ዘፀአት 32 – NASV & CCBT

New Amharic Standard Version

ዘፀአት 32:1-35

የወርቅ ጥጃ

1ሕዝቡ ሙሴ ከተራራው ላይ ሳይ ወርድ ብዙ እንደ ቈየ ባዩ ጊዜ፣ ወደ አሮን ተሰብስበው፣ “ናና በፊታችን የሚሄዱ አማልክት32፥1 በዚህ እንዲሁም በቍጥር 23 እና 31 ላይ አምላክ ሥራልን፤ ያ ከግብፅ ያወጣን ሙሴ ምን እንዳገኘው አናውቅም” አሉት።

2አሮንም፣ “የሚስቶቻችሁን፣ የወንድና የሴት ልጆቻችሁን የጆሮ ወርቅ አውልቃችሁ ወደ እኔ አምጡ” ብሎ መለሰላቸው። 3ሕዝቡም ሁሉ የጆሮ ወርቃቸውን አውልቀው ወደ አሮን አመጡ። 4እርሱም የሰጡትን ወስዶ በመሣሪያ በመቅረጽ በጥጃ ምስል ጣዖት አድርጎ ሠራው፤ ከዚያም እነርሱ፣ “እስራኤል ሆይ፤ ከግብፅ ያወጡህ አማልክት32፥4 በዚህና በቍጥር 8 ላይ፣ ይህ አምላካችሁ ነው። እነዚህ ናቸው” አሉ።

5አሮን ይህን ባየ ጊዜ በወርቅ ጥጃው ፊት ለፊት መሠዊያ ሠርቶ፣ “ነገ ለእግዚአብሔር (ያህዌ) በዓል ይሆናል” ብሎ ዐወጀ። 6በማግስቱም ሕዝቡ በማለዳ ተነሥተው የሚቃጠል መሥዋዕት ሠዉ፤ የኅብረት መሥዋዕት32፥6 በትውፊት፣ የሰላም መሥዋዕት በመባል ይታወቃል። አቀረቡ፤ ከዚህም በኋላ ይበሉና ይጠጡ ዘንድ ተቀመጡ፤ ሊዘፍኑም ተነሡ።

7ከዚያም እግዚአብሔር (ያህዌ) ሙሴን፣ “ከግብፅ ያወጣሃቸው ሕዝብህ ስተዋልና ውረድ” አለው። 8“ካዘዝኋቸው ፈቀቅ ለማለት ፈጣኖች ሆኑ፤ ለራሳቸውም በጥጃ ምስል የተቀረጸ ጣዖትን ሠሩ፤ ለእርሱም ሰገዱለት፤ ሠዉለትም፤ እንዲሁም፣ ‘እስራኤል ሆይ፤ ከግብፅ ምድር ያወጡህ አማልክትህ እነዚህ ናቸው’ ” አሉ።

9እግዚአብሔርም (ያህዌ) ሙሴን እንዲህ አለው፤ “እነዚህን ሕዝብ አይቻቸዋለሁ፤ ዐንገተ ደንዳናዎችም ናቸው። 10አሁንም በእነርሱ ላይ፣ ቍጣዬ እንዲነድድና እንዳጠፋቸው ተወኝ፤ ከዚያም አንተን ለታላቅ ሕዝብ አደርግሃለሁ።”

11ነገር ግን ሙሴ የአምላኩን የእግዚአብሔርን (ኤሎሂም ያህዌ) ቸርነት ፈለገ፤ እንዲህም አለ፤ “እግዚአብሔር (ያህዌ) ሆይ በታላቅ ሥልጣንህና በኀያል ክንድህ ከግብፅ ባወጣኸው ሕዝብህ ላይ ቍጣህ ለምን ይነድዳል? 12ግብፃውያን፣ ‘በተራራዎቹ ላይ ሊገድላቸው፣ ከገጸ ምድርም ሊያጠፋቸው ስለ ፈለገ ነው ያወጣቸው’ ለምን ይበሉ? ከክፉ ቍጣህ ተመለስ፤ ታገሥ፤ በሕዝብህም ላይ ጥፋት አታምጣ። 13ለባሪያዎችህ ለአብርሃም፣ ለይስሐቅና ለእስራኤል፣ ‘ዘርህን እንደ ሰማይ ከዋክብት አበዛዋለሁ፤ ለዘርህም ተስፋ አድርጌ የሰጠኋቸውን ይህችን ምድር ሁሉ እሰጣቸዋለሁ፤ ለዘላለምም ርስታቸው ትሆናለች’ በማለት በራስህ የማልኸውን አስታውስ።” 14ከዚያም እግዚአብሔር (ያህዌ) ታገሠ፤ በሕዝቡም ላይ አመጣባቸዋለሁ ያለውን ጥፋት አላመጣባቸውም።

