ኢሳይያስ 53 – NASV & CCBT

New Amharic Standard Version

ኢሳይያስ 53:1-12

1የሰማነውን ነገር ማን አመነ?

የእግዚአብሔርስ ክንድ ለማን ተገለጠ?

2በፊቱ እንደ ቡቃያ፣

ከደረቅም መሬት እንደ ወጣ ሥር በቀለ፤

የሚስብ ውበት ወይም ግርማ የለውም፤

እንድንወድደውም የሚያደርግ መልክ አልነበረውም።

3በሰዎች የተናቀና የተጠላ፣

የሕማም ሰውና ሥቃይ ያልተለየው ነበር።

ሰዎች ፊታቸውን እንደሚያዞሩበት ዐይነት፣

የተናቀ ነበር፤ እኛም አላከበርነውም።

4በርግጥ እርሱ ደዌያችንን ወሰደ፤

ሕመማችንንም ተሸከመ፤

እኛ ግን በእግዚአብሔር እንደ ተመታ፣

እንደ ተቀሠፈ፣ እንደ ተሠቃየም ቈጠርነው።

5ነገር ግን እርሱ ስለ መተላለፋችን ተወጋ፤

ስለ በደላችንም ደቀቀ፤

በእርሱ ላይ የወደቀው ቅጣት ለእኛ ሰላም አመጣልን፤

በእርሱም ቍስል እኛ ተፈወስን።

6እኛ ሁላችን እንደ በጎች ተቅበዝብዘን ጠፋን፤

እያንዳንዳችንም በየመንገዳችን ነጐድን፤

እግዚአብሔርም፣ የሁላችንን በደል

በእርሱ ላይ ጫነው።

7ተጨነቀ፤ ተሠቃየም፤

ነገር ግን አፉን አልከፈተም፤

እንደ ጠቦትም ለዕርድ ተነዳ፤

በሸላቾች ፊት ዝም እንደሚል በግ፣

አፉን አልከፈተም።

8በማስጨነቅና53፥8 ወይም፣ በእስር በፍርድ ተወሰደ፤

ስለ ሕዝቤ ኀጢአት ተመትቶ፣

ከሕያዋን ምድር እንደ ተወገደ፣

ከትውልዱ ማን አስተዋለ?

9በአፉ ተንኰል ሳይገኝበት፣

ምንም ወንጀል ሳይሠራ፣

አሟሟቱ ከክፉዎች፣

መቃብሩም ከባለጠጎች ጋር ሆነ።

10መድቀቁና መሠቃየቱ ግን የእግዚአብሔር ፈቃድ ነበር፤

እግዚአብሔር ነፍሱን የኀጢአት መሥዋዕት ቢያደርገውም እንኳ፣

ዘሩን ያያል፤ ዕድሜውም ይረዝማል፤

የእግዚአብሔርም ፈቃድ በእጁ ይከናወናል።

11ከነፍሱ ሥቃይ በኋላ፣

የሕይወት ብርሃን53፥11 የሙት ባሕር ጥቅሎች (እንዲሁም የሰብዓ ሊቃናት ትርጕምን ይመ) ከዚህ ጋር ይስማማሉ፤ የማሶሬቱ ቅጅ ግን፣ የሕይወት ብርሃን የሚለውን ሐረግ አይጨምርም። ያያል፤ ደስም ይለዋል፤

ጻድቅ ባሪያዬ በዕውቀቱ ብዙዎቹን ያጸድቃል፤

መተላለፋቸውንም ይሸከማል።

12ስለዚህ ድርሻውን ከታላላቆች53፥12 ወይም፣ ከብዙዎች ጋር ጋር እሰጠዋለሁ፤

ምርኮውን ከኀያላን53፥12 ወይም፣ እጅግ ብዙ ከሆኑ ጋር ጋር ይካፈላል፤

እስከ ሞት ድረስ ሕይወቱን አሳልፎ በመስጠቱ፣

ከክፉ አድራጊዎችም ጋር በመቈጠሩ፣

የብዙዎችን ኀጢአት ተሸከመ፤

ስለ ዐመፀኞችም ማለደ።

Chinese Contemporary Bible (Traditional)

以賽亞書 53:1-12

受苦的僕人

1誰相信我們所傳的呢?

耶和華的大能向誰彰顯過呢?

2祂像嫩芽一樣在耶和華面前長大,

像生長在旱地裡的根。

祂沒有軒昂俊美的外表可以吸引我們,

沒有令我們羡慕的容貌。

3祂被藐視,遭人厭棄,

飽受痛苦,歷盡憂患。

人們對祂不屑一顧,

我們也不尊重祂。

4其實祂擔當了我們的憂患,

背負了我們的痛苦。

我們卻以為是上帝責罰、

擊打、苦待祂。

5誰知祂是因我們的過犯而被刺透,

因我們的罪惡而被壓傷。

我們因祂所受的刑罰而得到平安,

因祂所受的鞭傷而得到醫治。

6我們都像迷路的羊,

各人偏行己路,

但上帝卻讓祂承擔我們眾人的罪惡。

7祂遭欺壓、受痛苦,

卻默然不語,

像被人牽去宰殺的羔羊,

又如在剪毛人手下一聲不吭的綿羊。

8祂被逮捕,受審判,被處死。

祂那個世代的人誰會想到祂受鞭打、

從世上被除去是因為我百姓的過犯呢?

9雖然祂沒有做過殘暴之事,

口中也沒有詭詐,

人卻將祂與惡人同葬,

祂死後葬在富人的墓穴。

10然而,祂被壓傷、

受痛苦是耶和華的旨意;

祂的性命作了贖罪祭53·10 祂的性命作了贖罪祭」或譯「耶和華以祂的性命作贖罪祭」。

祂必看見自己的後裔,

祂必長久活著。

耶和華的旨意必在祂手中實現。

11祂必看見自己勞苦的成果,

並心滿意足。

耶和華說:「我公義的僕人必憑祂的知識使許多人被算為義人,

祂要擔當他們的罪惡。

12我要使祂與偉人同享尊榮,

跟強者同分戰利品,

因為祂奉獻了自己的生命。

祂被列在罪犯中,

卻擔當了許多人的罪,

又為罪人代求。」