ዘፀአት 17 – NASV & CCBT

New Amharic Standard Version

ዘፀአት 17:1-16

ከዐለት የፈለቀ ውሃ

1መላው የእስራኤል ማኅበር ከሲና ምድረ በዳ ተነሥቶ እግዚአብሔር (ያህዌ) እንዳዘዘው ከስፍራ ወደ ስፍራ ተጕዞ በራፊዲም ሰፈረ፤ ነገር ግን ሕዝቡ የሚጠጡት ውሃ አልነበረም። 2ስለዚህ፣ “የምንጠጣውን ውሃ ስጠን” በማለት ሙሴን ተጣሉት።

ሙሴም፣ “እኔን ለምን ትጣሉኛላችሁ? እግዚአብሔርንስ (ያህዌ) ለምን ትፈታተኑታላችሁ?” አለ።

3ነገር ግን ሕዝቡ በዚያ ተጠምተው ስለ ነበር፣ በሙሴ ላይ አጕረመረሙ። እነርሱም፣ “እኛና ልጆቻችን እንዲሁም ከብቶቻችን በውሃ ጥም እንድናልቅ፣ ከግብፅ ለምን አወጣኸን?” አሉት።

4ከዚያም ሙሴ፤ “በዚህ ሕዝብ ምን ላድርግ? በድንጋይ ሊወግሩኝ ተዘጋጅተዋል” ብሎ ወደ እግዚአብሔር (ያህዌ) ጮኸ።

5እግዚአብሔር (ያህዌ) ለሙሴ እንዲህ መለሰለት፤ “ከሕዝቡ ፊት ሂድ፤ ከእስራኤል አለቆች አንዳንዶቹን እንዲሁም አባይን የመታህባትን በትር ያዝና ሂድ። 6ኮሬብ አጠገብ ባለው ዐለት በዚያ እኔ በአንተ ፊት እቆማለሁ። ዐለቱን ምታው፤ ከእርሱም ሕዝቡ የሚጠጡት ውሃ ይወጣል።” ስለዚህ ሙሴ በእስራኤል አለቆች ፊት ይህንኑ አደረገ። 7ስፍራውንም ማሳህና17፥7 ማሳህ ማለት መፈተን ማለት ነው። መሪባ17፥7 መሪባ ማለት መጣላት ማለት ነው። ብሎ ጠራው፤ እስራኤላውያን ጠብ ፈጥረው፣ “እግዚአብሔር (ያህዌ) ከእኛ ጋር ነው ወይስ አይደለም” በማለት እግዚአብሔርን (ያህዌ) ተፈታትነዋልና።

አማሌቃውያን ተሸነፉ

8አማሌቃውያን መጥተው እስራኤላውያንን ራፊዲም ላይ ወጉ፤ 9ሙሴም ኢያሱን፣ “ከሰዎቻችን አንዳንዶቹን ምረጥና አማሌቃውያንን ለመውጋት ውጣ፤ በነገው ዕለት የእግዚአብሔርን (ኤሎሂም) በትር በእጆቼ ይዤ በኰረብታው ጫፍ ላይ እቆማለሁ።”

10ስለዚህ ኢያሱ ሙሴ ባዘዘው መሠረት ከአማሌቃውያን ጋር ተዋጋ፤ ሙሴ፣ አሮንና ሖርም ወደ ኰረብታው ጫፍ ወጡ። 11ሙሴ እጆቹን ወደ ላይ በሚያነሣበት ጊዜ ሁሉ እስራኤላውያን ድል ያደርጉ ነበር። እጆቹን ባወረደ ጊዜ ግን አማሌቃውያን ያሸንፉ ነበር። 12የሙሴ እጆች እየዛሉ በሄዱ ጊዜ ድንጋይ ወስደው ከበታቹ አደረጉ፤ እርሱም ተቀመጠበት፤ አሮንና ሖርም አንዱ በአንዱ በኩል ሌላውም በሌላ በኩል ሆነው እጆቹን ወደ ላይ ያዙ። ይኸውም እጆቹ ፀሓይ እስክትጠልቅ ድረስ ጸንተው እንዲቈዩ ነው። 13ስለዚህ ኢያሱ የአማሌቃውያንን ሰራዊት በሰይፍ ድል አደረገ።

14ከዚያም እግዚአብሔር (ያህዌ) ሙሴን፣ “ሲታወስ እንዲኖር ይህን በጥቅልል መጽሐፍ ላይ ጻፈው፤ ኢያሱም መስማቱን አረጋግጥ፤ ምክንያቱም የአማሌቃውያንን ዝክር ከሰማይ በታች ፈጽሜ እደመስሳለሁ” አለው።

15ሙሴም መሠዊያውን ሠርቶ፣ “እግዚአብሔር (ያህዌ) አርማዬ ነው” ብሎ ሰየመው። 16“እጆች ወደ እግዚአብሔር (ያህዌ) ዙፋን ተዘርግተዋልና፤17፥16 ወይም፣ ምክንያቱም እጅ በእግዚአብሔር ዙፋን ላይ ተዘርግቷል… እግዚአብሔር (ያህ) አማሌቃውያንን ከትውልድ እስከ ትውልድ ይዋጋቸዋል” አለ።

Chinese Contemporary Bible (Traditional)

出埃及記 17:1-16

磐石出水

1以色列全體會眾按照耶和華的吩咐,從曠野啟程,一程一程往前行,來到利非訂安營,可是那裡沒有水喝。 2百姓便跟摩西吵鬧,要他給他們水喝。摩西便對他們說:「你們為什麼跟我吵鬧?為什麼試探耶和華?」 3百姓非常口渴,他們向摩西抱怨說:「你為什麼要把我們帶出埃及,讓我們一家大小和牲畜都在這裡渴死?」

4摩西就呼求耶和華說:「我拿這些百姓怎麼辦?他們準備拿石塊打死我!」 5耶和華對摩西說:「你帶著之前擊打尼羅河水的杖,率領以色列的幾個長老走在眾人前面。 6我必在何烈的磐石那裡等候你們,你用杖擊打磐石,磐石必流出水來給眾人喝。」摩西便當著以色列長老的面這樣做了。 7摩西稱那地方為瑪撒米利巴17·7 瑪撒」意思是「試探」;「米利巴」意思是「爭鬧」。,因為百姓在那裡吵鬧,又試探耶和華,說:「耶和華真的在我們當中嗎?」

戰勝亞瑪力人

8後來,亞瑪力人到利非訂攻打以色列人。 9摩西約書亞說:「選一些人出去迎戰亞瑪力人。明天,我會帶著上帝的杖站在山頂上。」 10約書亞便遵照摩西的吩咐迎戰亞瑪力人,摩西亞倫戶珥站在山頂上。 11摩西什麼時候舉手,以色列人就得勝;他的手什麼時候垂下來,亞瑪力人就佔上風。 12不久,摩西的手疲倦發軟,亞倫戶珥就抬來一塊石頭讓摩西坐下,然後站在他的兩邊扶著他的手,他就穩穩地舉著手,直到日落。 13這樣,約書亞用刀殺敗了亞瑪力人。

14耶和華對摩西說:「我要抹去世人對亞瑪力人的記憶。你要把這話記在書卷上作紀念,也要把這話告訴約書亞。」 15摩西在那裡築了一座壇,稱之為耶和華尼西17·15 耶和華尼西」意思是「耶和華是我的旌旗」。16摩西說:「耶和華已經起誓要世代與亞瑪力人為敵。」