ዘዳግም 13 – NASV & CCB

New Amharic Standard Version

ዘዳግም 13:1-18

ሌሎች አማልክትን ማምለክ

1ነቢይ ወይም ሕልም ዐላሚ ከመካከልህ ተነሥቶ ምልክት ወይም ድንቅ አደርጋለሁ ቢልህ፣ 2የተናገረው ምልክት ወይም ድንቅ ቢፈጸም፣ “አንተ የማታውቃቸውን ሌሎች አማልክት እናምልካቸው” ቢልህ፣ 3አምላካችሁ እግዚአብሔር (ኤሎሂም ያህዌ) በፍጹም ልባችሁና በፍጹም ነፍሳችሁ ትወድዱት እንደ ሆነ ያውቅ ዘንድ ሊፈትናችሁ ነውና፣ የዚያን ነቢይ ቃል ወይም ሕልም ዐላሚውን አትስማ። 4አምላካችሁን እግዚአብሔርን (ኤሎሂም ያህዌ) ተከተሉት፤ ፍሩት፤ ትእዛዞቹንም ጠብቁ፤ ታዘዙት፤ አገልግሉት፤ ከእርሱም ጋር ተጣበቁ። 5ከግብፅ ባወጣችሁና ከባርነት ምድር በዋጃችሁ በአምላካችሁ በእግዚአብሔር (ኤሎሂም ያህዌ) ላይ እንድታምፁ ተናግሯልና፣ አምላካችሁ እግዚአብሔር (ኤሎሂም ያህዌ) እንድትከተሉት ካዘዛችሁ መንገድ እንድትመለሱ አድርጓልና፣ ያ ነቢይ ወይም ሕልም ዐላሚ ይገደል፤ ስለዚህ ክፉውን ከመካከልህ አስወግድ።

6የእናትህ ልጅ ወንድምህ፣ ወንድ ወይም ሴት ልጅህ፣ ወይም የምትወድዳት ሚስትህ ወይም የልብ ጓደኛህ፣ (አንተም ሆንህ አባቶችህ የማታውቋቸውን አማልክት) “ሄደን ሌሎችን አማልክት እናምልክ” ብሎ በስውር ሊያስትህ ቢሞክር፣ 7በቅርብም ሆነ በሩቅ፣ ከአንዱ የምድር ጫፍ እስከ ሌላው ድረስ በዙሪያህ ያሉትን የአሕዛብ አማልክት እናምልክ ቢልህ፣ 8እሺ አትበለው፤ ወይም አታዳምጠው፤ አትራራለት፤ አትማረው፤ ወይም አትሸሽገው። 9ያለማመንታት ግደለው፤ እርሱንም ለመግደል በመጀመሪያ የአንተ እጅ፣ ከዚያም በኋላ የሕዝቡ ሁሉ እጅ ይነሣ። 10የባርነት ምድር ከሆነው ከግብፅ ካወጣህ ከአምላክህ ከእግዚአብሔር (ኤሎሂም ያህዌ) ሊያርቅህ ፈልጓልና እስኪሞት ድረስ በድንጋይ ውገረው። 11ከዚያም እስራኤል ሁሉ ሰምተው ይፈራሉ፤ ከመካከልህም ማንም እንደዚህ ያለውን ክፉ ነገር ዳግም አያደርግም።

