ዘፍጥረት 35 – NASV & CCBT

New Amharic Standard Version

ዘፍጥረት 35:1-29

ያዕቆብ ወደ ቤቴል ተመለሰ

1እግዚአብሔር (ኤሎሂም) ያዕቆብን፣ “ተነሥና ወደ ቤቴል ውጣ፤ እዚያም ተቀመጥ፤ ከወንድምህ ከዔሳው ሸሽተህ በሄድህ ጊዜ ለተገለጠልህ አምላክ (ኤል) በዚያ መሠዊያ ሥራ” አለው።

2ስለዚህም ያዕቆብ ለቤቱ ሰዎችና አብረውት ለነበሩት ሁሉ እንዲህ አላቸው፤ “በእናንተ ዘንድ ያሉትን ባዕዳን አማልክት አስወግዱ፤ ሰውነታችሁን አንጹ፤ ልብሳችሁንም ለውጡ። 3ተነሥተን ወደ ቤቴል እንውጣ፤ እዚያም በመከራዬ ጊዜ ለሰማኝ፣ በሄድሁበትም ስፍራ ሁሉ ላልተለየኝ አምላክ (ኤል) መሠዊያ እሠራለሁ።” 4ስለዚህ በእነርሱ ዘንድ የነበሩትን ባዕዳን አማልክት ሰብስበው፣ የጆሮ ጕትቾቻቸውን አውልቀው ለያዕቆብ ሰጡት። ያዕቆብም ወስዶ ሴኬም አጠገብ ካለው ወርካ ዛፍ ሥር ቀበራቸው። 5ያንንም ቦታ ለቅቀው ሄዱ፤ እግዚአብሔርም (ኤሎሂም) በዙሪያቸው በነበሩት ከተሞች ሁሉ ላይ ፍርሀትና ድንጋጤ ስለ ለቀቀባቸው ያሳደዳቸው አልነበረም።

6ያዕቆብና አብረውት የነበሩት ሰዎች ሁሉ፣ በከነዓን ወደምትገኘው፣ ቤቴል ወደተባለችው ወደ ሎዛ ደረሱ። 7ያዕቆብም በዚያ ስፍራ መሠዊያ ሠርቶ፣ ስሙን ኤል-ቤቴል35፥7 ኤል-ቤቴል ማለት የቤቴል አምላክ ማለት ነው። አለው፤ ምክንያቱም ከወንድሙ ሸሽቶ በሄደ ጊዜ እግዚአብሔር (ኤሎሂም) የተገለጠለት በዚህ ቦታ ነበር።

8በዚህ ጊዜ የርብቃ ሞግዚት ዲቦራ ሞተች፤ ከቤቴል ዝቅ ብሎ በሚገኘው ወርካ ዛፍ ሥር ተቀበረች። ከዚህ የተነሣም ያ ቦታ አሎንባኩት35፥8 አሎንባኩት ማለት የለቅሶ ወርካ ማለት ነው። ተባለ።

9ያዕቆብ ከሰሜን ምዕራብ መስጴጦምያ ከተመለሰ በኋላ፣ እግዚአብሔር (ኤሎሂም) ለያዕቆብ ዳግመኛ ተገለጠለት፤ ባረከውም። 10እግዚአብሔርም (ኤሎሂም)፣ “እስካሁን ስምህ ያዕቆብ35፥10 ያዕቆብ ማለት ተረከዝ ይይዛል ማለት ነው፤ በምሳሌያዊ አገላለጽ ያታልላል ማለት ነው። ነበረ፤ ከእንግዲህ ያዕቆብ ተብለህ አትጠራም፤ ነገር ግን ስምህ እስራኤል35፥10 እስራኤል ማለት ከእግዚአብሔር ጋር ታገለ ማለት ነው። ይባላል” አለው።

ስለዚህም እስራኤል ብሎ ጠራው።

11ደግሞም እግዚአብሔር (ኤሎሂም) ያዕቆብን እንዲህ አለው፤ “እኔ ሁሉን ማድረግ የሚችል35፥11 በዕብራይስጥ ኤልሻዳይ ማለት ነው። አምላክ ነኝ፤ ብዛ ተባዛ፤ ሕዝብና የሕዝቦች ማኅበር ከአንተ ይወጣሉ፤ ነገሥታትም ከአብራክህ ይከፈላሉ። 12ለአብርሃምና ለይስሐቅ የሰጠኋትን ምድር ለአንተ እሰጥሃለሁ፤ ከአንተም በኋላ ይህችኑ ምድር ለዘርህ እሰጣለሁ።” 13እግዚአብሔርም (ኤሎሂም) ከእርሱ ጋር ከተነጋገረበት ስፍራ ወደ ላይ ወጣ።

14ያዕቆብ እግዚአብሔር (ኤሎሂም) ከእርሱ ጋር በተነጋገረበት ስፍራ የድንጋይ ሐውልት አቆመ፤ በሐውልቱ ላይ የመጠጥ ቍርባን አፈሰሰ፤ ዘይትም አፈሰሰበት። 15ያዕቆብም፣ እግዚአብሔር (ኤሎሂም) ከእርሱ ጋር የተነጋገረበትን ስፍራ ቤቴል35፥15 ቤቴል ማለት የእግዚአብሔር ቤት ማለት ነው። ብሎ ጠራው።

