ዘዳግም 4 – NASV & CCB

New Amharic Standard Version

ዘዳግም 4:1-49

ሙሴ እስራኤላውያን እንዲታዘዙ ማስጠንቀቁ

1አሁንም እስራኤል ሆይ፤ በሕይወት እንድትኖሩ፣ የአባቶቻችሁ አምላክ እግዚአብሔር (ኤሎሂም ያህዌ) ወደሚሰጣችሁ ምድር እንድትገቡና እንድትወርሱ የማስተምራችሁን ሥርዐትና ሕግ ስሙ፤ ጠብቋቸውም። 2ባዘዝኋችሁ ላይ አትጨምሩ፤ ከእርሱም አትቀንሱ፤ ነገር ግን የምሰጣችሁን የአምላካችሁን የእግዚአብሔርን (ኤሎሂም ያህዌ) ትእዛዞች ጠብቁ።

3እግዚአብሔር (ያህዌ) በብዔልፌጎር ላይ ምን እንዳደረገ በዐይናችሁ አይታችኋል፤ አምላካችሁ እግዚአብሔር (ኤሎሂም ያህዌ) ከመካከላችሁ ብዔልፌጎርን የተከተሉትን ሁሉ አጥፍቷቸዋል፤ 4አምላካችሁን እግዚአብሔርን (ኤሎሂም ያህዌ) የተከተላችሁት እናንተ ሁላችሁ ግን ይኸው እስከ ዛሬ በሕይወት አላችሁ።

5ገብታችሁ በምትወርሷት ምድር፣ እንድትፈጽሟቸው እግዚአብሔር አምላኬ (ያህዌ ኤሎሂም) ባዘዘኝ መሠረት ሥርዐትንና ሕግን አስተምሬአችኋለሁ። 6በጥንቃቄ ጠብቋቸው፤ ስለ እነዚህ ሥርዐቶች ሁሉ ለሚሰሙና፣ “በእውነቱ ይህ ታላቅ ሕዝብ የቱን ያህል ጥበበኛና አስተዋይ ነው” ለሚሉ ሕዝቦች ይህ ጥበባችሁንና ማስተዋላችሁን ይገልጣልና። 7በምንጠራው ጊዜ ሁሉ አምላካችን እግዚአብሔር (ኤሎሂም ያህዌ) ለእኛ ቅርብ እንደ ሆነ አማልክቱ የሚቀርቡት ሌላ ታላቅ ሕዝብ ማነው? 8ዛሬ እኔ በፊታችሁ እንዳስቀመጥሁት ሕግ ያለ ጽድቅ የሆነ ሥርዐትና ሕግ ያሉት ሌላ ታላቅ ሕዝብስ ማነው?

9ዐይኖቻችሁ ያዩአቸውን ነገሮች እንዳትረሱ፣ ደግሞም በሕይወት እስካላችሁ ድረስ ከልባችሁ እንዳይጠፉ ብቻ ተጠንቀቁ፣ ነቅታችሁም ራሳችሁን ጠብቁ። እነዚህን ለልጆቻችሁና ከእነርሱ በኋላ ለሚወለዱት ልጆቻቸው አስተምሯቸው። 10“በምድሪቱ በሚኖሩበት ጊዜ ሁሉ እኔን ማክበር እንዲማሩ፣ ለልጆቻቸውም እንዲያስተምሩ ቃሌን ይሰሙ ዘንድ ሕዝቡን በፊቴ ሰብስብ” ባለኝ ጊዜ፣ በኮሬብ በአምላካችሁ በእግዚአብሔር (ኤሎሂም ያህዌ) ፊት የቆማችሁበትን ዕለት አስታውሱ። 11ተራራው በጥቍር ደመናና በድቅድቅ ጨለማ ተውጦ ሳለ ነበልባሉ ሰማይ እስከሚደርስ ድረስ በተቃጠለ ጊዜ መጥታችሁ ከተራራው ግርጌ ቆማችሁ። 12ከዚያም እግዚአብሔር (ያህዌ) በእሳቱ ውስጥ ሆኖ ተናገራችሁ፤ እናንተም የቃሉን ድምፅ ሰማችሁ፤ መልክ ግን አላያችሁም፤ ድምፅ ብቻ ነበርና። 13እርሱ ኪዳኑን ይኸውም እንድትከተሏቸው ያዘዛችሁን ዐሥርቱን ትእዛዛት ዐወጀላችሁ፤ ከዚያም በሁለት የድንጋይ ጽላቶች ላይ ጻፋቸው፤ 14ዮርዳኖስን ተሻግራችሁ በምትወርሷት ምድር ውስጥ የምትከተሏቸውን ሥርዐትና ሕግ እንዳስተምራችሁ በዚያን ጊዜ እግዚአብሔር (ያህዌ) አዘዘኝ።

