ዘሌዋውያን 15 – NASV & CCB

New Amharic Standard Version

ዘሌዋውያን 15:1-33

የሚያረክስ የሰውነት ፈሳሽ

1እግዚአብሔር (ያህዌ) ሙሴንና አሮንን እንዲህ አላቸው፤ 2“ለእስራኤላውያን እንዲህ ብላችሁ ንገሯቸው፤ ‘ማንም ሰው ከሰውነቱ ፈሳሽ ነገር ቢወጣ ያ ሰው ርኩስ ነው። 3ከሰውነቱ የሚወጣው ፈሳሽ መፍሰሱን ቢቀጥል ወይም ባይቀጥል ሰውየው ርኩስ ነው፤ ፈሳሹም ርኩሰት የሚያስከትለው እንደዚህ ነው፦

4“ ‘ፈሳሽ ነገር የሚወጣው ሰው የተኛበት የትኛውም መኝታ ርኩስ ይሆናል፤ እርሱ የተቀመጠበት ማንኛውም ነገር ርኩስ ይሆናል። 5ዐልጋውን የነካ ማንኛውም ሰው ልብሱን ይጠብ፤ ሰውነቱንም በውሃ ይታጠብ፤ እስከ ማታ ድረስ ግን ርኩስ ይሆናል። 6ፈሳሽ ነገር የሚወጣው ሰው በተቀመጠበት በየትኛውም ነገር ላይ የተቀመጠ ሰው ሁሉ ልብሱን ይጠብ፤ ሰውነቱንም በውሃ ይታጠብ፤ እስከ ማታ ድረስ ግን ርኩስ ይሆናል።

7“ ‘ፈሳሽ ነገር የሚወጣውን ሰው የነካ ማንኛውም ሰው ልብሱን ይጠብ፤ ሰውነቱንም በውሃ ይታጠብ፤ እስከ ማታ ድረስ ግን ርኩስ ይሆናል።

8“ ‘ፈሳሽ ነገር የሚወጣው ሰው ንጹሕ በሆነ ሰው ላይ ቢተፋ፣ የተተፋበት ሰው ልብሱን ይጠብ፤ ሰውነቱንም በውሃ ይታጠብ፤ እስከ ማታ ድረስ ግን ርኩስ ይሆናል።

9“ ‘ፈሳሽ ነገር የሚወጣው ሰው የተቀመጠበት ኮርቻ ሁሉ ርኩስ ይሆናል፤ 10ከበታቹ ያለውንም ነገር ሁሉ የነካ ማንም ሰው እስከ ማታ ድረስ ርኩስ ይሆናል። እነዚህንም ነገሮች የሚያነሣ ማንም ሰው ልብሱን ይጠብ፤ ሰውነቱንም በውሃ ይታጠብ፤ እስከ ማታ ድረስ ግን ርኩስ ይሆናል።

11“ ‘ፈሳሽ ነገር የሚወጣው ሰው እጁን በውሃ ሳይታጠብ ሌላውን ሰው ቢነካ፣ የተነካው ሰው ልብሱን ይጠብ፤ ሰውነቱንም በውሃ ይታጠብ፤ እስከ ማታ ድረስ ግን ርኩስ ይሆናል።

12“ ‘ፈሳሽ ነገር የሚወጣው ሰው የነካው የሸክላ ዕቃ ይሰበር፤ ከዕንጨት የተሠራ ዕቃ ከሆነ በውሃ ይታጠብ።

13“ ‘ፈሳሽ ነገር የሚወጣው ሰው ከፈሳሹ ሲነጻ፣ በሕጉ መሠረት ለመንጻቱ ሰባት ቀን ይቍጠር፤ ልብሱን ይጠብ፤ ሰውነቱንም በምንጭ ውሃ ይታጠብ፤ ንጹሕም ይሆናል። 14በስምንተኛውም ቀን ሁለት ርግቦች ወይም ሁለት የዋኖስ ጫጩቶች ይዞ በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ በእግዚአብሔር (ያህዌ) ፊት በመቅረብ ለካህኑ ይስጥ። 15ካህኑም አንዱን ለኀጢአት መሥዋዕት፣ ሌላውንም ለሚቃጠል መሥዋዕት ያቅርብ፤ በዚህ መሠረት ስለ ፈሳሹ በእግዚአብሔር (ያህዌ) ፊት ለሰውየው ያስተሰርይለታል።

