ኤርምያስ 18 – NASV & CCBT

New Amharic Standard Version

ኤርምያስ 18:1-23

በሸክላ ሠሪው ቤት

1ከእግዚአብሔር ወደ ኤርምያስ እንዲህ የሚል ቃል መጣ፦ 2“ተነሥተህ ወደ ሸክላ ሠሪው ቤት ውረድ፤ በዚያ መልእክቴን እሰጥሃለሁ።” 3እኔም ወደ ሸክላ ሠሪው ቤት ወረድሁ፤ ሸክላውንም በመንኰራኵር ላይ ይሠራ ነበር። 4ከጭቃ ይሠራው የነበረውም ሸክላ በእጁ ላይ ተበላሸ፤ ሸክላ ሠሪውም በሚፈልገው ሌላ ቅርጽ መልሶ አበጀው።

5የእግዚአብሔርም ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ፤ 6“የእስራኤል ቤት ሆይ፤ ሸክላ ሠሪው እንደሚሠራው፣ እኔ በእናንተ ላይ መሥራት አይቻለኝምን?” ይላል እግዚአብሔር፤ “የእስራኤል ቤት ሆይ፤ ጭቃው በሸክላ ሠሪው እጅ እንዳለ፣ እናንተም እንዲሁ በእጄ ውስጥ ናችሁ። 7አንድ ሕዝብ ወይም መንግሥት እንዲነቀል፣ እንዲፈርስና እንዲጠፋ በተናገርሁ ጊዜ፣ 8ያስጠነቀቅሁት ሕዝብ ከክፋቱ ቢመለስ፣ እኔ ላደርስበት ያሰብሁትን ክፉ ነገር እተዋለሁ። 9በሌላም ጊዜ አንድን ሕዝብ ወይም መንግሥት አንጸውና እተክለው ዘንድ ተናግሬ፣ 10በፊቴ ክፉ ነገር ቢያደርግና ባይታዘዘኝ፣ አደርግለታለሁ ብዬ ያሰብሁትን መልካም ነገር አስቀርበታለሁ።

11“አሁንም እንግዲህ ለይሁዳ ሕዝብና በኢየሩሳሌም ለሚኖሩ እንዲህ በላቸው፤ ‘እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “እነሆ፤ ጥፋትን እያዘጋጀሁላችሁ ነው፤ ክፋትንም እየጠነሰስሁላችሁ ነው። ስለዚህ ሁላችሁ ከክፉ መንገዳችሁ ተመለሱ፤ መንገዳችሁንና ተግባራችሁን አቅኑ።” ’ 12እነርሱ ግን፣ ‘በከንቱ አትድከም፤ ባቀድነው እንገፋበታለን፤ እያንዳንዳችንም የክፉ ልባችንን እልኸኝነት እንከተላለን’ ይላሉ።”

13ስለዚህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤

“እስቲ አሕዛብን፣

‘እንዲህ ዐይነት ነገር በመካከላችሁ ተሰምቶ ያውቃል?’ ብላችሁ ጠይቁ።

ድንግሊቱ እስራኤል፣

እጅግ ክፉ ነገር አድርጋለች።

14የሊባኖስ ተራራ ድንጋያማ ተረተር፣

በረዶ ተለይቶት ያውቃልን?

ከጋራው የሚወርደውስ ቀዝቃዛ ውሃ፤

መፍሰሱን ያቋርጣልን?18፥14 በዕብራይስጡ የዚህ ዐረፍተ ነገር ትርጕም በግልጽ አይታወቅም።

15ሕዝቤ ግን ረስቶኛል፤

ለማይረቡ ነገሮች ዐጥኗል፣

በራሱ መንገድ፣

በቀደሞው ጐዳና ተሰናክሏል፤

በሻካራው መሄጃ፣

ባልቀናውም ጥርጊያ መንገድ ሄዷል።

16ምድራቸው ባድማ፣

ለዘላለም መሣለቂያ ይሆናል፤

በዚያ የሚያልፍ ሁሉ ይደነቃል፤

በመገረምም ራሱን ይነቀንቃል።

17ከምሥራቅ እንደሚወጣ ነፋስ፣

በጠላቶቻቸው ፊት እበትናቸዋለሁ፤

በመጥፊያቸው ቀን፣

ጀርባዬን እንጂ ፊቴን አላሳያቸውም።”

18እነርሱም፣ “ሕግ ከካህናት፣ ምክር ከጠቢባን፣ ቃልም ከነቢያት ስለማይታጣ ኑና በኤርምያስ ላይ እንማከር፤ ኑ፤ በአንደበታችን እናጥቃው፣ እርሱ የሚናገረውንም ሁሉ አንስማ” አሉ።

19እግዚአብሔር ሆይ፤ ስማኝ፤

ባላንጣዎቼ የሚሉትን አድምጥ።

20የመልካም ተግባር ወሮታው ክፉ ነውን?