ጣዖትን ማምለክ ስለ መከልከሉ

15እግዚአብሔር (ያህዌ) በኮሬብ ተራራ ላይ በእሳት ውስጥ በተናገራችሁ ቀን ምንም ዐይነት መልክ ከቶ አላያችሁም፤ ስለዚህ ለራሳችሁ ተጠንቀቁ፤ 16ይኸውም እንዳትረክሱ፣ በወንድ ወይም በሴት መልክ በማናቸውም ዐይነት ምስል የተቀረጸ ጣዖት ለራሳችሁ እንዳታበጁ፣ 17ወይም በምድር ላይ የሚኖር የማናቸውንም እንስሳ ወይም በአየር ላይ የሚበርር የማናቸውንም ወፍ፣ 18ወይም በደረቱ የሚሳብ የማናቸውንም ፍጡር ወይም በውሃ ውስጥ የሚኖር የማናቸውንም ዓሣ ምስል እንዳታደርጉ ነው። 19ወደ ሰማይ ቀና ብለህ ፀሓይን፣ ጨረቃንና ከዋክብትን፣ የሰማይ ሰራዊትንም ሁሉ በምትመለከትበት ጊዜ፣ ወደ እነርሱ እንዳትሳብና እንዳትሰግድላቸው፣ አምላክህ እግዚአብሔር (ኤሎሂም ያህዌ) ከሰማይ በታች ላሉ ሕዝቦች ሁሉ ድርሻ አድርጎ የሰጣቸውንም ነገሮች እንዳታመልክ ተጠንቀቅ። 20እናንተን ግን ልክ ዛሬ እንደ ሆናችሁት ሁሉ ርስቱ ትሆኑለት ዘንድ፣ አምላካችሁ እግዚአብሔር (ኤሎሂም ያህዌ) እናንተን ከብረት ማቅለጫ ምድጃ፣ ከግብፅ አውጥቶ አመጣችሁ።

21በእናንተም ምክንያት እግዚአብሔር እኔን ተቈጣኝ፤ ዮርዳኖስንም እንዳልሻገርና አምላካችሁ እግዚአብሔር (ኤሎሂም ያህዌ) ርስት አድርጎ ወደሚሰጣችሁ ወደ መልካሚቱ ምድር እንዳልገባ ማለ። 22እኔም በዚህች ምድር እሞታለሁ፤ ዮርዳኖስን አልሻገርም፤ እናንተ ግን ልትሻገሩ ነው፤ ያችንም መልካም ምድር ትወርሳላችሁ። 23አምላካችሁ እግዚአብሔር (ኤሎሂም ያህዌ) ከእናንተ ጋር የገባውን ኪዳን እንዳትረሱ ተጠንቀቁ፤ አምላካችሁ እግዚአብሔር (ኤሎሂም ያህዌ) የከለከለውን ጣዖት በማናቸውም ዐይነት መልክ ለራሳችሁ አታብጁ። 24አምላካችሁ እግዚአብሔር (ኤሎሂም ያህዌ) የሚባላ እሳት ቀናተኛም አምላክ (ኤሎሂም) ነውና።

