ዘሌዋውያን 14 – NASV & CCB

New Amharic Standard Version

ዘሌዋውያን 14:1-57

ከተላላፊ የቈዳ በሽታ የመንጻት ሥርዐት

1እግዚአብሔር (ያህዌ) ሙሴን እንዲህ አለው፤ 2“የታመመው ሰው እንዲነጻ ወደ ካህኑ በሚወስዱት ጊዜ ሥርዐቱ እንዲህ ነው፦ 3ካህኑ ከሰፈር ወደ ውጭ ወጥቶ ይመርምረው፤ ሰውየው ከተላላፊ የቈዳ በሽታው14፥3 በትውፊት ለምጽ ይባላል። የዕብራይስጡ ቃል ከቈዳ ጋር ለተያያዘ በሽታ አንድ ቃል ነው፤ በዚህ ምዕራፍ በሌላ ስፍራም ይገኛል። ተፈውሶ ከሆነ፣ 4ካህኑ ስለሚነጻው ሰው፣ ለመብላት ከተፈቀደው የወፍ ዐይነት ሁለት ከነሕይወታቸው፣ የዝግባ ዕንጨት፣ ደመቅ ያለ ቀይ ድርና ሂሶጵ እንዲያመጣ ይዘዝ። 5ካህኑም ከወፎቹ አንዱን በሸክላ ዕቃ ውስጥ ባለ የምንጭ ውሃ ላይ እንዲታረድ ይዘዝ። 6በሕይወት ያለውንም ወፍ ከዝግባው ዕንጨት፣ ደመቅ ካለው ቀይ ድርና ከሂሶጵ ጋር በምንጩ ውሃ ላይ በታረደው ወፍ ደም ውስጥ ይንከር። 7ከተላላፊ በሽታ የሚነጻውንም ሰው ሰባት ጊዜ ይርጨው፤ መንጻቱንም ያስታውቅ፤ በሕይወት ያለውንም ወፍ ወደ ውጭ ይልቀቀው።

8“የሚነጻው ሰው ልብሱን ይጠብ፤ ጠጕሩን በሙሉ ይላጭ፤ ሰውነቱን በውሃ ይታጠብ፤ በሥርዐቱም መሠረት ንጹሕ ይሆናል። ከዚህም በኋላ ወደ ሰፈር መግባት ይችላል፤ ነገር ግን ሰባት ቀን ከድንኳኑ ውጭ ይቈይ። 9በሰባተኛውም ቀን ጠጕሩን በሙሉ ይላጭ፤ ራሱን፣ ጢሙን፣ ቅንድቡንና ሌላውንም ጠጕር ሁሉ ይላጭ። ልብሱን ይጠብ፤ ሰውነቱን በውሃ ይታጠብ፤ ንጹሕም ይሆናል።

10“በስምንተኛው ቀን ነውር የሌለባቸውን ሁለት ተባዕት የበግ ጠቦቶችና ነውር የሌለባትን አንዲት የአንድ ዓመት እንስት በግ ያቅርብ፤ እንዲሁም ለእህል ቍርባን የሚሆን በዘይት የተለወሰ የኢፍ ሦስት ዐሥረኛ14፥10 6.5 ሊትር ገደማ ይሆናል የላመ ዱቄት ያቅርብ፤ ደግሞ አንድ ሎግ14፥10 0.3 ሊትር ገደማ ይሆናል፤ እንዲሁም 12፡15፡21፡24 ይመ ዘይት ያምጣ። 11ሰውየው የነጻ መሆኑን የሚያስታውቀው ካህን የሚነጻውን ሰውና መሥዋዕቶቹን በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ ላይ በእግዚአብሔር (ያህዌ) ፊት ያቅርብ።