እነርሱ ግን ጕድጓድ ቈፈሩልኝ፤

ቍጣህን ከእነርሱ እንድትመልስ፣

በፊትህ ቆሜ፣

ስለ እነርሱ እንደ ተናገርሁ ዐስብ።

21ስለዚህ ልጆቻቸውን ለራብ፣

ለሰይፍም ስለት አሳልፈህ ስጥ፤

ሚስቶቻቸው የወላድ መካን፣ መበለትም ይሁኑ፤

ወንዶቻቸው በሞት ይቀሠፉ፤

ጕልማሶቻቸው በጦር ሜዳ ለሰይፍ ይዳረጉ።

22ሊይዙኝ ጕድጓድ ስለ ቈፈሩ፣

ለእግሮቼም በስውር ወጥመድ ስለ ዘረጉ፣

በድንገት ወራሪ ስታመጣባቸው፣

ከቤታቸው ጩኸት ይሰማ።

23አንተ ግን እግዚአብሔር ሆይ፤

ሊገድሉኝ ያሤሩብኝን ሤራ ሁሉ ታውቃለህ፤

በደላቸውን ይቅር አትበል፤

ኀጢአታቸውንም ከፊትህ አትደምስስ፤

በፊትህ ወድቀው የተጣሉ ይሁኑ፤

በቍጣህም ጊዜ አትማራቸው።

Chinese Contemporary Bible (Traditional)

耶利米書 18:1-23

陶器的比喻

1耶和華對耶利米說: 2「你去陶匠家,在那裡我有話告訴你。」 3我便到陶匠家,見他正用輪盤做器皿。 4每當他手中的器皿做壞了,他就用那塊泥重做,想怎麼做就怎麼做。 5這時,耶和華對我說: 6以色列人啊,難道我不能像陶匠對待陶泥一樣對待你們嗎?以色列人啊,你們在我手中就像陶泥在陶匠手中一樣。這是耶和華說的。 7當我宣佈要剷除、推翻、毀滅哪一邦或哪一國的時候, 8如果他們悔過自新,我必施憐憫,取消我原本要降給他們的災禍。 9當我宣佈要建造、栽培哪一邦或哪一國的時候, 10如果他們做我視為惡的事,不聽從我的話,我必改變心意,取消我原本要賜給他們的福氣。 11因此,你去告訴猶大人和耶路撒冷的居民,『耶和華說,我正計劃降災禍懲罰你們。你們要離開罪惡,改邪歸正。』 12他們卻說,『不!我們喜歡隨心所欲,為所欲為。』」

13因此耶和華說:

「你們問問列國,

看看誰曾聽過這樣的事?

少女般的以色列竟做了一件極可怕的事。

14黎巴嫩山嶺上的積雪會融化嗎?

從遠方流來的冰涼溪水會停止嗎?

15然而,我的子民卻把我拋諸腦後,

向虛無的神明燒香,

偏離古道,在歧途上絆絆跌跌。

16因此,他們的土地必荒涼,

永遠遭人嗤笑,

經過此地的人無不驚懼,

搖頭歎息。

17我要在敵人面前驅散他們,

就像東風吹散塵土一樣。

在他們遭難的時候,

我必以背相向,

不理睬他們。」

18他們說:「來!我們設計對付耶利米吧,反正我們有祭司教導律法,有智者出謀劃策,有先知傳講預言。來吧!我們抨擊他,不要理會他的話。」

19耶和華啊,求你眷顧我,

聽聽敵人對我的指控。

20人豈能以惡報善?

他們竟設陷阱謀害我,

求你回想我怎樣站在你面前為他們求情,

怎樣求你不要向他們發烈怒。

21因此,願他們喪身刀下,

兒女餓死,

妻子喪夫亡子,

年長的被殺,

年少的死於戰場!

22當你使敵軍突襲他們時,

願他們家中傳出哭喊聲,

因為他們挖陷阱要捕捉我,

設圈套要絆我的腳。

23耶和華啊,你知道他們害我的各種詭計,

求你不要赦免他們的罪過,

不要饒恕他們的惡行。

求你使他們倒在你面前,

求你在烈怒中懲罰他們。