ኢያሱ 1 – NASV & CCB

New Amharic Standard Version

ኢያሱ 1:1-18

እግዚአብሔር ኢያሱን አዘዘ

1የእግዚአብሔር ባሪያ ሙሴ ከሞተ በኋላ፣ እግዚአብሔር የሙሴን አገልጋይ የነዌን ልጅ ኢያሱን እንዲህ አለው፤ 2“እነሆ፤ ባሪያዬ ሙሴ ሞቷል፤ እንግዲህ አሁንም አንተና ይህ ሕዝብ ሁሉ ተነሡ፤ ለእስራኤላውያን ወደምሰጣቸው ምድር ለመግባት የዮርዳኖስን ወንዝ ተሻገሩ። 3ለሙሴ በሰጠሁትም ተስፋ መሠረት፣ እግራችሁ የሚረግጠውን ቦታ ሁሉ እሰጣችኋለሁ። 4የርስታችሁ ዳርቻ ከምድረ በዳው እስከ ሊባኖስ፣ ከታላቁ ወንዝ ከኤፍራጥስ አንሥቶ፣ የኬጢያውያንን ምድር በሙሉ ይዞ፣ በምዕራብ በኩል እስከ ታላቁ ባሕር1፥4 የሜድትራኒያን ባሕር ይደርሳል። 5በሕይወት በምትኖርበት ዘመን ሁሉ ማንም አይቋቋምህም፤ ከሙሴ ጋር እንደ ነበርሁ ሁሉ ከአንተም ጋር እሆናለሁ፤ ከቶ አልጥልህም፤ አልተውህም።

6“ጽና፤ ለቀደሙት አባቶቻቸው እሰጣችኋለሁ ብዬ የማልሁላቸውን ምድር እንዲወርሱ፣ ይህን ሕዝብ የምትመራው አንተ ነህና በርታ። 7አይዞህ፤ ብቻ አንተ በርታ፤ ባሪያዬ ሙሴ የሰጠህን ትእዛዝ ሁሉ በጥንቃቄ ጠብቅ፤ በምትሄድበትም ሁሉ እንዲሳካልህ፣ ወደ ቀኝም ወደ ግራም አትበል። 8ይህ የሕግ መጽሐፍ ከአፍህ አይለይ፤ በውስጡ የተጻፈውን ሁሉ በጥንቃቄ እንድትፈጽመውም ቀንም ሆነ ሌት ከሐሳብህ አትለየው፤ ይህን ካደረግህ ያሰብኸው ይቃናል፤ ይሳካልም፤ 9በምትሄድበት ሁሉ እግዚአብሔር አምላክህ ከአንተ ጋር ነውና አይዞህ፤ በርታ፤ ጽና፤ አትፍራ፤ አትደንግጥ ብዬ አላዘዝሁህምን?”

10ኢያሱም የሕዝቡን አለቆች እንዲህ ሲል አዘዛቸው፤ 11“ወደ ሰፈር ግቡ፤ ለሕዝቡም፣ ‘ስንቃችሁን አዘጋጁ፤ ከአሁን ጀምሮ ባሉት ሦስት ቀናት ውስጥ ዮርዳኖስን ተሻግራችሁ፣ እግዚአብሔር አምላካችሁ ርስት አድርጎ የሚሰጣችሁን ምድር ገብታችሁ ትወርሳላችሁ’ በሏቸው።”