12“ካህኑም ከተባዕቱ ጠቦቶች በመውሰድ ከሎግ ዘይቱ ጋር የበደል መሥዋዕት አድርጎ ያቅርብ፤ የሚወዘወዝ መሥዋዕት በማድረግም በእግዚአብሔር (ያህዌ) ፊት ይወዝውዛቸው። 13ጠቦቱንም፣ የኀጢአት መሥዋዕትና የሚቃጠል መሥዋዕት በሚታረድበት በተቀደሰው ስፍራ ይረደው፤ የኀጢአት መሥዋዕቱ ለካህኑ እንደሚሰጥ ሁሉ የበደል መሥዋዕቱም ለካህኑ ይሰጥ፤ ይህም እጅግ የተቀደሰ ነው። 14ካህኑ ከበደል መሥዋዕቱ ደም ወስዶ የሚነጻውን ሰው ቀኝ ጆሮ ታችኛውን ጫፍ፣ የቀኝ እጁን አውራ ጣትና የቀኝ እግሩን አውራ ጣት ያስነካ። 15ካህኑም ከሎግ ዘይት ወስዶ በራሱ ግራ እጅ መዳፍ ውስጥ ይጨምር፤ 16የቀኝ እጁንም ጣት በመዳፉ በያዘው ዘይት ውስጥ በመንከር በእግዚአብሔር (ያህዌ) ፊት ሰባት ጊዜ በጣቱ ይርጭ። 17ካህኑ በመዳፉ ውስጥ ከቀረው ዘይት ጥቂቱን ወስዶ የሚነጻውን ሰው ቀኝ ጆሮ ታችኛውን ጫፍ፣ የቀኝ እጁን አውራ ጣትና የቀኝ እግሩን አውራ ጣት በበደል መሥዋዕቱ ደም ላይ ደርቦ ይቅባ። 18በመዳፉ ላይ የቀረውንም ዘይት በሚነጻው ሰው ራስ ላይ ያድርግ፤ በእግዚአብሔርም (ያህዌ) ፊት ያስተስርይለት።

19“ካህኑም የኀጢአት መሥዋዕቱን ያቅርብ፤ ከርኩሰቱ ለሚነጻውም ሰው ያስተስርይለት፤ ከዚህ በኋላ የሚቃጠለውን መሥዋዕት ይረድ፤ 20ከእህል ቍርባኑም ጋር በመሠዊያው ላይ በማቅረብ ያስተስርይለት፤ ሰውየውም ንጹሕ ይሆናል።

21“ሰውየው ድኻ ከሆነና እነዚህን ለማቅረብ ዐቅሙ ካልፈቀደለት፣ ማስተስረያ እንዲሆነው የሚወዘወዝ አንድ ተባዕት የበግ ጠቦት ለበደል መሥዋዕት፣ በዘይት የተለወሰ የኢፍ አንድ ዐሥረኛ14፥21 2 ሊትር ገደማ ይሆናል የላመ ዱቄት ለእህል ቍርባን ያቅርብ፤ ደግሞም አንድ ሎግ ዘይት ያምጣ፤ 22እንዲሁም ሁለት ርግቦች ወይም ሁለት የዋኖስ ጫጩቶች ዐቅሙ የፈቀደውን አንዱን ለኀጢአት መሥዋዕት፣ ሌላውን ለሚቃጠል መሥዋዕት ያቅርብ።

23“እነዚህንም በስምንተኛው ቀን ስለ መንጻቱ ሥርዐት ወደ ካህኑ ወደ መገናኛው ድንኳን ደጃፍ በእግዚአብሔር (ያህዌ) ፊት ያቅርብ። 24ካህኑም ለበደል መሥዋዕት የሚሆነውን የበግ ጠቦትና አንድ ሎግ ዘይት ይቀበል፤ የሚወዘወዝ መሥዋዕት በማድረግም በእግዚአብሔር (ያህዌ) ፊት ይወዝውዛቸው። 25ለበደል መሥዋዕት የሚሆነውንም የበግ ጠቦት ይረድ፤ ከደሙም ጥቂት ወስዶ የሚነጻውን ሰው የቀኝ ጆሮ ታችኛ ጫፍ፣ የቀኝ እጁን አውራ ጣትና የቀኝ እግሩን አውራ ጣት ያስነካ፤ 26ከዘይቱም ጥቂቱን በግራ እጁ መዳፍ ውስጥ ያፍስስ፤ 27የቀኝ እጁንም ጣት በመዳፉ በያዘው ዘይት ውስጥ በመንከር በእግዚአብሔር (ያህዌ) ፊት ሰባት ጊዜ ይርጭ። 28በመዳፉ ከያዘው ዘይት ጥቂቱን ወስዶ የበደል መሥዋዕቱን ደም ባስነካበት ቦታ፣ ይኸውም የሚነጻውን ሰው ቀኝ ጆሮ ጫፍ፣ የቀኝ እጁን አውራ ጣትና የቀኝ እግሩን አውራ ጣት ያስነካ። 29ካህኑ በእግዚአብሔር (ያህዌ) ፊት ያስተሰርይለት ዘንድ በመዳፉ ከያዘው ዘይት የቀረውን በሚነጻው ሰው ራስ ላይ ያፍስስ፤ 30ካህኑም ርግቦቹን ወይም የዋኖሶቹን ጫጩቶች የሰውየው ዐቅም የፈቀደውን ይሠዋል፤ 31ከእነዚህም አንዱን14፥31 የሰብዓ ሊቃናትና የሱርሰት ትርጕሞች ከዚህ ጋር ይስማማሉ፤ ዕብራይስጡ 31 የሰውየው ዐቅም የፈቀደውን ያህል አንዱን ለኀጢአት ይላል ለኀጢአት መሥዋዕት፣ ሌላውን ለሚቃጠል መሥዋዕት አድርጎ ከእህሉ ቍርባን ጋር ያቅርብ፤ በዚህም ሁኔታ ካህኑ ለሚነጻው ሰው በእግዚአብሔር (ያህዌ) ፊት ያስተሰርይለታል።”

