆ፤ ሕዝቤን ከላይ ተመልክቻለሁ፤ ጩኸቱ ከእኔ ዘንድ ደርሷልና።”

17ሳሙኤል ሳኦልን ባየው ጊዜ እግዚአብሔር፣ “ያ የነገርሁህ ሰው እነሆ፤ እርሱም ሕዝቤን ይገዛል” አለው።

18ሳኦልም በቅጥሩ በር ላይ ወደ ሳሙኤል ቀረብ ብሎ፣ “የባለ ራእዩ ቤት የት እንደ ሆነ ትነግረኛለህ?” ሲል ጠየቀው።

19ሳሙኤልም እንዲህ ሲል መለሰለት፤ “ባለ ራእዩ እኔ ነኝ፤ ዛሬ ከእኔ ጋር ስለምትበሉ ከፊቴ ቀድማችሁ ወደ ማምለኪያው ኰረብታ ውጡ፤ ነገ ጧት አሰናብትሃለሁ፤ በልብህ ያለውንም እነግርሃለሁ። 20ከሦስት ቀን በፊት ስለ ጠፉብህ አህዮች አትጨነቅ፤ ተገኝተዋልና። የእስራኤል ምኞት ሁሉ ያዘነበለው ወደ አንተና ወደ አባትህ ቤተ ሰብ ሁሉ አይደለምን?”

21ሳኦልም፣ “እኔ ከእስራኤል ነገዶች ውስጥ በጣም አነስተኛ ከሆነው ከብንያም ወገን አይደለሁምን? ጐሣዬስ ከብንያም ነገድ ጐሣዎች ሁሉ የሚያንስ አይደለምን? ታዲያ እንዲህ ያለውን ነገር ስለ ምን ትነግረኛለህ?” ብሎ መለሰለት።

22ከዚያም ሳሙኤል ሳኦልንና አገልጋዩን ወደ አዳራሹ አመጣ፤ ከተጋበዙትም ሠላሳ ያህል ሰዎች ሁሉ በላይ አስቀመጣቸው። 23ሳሙኤልም ወጥ ቤቱን፣ “ለይተህ አስቀምጥ ብዬ የሰጠሁህን የሥጋ ብልት አምጣው” አለው።

24ወጥ ቤቱም የጭኑን ሥጋ እንዳለ አምጥቶ በሳኦል ፊት አስቀመጠው። ሳሙኤልም፣ “ይህ፣ ‘እንግዶችን ጋብዣለሁ’ ካልሁበት ጊዜ ጀምሮ እስከ ተወሰነው ጊዜ ድረስ ለአንተ ተለይቶ የተቀመጠልህ ስለሆነ ብላው” አለው። ሳኦልም በዚያች ዕለት ከሳሙኤል ጋር አብሮ በላ።

25ከማምለኪያው ኰረብታ ወደ ከተማዪቱ ከወረዱ በኋላ ሳሙኤል በቤቱ ሰገነት ላይ ከሳኦል ጋር ተነጋገረ። 26በማለዳ ተነሡ፤ ሳሙኤል ሳኦልን ከሰገነቱ ላይ ጠርቶ፣ “ላሰናብትህ ስለሆነ ተዘጋጅ” አለው። ሳኦልም ተዘጋጅቶ እንዳበቃ፣ ከሳሙኤል ጋር ተያይዘው ወደ ውጭ ወጡ። 27ወደ ከተማዪቱ ዳርቻ እየወረዱ ሳለ፣ ሳሙኤል ሳኦልን፣ “አገልጋይህ ወደ ፊት ቀድሞን እንዲሄድ ንገረው” አለው፤ አገልጋዩም እንደ ተነገረው አደረገ፤ ከዚህ በኋላ ሳሙኤል፣ “አንተ ግን ከእግዚአብሔር የተላከ መልእክት እነግርህ ዘንድ ለጥቂት ጊዜ እዚህ ቈይ” አለው።

