ዳንኤል 7 – NASV & CCB

New Amharic Standard Version

ዳንኤል 7:1-28

ዳንኤል ስለ አራቱ አራዊት ያየው ሕልም

1የባቢሎን ንጉሥ ቤልሻዛር በነገሠ በመጀመሪያው ዓመት ዳንኤል በዐልጋው ላይ ተኝቶ ሳለ ሕልም ዐለመ፤ ራእይም አየ፤ የሕልሙንም ዋና ሐሳብ ጻፈው።

2ዳንኤል እንዲህ አለ፤ “አራቱ የሰማይ ነፋሳት ታላቁን ባሕር ሲያናውጡት ሌሊት በራእይ አየሁ። 3እርስ በርሳቸው የማይመሳሰሉ አራት ታላላቅ አራዊት ከባሕሩ ወጡ።

4“የመጀመሪያው፣ አንበሳ ይመስል ነበር፤ የንስርም ክንፎች ነበሩት፤ ክንፎቹ እስኪነቃቀሉ ድረስ ተመለከትሁ፤ እንደ ሰው በሁለት እግሩ እንዲቆም ከምድር ከፍ ከፍ ተደረገ፤ የሰውም ልብ ተሰጠው።

5“እነሆም፤ ሁለተኛው አውሬ ድብ ይመስል ነበር፤ በአንድ ጐኑ ከፍ ብሏል፤ በአፉ ውስጥ በጥርሶቹ መካከል ሦስት የጐድን ዐጥንቶች ነበሩት። እርሱም፤ ‘ተነሥ፤ እስክትጠግብ ድረስ ሥጋ ብላ!’ ተባለ።

6“ከዚያ በኋላ ተመለከትሁ፤ በፊቴ ነብር የሚመስል ሌላ አውሬ ነበር፤ በጀርባውም በኩል የወፍ ክንፍ የሚመስሉ አራት ክንፎች ነበሩት፤ ይህ አውሬ አራት ራስ ነበረው፤ ለመግዛትም ሥልጣን ተሰጠው።

7“ከዚህ በኋላ በሌሊት ራእይ አየሁ፤ በፊቴም የሚያስፈራና የሚያስደነግጥ በጣም ኀይለኛ የሆነ አራተኛ አውሬ ነበር፤ ትልልቅ የብረት ጥርሶች ነበሩት፤ ያደቅቅና ይበላ፣ የቀረውንም ሁሉ በእግሮቹ ይረጋግጥ ነበር። ከእርሱ በፊት ከነበሩት አራዊት ሁሉ የተለየ ሲሆን፣ ዐሥር ቀንዶች ነበሩት።

8“ስለ ቀንዶቹ ሳስብ ሳለሁ፣ ከመካከላቸው አንድ ሌላ ትንሽ ቀንድ ብቅ ሲል አየሁ፤ ከመጀመሪያዎቹ ቀንዶች ሦስቱ ከፊቱ ተነቃቀሉ፤ ይህም ቀንድ የሰው ዐይኖችን የሚመስሉ ዐይኖች፣ በትዕቢትም የሚናገር አፍ ነበረው።

9“እኔም ስመለከት፣

“ዙፋኖች ተዘረጉ፤

ጥንታዌ ጥንቱም ተቀመጠ፤

ልብሱ እንደ በረዶ ነጭ ነበረ፤

የራሱም ጠጕር እንደ ጥጥ ነጭ ነበረ፤

ዙፋኑ የእሳት ነበልባል፣

መንኰራኵሮቹም ሁሉ እንደሚነድድ እሳት ነበሩ።

10የእሳት ወንዝ፣ ከፊት ለፊቱ ፈልቆ

ይፈስስ ነበር፤

ሺሕ ጊዜ ሺሖች ያገለግሉት ነበር፤

እልፍ ጊዜ እልፍ በፊቱ ቆመዋል፤

የፍርድ ጉባኤ ተሰየመ፤

መጻሕፍትም ተከፈቱ።

11“ቀንዱም ከሚናገረው የትዕቢት ቃል የተነሣ፣ መመልከቴን ቀጠልሁ፤ አውሬው እስኪታረድና አካሉ ደቅቆ ወደሚንበለበለው እሳት እስኪጣል ድረስ ማየቴን አላቋረጥሁም። 12ሌሎቹም አራዊት ሥልጣናቸው ተገፍፎ ነበር፤ ነገር ግን ለተወሰነ ጊዜና ወቅት በሕይወት እንዲኖሩ ተፈቀደላቸው።