32ተላላፊ የቈዳ በሽታ ይዞት የሚነጻበትን መደበኛ መሥዋዕት ለማቅረብ ዐቅም ላነሰው ሰው ሕጉ ይህ ነው።

ልብስ ላይ ከሚታይ ተላላፊ በሽታ መንጻት

33እግዚአብሔር (ያህዌ) ሙሴንና አሮንን እንዲህ አላቸው፤ 34“ርስት አድርጌ ወደምሰጣቸው ወደ ከነዓን ምድር በገባችሁ ጊዜ፣ በዚያ አገር አንዱን ቤት በተላላፊ በሽታ የበከልሁ እንደ ሆነ፣ 35ባለቤቱ ወደ ካህኑ ሄዶ፣ ‘በቤቴ ውስጥ ተላላፊ በሽታ የሚመስል ነገር አይቻለሁ’ ብሎ ይንገረው። 36ካህኑ ወደዚያ ቤት በመግባት በሽታውን መርምሮ ርኩስ መሆኑን ከማስታወቁ በፊት፣ ቤቱን ባዶ እንዲያደርጉት ይዘዝ፤ ከዚህ በኋላ ካህኑ ወደ ቤቱ ገብቶ ይመርምር። 37በግድግዳው ላይ ያለውን ተላላፊ በሽታ በሚመረምርበት ጊዜ፣ መልኩ ወደ አረንጓዴነት ወይም ወደ ቀይነት የሚያደላ የተቦረቦረ ነገር በግድግዳው ቢታይ፣ 38ካህኑ ከቤቱ ወደ ደጅ ወጥቶ ቤቱን ሰባት ቀን ይዝጋው። 39ካህኑም በሰባተኛው ቀን ቤቱን ለመመርመር ይመለስ፤ ተላላፊው በሽታ በግድግዳው ተስፋፍቶ ቢገኝ፣ 40የተበከሉት ድንጋዮች ተሰርስረው እንዲወጡና ከከተማው ውጭ ባለው ርኩስ ስፍራ እንዲጣሉ ይዘዝ፤ 41የቤቱ ግድግዳ በሙሉ በውስጥ በኩል እንዲፋቅና ፍቅፋቂው ከከተማው ውጭ ባለው ርኩስ ስፍራ እንዲደፋ ያድርግ። 42በወጡትም ድንጋዮች ቦታ ሌሎች ድንጋዮች አምጥተው ይተኩ፤ ሌላም ጭቃ ወስደው ቤቱን ይምረጉ።

43“ድንጋዮቹ ወጥተው፣ ቤቱ ከተፈቀፈቀና ከተመረገ በኋላ ተላላፊው በሽታ እንደ ገና በቤቱ ውስጥ ከታየ፣ 44ካህኑ ሄዶ ይመርምረው፤ ተላላፊው በሽታ በቤቱ ውስጥ ተስፋፍቶ ከተገኘ፣ አደገኛ በሽታ ነው፤ ቤቱም ርኩስ ነው። 45ስለዚህ ቤቱ ይፍረስ፤ ድንጋዩ፣ ዕንጨቱና ምርጊቱ በሙሉ ከከተማ ውጭ ባለው ርኩስ ስፍራ ይጣል።

