ኢሳይያስ 28 – NASV & NIV

New Amharic Standard Version

ኢሳይያስ 28:1-29

ወዮ ለኤፍሬም

1ለኤፍሬም ሰካራሞች የመታበያ አክሊል ለሆነች፣

በለመለመ ሸለቆ ዐናት ላይ ጕብ ብላ፣

የክብሩ ውበት ለሆነች ጠውላጋ አበባ፣

የወይን ጠጅ ለዘራቸው መኵራሪያ ለሆነች፣

ለዚያች ከተማ ወዮላት!

2እነሆ፤ ጌታ ኀያልና ብርቱ የሆነ ነገር አለው፤

ይህም እንደ በረዶ ወጀብ፣ እንደሚያጠፋ ዐውሎ ነፋስ፣

እንደ ኀይለኛ ማዕበል፣ እንደ ከባድ ዝናብ፣

በኀይል ወደ ምድር ይጥላታል።

3የኤፍሬም ሰካራሞች የመታበያ አክሊል፣

በእግር ይረገጣል።

4በለምለሙ ሸለቆ ዐናት ላይ ጕብ ብላ፣

የክብሩ ውበት የሆነች ጠውላጋ አበባ፣

ከመከር በፊት እንደ ደረሰች፣

ሰውም ድንገት አይቶ እንደሚቀጥፋት

ወዲያውኑም እንደሚውጣት በለስ ትሆናለች።

5በዚያን ቀን የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር

ለተረፈው ሕዝቡ፣

የክብር ዘውድ፣

የውበትም አክሊል ይሆናል።

6እርሱም በፍርድ ወንበር ላይ ለሚቀመጠው፣

የፍትሕ መንፈስ፣

ጦርን ከከተማዪቱ በር ላይ ለሚመልሱም፣

የኀይል ምንጭ ይሆናል።

7እነዚህም በወይን ጠጅ ይንገዳገዳሉ፤

በሚያሰክርም መጠጥ ይወላገዳሉ፤

ካህናቱና ነቢያቱ በሚያሰክር መጠጥ ተንገዳገዱ፤

በወይን ጠጅ ነገር ተምታታባቸው፤

በሚያሰክር መጠጥ ተወላገዱ፤

ራእይ ሲያዩ ይስታሉ፤

ፍርድ ሲሰጡም ይሰናከላሉ።

8የማእድ ገበታቸው ሁሉ በትፋት ተሞልቷል፤

ከትውኪያም የጸዳ ቦታ የለም።

9እነርሱም እንዲህ ይላሉ፤ “የሚያስተምረው ማንን ነው?

መልእክቱን የሚያብራራውስ ለማን ነው?

ወተት ለተዉት ሕፃናት?

ወይስ ጡት ለጣሉት?

10በትእዛዝ ላይ ትእዛዝ፣ በትእዛዝ ላይ

ትእዛዝ፤

በደንብ ላይ ደንብ፣ በደንብ ላይ ደንብ፤28፥10 በዚህና በቍጥር 13 ላይ ዕብራይስጡ፣ ላቨ ላሳቨ ሳቨ ላሳቨ፣ ካቨ ላካቨ ካቨ ለካቨ ይላል፤ ምናልባት ትርጕም የለሽ ንግግርን ለማሳየት ይሆናል፤ ይኸውም የነቢያትን ቃል አስመስሎ መናገርን ሊሆን ይችላል።

እዚህ ጥቂት፣ እዚያ ጥቂት ነውና።”

11እንግዲያማ እግዚአብሔር

በባዕድ ልሳን በእንግዳ ቋንቋ ለዚህ ሕዝብ ይናገራል።

12እርሱ፣

“ይህች የዕረፍት ቦታ ናት፤ የደከመው ይረፍ፤

ይህች የእፎይታ ቦታ ናት” ያለው ለማን ነበር?