16“ ‘አንድ ሰው ዘሩ በሚፈስስበት ጊዜ ሰውነቱን በሙሉ በውሃ ይታጠብ፤ እስከ ማታ ድረስ ግን ርኩስ ይሆናል። 17የፈሰሰው ዘር የነካው ማንኛውም ልብስ ወይም ቍርበት በውሃ ይታጠብ፤ እስከ ማታ ድረስ ግን ርኩስ ይሆናል። 18አንድ ሰው ከአንዲት ሴት ጋር ግብረ ሥጋ ፈጽሞ ዘር ቢፈስሰው፣ ሁለቱም በውሃ ይታጠቡ፤ እስከ ማታ ድረስ ግን ርኩሳን ይሆናሉ።

19“ ‘ሴት ጊዜውን እየጠበቀ የሚመጣው የደም መፍሰስ ቢኖርባት፣ የወር አበባዋ ርኩሰት እስከ ሰባት ቀን ይቈያል፤ በዚህ ጊዜ ማንም ሰው ቢነካት እስከ ማታ ድረስ ርኩስ ይሆናል።

20“ ‘በወር አበባዋ ጊዜ የምትተኛበት ማንኛውም ነገር ርኩስ ይሆናል፤ የተቀመጠችበትም ነገር ርኩስ ይሆናል። 21መኝታዋን የነካ ማንኛውም ሰው ልብሱን ይጠብ፤ ሰውነቱንም በውሃ ይታጠብ፤ እስከ ማታ ድረስ ግን ርኩስ ይሆናል። 22የተቀመጠችበትን ማንኛውንም ነገር የነካ ሰው ልብሱን ይጠብ፤ ሰውነቱንም በውሃ ይታጠብ፤ እስከ ማታ ድረስ ግን ርኩስ ይሆናል፤ 23መኝታዋን ወይም የተቀመጠችበትን ማንኛውንም ነገር የነካ ሰው እስከ ማታ ድረስ ርኩስ ይሆናል።

24“ ‘አንድ ሰው ከእርሷ ጋር ቢተኛና የወር አበባዋ ቢነካው፣ እስከ ሰባት ቀን ድረስ ርኩስ ይሆናል፤ እርሱ የሚተኛበት መኝታ ሁሉ ርኩስ ይሆናል።

25“ ‘ሴት ከወር አበባዋ ጊዜ ሌላ ብዙ ቀን ደም ቢፈስሳት፣ ወይም የወር አበባዋ ጊዜ ካለፈ በኋላ የደሙ መፍሰስ ባይቋረጥ፣ ልክ እንደ ወር አበባዋ ጊዜ፣ ደም መፍሰሱ እስኪቆም ድረስ ርኩስ ትሆናለች። 26ደሟ መፍሰሱን በቀጠለበት ጊዜ ሁሉ፣ የምትተኛበት ማንኛውም መኝታ ልክ በወር አበባዋ ጊዜ እንደ ነበረው መኝታ ርኩስ ይሆናል፤ የምትቀመጥበትም ማንኛውም ነገር ልክ እንደ ወር አበባዋ ጊዜ ርኩስ ይሆናል። 27እነዚህንም የሚነካ ማንኛውም ሰው ርኩስ ይሆናል፤ ልብሱን ይጠብ፤ ሰውነቱንም በውሃ ይታጠብ፤ እስከ ማታ ድረስ ግን ርኩስ ይሆናል።

28“ ‘ከደሟ ፍሳሽ ሳትነጻ ሰባት ቀን ትቍጠር፤ ከዚያም በኋላ በሥርዐቱ መሠረት ንጹሕ ትሆናለች። 29በስምንተኛውም ቀን ሁለት ርግቦች ወይም ሁለት የዋኖስ ጫጩቶች ይዛ በመቅረብ በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ ለካህኑ ትሰጣለች። 30ካህኑም አንዱን ለኀጢአት መሥዋዕት፣ ሌላውንም ለሚቃጠል መሥዋዕት ያቅርብ፤ በዚህ መሠረት ስለ ፈሳሽዋ ርኩሰት በእግዚአብሔር (ያህዌ) ፊት ያስተሰርይላታል።

