ዕብራውያን 2 – NASV & KJV

New Amharic Standard Version

ዕብራውያን 2:1-18

ትኵረት የሚያሻው ጕዳይ

1ስለዚህ ከሰማነው ነገር ስተን እንዳንወድቅ፣ ለሰማነው ነገር አብልጠን ልንጠነቀቅ ይገባናል። 2ምክንያቱም በመላእክት በኩል የተነገረው ቃል ጽኑ ከሆነና ማንኛውም መተላለፍና አለመታዘዝ ተገቢውን ቅጣት ከተቀበለ፣ 3እኛስ እንዲህ ያለውን ታላቅ ድነት ቸል ብንል እንዴት ልናመልጥ እንችላለን? ይህ ድነት በመጀመሪያ በጌታ ተነገረ፤ ከእርሱ የሰሙትም ለእኛ አረጋገጡልን። 4እግዚአብሔርም በምልክት፣ በድንቅና በልዩ ልዩ ታምራት እንዲሁም እንደ ፈቃዱ በታደሉት የመንፈስ ቅዱስ ስጦታዎች ስለዚሁ ነገር መስክሯል።

ኢየሱስ ወንድሞቹን መሰለ

5ይህን የምንናገርለትን መጪውን ዓለም ለመላእክት አላስገዛም፤ 6ነገር ግን አንዱ በሌላ ስፍራ እንዲህ ብሎ መስክሯል፤

“ታስታውሰው ዘንድ ሰው ምንድን ነው?

ታስብለትስ ዘንድ የሰው ልጅ ምንድን ነው”

7ከመላእክት ጥቂት2፥7 ወይም ለጥቂት ጊዜ አሳነስኸው፤

የክብርና የምስጋና ዘውድ ጫንህለት፤

8ሁሉንም ከእግሮቹ በታች አስገዛህለት።

እግዚአብሔር ሁሉን ከበታቹ ሲያስገዛለት፣ ያላስገዛለት ምንም ነገር የለም፤ ይሁን እንጂ በአሁኑ ጊዜ ሁሉም ነገር ተገዝቶለት አናይም። 9ነገር ግን በእግዚአብሔር ጸጋ ስለ ሰው ሁሉ ሞትን ይቀምስ ዘንድ ከመላእክት ጥቂት እንዲያንስ ተደርጎ የነበረው ኢየሱስ፣ የሞትን መከራ በመቀበሉ አሁን የክብርና የምስጋና ዘውድ ተጭኖለት እናየዋለን።

10ሁሉ ነገር ለእርሱና በእርሱ የሚኖር እግዚአብሔር፣ ብዙ ልጆችን ወደ ክብር ለማምጣት፣ የድነታቸውን መሥራች በመከራ ፍጹም ሊያደርገው የተገባ ነበር። 11ሰዎችን የሚቀድሰውና የሚቀደሱት ሰዎች ከአንድ ቤተ ሰብ ናቸው፤ ስለዚህ ኢየሱስ ወንድሞች ብሎ ሊጠራቸው አያፍርም፤ 12እንዲህም ይላል፤

“ስምህን ለወንድሞቼ እነግራቸዋለሁ፤

በጉባኤም መካከል ምስጋናህን እዘምራለሁ።”

13እንዲሁም፣

“እኔ በእርሱ እታመናለሁ።”

ደግሞም እንዲህ ይላል፤

“እነሆ፤ እኔና እግዚአብሔር የሰጠኝ ልጆች።”

14ልጆቹ በሥጋና በደም እንደሚካፈሉ፣ እርሱ ራሱ ደግሞ ያንኑ ተካፈለ፤ ይኸውም በሞት ላይ ኀይል ያለውን ዲያብሎስን በሞቱ ኀይል እንዲደመስስ ነው፤ 15እንዲሁም በሕይወት ዘመናቸው ሁሉ በሞት ፍርሀት ባርነት የታሰሩትን ነጻ እንዲያወጣ ነው። 16እርሱ የመጣው መላእክትን ለመርዳት ሳይሆን፣ የአብርሃምን ዘር ለመርዳት እንደ ሆነ ግልጽ ነው። 17ስለዚህ በሁሉም ነገር ወንድሞቹን መምሰል ተገባው፤ ይህንም ያደረገው መሓሪና ታማኝ ሊቀ ካህናት ሆኖ፣ እግዚአብሔርን ለማገልገልና ለሕዝቡ የኀጢአትን ስርየት ለማስገኘት2፥17 የእግዚአብሔርን ቍጣ ለመመለስ ነው። 18እርሱ ራሱ በተፈተነ ጊዜ መከራን ስለ ተቀበለ፣ የሚፈተኑትን ሊረዳቸው ይችላልና።

King James Version

Hebrews 2:1-18

1Therefore we ought to give the more earnest heed to the things which we have heard, lest at any time we should let them slip. 2For if the word spoken by angels was stedfast, and every transgression and disobedience received a just recompence of reward; 3How shall we escape, if we neglect so great salvation; which at the first began to be spoken by the Lord, and was confirmed unto us by them that heard him; 4God also bearing them witness, both with signs and wonders, and with divers miracles, and gifts of the Holy Ghost, according to his own will?

5For unto the angels hath he not put in subjection the world to come, whereof we speak. 6But one in a certain place testified, saying, What is man, that thou art mindful of him? or the son of man, that thou visitest him? 7Thou madest him a little lower than the angels; thou crownedst him with glory and honour, and didst set him over the works of thy hands: 8Thou hast put all things in subjection under his feet. For in that he put all in subjection under him, he left nothing that is not put under him. But now we see not yet all things put under him. 9But we see Jesus, who was made a little lower than the angels for the suffering of death, crowned with glory and honour; that he by the grace of God should taste death for every man. 10For it became him, for whom are all things, and by whom are all things, in bringing many sons unto glory, to make the captain of their salvation perfect through sufferings. 11For both he that sanctifieth and they who are sanctified are all of one: for which cause he is not ashamed to call them brethren, 12Saying, I will declare thy name unto my brethren, in the midst of the church will I sing praise unto thee. 13And again, I will put my trust in him. And again, Behold I and the children which God hath given me. 14Forasmuch then as the children are partakers of flesh and blood, he also himself likewise took part of the same; that through death he might destroy him that had the power of death, that is, the devil; 15And deliver them who through fear of death were all their lifetime subject to bondage. 16For verily he took not on him the nature of angels; but he took on him the seed of Abraham. 17Wherefore in all things it behoved him to be made like unto his brethren, that he might be a merciful and faithful high priest in things pertaining to God, to make reconciliation for the sins of the people. 18For in that he himself hath suffered being tempted, he is able to succour them that are tempted.