13“ሌሊት ባየሁት ራእይ፣ የሰውን ልጅ የሚመስል ከሰማይ ደመና ጋር ሲመጣ አየሁ፤ ወደ ጥንታዌ ጥንቱ መጣ፤ ወደ ፊቱም አቀረቡት። 14ሥልጣን፣ ክብርና ታላቅ ኀይል ተሰጠው፤ በልዩ ልዩ ቋንቋ የሚናገሩ ሰዎች፣ መንግሥታትና ሕዝቦች ሰገዱለት፤ ግዛቱም ለዘላለም የማያልፍ ነው፤ መንግሥቱም ፈጽሞ የማይጠፋ ነው።

የሕልሙ ትርጕም

15“እኔ ዳንኤል በመንፈሴ ታወክሁ፤ ያየሁትም ራእይ እጅግ አስጨነቀኝ። 16በዚያ ከቆሙት ወደ አንዱ ቀርቤ፣ የዚህ ሁሉ እውነተኛ ትርጕም ምን እንደ ሆነ ጠየቅሁት።

“እርሱም መለሰልኝ፤ የእነዚህንም ነገሮች ትርጕም እንዲህ ሲል ነገረኝ፤ 17‘አራቱ ታላላቅ አራዊት ከምድር የሚነሡ መንግሥታት ናቸው፤ 18ነገር ግን የልዑሉ ቅዱሳን መንግሥቱን ይወስዳሉ፤ ለዘላለምም ይይዙታል፤ አዎን፤ ለዘላለም ይይዙታል።’

19“ከዚያም የሚያደቅቀውንና የሚበላውን፣ የቀረውንም ሁሉ በእግሮቹ የሚረጋግጠውን፣ የብረት ጥርሶችና የናስ ጥፍሮች የነበሩትን፣ ከሌሎቹ አራዊት የተለየና እጅግ አስፈሪ የሆነውን የአራተኛውን አውሬ እውነተኛ ትርጕም ማወቅ ፈለግሁ። 20ደግሞም በራሱ ላይ ስላሉት ዐሥር ቀንዶች፣ ከመካከላቸው ብቅ ስላለው ቀንድና ከዚሁ ቀንድ ፊት ስለ ተነቃቀሉት ሦስት ቀንዶች፣ እንደዚሁም ከሌሎች ስለ በለጠው የሰው ዐይኖች የሚመስሉ ዐይኖች፣ በትዕቢትም የሚናገር አፍ ስለ ነበሩት ስለዚሁ ቀንድ ማወቅ ፈለግሁ። 21እነሆም፤ ይህ ቀንድ በቅዱሳን ላይ ጦርነት ዐውጆ አሸነፋቸው፤ 22ይህም የሆነው ጥንታዌ ጥንቱ እስኪመጣና ለልዑሉ ቅዱሳን እስኪፈርድላቸው ድረስ ነበር፤ ከዚያም የልዑሉ ቅዱሳን መንግሥቱን የሚወርሱበት ዘመን መጣ።

23“እርሱም እንዲህ አለኝ፣ ‘አራተኛው አውሬ በምድር ላይ የሚነሣ አራተኛው መንግሥት ነው። ከሌሎች መንግሥታት ሁሉ የተለየ ይሆናል፤ መላውንም ምድር እየረገጠና እያደቀቀ ይበላል። 24ዐሥሩ ቀንዶች ከዚህ መንግሥት የሚወጡ ዐሥር ነገሥታት ናቸው፤ ከዚያም በኋላ ከእነርሱ የተለየ ሌላ ንጉሥ ይነሣል፤ ሦስቱንም ነገሥታት ያንበረክካል። 25በልዑል ላይ የዐመፅ ቃል ይናገራል፤ የልዑልንም ቅዱሳን ያስጨንቃል፤ ለበዓላት የተመደበውን ጊዜና ሕግን ለመለወጥ ይሞክራል፤ ቅዱሳንም ለዘመን፣ ለዘመናት፣ ለዘመን እኩሌታም7፥25 ወይም ለአንድ ዓመት፣ ለሁለት ዓመት እንዲሁም ለዓመት እኩሌታም ለእርሱ ዐልፈው ይሰጣሉ።