46“ቤቱ ተዘግቶ ሳለ ማንኛውም ሰው ቢገባበት፣ ያ ሰው እስከ ማታ ድረስ ርኩስ ይሆናል። 47በዚያ ቤት ገብቶ የተኛ ወይም የበላ ማንኛውም ሰው ልብሶቹን ይጠብ።

48“ነገር ግን ቤቱ ከተመረገ በኋላ፣ ካህኑ ሊመረምረው በሚመጣበት ጊዜ ተላላፊው በሽታ ሳይስፋፋ ቢገኝ፣ በሽታው ስለ ለቀቀው ቤቱ ንጹሕ መሆኑን ያስታውቅ። 49ቤቱንም ለማንጻት ሁለት ወፎች፣ የዝግባ ዕንጨት፣ ደመቅ ያለ ቀይ ድርና ሂሶጵ ያቅርብ። 50ከወፎቹም አንዱን በሸክላ ዕቃ ውስጥ ባለ የምንጭ ውሃ ላይ ይረድ። 51የዝግባውን ዕንጨት፣ ሂሶጱን፣ ደመቅ ያለውን ቀይ ድርና በሕይወት ያለውን ወፍ ወስዶ በታረደው ወፍ ደምና በምንጩ ውሃ ውስጥ ይንከር፤ ቤቱንም ሰባት ጊዜ ይርጭ። 52ቤቱንም በወፉ ደም፣ በምንጩ ውሃ፣ በሕይወት ባለው ወፍ፣ በዝግባው ዕንጨት፣ በሂሶጱና ደመቅ ባለው ቀይ ድር ያንጻው። 53በሕይወት ያለውንም ወፍ ከከተማ ወደ ውጭ ይልቀቀው፤ በዚህ ሁኔታ ለቤቱ ያስተሰርይለታል፤ ቤቱም ንጹሕ ይሆናል።”

54ይህ ሕግ ለማንኛውም ተላላፊ የቈዳ በሽታ፣ ለሚያሳክክ ሕመም፣ 55በልብስና በቤት ላይ ለሚመጣ ተላላፊ በሽታ፣ 56ለዕብጠት፣ ለችፍታ ወይም ለቋቍቻ፣ 57አንድ ነገር ንጹሕ ወይም ርኩስ መሆኑ የሚታወቅበት ነው። ይህ ለተላላፊ የቈዳ በሽታ እንዲሁም በልብስና በቤት ላይ ለሚወጣ ተላላፊ በሽታ የሚያገለግል ሕግ ነው።

Chinese Contemporary Bible (Simplified)

利未记 14:1-57

麻风病患者的洁净条例

1耶和华对摩西说: 2“以下是有关麻风病患者的洁净条例。

“麻风病患者痊愈后,要通知祭司。 3祭司要到营外去检查,如果发现他的病已痊愈, 4要吩咐人为他拿来两只洁净的鸟、香柏木、朱红色线和牛膝草。 5祭司要吩咐人在一个盛清水的陶器上宰杀一只鸟, 6然后祭司要把另一只鸟,连同香柏木、朱红色线和牛膝草一起蘸在掺了清水的鸟血里。 7祭司要用鸟血在他身上洒七次,宣布他是洁净的,然后放走那只活鸟,让它飞向田野。 8他要洗净衣服,剃去所有毛发,沐浴之后便洁净了,可以回到营内,但要住在自己的帐篷外七天。 9第七天,他要再次剃掉头发、胡须和眉毛等各处毛发,并洗衣、沐浴,之后便洁净了。