Thai New Contemporary Bible

1ซามูเอล 9:1-27

ซามูเอลเจิมตั้งซาอูล

1มีชายเผ่าเบนยามินคนหนึ่งซึ่งเป็นคนมีฐานะชื่อคีช เป็นบุตรอาบีเอล ผู้เป็นบุตรเศโรร์ ผู้เป็นบุตรเบโครัท ผู้เป็นบุตรอาฟียาห์แห่งเบนยามิน 2บุตรชายคนหนึ่งของเขาชื่อซาอูล เป็นคนสง่างามที่สุดในอิสราเอล เขาสูงกว่าคนอื่นๆ ราวหนึ่งช่วงศีรษะ

3วันหนึ่งฝูงลาของคีชบิดาของซาอูลหายไป เขาจึงสั่งซาอูลบุตรชายว่า “จงออกตามหาลา และเอาคนรับใช้คนหนึ่งไปด้วย” 4ทั้งสองเดินทางทั่วแดนเทือกเขาแห่งเอฟราอิม ผ่านดินแดนชาลิชา ชาอาลิม และทั่วเขตเบนยามินแต่ก็ไม่พบลาเลย

5เมื่อมาถึงดินแดนศูฟ ซาอูลพูดกับคนรับใช้ที่มาด้วยว่า “กลับบ้านกันเถอะ เกรงว่าป่านนี้พ่อคงจะเลิกห่วงลา หันมากังวลใจเรื่องเราแทน”

6แต่คนรับใช้นั้นตอบว่า “ดูเถิด ในเมืองนี้มีคนของพระเจ้าอยู่คนหนึ่ง ผู้คนเคารพนับถือมาก เขากล่าวอะไรก็เป็นไปตามนั้นทุกประการ เราไปหาเขากันเถอะ เขาอาจบอกเราได้ว่าควรไปทางไหน”

7ซาอูลกล่าวกับคนรับใช้ว่า “หากเราไป เราจะให้อะไรเขาได้บ้าง? อาหารในถุงเสบียงของเราก็หมดแล้ว เราไม่มีของที่จะมอบให้คนของพระเจ้า เรามีอะไรบ้าง?”

8คนรับใช้ตอบว่า “ข้าพเจ้ามีเงินอยู่หนึ่งในสี่เชเขล9:8 1 เชเขล คือเงินหนักประมาณ 11.5 กรัม มีค่าเท่ากับค่าแรงสองเดือนจะมอบให้คนของพระเจ้า เพื่อเขาจะบอกทางแก่เรา” 9(ในอิสราเอลสมัยนั้นหากมีใครจะไปทูลถามจากพระเจ้า เขาจะพูดว่า “ให้เราไปหาผู้ทำนายกันเถิด” เพราะผู้เผยพระวจนะในปัจจุบันเคยถูกเรียกว่าผู้ทำนาย)

10ซาอูลกล่าวกับคนรับใช้ว่า “ดีแล้ว ให้เราไปกันเถิด” พวกเขาจึงมุ่งหน้าไปยังเมืองที่คนของพระเจ้าอยู่

11เมื่อพวกเขาขึ้นเนินเขาเพื่อไปยังเมืองนั้นก็พบพวกหญิงสาวที่ออกมาตักน้ำ จึงถามว่า “ผู้ทำนายอยู่ที่นี่หรือเปล่า?”

12หญิงสาวตอบว่า “อยู่เจ้าข้า เขาเพิ่งล่วงหน้าไป รีบๆ เถิด เขาเพิ่งมาถึงเมืองของเราวันนี้เอง เพราะผู้คนจะถวายเครื่องบูชาบนสถานสูง 13เมื่อพวกท่านไปถึงตัวเมืองก็จะพบเขาก่อนที่เขาจะขึ้นไปรับประทานอาหารบนสถานสูง คนทั้งหลายจะไม่เริ่มรับประทานจนกว่าเขาจะไปถึงเพราะเขาต้องอวยพรเครื่องบูชา หลังจากนั้นคนที่ได้รับเชิญจึงจะรับประทาน พวกท่านรีบไปตอนนี้จะได้พบแน่”

14คนทั้งสองจึงไป ขณะกำลังเดินเข้าเมือง พวกเขาก็พบซามูเอลกำลังเดินมุ่งหน้ามาทางพวกเขาตามทางขึ้นไปสถานสูง

