ኢዮብ 32 – NASV & CCBT

New Amharic Standard Version

ኢዮብ 32:1-22

ኤሊሁ

1ኢዮብ በበኩሉ ራሱን እንደ ጻድቅ ቈጥሮ ስለ ነበር፣ እነዚህ ሦስት ሰዎች ለእርሱ መልስ መስጠታቸውን ተዉ። 2ከራም ወገን የሆነው፣ የቡዛዊው የባርክኤል ልጅ ኤሊሁ ግን ኢዮብ ከእግዚአብሔር ይልቅ ራሱን ጻድቅ ስላደረገ እጅግ ተቈጣው። 3ሦስቱ የኢዮብ ጓደኞች በኢዮብ ላይ መፍረድ32፥3 የማሶሬቱ ቅጅ ከዚህ ጋር ይስማማል፤ ጥንታዊው የዕብራውያን ጸሐፍት ትውፊት ግን ኢዮብንም ሆነ እግዚአብሔርን ኰነኑ ይላል። እንጂ፣ ነገሩን ሊያሳምኑት ስላልቻሉ፣ በእነርሱም ላይ ተቈጣ። 4ኤሊሁ፣ ሌሎቹ በዕድሜ ይበልጡት ስለ ነበር ከእነርሱ ቀድሞ ለኢዮብ ሳይናገር ቈየ። 5ነገር ግን እነዚህ ሦስቱ የሚሉትን ባጡ ጊዜ ቍጣው ነደደ።

6ስለዚህ የቡዛዊው የባርክኤል ልጅ ኤሊሁ እንዲህ አለ፤

“እኔ በዕድሜ ታናሽ ነኝ፤

እናንተ ግን አዛውንቶች ናችሁ፤

ከዚህም የተነሣ የማውቀውን ለመናገር አልደፈርሁም፤

ፈርቼ ዝም አልሁ።

7‘ዕድሜ ይናገራል፤

ረዥም ዘመን ጥበብን ያስተምራል’ ብዬ ነበር።

8ነገር ግን በሰው ያለው መንፈስ፣

ሁሉን የሚችል አምላክ እስትንፋስ፣

ማስተዋልን ይሰጣል።

9ጠቢባን የሚሆኑት በዕድሜ የገፉ32፥9 ወይም፣ ብዙ ወይም፣ ታላቅ ብቻ አይደሉም፤

የሚያስተውሉም ሽማግሌዎች ብቻ አይደሉም።

10“ስለዚህ፣ ‘ስሙኝ፣

እኔም የማውቀውን ልንገራችሁ’ እላለሁ።

11እናንተ በምትነጋገሩበት ጊዜ ታገሥሁ፤

ቃላት እየመረጣችሁ ስትናገሩ፣

በጥሞና ሰማኋችሁ፤

12በሙሉ ልብ አደመጥኋችሁ፤

ነገር ግን ከእናንተ የኢዮብን ቃል ያስተባበለ ማንም የለም፤

ለንግግሩም አጸፋ የመለሰ አልተገኘም።

13‘እኛ ጥበብ አግኝተናል፤

ሰው ሳይሆን እግዚአብሔር ይርታው’ አትበሉ።

14ኢዮብ ግን ቃሉን በእኔ ላይ አልሰነዘረም፤

እኔም እንደ እናንተ አነጋገር መልስ አልሰጠውም።

15“እነርሱ ተስፋ ቈርጠው የሚሉት የላቸውም፤

የሚናገሩትም ጠፍቷቸዋል።

16እንግዲህ እነርሱ መልስ ስላጡ፣

ጸጥ ብለውም ስለ ቆሙ፣ በትዕግሥት ልጠብቅን?

17እኔም የምለው ይኖረኛል፤

የማውቀውንም እገልጣለሁ።

18የምናገረው ሞልቶኛልና፤

በውስጤ ያለውም መንፈስ ገፋፍቶኛል።

19ውስጤ እንደ ተከደነና መተንፈሻ እንዳጣ የወይን ጠጅ፣

ሊፈነዳ እንደ ተቃረበም አዲስ የወይን ጠጅ አቁማዳ ሆኗል።

20ተናግሬ መተንፈስ አለብኝ፤

አፌንም ከፍቼ መልስ መስጠት ይገባኛል።

21ለማንም አላደላም፤

ሰውንም አላቈላምጥም።

22ማቈላመጥን ባውቅበትማ ኖሮ፣

ፈጣሪዬ ፈጥኖ ባጠፋኝ ነበር።

Chinese Contemporary Bible (Traditional)

約伯記 32:1-22

以利戶的回答

1三人見約伯自以為義,便不再回答他。 2那時,族的布西巴拉迦的兒子以利戶約伯很惱火,因為約伯自以為義,不承認上帝的公義。 3他對約伯的三個朋友也很惱火,因為他們說約伯有罪,卻無法回答約伯的質問32·3 因為他們說約伯有罪,卻無法回答約伯的質問」有古卷作「因為他們無法回答約伯的質問,因而置上帝於不公」。4由於不及他們年長,以利戶便等他們說完才向約伯發言。 5他見三人無法回答約伯,很惱火, 6就說:

「我年紀輕,你們是長輩,

所以我畏懼,不敢陳明觀點。

7我想,前輩當先發言,

長者當傳授智慧。

8但只有人裡面的靈——

全能者的氣息賜人悟性。

9長者不一定有智慧,

年老不一定明白是非。

10因此,請聽我說,

我也要陳明觀點。

11看啊,我一直等候你們發言,

傾聽你們的理論,

等你們斟詞酌句。

12我仔細聆聽,

發現你們無人能駁倒約伯

無人能答覆他。

13你們不要說,『我們找到了智慧,

使他折服的是上帝而非人。』

14約伯沒有與我辯論,

我也不會用你們的理論答覆他。

15「他們驚慌失措,無言以對,

再也說不出話來。

16難道他們不說話,站在那裡無言以對,

我就要等下去嗎?

17我也要作出答覆,

陳明我的觀點。

18因為我心裡積滿了話,

我裡面的靈催促我說出來。

19我裡面像盛滿了酒,卻沒有出口,

又如將要破裂的新酒袋。

20我要一吐為快,

我要開口答覆。

21我不看人的情面,

也不奉承人。

22我不善奉承,

否則,造物主會很快把我除掉。