10“第八天,他要带来两只毫无残疾的公羊羔、一只毫无残疾的一岁母羊羔、三公斤作素祭的调油的细面粉和一杯油。 11主持洁净礼的祭司要把他及其祭物带到会幕门口、耶和华面前, 12并献上一只公羊羔和一杯油作赎过祭,作为摇祭在耶和华面前摇一摇。 13他要在杀赎罪祭牲和燔祭牲的圣洁之处宰公羊羔。赎过祭的祭物要归祭司,像赎罪祭一样,这是至圣之物。 14祭司要拿一些赎过祭祭牲的血抹在求洁净者的右耳垂、右手大拇指和右脚大脚趾上。 15祭司要拿那杯油,倒一些在自己左手掌中, 16用一根右手指蘸左手掌里的油,在耶和华面前弹洒七次, 17然后用手掌中剩下的油抹求洁净者的右耳垂、右手大拇指和右脚大脚趾,就是抹了赎过祭祭牲血的地方。 18祭司要把手掌里剩下的油抹在求洁净者的头上。这样,祭司在耶和华面前为他赎了罪。 19祭司要献上赎罪祭,为求洁净者赎罪。然后,祭司要宰杀燔祭牲, 20在祭坛上献燔祭和素祭,为他赎罪,他就洁净了。

21“他如果贫穷,献不起那么多祭物,可以献一只公羊羔作赎过祭,用摇祭的方式赎罪;也要献一公斤作素祭的调油的细面粉和一杯油; 22还要按自己的能力献两只斑鸠或雏鸽,一只作赎罪祭,一只作燔祭。 23第八天,他必须把这些祭物带到会幕门口,在耶和华面前交给祭司。 24祭司要用作赎过祭的羊羔和一杯油作摇祭,在耶和华面前摇一摇。 25接着,祭司要宰杀作赎过祭的羊羔,拿一些羊血抹在他的右耳垂、右手大拇指和右脚大脚趾上。 26祭司也要把一些油倒在自己左手掌中, 27用一根右手指蘸左手掌中的油,在耶和华面前弹洒七次, 28然后把手掌中的一些油抹在他的右耳垂、右手大拇指和右脚大脚趾上,就是抹了赎过祭祭牲血的地方。 29祭司要把手掌里剩下的油抹在他头上,在耶和华面前为他赎罪。 30然后献上那人按自己能力带来的两只斑鸠或雏鸽, 31一只作赎罪祭,一只作燔祭。这样,祭司在耶和华面前为他赎了罪。 32这是献不起洁净礼所需祭物的麻风病患者应当遵守的条例。”

处理房子发霉的条例

33耶和华对摩西亚伦说:

34“你们到了我赐给你们作产业的迦南以后,如果我使那里的房屋中有发霉现象, 35屋主必须去告诉祭司,‘我的房子里好像有发霉现象。’ 36祭司进去检查前,要吩咐人把房子腾空,免得房子里的一切都变得不洁净。之后,祭司要进去检查, 37如发现墙壁上出现红色或绿色霉斑,并且侵入墙中, 38就要封闭房子七天。 39第七天,祭司要回去检查。若发现墙壁上的霉斑蔓延, 40就要下令拆掉有霉斑的石块,丢到城外不洁净的地方, 41然后命人刮掉屋内墙壁上的灰泥,倒在城外不洁净的地方。 42要另找石块补被拆掉的地方,并用灰泥重新粉刷房子。

43“如果拆掉石块、刮掉灰泥、重新粉刷以后,霉斑再度出现并蔓延, 44祭司要去检查,若发现霉斑已蔓延,那房子就不洁净。 45房主要拆掉房子,把石块、木料和所有灰泥都丢到城外不洁净的地方。 46房子封闭期间,任何人进去,都不洁净,要等到傍晚才能洁净。 47凡在房内睡觉或吃饭的人,都必须洗净衣服。

48“祭司检查粉刷后的房子,若发现房内没有再度出现霉斑,就要宣布房子是洁净的。 49为洁净房子,祭司要取两只鸟、香柏木、朱红色线和牛膝草, 50在一个盛清水的陶器上宰杀一只鸟, 51然后用香柏木、牛膝草、朱红色线和另一只活鸟蘸掺了清水的鸟血,向房子洒七次。 52祭司用鸟血、清水、活鸟、香柏木、牛膝草和朱红色线洁净那房子后, 53要放走那只活鸟,让它飞到城外的田野。这样,祭司为那房子赎了罪,房子就洁净了。”

54以上是有关麻风病、疥癣、 55衣物或房子发霉、 56肿包、皮疹或白斑的条例。 57根据这些条例,可以分辨有关的人或物何时洁净、何时不洁净。