ዘፍጥረት 36 – NASV & CCBT

New Amharic Standard Version

ዘፍጥረት 36:1-43

የዔሳው ዝርያዎች

36፥10-14 ተጓ ምብ – 1ዜና 1፥35-37

36፥20-28 ተጓ ምብ – 1ዜና 1፥38-42

1ኤዶም የተባለው የዔሳው ትውልድ ይህ ነው፦

2ዔሳው ከከነዓን ሴቶች አገባ፤ እነርሱም፦ የኬጢያዊው የዔሎን ልጅ ዓዳን፣ የኤዊያዊው የፅብዖን ልጅ ዓና የወለዳት አህሊባማ፣ 3እንዲሁም የነባዮት እኅት የሆነችው የእስማኤል ልጅ ቤሴሞት ነበሩ።

4ዓዳ ለዔሳው ኤልፋዝን ወለደችለት፤ ቤሴሞት ደግሞ ራጉኤልን ወለደችለት። 5እንደዚሁም አህሊባማ የዑስን፣ የዕላምንና ቆሬን ወለደችለት፤ እነዚህ ዔሳው በከነዓን አገር የወለዳቸው ልጆች ናቸው።

6ዔሳው ሚስቶቹን፣ ወንዶችና ሴቶች ልጆቹን፣ ቤተ ሰቦቹን በሙሉ እንደዚሁም የቀንድ ከብቶቹንና ሌሎቹንም እንስሳት ሁሉ በከነዓን ምድር ያፈራውን ሀብት እንዳለ ይዞ ከወንድሙ ከያዕቆብ ራቅ ወዳለ ቦታ ሄደ። 7ብዙ ሀብት ስለ ነበራቸው አብረው መኖር አልቻሉም፤ የነበሩበትም ስፍራ ከከብቶቻቸው ብዛት የተነሣ ሊበቃቸው አልቻለም። 8ስለዚህ ኤዶም የተባለው ዔሳው መኖሪያውን በተራራማው አገር በሴይር አደረገ።

9በሴይር ተራራማ አገር የሚኖሩ የኤዶማውያን አባት፣ የዔሳው ዝርያዎች እነዚህ ናቸው፤

10የዔሳው ልጆች ስም፦

የዔሳው ሚስት የዓዳ ልጅ ኤልፋዝና የዔሳው ሚስት የቤሴሞት ልጅ ራጉኤል፤

11የኤልፋዝ ልጆች፦

ቴማን፣ ኦማር፣ ስፎ፣ ጎቶምና ቄኔዝ፤ 12የዔሳው ልጅ ኤልፋዝ ትምናዕ የምትባል ቁባት ነበረችው፤ እርሷም አማሌቅን ወለደችለት፤ የዔሳው ሚስት የዓዳ የልጅ ልጆች እነዚህ ናቸው።

13የራጉኤል ልጆች፦

ናሖት፣ ዛራ፣ ሣማና ሚዛህ፤ እነዚህ ደግሞ የዔሳው ሚስት የቤሴሞት የልጅ ልጆች ናቸው።

14የፅብዖን የልጅ ልጅ፣ የዓና ልጅ የዔሳው ሚስት አህሊባማ ለዔሳው የወለደቻቸው ልጆች፦

የዑስ፣ የዕላማና ቆሬ።

15ከዔሳው ዝርያዎች እነዚህ የነገድ አለቆች ነበሩ፤

የዔሳው የበኵር ልጅ የኤልፋዝ ልጆች፦

አለቃ ቴማን፣ አለቃ ኦማር፣ አለቃ ስፎ፣ አለቃ ቄኔዝ፣ 16አለቃ ቆሬ፣36፥16 ከማሶሬቲኩ ጽሑፍ ጋር ተመሳሳይ ሲሆን በኦሪተ ሳምራውያን ግን (በተጨማሪ ዘፍ 36፥11 እና 1ዜና 1፥36 ይመ) ውስጥ “ቆሬ” የሚለው ቃል የለም። አለቃ ጎቶምና አለቃ አማሌቅ፤ እነዚህ በኤዶም ምድር ከኤልፋዝ የተገኙ የነገድ አለቆች፣ የዓዳ የልጅ ልጆች ነበሩ።

17የዔሳው ልጅ ራጉኤል ልጆች፦

አለቃ ናሖት፣ አለቃ ዛራ፣ አለቃ ሣማና አለቃ ሚዛህ፤ እነዚህ በኤዶም ምድር ከራጉኤል የተገኙ የነገድ አለቆች፣ የዔሳው ሚስት የቤሴሞት የልጅ ልጅ ነበሩ።