26“ ‘ነገር ግን የፍርድ ዙፋን ይዘረጋል፤ ሥልጣኑም ይወሰድበታል፤ ፈጽሞ ለዘላለም ይደመሰሳል። 27ከዚያም ከሰማይ በታች ያሉ መንግሥታት ልዕልና፣ ሥልጣንና ታላቅነት ለልዑሉ ሕዝብ፣ ለቅዱሳን ይሰጣል። መንግሥቱ የዘላለም መንግሥት ይሆናል፤ ገዦች ሁሉ ያመልኩታል፤ ይታዘዙታልም።’

28“የነገሩ ፍጻሜ ይህ ነው፤ እኔም ዳንኤል በሐሳቤ እጅግ ተጨነቅሁ፤ መልኬም ተለዋወጠ፤ ይሁን እንጂ ነገሩን በልቤ ጠበቅሁት።”

Chinese Contemporary Bible (Simplified)

但以理书 7:1-28

但以理梦见四兽

1巴比伦伯沙撒元年,但以理在床上做了一个梦,脑中出现了异象,便把梦记录下来,讲述其中的大意。 2但以理说:“我在夜间的异象中看见天风四面吹来,搅动大海。 3接着,四只巨兽从海中上来,各有不同的形状。 4第一只兽像狮子,但有鹰的翅膀。我观看时,见它的翅膀被拔掉。它被扶起来,像人一样双脚站在地上,并被赋予人的头脑。 5第二只兽像熊,用两只后腿站立,牙齿间叼着三根肋骨,有声音对它说,‘起来,多吞吃肉吧!’

6“此后,我继续观看,见还有一只兽像豹,背上有四个如鸟翼般的翅膀。这兽有四个头,并被赋予权柄。 7此后,我在夜间的异象中看见第四只兽,恐怖可怕,极其强壮,用大铁牙吞吃、咬碎猎物,用脚践踏所剩的。这兽与前三只兽不同,它有十个角。 8我观看这些角时,见其中长出一个小角,先前的角中有三个被连根拔出,让它取而代之。这小角有人的眼睛和说狂言的口。

9“我看见宝座已设立,

上面坐着亘古长存者,

祂的衣服洁白如雪,

头发如纯净的羊毛。

祂的宝座是火焰,

宝座的轮子是烈火。

10从祂面前流出火河,

事奉祂的有千千,

侍立在祂面前的有万万。

祂坐下要审判,

案卷已经展开。

11“我继续观看,见那兽被杀,身体被毁并被扔进火中,因为它的小角口出狂言。 12至于其余的兽,它们的权柄都被夺去,但获准再存活一段时间。

13“我在夜间的异象中看见一位像人子的,驾着天云而来,到亘古长存者那里,被引到祂面前。 14他得到权柄、荣耀和国度,各族、各邦、各语种的人都要事奉他。他的统治直到永远、没有穷尽,他的国度永不灭亡。

解释异象

15“我但以理心中不安,脑中出现的异象令我恐惧, 16便走近一位侍立一旁的,问他这些事的意思。他就向我解释这些事的意思,说, 17‘这四只巨兽是指四个将要在世上兴起的国。 18但至高者的圣民必承受国度,并永永远远拥有国度。’

19“那时,我想知道关于第四兽的事,它与其余三兽不同,极其可怕,有铁牙铜爪,吞吃、咬碎猎物,用脚践踏所剩的。 20我也想知道有关它头上的十角及后来长出的小角的事。这小角取代了三角,它有眼和说狂言的口,比其他的角更强大。 21我看见这小角与圣民争战,并占了上风。 22后来亘古长存的至高者来为祂的圣民申冤。圣民拥有国度的时候到了。

23“那位侍立一旁的说,‘第四只兽是指世上将兴起的第四个国,与其他各国不同,它将吞吃、践踏、咬碎天下。 24十角是指这国中将兴起十个王,后来又兴起一王,与先前的王不同,他将制服三个王。 25他必亵渎至高者,迫害至高者的圣民,试图改变节期和律法。圣民将被交在他手中三年半。 26然而,审判者将坐下来审判,夺去并永远废除他的权柄。 27那时,国度、权柄和天下万国的尊荣必赐给至高者的圣民。祂的国度直到永远,一切掌权者都要事奉祂,顺服祂。’

28“这就是我的梦。我但以理心中十分害怕,脸色苍白,但我没有把这事告诉别人。”