የራሔልና የይስሐቅ መሞት

35፥23-26 ተጓ ምብ – 1ዜና 2፥1-2

16ከዚያም ከቤቴል ተነሥተው ሄዱ፤ ኤፍራታ ለመድረስ ጥቂት ሲቀራቸው ራሔልን ምጥ ያዛት፤ ምጡም ጠናባት። 17ምጡ አስጨንቋት ሳለ፣ አዋላጇ፣ “አይዞሽ አትፍሪ፤ ሌላ ወንድ ልጅ ልትገላገይ ነው” አለቻት። 18እርሷ ግን ሕይወቷ ልታልፍ በማጣጣር ላይ ሳለች፣ ልጇን ቤንኦኒ35፥18 ቤንኦኒ ማለት የመከራዬ ልጅ ማለት ነው። አለችው፤ አባቱ ግን ብንያም35፥18 ብንያም ማለት የቀኜ ልጅ ማለት ነው። አለው።

19ራሔልም ሞተች፤ ወደ ኤፍራታ በሚወስደው መንገድ በቤተ ልሔም ተቀበረች። 20ያዕቆብም በራሔል መቃብር ላይ ሐውልት አቆመ፤ እስከ ዛሬም የራሔል መቃብር ምልክት ይኸው ሐውልት ነው።

21እስራኤልም ጕዞውን በመቀጠል ከጋዴር ወንዝ ባሻገር ድንኳኑን ተከለ። 22እስራኤልም በዚያ ምድር ሳለ፣ ሮቤል ከአባቱ ቁባት ከባላ ጋር ተኛ፤ እስራኤልም ድርጊቱን ሰማ።

ያዕቆብ ዐሥራ ሁለት ልጆች ነበሩት፤ እነርሱም፦

23የልያ ልጆች፦

የያዕቆብ የበኵር ልጅ ሮቤል፣

ስምዖን፣ ሌዊ፣ ይሁዳ፣ ይሳኮር፣ ዛብሎን፤

24የራሔል ልጆች፦

ዮሴፍ፣ ብንያም፤

25የራሔል አገልጋይ የባላ ልጆች፦

ዳን፣ ንፍታሌም፤

26የልያ አገልጋይ የዘለፋ ልጆች፦

ጋድ፣ አሴር ናቸው።

እነዚህ ያዕቆብ በሰሜን ምዕራብ መስጴጦምያ ሳለ የተወለዱለት ወንዶች ልጆች ነበሩ።

27ያዕቆብ አባቱ ወዳለበት ወደ መምሬ መጣ፤ አብርሃምና ይስሐቅ የኖሩባት፣ ቂርያትአርባቅ ወይም ኬብሮን የተባለችው ቦታ ናት። 28ይስሐቅ መቶ ሰማንያ ዓመት ኖረ፤ 29አርጅቶ፣ ዕድሜ ጠግቦ ሞተ፤ ወደ ወገኖቹ ተሰበሰበ፤ ልጆቹም ዔሳውና ያዕቆብ ቀበሩት።

Chinese Contemporary Bible (Traditional)

創世記 35:1-29

雅各遷往伯特利

1上帝對雅各說:「你到伯特利去住,你要在那裡為上帝築一座壇,祂在你逃避你哥哥以掃時曾向你顯現。」 2於是,雅各吩咐家人和所有的隨從:「你們要除掉你們當中的外族神像,沐浴更衣,潔淨自己。 3我們要上伯特利去,在那裡為上帝築一座壇,祂在我遭遇患難時聽了我的禱告,一路都與我同在。」 4他們把所有外族的神像和自己的耳環都交給雅各雅各把這些東西埋在示劍的橡樹下。

5他們就出發了,上帝使恐懼籠罩周圍的城邑,沒有人敢追趕他們。 6雅各和所有的隨從來到迦南路斯,也就是伯特利7他在那裡建造了一座壇,稱那地方為伊勒·伯特利35·7 伊勒·伯特利」意思是「伯特利的上帝」。,因為在他逃避哥哥的時候,上帝曾在那裡向他顯現。 8後來利百加的奶媽底波拉死了,葬在伯特利山谷下面的橡樹下,那棵樹叫亞倫·巴古35·8 亞倫·巴古」意思是「哭泣的橡樹」。

9雅各巴旦·亞蘭回來後,上帝又向他顯現,賜福給他。 10上帝對他說:「你叫雅各,但從今以後不要再叫雅各了,你要改名叫以色列。」這樣雅各改名為以色列11上帝又說:「我是全能的上帝,你要生養眾多,一國,甚至多國必從你而出,許多君王必出自你的子孫。 12我要把賜給亞伯拉罕以撒的土地賜給你和你的後代。」 13上帝說完就離開雅各升上天去。 14雅各在上帝跟他說話的地方立了一根石柱,又在柱子上奠酒、澆油, 15稱那地方為伯特利

拉結和以撒去世

16他們從伯特利繼續前行,離以法他還有一段路時,拉結難產。 17在難產的痛苦中,接生婆對她說:「不要害怕,你又添了一個兒子!」 18拉結臨死前給兒子取名叫便·俄尼35·18 便·俄尼」意思是「我在苦難中生的兒子」。雅各卻叫他便雅憫35·18 便雅憫」意思是「右手之子」,「右手」希伯來文有幸運或力量的意思。19拉結死後就葬在通往以法他的路旁,以法他伯利恆20雅各在她的墳上立了石碑,至今還在。 21以色列繼續前行,在以得塔附近搭起了帳篷。 22以色列在那裡居住時,呂便和父親的妾辟拉通姦,以色列也知道這件事。

雅各有十二個兒子。 23利亞生了雅各的長子呂便西緬利未猶大以薩迦西布倫24拉結生了約瑟便雅憫25拉結的婢女辟拉生了拿弗他利26利亞的婢女悉帕生了迦得亞設。他們都是雅各的兒子,是在巴旦·亞蘭出生的。

27雅各來到他父親以撒住的幔利,即基列·亞巴,也就是亞伯拉罕以撒寄居的地方。基列·亞巴就是希伯崙28以撒共活了一百八十歲, 29年紀老邁,壽終正寢。他的兒子以掃雅各把他安葬了。