15ሙሴም ሁለቱን የምስክር ጽላቶች በእጆቹ ይዞ ከተራራው ወረደ፤ ጽላቶቹም ከፊትና ከኋላ በሁለቱም ጐኖች ተጽፎባቸው ነበር። 16ጽላቶቹ የእግዚአብሔር (ኤሎሂም) ሥራ ነበሩ፤ በጽላቶቹ ላይ የተቀረጸ ጽሕፈትም የእግዚአብሔር (ያህዌ) ጽሕፈት ነበር።

17ኢያሱ የሕዝቡን የጩኸት ድምፅ በሰማ ጊዜ ሙሴን፣ “በሰፈሩ ውስጥ የጦርነት ድምፅ አለ አለው።”

18ሙሴም፣

“የድል ድምፅ አይደለም፤

የሽንፈትም ድምፅ አይደለም፤

የምሰማው የዘፈን ድምፅ ነው”

ብሎ መለሰለት።

19ሙሴ ወደ ሰፈሩ ደርሶ ጥጃውንና ጭፈራውን ባየ ጊዜ ቍጣው ነደደ፤ ጽላቶቹን ከእጁ በመወርወር ከተራራው ግርጌ ሰባበራቸው። 20የሠሩትን ጥጃ ወስዶ በእሳት አቃጠለው፤ ከዚያም ዱቄት እስኪሆን ፈጨው፤ በውሃ ላይ በተነው፤ እስራኤላውያንም እንዲጠጡት አደረገ።

21አሮንንም፣ “ወደዚህ አስከፊ ኀጢአት ትመራቸው ዘንድ እነዚህ ሕዝብ ምን አደረጉህ?” አለው።

22አሮንም መልሶ፣ “ጌታዬ ሆይ፤ አትቈጣ” ብሎ መለሰለት፤ “ይህ ሕዝብ ሁልጊዜ ለክፋት ያዘነበለ መሆኑን አንተ ታውቃለህ። 23እነርሱም ‘በፊታችን የሚሄዱ አማልክት ሥራልን፤ ይህ ከግብፅ ያወጣን ሙሴ ምን እንዳገኘው አናውቅም’ አሉኝ። 24ስለዚህ፣ ‘ማንኛውም ዐይነት የወርቅ ጌጣጌጥ ያለው ሁሉ ያውልቀው’ አልኋቸው፤ ከዚያም ወርቁን ሰጡኝ፤ ወደ እሳቱ ጣልሁት፤ ይህም ጥጃ ወጣ።”

25ሕዝቡ ከቍጥጥር ውጭ እንደ ሆኑ፣ አሮንም መረን እንደ ለቀቃቸውና በጠላቶቻቸውም ዘንድ መሣለቂያ እንደ ሆኑ ሙሴ አስተዋለ። 26ስለዚህ በሰፈሩ መግቢያ ላይ ቆሞ፣ “የእግዚአብሔር (ያህዌ) የሆነ ሁሉ ወደ እኔ ይምጣ” አለ፤ ሌዋውያኑም ሁሉ ከእርሱ ጋር ሆኑ።

27ከዚያም፣ “የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር (ያህዌ) የሚለው ይህ ነው፤ ‘እያንዳንዱ ሰው በወገቡ ላይ ሰይፍ ይታጠቅ፤ በሰፈር ውስጥ ከዳር እዳር እየተመላለሰ እያንዳንዱ ወንድሙን፣ ጓደኛውንና ጎረቤቱን ይግደል’ ” አላቸው። 28ሌዋውያኑ ሙሴ እንዳዘዛቸው ፈጸሙ፤ በዚያኑም ዕለት ከሕዝቡ ሦስት ሺሕ ያህል ዐለቁ። 29ከዚያም ሙሴ፣ “በራሳችሁ ወንዶች ልጆችና ወንድሞች ላይ በመነሣታችሁ፣ በዛሬዋ ቀን ለእግዚአብሔር (ያህዌ) የተለያችሁ ሆናችኋል፤ በዛሬዋም ዕለት ባርኳችኋል” አለ።

30በማግስቱም ሙሴ ሕዝቡን፣ “እጅግ የከፋ ኀጢአት ሠርታችኋል፤ አሁን ግን ወደ እግዚአብሔር (ያህዌ) እወጣለሁ፤ ምናልባት ኀጢአታችሁን ማስተስረይ እችል ይሆናል” አላቸው።

31ስለዚህ ሙሴ ወደ እግዚአብሔር (ያህዌ) ተመልሶ እንዲህ አለው፤ “ወዮ እነዚህ ሕዝብ የሠሩት ምን ዐይነት የከፋ ኀጢአት ነው! ለራሳቸውም የወርቅ አማልክት ሠሩ። 32አሁን ግን አቤቱ ኀጢአታቸውን ይቅር በል፤ ያለዚያ ግን ከጻፍኸው መጽሐፍ እኔን ደምስሰኝ።” 33እግዚአብሔር (ያህዌ) ለሙሴ እንዲህ ሲል መለሰለት፤ “የበደለኝን ሁሉ ከመጽሐፌ እደመስሰዋለሁ። 34አሁን ሂድ፤ ሕዝቡን ወደ ተናገርሁት ስፍራ ምራው፤ መልአኬም በፊትህ ይሄዳል፤ ሆኖም የምቀጣበት ጊዜ ሲደርስ፣ ስለ ኀጢአታቸው እቀጣቸዋለሁ።”

