የሬካባውያን ታማኝነት
1በይሁዳ ንጉሥ በኢዮስያስ ልጅ፣ በኢዮአቄም ዘመነ መንግሥት፣ ከእግዚአብሔር ዘንድ እንዲህ የሚል ቃል ወደ ኤርምያስ መጣ፤ 2“ወደ ሬካባውያን ሄደህ ወደ እግዚአብሔር ቤት አምጣቸው፤ ወደ አንዱም ክፍል አስገብተህ የሚጠጡትን ወይን ጠጅ ስጣቸው።”
3ስለዚህ የካባስን ልጅ የኤርምያስን ልጅ ያእዛንያን፣ ወንድሞቹንና ወንዶች ልጆቹን ሁሉ፣ የሬካባውያንን ወገን በአጠቃላይ ሄጄ ጠራኋቸው፤ 4ወደ እግዚአብሔር ቤት አመጣኋቸው፤ ወደ ሐናን ልጆች ክፍልም አስገባኋቸው፤ የሐናን አባት ጌዴልያም የእግዚአብሔር ሰው ነበረ። ክፍሉም በመኳንንቱ ክፍል አጠገብ፣ ከመዕሤያ ክፍል በላይ ነበር፤ መዕሤያም የበር ጠባቂው የሰሎም ልጅ ነበረ፤ 5በሬካባውያንም ሰዎች ፊት በወይን ጠጅ የተሞሉ ማድጋዎችን አቀረብሁ፤ ዋንጫዎችንም ሰጥቻቸው፣ “በሉ፤ የወይን ጠጅ ጠጡ” አልኋቸው።
6እነርሱ ግን እንዲህ አሉ፤ “የወይን ጠጅ አንጠጣም፤ አባታችን የሬካብ ልጅ ኢዮናዳብ እንዲህ ብሎ አዝዞናል፤ ‘እናንተና ዘራችሁ ከቶ የወይን ጠጅ አትጠጡ፤ 7ቤት አትሥሩ፤ ዘር አትዝሩ፤ ወይን አትትከሉ፤ ሁልጊዜ በድንኳን ኑሩ እንጂ ከእነዚህ ነገሮች አንዱም አይኑራችሁ፤ ይህም ሲሆን እንደ መጻተኛ በሆናችሁበት ምድር ረዥም ዘመን ትኖራላችሁ።’ 8እኛም አባታችን የሬካብ ልጅ ኢዮናዳብ ያዘዘንን ሁሉ ፈጽመናል፤ እኛና ሚስቶቻችን፣ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻችንም የወይን ጠጅ ጠጥተን አናውቅም፤ 9የምንቀመጥበትም ቤት አልሠራንም፤ የወይን ቦታ፣ የዕርሻ ስፍራ ወይም የእህል ዘር የለንም። 10በድንኳን ኖረናል፤ አባታችን ኢዮናዳብ ያዘዘንንም ሁሉ ጠብቀናል። 11ነገር ግን የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር ይህችን ምድር በወረረ ጊዜ፣ ‘ኑ፤ ከባቢሎን35፥11 ወይም ከለዳውያን ሰራዊትና ከሶርያ ሰራዊት ሸሽተን ወደ ኢየሩሳሌም እንሂድ’ ተባባልን፤ ስለዚህም በኢየሩሳሌም ተቀመጥን።” 12የእግዚአብሔር ቃል ወደ ኤርምያስ እንዲህ ሲል መጣ፤ 13“የእስራኤል አምላክ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ሂድ፤ ለይሁዳ ሰዎችና ለኢየሩሳሌም ሕዝብ እንዲህ ብለህ ተናገር፤ ‘ቃሌን ትጠብቁ ዘንድ ከዚህ አትማሩምን?’ ይላል እግዚአብሔር፤ 14‘የሬካብ ልጅ ኢዮናዳብ ልጆቹ የወይን ጠጅ እንዳይጠጡ አዘዛቸው፤ ይህም ትእዛዝ ተጠብቋል፤ የአባታቸውን ትእዛዝ ስለ ጠበቁ እስከ ዛሬ ድረስ የወይን ጠጅ አይጠጡም፤ እናንተ ግን እኔ ደጋግሜ ብናገራችሁም፤ አልታዘዛችሁኝም። 15አገልጋዮቼን ነቢያትን ሁሉ ደጋግሜ ወደ እናንተ ላክሁ፤ እነርሱም፣ “እያንዳንዳችሁ ከክፉ መንገዳችሁ ተመለሱ፤ ምግባራችሁን አስተካክሉ፤ ለእናንተና ለአባቶቻችሁ በሰጠኋቸው ምድር ትኖሩ ዘንድ ሌሎቹን አማልክት ለማገልገል አትከተሉ” አልኋችሁ። እናንተ ግን ጆሯችሁን ወደ እኔ አላዘነበላችሁም፤ አልሰማችሁኝምም። 16የሬካብ ልጅ የኢዮናዳብ ዘሮች አባታቸው የሰጣቸውን ትእዛዝ ጠብቀዋል፤ ይህ ሕዝብ ግን አልታዘዘኝም።’
17“ስለዚህ የእስራኤል አምላክ፤ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘እነሆ፤ በይሁዳና በኢየሩሳሌም በሚኖሩት ሁሉ ላይ አደርሳለሁ ያልሁትን ጥፋት ሁሉ አመጣባቸዋለሁ፤ በተናገርኋቸው ጊዜ፣ አልሰሙኝምና በጠራኋቸውም ጊዜ አልመለሱልኝም።’ ”
18ኤርምያስም ሬካባውያንን እንዲህ አላቸው፤ “የእስራኤል አምላክ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘የአባታችሁን የኢዮናዳብን ትእዛዝ ስለ ጠበቃችሁ፤ መመሪያውን ስለ ተከተላችሁ፤ ያዘዛችሁንም ሁሉ ስለ ፈጸማችሁ’ 19የእስራኤል አምላክ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘ከሬካብ ልጅ ከኢዮናዳብ ወገን የሚያገለግለኝ ሰው ለዘላለም አይታጣም።’ ”
ارميا و طايفه ركابیها
1زمانی كه يهوياقيم (پسر يوشيا) پادشاه يهودا بود، خداوند به من فرمود:
