ዘዳግም 23 – NASV & CCB

New Amharic Standard Version

ዘዳግም 23:1-25

ከእግዚአብሔር ጉባኤ መለየት

1ብልቱ የተቀጠቀጠ ወይም የተቈረጠ ማናቸውም ሰው ወደ እግዚአብሔር (ያህዌ) ጉባኤ አይግባ።

2ዲቃላም ይሁን የዲቃላው ዘር የሆነ ሁሉ፣ እስከ ዐሥር ትውልድ ድረስ እንኳን ቢሆን ወደ እግዚአብሔር (ያህዌ) ጉባኤ አይግባ።

3አሞናዊም ሆነ ሞዓባዊ ወይም ማናቸውም የእርሱ ዘር፣ እስከ ዐሥር ትውልድ እንኳ ቢሆን ወደ እግዚአብሔር (ያህዌ) ጉባኤ አይግባ። 4ምክንያቱም ከግብፅ ከወጣችሁ በኋላ በጕዞ ላይ በነበራችሁበት ጊዜ እህል ውሃ ይዘው አልተቀበሏችሁም፤ በመስጴጦምያ በምትገኘው በፐቶር23፥4 ይኸውም ሰሜን ምዕራብ መስጴጦምያ ነው። ይኖር የነበረውን የቢዖር ልጅ በለዓምን አንተን እንዲረግም በገንዘብ ገዙት። 5ይሁን እንጂ አምላክህ እግዚአብሔር (ኤሎሂም ያህዌ) በለዓምን አልሰማውም፤ አምላክህ እግዚአብሔር (ኤሎሂም ያህዌ) ስለሚወድህ ርግማኑን በረከት አደረገልህ። 6በሕይወት ዘመንህ ሁሉ ሰላምን ለእነርሱ አትመኝ።

7ወንድምህ ስለሆነ ኤዶማዊውን አትጸየፈው፤ መጻተኛ ሆነህ በአገሩ ኖረሃልና ግብፃዊውን አትጥላው። 8ለእነርሱ የተወለዱላቸው የሦስተኛው ትውልድ ልጆች ወደ እግዚአብሔር (ያህዌ) ጉባኤ መግባት ይችላሉ።

የጦር ሰፈር ንጽሕና አጠባበቅ

9ጠላትህን ለመውጋት ወጥተህ በሰፈርህ ጊዜ፣ ከማናቸውም ርኩሰት ራስህን ጠብቅ። 10ከመካከላችሁ ሌሊት ዘር በማፍሰስ የረከሰ ሰው ቢኖር፣ ከሰፈር ወጥቶ እዚያው ይቈይ። 11እየመሸ ሲመጣ ግን ገላውን ይታጠብ፤ ፀሓይ ስትጠልቅም ወደ ሰፈሩ ይመለስ።

12ለመጸዳጃ የሚሆንህን ቦታ ከሰፈር ውጭ አዘጋጅ። 13ከትጥቅህም ጋር መቈፈሪያ ያዝ፤ በምትጸዳዳበት ጊዜ ዐፈር ቈፍረህ በዐይነ ምድርህ ላይ መልስበት። 14አምላክህ እግዚአብሔር (ኤሎሂም ያህዌ) ሊጠብቅህ ጠላቶችህንም በእጅህ አሳልፎ ሊሰጥህ በሰፈር ውስጥ ስለሚዘዋወር፣ በመካከልህ አንዳች ነውር አይቶ ከአንተ እንዳይመለስ፣ ሰፈርህ የተቀደሰ ይሁን።

ልዩ ልዩ ሕጎች

15አንድ ባሪያ ከአሳዳሪው ኰብልሎ ወደ አንተ ቢመጣ፣ ለአሳዳሪው አሳልፈህ አትስጠው። 16ደስ በሚያሰኘው ቦታና ራሱ በመረጠው ከተማ በመካከልህ ይኑር፤ አንተም አታስጨንቀው።

17ወንድ ወይም ሴት እስራኤላዊ የቤተ ጣዖት አመንዝራ አይሁን። 18ለዝሙት ዐዳሪ ሴት ወይም ለወንደቃ23፥18 ዕብራይስጡ፣ ውሻ ይላል። የተከፈለውን ዋጋ ለማናቸውም ስእለት አድርገህ ለመስጠት ወደ አምላክህ ወደ እግዚአብሔር (ኤሎሂም ያህዌ) ቤት አታምጣ፤ አምላክህ እግዚአብሔር (ኤሎሂም ያህዌ) ሁለቱንም ይጸየፋቸዋልና።