እነርሱ ግን መስማት አልፈለጉም።

13ስለዚህ የእግዚአብሔር ቃል፣

በትእዛዝ ላይ ትእዛዝ፣ በትእዛዝ ላይ ትእዛዝ፤

በደንብ ላይ ደንብ፣ በደንብ ላይ ደንብ፤

እዚህ ጥቂት እዚያ ጥቂት ይሆንባቸዋል።

ይህ የሚሆንባቸው ሄደው ወደ ኋላ እንዲወድቁ፣

እንዲቈስሉና በወጥመድ እንዲያዙ፣

እንዲማረኩም ነው።

14ስለዚህ በኢየሩሳሌም ያለውን ሕዝብ የምትገዙ፣

እናንት ፌዘኞች የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ።

15እናንት፣ “ከሞት ጋር ቃል ኪዳን ገብተናል፤

ከሲኦልም ጋር ስምምነት አድርገናል፤

ውሸትን መጠጊያችን፣

ሐሰትን28፥15 ወይም፣ ሐሰተኛ ጣዖታትን መደበቂያችን አድርገናል፤

ታላቅ መቅሠፍት እየጠራረገ ሲያልፍ፣

ሊነካን አይችልም” በማለት ታብያችኋል።

16ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤

“እነሆ፤ የተፈተነ ድንጋይ፣ የመሠረት ድንጋይ፣

ለጽኑ መሠረት የሚሆን የከበረ የማእዘን ድንጋይ፣

በጽዮን አስቀምጣለሁ፤

በእርሱም የሚያምን አያፍርም።

17ፍትሕን የመለኪያ ገመድ፣

ጽድቅንም ቱንቢ አደርጋለሁ፤

ውሸት መጠጊያችሁን የበረዶ ዝናብ ይጠራርገዋል፤

መደበቂያችሁንም ውሃ ያጥለቀልቀዋል።

18ከሞት ጋር የገባችሁት ቃል ኪዳን ይሻራል፤

ከሲኦልም ጋር ያደረጋችሁት ስምምነት ይፈርሳል፤

ታላቁ መቅሠፍት እየጠራረገ ሲያልፍ፣

እናንተም ትጠራረጋላችሁ።

19በመጣ ቍጥር ይዟችሁ ይሄዳል፤

ማለዳ ማለዳ፣ በቀንና በሌሊትም

ይጠራርጋል።”

ይህን ቃል ብታስተውሉ፣

ሽብር በሽብር በሆነ ነበር።

20እግር ዘርግቶ እንዳይተኛ ዐልጋው ዐጭር ነው፤

ሰውነትንም ለመሸፋፈን ብርድ ልብሱ ጠባብ ነው።

21እግዚአብሔር ሥራውን፣ አዎን ድንቅ ሥራውን ሊሠራ፣

ተግባሩን፣ እንግዳ የሆነ ተግባሩን ሊያከናውን፣

በፐራሲም ተራራ እንዳደረገው ይነሣል፣

በገባዖን ሸለቆ እንዳደረገው ይነሣሣል።

22እንግዲህ ፌዛችሁን አቁሙ፤

አለዚያ እስራታችሁ ይጸናባችኋል፤

ጌታ፣ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር

መላውን ምድር ለማጥፋት ያወጀውን ዐዋጅ ሰምቻለሁ።

23አድምጡ ድምፄን ስሙ፤

አስተውሉ ቃሌንም ስሙ።

24ገበሬ ሊዘራ መሬቱን ሲያዘጋጅ ያለ ማቋረጥ ያርሳልን?

ጓሉን ሲከሰክስ፣ ዐፈሩን ሲያለሰልስ ይከርማልን?

25ዕርሻውን አስተካክሎ፣

ጥቍር አዝሙድና ከሙን አይዘራምን?

ስንዴውንስ በትልሙ28፥25 በዕብራይስጡ የዚህ ቃል ትርጕም በትክክል አይታወቅም።

ገብሱን በተገቢ ቦታው፣

አጃውንም በተመደበው ስፍራ አይዘራምን?

26አምላኩ ያስተምረዋል፤

ትክክለኛውንም መንገድ ያሳየዋል።

27ጥቍር አዝሙድ በመውቂያ መሣሪያ አይወቃም፤

ከሙን የሠረገላ መንኰራኵር አይሄድበትም፤

ጥቍር አዝሙድ በበትር፣

ከሙንም በዘንግ ይወቃል።

28እንጀራን ለመጋገር እህል ይፈጫል፤

ስለዚህ አንድ ሰው ለዘላለም እህል ሲወቃ አይኖርም።

የመውቂያውን መንኰራኵር ቢያኼድበትም፣

ፈረሶቹ አይደፈጥጡትም።

29ይህ ሁሉ የሚሆነው በምክሩ ድንቅ፣ በጥበቡ

ታላቅ ከሆነው፣

ከሰራዊት ጌታ ከእግዚአብሔር ዘንድ ነው።

New International Version

Isaiah 28:1-29

Woe to the Leaders of Ephraim and Judah

1Woe to that wreath, the pride of Ephraim’s drunkards,

to the fading flower, his glorious beauty,

set on the head of a fertile valley—

to that city, the pride of those laid low by wine!