12አምላክህ እግዚአብሔር (ኤሎሂም ያህዌ) እንድትኖርባቸው ከሚሰጥህ ከተሞች በአንዲቱ ውስጥ እንዲህ ሲባል ብትሰማ፣ 13ክፉ ሰዎች ከመካከላችሁ ተነሥተው አንተ የማታውቃቸውን፣ “ሌሎች አማልክትን ሄደን እናምልክ” በማለት የከተማቸውን ሕዝብ እያሳቱ ቢሆን፣ 14ጕዳዩን አጣራ፤ መርምር፤ በሚገባም ተከታተል፤ ነገሩ እውነት ሆኖ ከተገኘና ይህ አስጸያፊ ነገር በመካከልህ መፈጸሙ ከተረጋገጠ፣ 15በዚያች ከተማ የሚኖሩትን ሁሉ በሰይፍ ግደላቸው፤ ከተማዪቱን ከነሕዝቧና ከነቀንድ ከብቷ ፈጽሞ ደምስሳት13፥15 የዕብራይስጡ ቃል አንድን ነገር ወይም አንድን ሰው ሙሉ በሙሉ በማጥፋት ለእግዚአብሔር መስጠትን የሚያሳይ ነው።16በከተማዪቱ የተገኘውን የምርኮ ዕቃ ሁሉ በአደባባይዋ መካከል ላይ ሰብስበህ፣ ከተማዪቱን ከነምርኮዋ እንዳለ ለአምላክህ ለእግዚአብሔር (ኤሎሂም ያህዌ) የሚቀርብ መሥዋዕት አድርገህ በሙሉ አቃጥል። ለዘላለም እንደ ፈረሰች ትቅር፤ ተመልሳም አትሠራ። 17እግዚአብሔር (ያህዌ) ከብርቱ ቍጣው ይመለስ ዘንድ ዕርም ነገሮች በእጅህ አይገኙ13፥17 የዕብራይስጡ ቃል አንድን ነገር ወይም አንድን ሰው ሙሉ በሙሉ በማጥፋት ለእግዚአብሔር መስጠትን የሚያሳይ ነው።፤ እርሱ ምሕረቱን ያሳይሃል፤ ይራራልሃል፤ ለአባቶችህ በመሐላ ተስፋ በሰጠው መሠረት ቍጥርህን ያበዛዋል፤ 18ይህም የሚሆነው ዛሬ እኔ የምሰጥህን ትእዛዞቹን ሁሉ በመጠበቅና መልካም የሆነውን በአምላክህ በእግዚአብሔር (ኤሎሂም ያህዌ) ፊት በማድረግ ለአምላክህ ለእግዚአብሔር (ኤሎሂም ያህዌ) ስለ ታዘዝህለት ነው።

Chinese Contemporary Bible (Simplified)

申命记 13:1-18

不可拜假神

1“如果你们中间出现了先知或解梦的人,要显神迹奇事给你们看, 2劝你们随从、供奉素不认识的神明,即使他们显的神迹奇事应验了, 3你们也不可听从他们。因为这是你们的上帝耶和华在试验你们,要看看你们是否全心全意地爱祂。 4你们要跟从你们的上帝耶和华,敬畏祂,遵守祂的诫命,听从祂的话,事奉祂,倚靠祂。 5必须处死那些先知或解梦的人,因为他们怂恿你们背叛你们的上帝耶和华、偏离祂吩咐你们当走的道路。你们的上帝耶和华曾带你们离开埃及,救你们脱离奴役。你们必须清除你们当中的邪恶。

6“如果你们的兄弟、儿女、爱妻或挚友引诱你们去拜你们和你们祖先都不认识的神明, 7引诱你们去拜你们周围各族的神明,或在附近或远在天边, 8你们不可迁就、听从他们,不可怜惜他们,不可放过或包庇他们。 9必须处死他们。你们要首先下手,然后众人一起打死他们。 10你们要用石头打死他们,因为他们企图使你们背弃你们的上帝耶和华,祂曾把你们从受奴役之地——埃及领出来。 11这样,所有以色列人听了就会害怕,必无人再敢做这种恶事。

12-13“在你们的上帝耶和华将要赐给你们居住的各城中,如果你们听说某城里有恶人引诱城中的居民偏离正路,唆使他们去供奉你们不认识的神明, 14你们要认真查明真相。如果传闻属实,你们当中确有此恶行, 15你们一定要杀光那城中的居民和牲畜。 16你们要把城中的财物堆在广场中心,然后放火焚烧那城和城中的财物,作为燔祭献给你们的上帝耶和华。城要永远荒废,不可重建。 17-18你们不可保留任何应当被毁灭的东西,这样耶和华就不再向你们发怒,转而施恩怜悯你们。

“只要你们遵守我今天吩咐你们的一切诫命,做耶和华视为正的事,祂必按照祂对你们祖先所起的誓,怜悯你们,使你们人丁兴旺。