19የገንዘብ፣ የእህል ወይም የማንኛውንም ነገር ወለድ ለማግኘት ለወንድምህ በወለድ አታበድር። 20ባዕድ ለሆነ ሰው ወለድ ማበደር ትችላለህ፤ ነገር ግን ልትወርሳት በምትገባባት ምድር እጅህ በሚነካው በማናቸውም ነገር አምላክህ እግዚአብሔር (ኤሎሂም ያህዌ) እንዲባርክህ ለእስራኤላዊ ወንድምህ በወለድ አታበድረው።

21ለአምላክህ ለእግዚአብሔር (ኤሎሂም ያህዌ) ስእለት ከተሳልህ፣ አምላክህ እግዚአብሔር (ኤሎሂም ያህዌ) አጥብቆ ከአንተ ይሻዋልና፣ ኀጢአት እንዳይሆንብህ ለመክፈል አትዘግይ። 22ሳትሳል ብትቀር ግን በደለኛ አትሆንም። 23በአንደበትህ የተናገርኸውን ሁሉ ለመፈጸም ጠንቃቃ ሁን፤ ለአምላክህ ለእግዚአብሔር (ኤሎሂም ያህዌ) በገዛ አንደበትህ ፈቅደህ ስእለት ተስለሃልና።

24ወደ ባልንጀራህ የወይን ተክል ቦታ በምትገባበት ጊዜ፣ ያሰኘህን ያህል መብላት ትችላለህ፤ ነገር ግን አንዳችም በዕቃህ አትያዝ። 25ወደ ባልንጀራህ ዕርሻ በምትገባበት ጊዜ፣ እሸት መቅጠፍ ትችላለህ፤ በሰብሉ ላይ ግን ማጭድ አታሳርፍበት።

Chinese Contemporary Bible (Simplified)

申命记 23:1-25

会众的资格

1“凡睪丸受损或被阉割的,不可加入耶和华的会众。

2“私生子及其十代以内的子孙都不可加入耶和华的会众。

3亚扪人或摩押人及其十代以内的子孙都不可加入耶和华的会众。 4因为在你们离开埃及的途中,他们没有用水和食物款待你们,还雇用美索不达米亚毗夺人——比珥的儿子巴兰咒诅你们。 5但你们的上帝耶和华不听巴兰的话,反而把咒诅变为祝福,因为祂爱你们。 6你们一生一世永不可为他们谋求平安和好处。

7“不可憎恶以东人,因为他们是你们的弟兄;也不可憎恶埃及人,因为你们曾经在埃及寄居。 8他们的第三代子孙可以加入耶和华的会众。

保持军营圣洁的条例

9“你们出兵征战时,一定要远离恶事。 10如果有人因梦遗而不洁净,他就要离开营地住在营外。 11傍晚他要沐浴,日落才可以回营。 12要在营外指定一个地方作方便之处。 13你们每人都要有一把铲子,便溺时要挖个洞,事后要掩埋。 14因为你们的上帝耶和华常在营中巡视,要保护你们,击败你们的仇敌。军营必须保持圣洁,免得祂在你们中间看到任何污秽之事,便离开你们。

其他条例

15“如果有奴隶逃到你们那里避难,不可把逃亡的奴隶送交他们的主人。 16要让他们在你们当中选择他们喜欢的城邑与你们同住,不可压迫他们。

17“任何以色列人,不论男女,都不可做庙妓。 18不可把男女庙妓的收入带到你们上帝耶和华的殿还愿,因为你们的上帝耶和华憎恶他们。

19“你们借给同胞钱、粮食或其他任何东西,都不可收取利息。 20你们可以向外族人收取利息,但不可向同胞收取。这样,在你们将要占领的土地上,你们的上帝耶和华必使你们凡事蒙福。

21“如果你们向你们的上帝耶和华许愿,不可迟迟不还愿,因为你们的上帝耶和华必追讨许愿不还的罪。 22如果你们不许愿,反倒无罪; 23但如果你们亲口许了愿,一定要向你们的上帝耶和华信守诺言。

24“如果你们进了邻居的葡萄园,可以随意吃,但不可把葡萄放在篮子里带走。 25如果你们进了邻居的麦田,可以用手摘麦穗,但不可用镰刀割麦子。