2See, the Lord has one who is powerful and strong.

Like a hailstorm and a destructive wind,

like a driving rain and a flooding downpour,

he will throw it forcefully to the ground.

3That wreath, the pride of Ephraim’s drunkards,

will be trampled underfoot.

4That fading flower, his glorious beauty,

set on the head of a fertile valley,

will be like figs ripe before harvest—

as soon as people see them and take them in hand,

they swallow them.

5In that day the Lord Almighty

will be a glorious crown,

a beautiful wreath

for the remnant of his people.

6He will be a spirit of justice

to the one who sits in judgment,

a source of strength

to those who turn back the battle at the gate.

7And these also stagger from wine

and reel from beer:

Priests and prophets stagger from beer

and are befuddled with wine;

they reel from beer,

they stagger when seeing visions,

they stumble when rendering decisions.

8All the tables are covered with vomit

and there is not a spot without filth.

9“Who is it he is trying to teach?

To whom is he explaining his message?

To children weaned from their milk,

to those just taken from the breast?

10For it is:

Do this, do that,

a rule for this, a rule for that28:10 Hebrew / sav lasav sav lasav / kav lakav kav lakav (probably meaningless sounds mimicking the prophet’s words); also in verse 13;

a little here, a little there.”

11Very well then, with foreign lips and strange tongues

God will speak to this people,

12to whom he said,

“This is the resting place, let the weary rest”;

and, “This is the place of repose”—

but they would not listen.

13So then, the word of the Lord to them will become:

Do this, do that,

a rule for this, a rule for that;

a little here, a little there—

so that as they go they will fall backward;

they will be injured and snared and captured.

14Therefore hear the word of the Lord, you scoffers

who rule this people in Jerusalem.

15You boast, “We have entered into a covenant with death,

with the realm of the dead we have made an agreement.

When an overwhelming scourge sweeps by,

it cannot touch us,

for we have made a lie our refuge

and falsehood28:15 Or false gods our hiding place.”

16So this is what the Sovereign Lord says:

“See, I lay a stone in Zion, a tested stone,

a precious cornerstone for a sure foundation;

the one who relies on it

will never be stricken with panic.

17I will make justice the measuring line

and righteousness the plumb line;

hail will sweep away your refuge, the lie,

and water will overflow your hiding place.

18Your covenant with death will be annulled;

your agreement with the realm of the dead will not stand.

When the overwhelming scourge sweeps by,

you will be beaten down by it.

19As often as it comes it will carry you away;

morning after morning, by day and by night,

it will sweep through.”

The understanding of this message

will bring sheer terror.

20The bed is too short to stretch out on,

the blanket too narrow to wrap around you.

21The Lord will rise up as he did at Mount Perazim,

he will rouse himself as in the Valley of Gibeon—

to do his work, his strange work,

and perform his task, his alien task.

22Now stop your mocking,

or your chains will become heavier;

the Lord, the Lord Almighty, has told me

of the destruction decreed against the whole land.

23Listen and hear my voice;

pay attention and hear what I say.

24When a farmer plows for planting, does he plow continually?

Does he keep on breaking up and working the soil?

25When he has leveled the surface,

does he not sow caraway and scatter cumin?

Does he not plant wheat in its place,28:25 The meaning of the Hebrew for this word is uncertain.

barley in its plot,28:25 The meaning of the Hebrew for this word is uncertain.

and spelt in its field?

26His God instructs him

and teaches him the right way.

27Caraway is not threshed with a sledge,

nor is the wheel of a cart rolled over cumin;

caraway is beaten out with a rod,

and cumin with a stick.

28Grain must be ground to make bread;

so one does not go on threshing it forever.

The wheels of a threshing cart may be rolled over it,

but one does not use horses to grind grain.

29All this also comes from the Lord Almighty,

whose plan is wonderful,

whose wisdom is magnificent.