15องค์พระผู้เป็นเจ้าได้สำแดงแก่ซามูเอลตั้งแต่วันก่อนที่ซาอูลจะมาถึงว่า 16“วันพรุ่งนี้เวลาประมาณนี้ เราจะส่งชายคนหนึ่งจากเขตแดนเบนยามินมาหาเจ้า จงเจิมคนนั้นให้เป็นผู้นำอิสราเอลประชากรของเรา เขาจะช่วยเหล่าประชากรให้รอดพ้นจากเงื้อมมือชาวฟีลิสเตีย เราเอ็นดูสงสารประชากรของเรา เพราะเสียงร่ำร้องของพวกเขามาถึงเราแล้ว”

17เมื่อซามูเอลเห็นซาอูล องค์พระผู้เป็นเจ้าตรัสว่า “คนนี้แหละที่เราบอกเจ้าไว้ เขาจะปกครองประชากรของเรา”

18ซาอูลเดินเข้ามาหาซามูเอลที่ประตูเมืองและกล่าวว่า “ช่วยบอกทางไปบ้านผู้ทำนายด้วยเถิด”

19ซามูเอลตอบว่า “ข้าพเจ้านี่แหละเป็นผู้ทำนาย เชิญนำหน้าข้าพเจ้าขึ้นไปยังสถานสูง เพราะวันนี้ท่านจะรับประทานอาหารกับข้าพเจ้า แล้วพรุ่งนี้เช้าข้าพเจ้าจะบอกทุกอย่างที่อยู่ในใจของท่านและจะให้ท่านไป 20ส่วนฝูงลาที่หายไปเมื่อสามวันก่อนนั้น ไม่ต้องห่วง เขาพบแล้ว ใครเล่าที่อิสราเอลปรารถนาเป็นอย่างมาก? ก็คือตัวท่านและครอบครัวของบิดาของท่านนั่นเอง”

21ซาอูลตอบว่า “แต่ว่าข้าพเจ้าเป็นคนเบนยามินซึ่งเป็นเผ่าเล็กน้อยที่สุดของอิสราเอลไม่ใช่หรือ? และตระกูลของข้าพเจ้าก็เล็กที่สุดในบรรดาตระกูลในเผ่าเบนยามินไม่ใช่หรือ? เหตุใดท่านจึงกล่าวกับข้าพเจ้าเช่นนั้น?”

22ซามูเอลจึงนำซาอูลกับคนรับใช้เข้าไปในห้องโถง และให้นั่งหัวโต๊ะท่ามกลางแขกรับเชิญซึ่งมีราวสามสิบคน 23ซามูเอลสั่งพ่อครัวว่า “จงนำเนื้อชิ้นที่เราบอกให้เจ้าเก็บไว้ต่างหากออกมา”

24พ่อครัวจึงนำเนื้อส่วนขามาวางตรงหน้าซาอูล ซามูเอลกล่าวว่า “นี่คือสิ่งที่เก็บไว้สำหรับท่าน เชิญรับประทานเถิด เพราะเนื้อนี้ได้แยกไว้สำหรับท่านในโอกาสนี้ ตั้งแต่เวลาที่ข้าพเจ้ากล่าวว่า ‘ข้าพเจ้าได้เชิญแขกมาแล้ว’ ” ซาอูลก็รับประทานอาหารร่วมกับซามูเอลในวันนั้น

25หลังจากพวกเขากลับจากสถานสูงเข้ามาในเมืองแล้ว ซามูเอลสนทนากับซาอูลบนดาดฟ้าบ้านของเขา 26วันรุ่งขึ้นเมื่อฟ้าเริ่มสาง ซามูเอลเรียกซาอูลบนดาดฟ้าว่า “จงเตรียมตัว เราจะไปส่ง” เมื่อซาอูลพร้อมแล้ว ทั้งสองก็เดินออกไปด้วยกัน 27ขณะที่มาถึงสุดเขตเมือง ซามูเอลบอกซาอูลว่า “จงให้คนรับใช้ล่วงหน้าไปก่อน” เมื่อคนรับใช้ไปแล้ว ซามูเอลก็บอกซาอูลว่า “จงรอสักครู่เถิด เพื่อเราจะแจ้งพระดำรัสของพระเจ้าแก่ท่าน”