25ልጆችንና የልጅ ልጆችን ከወለዳችሁና በምድሪቱም ላይ ለረዥም ጊዜ ከኖራችሁ በኋላ ራሳችሁን በማርከስ ማንኛውንም ዐይነት ጣዖት ብታበጁ፣ በአምላካችሁም በእግዚአብሔር (ኤሎሂም ያህዌ) ፊት ክፋት በማድረግ ለቍጣ ብታነሣሡት፣ 26ዮርዳኖስን ተሻግራችሁ ከምትወርሷት ምድር ላይ ፈጥናችሁ እንደምትጠፉ በዚህ ቀን ሰማይንና ምድርን በእናንተ ላይ ምስክሮች አድርጌ እጠራለሁ፤ በዚያ ቦታ ብዙ ዘመን አትኖሩም፤ ፈጽሞ ትጠፋላችሁ። 27እግዚአብሔር (ያህዌ) እናንተን በአሕዛብ መካከል ይበትናችኋል፤ እግዚአብሔር በሚበትናችሁ አሕዛብ መካከል የምትተርፉት ጥቂቶቻችሁ ብቻ ናችሁ። 28እዚያም፣ ማየት ወይም መስማት ወይም መብላት ወይም ማሽተት በማይችሉ በሰው እጅ በተሠሩ የዕንጨትና የድንጋይ አማልክት ታመልካላችሁ። 29ነገር ግን እዚያም ሆናችሁ አምላካችሁን እግዚአብሔርን (ኤሎሂም ያህዌ) በፍጹም ልባችሁና በፍጹም ነፍሳችሁ ብትፈልጉት ታገኙታላችሁ። 30ስትጨነቅና ይህ ሁሉ ነገር ሲደርስብህ ያን ጊዜ፣ በኋለኞቹ ዘመናት ወደ አምላክህ ወደ እግዚአብሔር (ኤሎሂም ያህዌ) ትመለሳለህ፤ ትታዘዝለታለህም። 31አምላክህ እግዚአብሔር (ኤሎሂም ያህዌ) መሓሪ አምላክ (ኤሎሂም) ነውና አይተውህም ወይም አያጠፋህም፤ ወይም ደግሞ ለአባቶችህ በመሐላ ያጸናላቸውን ቃል ኪዳን አይረሳም።

እግዚአብሔር አምላክ ነው

32እግዚአብሔር ሰውን በምድር ላይ ከፈጠረበት ቀን ጀምሮ እናንተ ከመኖራችሁ በፊት ስለ ነበረው የቀድሞ ዘመን ጠይቁ፤ ከአንዱ የሰማይ ጫፍ እስከ ሌላው የሰማይ ጫፍ ድረስ ጠይቁ፤ እንደዚህ ያለ ታላቅ ነገር ከቶ ተደርጎ ወይስ እንደዚህ ዐይነት ነገር ከቶ ተሰምቶ ያውቃልን? 33ከእሳት ውስጥ የእግዚአብሔርን (ኤሎሂም) ድምፅ እንደ እናንተ የሰማና በሕይወት የኖረ ከቶ ሌላ ሕዝብ አለን? 34አምላካችሁ እግዚአብሔር (ኤሎሂም ያህዌ) በዐይናችሁ እያያችሁ ለእናንተ በግብፅ እንዳደረገው ሁሉ በፈተና፣ በታምራዊ ምልክቶችና በድንቆች፣ በጦርነት፣ በጸናች እጅና በተዘረጋች ክንድ ወይም በታላቅና በአስፈሪ ሥራዎች ከሌላ ሕዝብ መካከል አንድን ሕዝብ የራሱ ለማድረግ የቻለ አምላክ አለን?

35እግዚአብሔር እርሱ አምላክ (ያህዌ ኤሎሂም) መሆኑን፣ ከእርሱም በቀር ሌላ አምላክ አለመኖሩን ታውቁ ዘንድ እነዚህን ነገሮች እንድታዩ ተደረገ። 36ሊገሥጽህ ድምፁን ከሰማይ እንድትሰማ አደረገ፤ በምድርም ላይ አስፈሪ እሳቱን አሳየህ፤ ከእሳቱም ውስጥ ቃሉን ሰማህ። 37አባቶችህን ከመውደዱ የተነሣና ከእነርሱም በኋላ ዘራቸውን ስለ መረጠ፣ ከአንተ ጋር በመሆን በታላቅ ኀይሉ ከግብፅ አወጣህ፤ 38ዛሬ እንደ ሆነው ሁሉ ከአንተ ይልቅ ታላቅና ብርቱ የሆኑትን አሕዛብ ከፊትህ በማስወጣት ወደ ምድራቸው አስገብቶህ ለአንተ ርስት አድርጎ ለመስጠት ነው።

39እንግዲህ በላይ በሰማይ፣ በታችም በምድር እግዚአብሔር እርሱ አምላክ (ያህዌ ኤሎሂም) መሆኑን ዛሬ ዕወቅ፤ በልብህም ያዘው፤ ሌላም የለም። 40ለአንተና ከአንተም በኋላ ለልጆችህ መልካም እንዲሆንላችሁ፣ አምላክህ እግዚአብሔር (ኤሎሂም ያህዌ) ለዘላለም በሚሰጥህም ምድር ዕድሜህ እንዲረዝም፣ ዛሬ እኔ የማዝዝህን ሥርዐቱንና ሕግጋቱን ጠብቅ።