2«نزد طايفهٔ ركابیها برو و ايشان را به خانهٔ خداوند دعوت كن و آنها را به يكی از اتاقهای درونی ببر و به ايشان شراب تعارف كن.»
3پس پيش يازنيا، كه نام پدرش ارميا و نام پدر بزرگش حبصنيا بود، رفتم و او را با همه برادران و پسرانش كه نمايندهٔ طايفهٔ ركابیها بودند، 4به خانهٔ خداوند آوردم و به اتاق پسران حانان نبی (پسر يجدليا) بردم. اين اتاق كنار اتاق مخصوص درباريان و بالای اتاق معسيا (پسر شلوم) نگهبان خانهٔ خدا قرار داشت. 5آنگاه جام و كوزههای شراب مقابل ايشان گذاشتم و تعارف كردم تا بنوشند.
6اما ايشان گفتند: «نه، ما شراب نمینوشيم، چون پدرمان يوناداب (پسر ركاب) وصيت نموده است كه نه ما و نه فرزندانمان، هرگز لب به شراب نزنيم. 7همچنين به ما سفارش كرده است كه نه خانه بسازيم، نه زراعت كنيم؛ نه تاكستان داشته باشيم و نه مزرعه؛ بلكه هميشه چادرنشين باشيم؛ و گفته است اگر اطاعت كنيم، در اين سرزمين عمر طولانی و زندگی خوبی خواهيم داشت. 8ما هم تمام دستورات او را اطاعت كردهايم. از آن زمان تا به حال نه خودمان لب به شراب زدهايم، نه زنان و پسران و دخترانمان! 9ما نه خانه ساختهايم، نه صاحب مزرعه هستيم و نه كشاورزی میكنيم. 10ما در چادرها ساكنيم و دستور پدرمان يوناداب را اطاعت كردهايم. 11اما وقتی نبوكدنصر، پادشاه بابل، به اين سرزمين حمله كرد، ترسيديم و تصميم گرفتيم به اورشليم بياييم و در شهر زندگی كنيم. برای همين است كه اينک در اينجا هستيم.»
12-13پس از اين ماجرا، خداوند به ارميا فرمود كه كلام او را به اهالی يهودا و ساكنين اورشليم اعلام داشته، از جانب او چنين بگويد: «آيا شما نمیخواهيد از ركابیها درس عبرت بگيريد؟ 14آنها دستور جدشان را اطاعت كردهاند و تا به امروز لب به شراب نزدهاند، ولی شما از دستورات من هرگز اطاعت نكردهايد. با اينكه همواره شما را نصيحت نمودم، 15و انبيای خود را نزد شما فرستادم تا بگويند كه از راههای بد بازگرديد و از بتپرستی دست بكشيد تا اجازه دهم در اين سرزمينی كه به شما و پدرانتان بخشيدهام، در صلح و آرامش زندگی كنيد، اما شما گوش نداديد و اطاعت نكرديد. 16ركابیها دستور جدشان يوناداب را به طور كامل اجرا میكنند، ولی شما دستورات مرا اطاعت نمیكنيد. 17هر بار با شما سخن گفتم، توجه نكرديد و هر بار شما را خواندم، جواب نداديد! بنابراين ای اهالی يهودا و ساكنين اورشليم، من تمام بلاهايی را كه گفتهام، بر شما نازل خواهم نمود!»
18-19سپس رو به ركابیها كرده، گفتم: «خداوند قادر متعال، خدای اسرائيل میفرمايد كه چون شما دستور جدتان يوناداب را از هر حيث اطاعت كردهايد، بنابراين از دودمان او هميشه مردانی باقی خواهند بود تا مرا عبادت و خدمت نمايند.»