31“ ‘በመካከላቸው ያለችውን ማደሪያዬን15፥31 ወይም የመገናኛ ድንኳኔን እንዳያረክሱና በርኩሰታቸው እንዳይሞቱ፣ እስራኤላውያንን ከሚያረክሳቸው ነገር ለዩአቸው።’ ”

32ፈሳሽ ነገር የሚወጣውን፣ ዘሩም በመፍሰሱ ርኩስ የሆነውን ሰው ሁሉ፣ 33በወር አበባ ላይ ያለችን ሴት፣ ፈሳሽ ነገር የሚወጣቸውን ወንድ ወይም ሴት፣ በሥርዐቱ መሠረት ርኩስ ከሆነች ሴት ጋር የሚተኛውን ወንድ በሚመለከት ሕጉ ይኸው ነው።

Chinese Contemporary Bible (Simplified)

利未记 15:1-33

有关漏症患者的条例

1耶和华对摩西亚伦说: 2“你们把以下条例告诉以色列人。

“如果有男人患了漏症,他下体的排泄物是不洁净的。 3不论他下体的排泄物止住与否,他都是不洁净的。 4他睡过的床或坐过的东西都不洁净。 5凡碰到他睡过的床的人都不洁净,必须洗衣、沐浴,等到傍晚才能洁净。 6凡坐他坐过之物的人都不洁净,必须洗衣、沐浴,等到傍晚才能洁净。 7凡碰到他的人都不洁净,必须洗衣、沐浴,等到傍晚才能洁净。 8如果他吐唾沫在一个洁净的人身上,那人便不洁净,必须洗衣、沐浴,等到傍晚才能洁净。 9他骑过的鞍子是不洁净的。 10凡碰到他坐过之物的人都不洁净,要等到傍晚才能洁净。碰到这些东西的人都不洁净,必须洗衣、沐浴,等到傍晚才能洁净。 11如果他没有洗手就碰到别人,那人便不洁净,必须洗衣、沐浴,等到傍晚才能洁净。 12必须打碎他摸过的陶器,用水清洗他摸过的木器。 13他病愈后,必须经过七天的洁净期,要洗净衣服,用清水沐浴,这样就洁净了。 14第八天,他要把两只斑鸠或雏鸽带到会幕门前,在耶和华面前交给祭司献祭, 15一只作赎罪祭,一只作燔祭。这样,祭司便在耶和华面前为他的漏症赎了罪。

有关遗精的条例

16“男人若遗精,便不洁净,必须沐浴全身,等到傍晚才能洁净。 17沾了精液的衣物或皮革都不洁净,必须用水清洗,等到傍晚才能洁净。 18如果男女同房,二人都不洁净,必须沐浴,等到傍晚才能洁净。

有关女人月经的条例

19“女人在月经期间,要不洁净七天。凡接触到她的人都不洁净,要等到傍晚才能洁净。 20月经期间,她躺过或坐过的东西都不洁净。 21凡碰过她床的人都不洁净,必须洗衣、沐浴,等到傍晚才能洁净。 22人若碰到她坐过的地方,也不洁净,必须洗衣、沐浴,等到傍晚才能洁净。 23不论是她的床,还是她坐的东西,碰到的人都不洁净,要等到傍晚才能洁净。 24男人若与她同房,沾染了她的经血,就要不洁净七天,他躺过的床也不洁净。

25“女人若在经期以外多日血漏或经期过长,在此期间便不洁净,像在经期内一样。 26在血漏期间,她躺的床或坐的东西都不洁净,像在经期内一样。 27凡碰到这些东西的人都不洁净,必须洗衣、沐浴,等到傍晚才能洁净。 28血漏停止后,她要等七天才洁净。 29第八天,她要把两只斑鸠或雏鸽带到会幕门口,交给祭司献祭, 30一只作赎罪祭,一只作燔祭。这样,祭司便在耶和华面前为她赎了血漏的不洁之罪。 31你们要使以色列人远离不洁之物,免得他们因玷污我的圣幕而死亡。”

32以上是为患漏症的人,包括遗精、 33行经的女人、患漏症的男女、与不洁净女人同房的男人所设立的条例。