18የዔሳው ሚስት የአህሊባም ልጆች፦

አለቃ የዑስ፣ አለቃ የዕላማና፣ አለቃ ቆሬ፤ እነዚህ ከዓና ልጅ፣ ከዔሳው ሚስት ከአህሊባማ የተገኙ የነገድ አለቆች ነበሩ።

19እነዚህም ኤዶም የተባለው የዔሳው ልጆችና የነገድ አለቆቻቸው ነበሩ።

20በዚያች ምድር ይኖሩ የነበሩ የሖሪው የሴይር ልጆች እነዚህ ነበሩ፦

ሎጣን፣ ሦባል፣ ፅብዖን፣ ዓና፣ 21ዲሶን፣ ኤጽርና ዲሳን፤ እነዚህ በኤዶም የነበረው የሴይር ልጆች፣ የሖሪውያን የነገድ አለቆች ነበሩ።

22የሎጣን ልጆች፦

ሖሪና ሔማም36፥22 ሔማም የሚለው የዕብራይስጥ ቃል ሖማም ለሚለው ቃል አማራጭ ትርጕም ነው (1ዜና 1፥39 ይመ)።፤ የሎጣንም እኅት ቲምናዕ ትባል ነበር።

23የሦባል ልጆች፦

ዓልዋን፣ ማኔሐት፣ ዔባል፣ ስፎና አውናም፤

24የፅብዖን ልጆች፦

አያና ዓና፤ ይህ ዓና የአባቱን የፅብዖንን አህዮች ሲጠብቅ፣ የፍል ውሃ ምንጮችን36፥24 ከቩልጌት ጋር ተመሳሳይ ሲሆን ሱርስቱ ግን የተገኘ ውሃ ይለዋል፤ በዕብራይስጥ የዚህ ቃል ትርጕም አይታወቅም። በምድረ በዳ ያገኘ ሰው ነው።

25የዓና ልጆች፦

ዲሶንና የዓና ሴት ልጅ አህሊባማ፤

26የዲሶን36፥26 በዕብራይስጥ ዲሳን፣ የዲሶን አማራጭ ትርጕም ነው። ልጆች፦

ሔምዳን፣ ኤስባን፣ ይትራንና ክራን፤

27የኤጽር ልጆች፦

ቢልሐን፣ ዛዕዋንና ዓቃን፤

28የዲሳን ልጆች፦

ዑፅና አራን።

29የሖሪውያን የነገድ አለቆች እነዚህ ነበሩ፦

ሎጣን፣ ሦባል፣ ፅብዖን፣ ዓና፣ 30ዲሶን፣ ኤጽርና ዲሳን፤ እነዚህ በሴይር ምድር እንደየነገዳቸው የሖሪውያን የነገድ አለቆች ነበሩ።

የኤዶም ነገሥታት

36፥31-43 ተጓ ምብ – 1ዜና 1፥43-54

31ንጉሥ በእስራኤል ከመንገሡ በፊት፣36፥31 ወይም እስራኤላዊ መንግሥት በእነርሱ ላይ ከመንገሡ በፊት በኤዶም የነገሡ ነገሥታት እነዚህ ነበሩ፦

32የቢዖር ልጅ ባላቅ በኤዶም ነበር፤ የከተማውም ስም ዲንሃባ ይባል ነበር።

33ባላቅ ሲሞት፣ የባሶራው የዛራ ልጅ ኢዮባብ በምትኩ ነገሠ።

34ኢዮባብ ሲሞት፣ የቴማኒው ሑሳም በምትኩ ነገሠ።

35ሑሳም ሲሞት፣ የምድያምን ሰዎች በሞዓብ ምድር ድል ያደረጋቸው የባዳድ ልጅ ሃዳድ በምትኩ ነገሠ፤ የከተማውም ስም ዓዊት ይባል ነበር።

36ሃዳድ ሲሞት፣ የመሥሬቃው ሠምላ በምትኩ ነገሠ።

37ሠምላ ሲሞት፣ በወንዙ36፥37 የኤፍራጥስ ወንዝ ሊሆን ይችላል። አጠገብ ያለው የርሆቦቱ ሳኦል በምትኩ ነገሠ።

38ሳኦል ሲሞት፣ የዓክቦር ልጅ በኣልሐናን በምትኩ ነገሠ።

39የዓክቦር ልጅ በኣልሐናን ሲሞት፣ ሃዳር በምትኩ ነገሠ፤ የከተማውም ስም ፋዑ ይባል ነበር፤ የሚስቱም ስም መሄጣብኤል ሲሆን፣ እርሷም የሜዛሃብ ልጅ መጥሬድ የወለደቻት ነበረች።