የመማፀኛ ከተሞች

4፥41-43 ተጓ ምብ – ዘኍ 35፥6-34ዘዳ 19፥1-14ኢያ 20፥1-9

41በዚያን ጊዜ ሙሴ ከዮርዳኖስ በስተ ምሥራቅ ሦስት ከተሞችን ለየ፤ 42ይኸውም የቈየ ጠላትነት ሳይኖር፣ በድንገት ባልንጀራውን የገደለ ማናቸውም ሰው ሸሽቶ ከእነዚህ ከተሞች ወደ አንዲቱ በመሄድ ሕይወቱን ማትረፍ ይችል ዘንድ ነው። 43ከተሞቹም በምድረ በዳው በከፍተኛ ቦታ ላይ የምትገኘው ቦሶር ለሮቤላውያን፣ በገለዓድ የምትገኘው ራሞት ለጋዳውያን፣ በባሳን ያለችው ጎላን ለምናሴያውያን ነበሩ።

ስለ ሕጉ የተሰጠ ማብራሪያ

44ሙሴ በእስራኤላውያን ፊት የደነገገው ሕግ ይህ ነው። 45ከግብፅ በወጡ ጊዜ ሙሴ ለእስራኤላውያን የሰጣቸው መመሪያዎች፣ ሥርዐቶችና ሕጎች እነዚህ ናቸው፤ 46ይህም ከግብፅ በወጡ ጊዜ በሙሴና በእስራኤላውያን ድል በተደረገው፣ በሐሴቦን በነገሠው በአሞራውያን ንጉሥ በሴዎን ምድር፣ ከዮርዳኖስ በስተ ምሥራቅ በቤተ ፌጎር አጠገብ ባለው ሸለቆ ውስጥ በነበሩበት ጊዜ ነው። 47ከዮርዳኖስ በስተ ምሥራቅ ያለውን፣ የእርሱን ምድርና የባሳንን ንጉሥ የዐግን፣ የሁለቱን አሞራውያን ነገሥታት ምድር ርስት አድርገው ወሰዱ። 48ይህም ምድር በአርኖን ሸለቆ ዳርቻ ካለው ከአሮዔር አንሥቶ እስከ ሴዎን4፥48 የዕብራይስጡና የሱርስቱ ትርጕም፣ ሢርዮን ይለዋል (ዘዳ 3፥9 ይመ) ተራራ ማለትም እስከ አርሞንዔም የሚደርስ ሲሆን፣ 49በዮርዳኖስ ምሥራቅ ያለውን ዓረባን በሙሉና ከፈስጋ ተረተር በታች ያለውን የዓረባ ባሕር4፥49 ይኸውም የሙት ባሕር ነው። ያጠቃልላል።

Chinese Contemporary Bible (Simplified)

申命记 4:1-49

当守律法

1以色列人啊,要聆听我传授给你们的律法,要切实遵行,以便你们可以存活,并进入你们祖先的上帝耶和华赐给你们的那片土地。 2我吩咐你们的,你们不可做任何增减,这是你们的上帝耶和华的命令,你们要遵守。 3你们亲眼看见耶和华在巴力·毗珥事件中的作为,你们的上帝耶和华毁灭了你们中间所有拜巴力·毗珥的人, 4但你们这些信靠你们的上帝耶和华的人至今还活着。 5看啊,遵照我的上帝耶和华的吩咐,我把律例和典章传授给你们,好让你们在将要占领的土地上遵守。 6你们要谨遵这些律例和典章,因为这样就会让外族人看见你们的智慧和聪明。他们听见这些律法后,必说,‘这伟大的民族真有智慧和聪明!’ 7我们的上帝耶和华与我们如此亲近,随时垂听我们的呼求,有哪个伟大民族的神明能与之相比? 8有哪个伟大的民族拥有我今天所传授给你们的如此公义的律例和典章?