12ኢያሱ የሮቤልን ነገድ፣ የጋድን ነገድና የምናሴን ነገድ እኩሌታ እንዲህ አላቸው፤ 13የእግዚአብሔር ባሪያ ሙሴ እንዲህ ሲል የሰጣችሁን ትእዛዝ አስቡ፤ ‘እግዚአብሔር አምላካችሁ ያሳርፋችኋል፤ ይህችንም ምድር ይሰጣችኋል።’ 14ሚስቶቻችሁና ልጆቻችሁ እንዲሁም ከብቶቻችሁ ሙሴ በሰጣችሁ ከዮርዳኖስ በስተ ምሥራቅ ባለው ምድር ይቈዩ፤ ነገር ግን ተዋጊዎቻችሁ ሁሉ፣ ከነሙሉ ትጥቃቸው፣ ከወንድሞቻችሁ ቀድመው ይሻገሩ፤ እናንተም ከወንድሞቻችሁ ጐን ተሰለፉ። 15ይህም፣ እግዚአብሔር እስኪያሳርፋቸውና ለእናንተም እንዳደረገው ሁሉ፣ እነርሱም እግዚአብሔር አምላካችሁ የሰጣቸውን ምድር እስኪወርሱ ድረስ ነው። ከዚህ በኋላ እናንተም ተመልሳችሁ የእግዚአብሔር ባሪያ ሙሴ የሰጣችሁን፣ በፀሓይ መውጫ ከዮርዳኖስ በስተ ምሥራቅ ያለውን ምድር ትወርሳላችሁ።”

16እነርሱም ለኢያሱ እንዲህ ሲሉ መለሱለት፤ “ያዘዝኸንን ሁሉ እናደርጋለን፤ ወደምትልከንም ሁሉ እንሄዳለን። 17ለሙሴ ሙሉ በሙሉ እንደ ታዘዝን ሁሉ፣ ለአንተም እንታዘዛለን፤ ብቻ እግዚአብሔር አምላክህ ከሙሴ ጋር እንደ ነበረ፣ አሁንም ከአንተ ጋር ይሁን። 18በትእዛዝህ ላይ የሚያምፅና ለቃልህ የማይታዘዝ ሁሉ ይገደል፤ ብቻ አንተ ጽና፤ አይዞህ፤ በርታ።”

Chinese Contemporary Bible (Simplified)

约书亚记 1:1-18

主对约书亚的吩咐

1耶和华的仆人摩西死了以后,耶和华对摩西的助手——的儿子约书亚说: 2“我的仆人摩西已经死了,现在你和全体以色列人要准备渡过约旦河,到我要赐给你们的地方去。 3我已把你们脚掌将踏之地都赐给了你们,正如我对摩西的应许。 4从南部的旷野直到北部的黎巴嫩,从东部的幼发拉底大河直到西部的地中海,包括人居住的全境,都将是你们的领土。 5在你有生之年,没有人能够抵挡你。过去我怎样与摩西同在,也必照样与你同在,我必不离开你,也不丢弃你。 6你要刚强勇敢,因为你要带领这些人占领我起誓赐给他们祖先的土地。 7你只要刚强勇敢,谨遵我仆人摩西所吩咐你的一切律法,毫不偏离,就可以无往不利。 8你要常常诵读这律法书,昼夜不断地思想,以便谨遵律法书上的一切指示。这样,你必亨通、顺利。 9我再次吩咐你,要刚强勇敢!不要害怕,也不要灰心,因为你无论走到哪里,你的上帝耶和华必与你同在。”

10于是,约书亚吩咐民众的首领说: 11“你们要走遍全营,吩咐大家预备好食物。因为三天之内,你们就要过约旦河,去占领你们的上帝耶和华赐给你们的土地。”

12约书亚又对吕便支派、迦得支派和玛拿西半个支派的人说: 13“你们要牢记耶和华的仆人摩西吩咐你们的话,他说你们的上帝耶和华要把约旦河东面的土地赐给你们,让你们安居。 14你们的妻子儿女和牲畜可以留在约旦河东岸摩西分给你们的土地上,但你们当中所有的勇士要带着兵器先过约旦河,帮助你们的弟兄。 15要等到你们的上帝耶和华使你们的弟兄像你们一样得到祂所赐的土地,安居以后,你们才可以回到约旦河东,在耶和华的仆人摩西分给你们的土地上定居。” 16他们回答约书亚说:“凡你命令我们的,我们一定遵行。无论你派我们去哪里,我们一定去。 17我们在一切的事上怎样服从摩西,也必照样服从你,愿你的上帝耶和华与你同在,像与摩西同在一样。 18任何人违抗你的命令,不照你的吩咐去做,都要被处死。你要刚强勇敢!”