40ከዔሳው የተገኙት የነገድ አለቆች ስም፣ እንደየነገዳቸውና እንደየአገራቸው ይህ ነው፦

ቲምናዕ፣ ዓልዋ፣ የቴት፣

41አህሊባማ፣ ኤላ፣ ፊኖን፣

42ቄኔዝ፣ ቴማን፣ ሚብሳር፣

43መግዲኤልና ዒራም።

እነዚህ፣ በያዙት ምድር እንደየይዞታቸው ከኤዶም የተገኙ የነገድ አለቆች ነበሩ።

ይህም ዔሳው፣ የኤዶማውያን አባት ነው።

Chinese Contemporary Bible (Traditional)

創世記 36:1-43

以掃的後代

1以下是以掃的後代,即以東的後代。

2以掃娶了迦南女子為妻,她們是以倫的女兒亞大希未祭便的孫女、亞拿的女兒阿何利巴瑪3他還娶了以實瑪利的女兒、尼拜約的妹妹巴實抹4亞大以掃生了以利法巴實抹生了流珥5阿何利巴瑪生了耶烏施雅蘭可拉。他們都是以掃的兒子,是在迦南出生的。

6以掃帶著他在迦南所得的妻子、兒女和家中所有的人員,以及所有的牲畜和財產離開雅各,遷往別處。 7以掃雅各兩家的財產和牲畜太多,那地方不夠他們住, 8於是以掃,即以東,搬到了西珥山居住。

9以掃西珥山區以東人的祖先,以下是他的子孫。

10以掃的妻子亞大生了以利法巴實抹生了流珥11以利法的兒子是提幔阿抹洗玻迦坦基納斯12以利法的妾亭納為他生了亞瑪力,他們都是以掃妻子亞大的子孫。 13流珥的兒子是拿哈謝拉沙瑪米撒,他們都是以掃妻子巴實抹的子孫。 14以掃的妻子阿何利巴瑪祭便的孫女、亞拿的女兒,她給以掃生了耶烏施雅蘭可拉

15以下是以掃子孫中的族長。

以掃的長子以利法的子孫中有提幔族長、阿抹族長、洗玻族長、基納斯族長、 16可拉族長、迦坦族長、亞瑪力族長,他們都是以利法以東的後代,即亞大的子孫。 17以掃的兒子流珥的子孫中有拿哈族長、謝拉族長、沙瑪族長、米撒族長,他們都是流珥以東的後代,即以掃的妻子巴實抹的子孫。 18以掃的妻子阿何利巴瑪的子孫中有耶烏施族長、雅蘭族長和可拉族長。這些都是以掃的妻子、亞拿的女兒阿何利巴瑪子孫中的族長。

19這些族長都是以掃的子孫,以掃又名以東

20以下是住在以東境內何利西珥的子孫:羅坍朔巴祭便亞拿21底順以察底珊。他們都是以東境內何利西珥的子孫中的族長。

22羅坍的兒子是何利希幔羅坍的妹妹是亭納23朔巴的兒子是亞勒文瑪拿轄以巴錄示玻阿南24祭便的兒子是亞雅亞拿,在曠野為父親放驢時發現溫泉的就是亞拿25亞拿的兒子名叫底順、女兒名叫阿何利巴瑪26底順的兒子是欣但伊是班益蘭基蘭27以察的兒子是辟罕撒番亞干28底珊的兒子是烏斯亞蘭

29以下是何利人的族長:羅坍族長、朔巴族長、祭便族長、亞拿族長、 30底順族長、以察族長、底珊族長。他們是西珥地區何利人各宗族的族長。

31以色列人還沒有君王統治之前,在以東做王的人如下: 32比珥的兒子比拉以東做王,定都亭哈巴33比拉死後,波斯拉謝拉的兒子約巴繼位。 34約巴死後,提幔地區的戶珊繼位。 35戶珊死後,比達之子哈達繼位,定都亞未得,他曾在摩押地區擊敗米甸人。 36哈達死後,瑪士利加桑拉繼位。 37桑拉死後,大河邊的利河伯掃羅繼位。 38掃羅死後,亞革波的兒子巴勒·哈南繼位。 39巴勒·哈南死後,哈達繼位,定都巴烏,他的妻子名叫米希她別,是米·薩合的孫女、瑪特列的女兒。

40以下是按宗族在各地區做族長的以掃的後代:亭納亞勒瓦耶帖41阿何利巴瑪以拉比嫩42基納斯提幔米比薩43瑪基疊以蘭。這些人在所住的以東各地做族長。以掃以東人的始祖。