9“要谨慎、小心,不可忘记亲眼所见的事,要一生铭记在心,并且告诉子子孙孙。 10那天,你们在何烈山站在你们的上帝耶和华面前,耶和华对我说,‘把民众招聚起来,让他们听我的教诲,学习一生敬畏我,并传授给自己的儿女。’ 11你们来到山脚下,站在那里,山上烈焰冲天、乌云密布、极其幽暗。 12耶和华在火焰中对你们说话,你们只听见祂的声音,却看不见祂的形象。 13祂向你们宣告祂的约,就是祂吩咐你们遵守的十诫,并写在两块石版上。 14那时,耶和华吩咐我把律例和典章传授给你们,好让你们在将要占领的土地上遵守。

不可拜偶像

15“你们要格外小心,耶和华在何烈山的火焰中对你们说话时,你们没有看见任何形象, 16所以不可堕落,去为自己制造任何形状的神像——男人、女人、 17飞禽走兽、 18爬虫或鱼类。 19当你们举目观看你们的上帝耶和华赐给天下万民的日、月、星辰等天上万象时,不要受诱惑去跪拜、供奉它们。 20耶和华拯救你们脱离埃及那座熔铁炉,让你们做祂自己的子民,正如今日的情形。 21因你们的缘故,耶和华向我发怒,起誓不让我过约旦河、进入祂赐给你们作产业的那片佳美之地。 22我将死在约旦河这边,过不了约旦河。但你们必过去得到那片佳美之地。 23你们要谨慎,不可忘记你们的上帝耶和华与你们所立的约,不可违背你们上帝耶和华的禁令,去制造任何形状的神像。 24因为你们的上帝耶和华是烈火,是痛恨不贞的上帝。

25“将来,即使你们在那里安顿已久、子孙满堂,也不可堕落、制造任何形状的神像,不可做你们的上帝耶和华视为邪恶的事,惹祂发怒。 26否则,今天我叫天地作证,你们必很快从约旦河对面将要占领的土地上灭亡,你们必被彻底消灭,不得在那里长久居住。 27耶和华必把你们驱散到列邦,使你们在列邦中的人数所剩无几。 28你们必在那里供奉人用木石造的不会看、不会听、不会吃、不会闻的神像。 29但你们若在那里寻求你们的上帝耶和华,全心全意地寻求祂,就必寻见。 30日后,当你们遭遇这些事,受尽苦难的时候,必归向你们的上帝耶和华,听从祂。 31因为你们的上帝耶和华充满怜悯,祂不会抛弃你们,灭绝你们,也不会忘记祂与你们祖先所立的誓约。

独一的上帝

32“你们可以查考历史,自上帝创造世人以来,这样的奇事,天地之间何曾有过?谁曾听闻? 33有哪个民族像你们一样,听见了上帝在火中说话,还活了下来? 34有哪个神明像你们的上帝耶和华那样在埃及当着你们的面降灾祸、行神迹奇事、兴起战争、伸出臂膀、施展大能的手、以伟大而可畏的作为拯救一族脱离异邦? 35耶和华行这样的事,是要叫你们知道祂是上帝,除祂以外,别无他神。 36祂让你们听见祂从天上来的声音,好教导你们,又在地上让你们看见祂的烈火,并听见祂在烈火中说的话。 37因为祂爱你们的祖先,所以拣选你们,亲自用大能把你们从埃及领出来, 38赶走比你们强大的民族,领你们进入他们的土地,把他们的土地赐给你们作产业,正如今日的情形。 39所以,今天你们要知道并谨记,耶和华是天上地下的上帝,此外别无他神。 40我今天将祂的律例和诫命传授给你们,你们要遵守,以便你们及子孙都蒙福,在你们上帝耶和华所赐的土地上得享长寿。”

设立避难城

41那时,摩西约旦河东划出三座城作避难城, 42供素无冤仇却误杀他人者逃往避难。 43三座城分别是旷野高原的比悉——供吕便人避难,基列拉末——供迦得人避难,巴珊哥兰——供玛拿西人避难。

重申律法

44以下是摩西颁布给以色列人的律法, 45即在离开埃及后传授给他们的法度、律例和典章。 46当时他们在约旦河以东伯·毗珥对面的山谷,那里原属于希实本亚摩利西宏摩西以色列人离开埃及后消灭了西宏47占领了他的土地,还占领了巴珊的土地。西宏约旦河东亚摩利人的两个王, 48其国土从亚嫩谷边的亚罗珥一直到西云山,即黑门山, 49包括约旦河东的整个亚拉巴,远至毗斯迦山脚的亚拉巴海。