35አሮን በሠራው ጥጃ ባደረጉት ነገር እግዚአብሔር (ያህዌ) ሕዝቡን በመቅሠፍት መታ።

Chinese Contemporary Bible (Traditional)

出埃及記 32:1-35

金牛犢

1百姓見摩西遲遲沒有下山,就聚集到亞倫那裡,對他說:「領我們離開埃及的那個摩西不知怎樣了,你給我們造神像來帶領我們吧。」 2亞倫對他們說:「你們去摘下妻子、兒女的金耳環,拿來給我。」 3百姓就都摘下金耳環交給亞倫4亞倫用這些金耳環鑄造了一頭牛犢。他們說:「以色列人啊,這就是把你們帶出埃及的神明。」 5亞倫見狀,便在牛犢前面築了一座壇,然後宣告說:「明天是耶和華定的節期。」 6第二天清晨,百姓都上前來獻燔祭和平安祭,獻完祭後就坐下吃喝,起來狂歡。

7耶和華對摩西說:「你快下山吧,你的百姓,就是你從埃及領出來的那些人已經敗壞了。 8他們這麼快就偏離了我吩咐他們走的道路,為自己造了一頭牛犢來叩拜獻祭,說,『以色列人啊,這就是把你們帶出埃及的神明。』」 9耶和華又說:「我看到了,這些百姓真是頑固不化。 10你不要阻止我,我要向他們發烈怒,毀滅他們。我要使你的後代成為大國。」

11摩西懇求他的上帝耶和華說:「耶和華啊,你為什麼要向你的子民發烈怒呢?這些子民是你親自用神蹟和大能從埃及領出來的。 12難道你要讓埃及人議論說你領他們出來是出於惡意,是為了在山野之間殺掉他們,從地上滅絕他們嗎?求你息怒,施憐憫,不要降禍給你的子民。 13求你顧念你的僕人亞伯拉罕以撒以色列,你曾憑自己向他們起誓說,『我必使你們的後代像天上的星星那麼多。我應許給你們後代的這整片土地,我必賜給他們作永遠的產業。』」 14耶和華聽了摩西的話,就心生憐憫,不把所說的災禍降在百姓身上。

15摩西轉身下山,手裡拿著兩塊石版,石版的正反兩面都有字。 16石版是上帝做的,字是上帝刻的。 17約書亞聽見山下百姓嘈雜的喊叫聲,便對摩西說:「營地裡有打仗的聲音。」 18摩西對他說:「這不是打勝仗的聲音,也不是打敗仗的聲音,而是狂歡的聲音。」 19摩西走近營地的時候,看見牛犢,又看見百姓在跳舞,心中大怒,便把手上的兩塊石版摔碎在山腳下, 20又把他們鑄造的牛犢熔化掉,磨成粉末撒在水面上,叫以色列百姓喝。 21摩西亞倫說:「這些百姓對你做了什麼?你竟使他們陷入大罪中!」 22亞倫回答說:「求我主不要動怒,你知道這些人專門作惡。 23他們對我說,『為我們造神明來帶領我們吧,因為領我們離開埃及的那個摩西不知怎樣了。』 24於是,我吩咐他們摘下金耳環給我,我把這些金耳環丟進火裡,這頭牛犢就出來了。」

25摩西見百姓放肆,亞倫縱容他們,使他們成為敵人的笑柄, 26便站在營門口對會眾說:「凡跟從耶和華的,都站到我這邊來。」所有的利未人都聚集到摩西身邊。 27摩西對他們說:「以色列的上帝耶和華這樣說,『你們各人帶著刀,從這個門到那個門,走遍整個營,不論遇見的是兄弟、夥伴還是鄰居,只管殺他們。』」 28利未人便照摩西的話去做。那一天,約有三千人被殺。 29摩西利未人說:「今天你們已經把自己奉獻給耶和華了,因為你們大義滅親,祂必賜福給你們。」

30第二天,摩西對百姓說:「你們犯了大罪,我現在要到耶和華那裡,也許可以為你們求得赦免。」 31摩西回到耶和華那裡,說:「唉,百姓犯了大罪,用金子為自己造了神像。 32懇求你赦免他們的罪,不然請你從你的冊子上抹掉我的名字吧。」 33耶和華對摩西說:「誰得罪我,我就從我的冊子上抹掉誰的名字。 34你現在回去帶領這些百姓,往我指示你的地方去,我的天使必在你前面引路。只是到我懲罰的日子,我必因他們的罪懲罰他們。」

35耶和華擊殺百姓,是因為他們曾與亞倫一起造牛犢。