ማርቆስ 3 – NASV & CCBT

New Amharic Standard Version

ማርቆስ 3:1-35

1በሌላ ጊዜ ወደ ምኵራብ ገባ፤ በዚያም እጁ የሰለለች ሰው ነበር። 2በምክንያት ሊከስሱት የሚፈልጉ ሰዎችም በሰንበት ቀን ይፈውሰው እንደ ሆነ ለማየት ይጠባበቁ ነበር። 3እርሱም እጁ የሰለለችውን ሰው፣ “በተሰበሰበው ሕዝብ ፊት ተነሥተህ ቁም” አለው።

4ኢየሱስም፣ “በሰንበት ቀን የተፈቀደው መልካም ማድረግ ነው ወይስ ክፉ? ሕይወት ማዳን ነውን ወይስ ማጥፋት?” አላቸው። እነርሱ ግን ዝም አሉ።

5በልባቸው ደንዳናነት ዐዝኖ በዙሪያው የቆሙትን በቍጣ ተመለከታቸውና ሰውየውን፣ “እጅህን ዘርጋ!” አለው፤ ሰውየውም እጁን ዘረጋ፤ እጁም ፍጹም ደኅና ሆነችለት።

6ፈሪሳውያንም እንዴት ሊያጠፉት እንደሚችሉ ከሄሮድስ ወገን ከሆኑት ጋር መመካከር ጀመሩ።

ብዙ ሰዎች ኢየሱስን ተከተሉ

3፥7-12 ተጓ ምብ – ማቴ 12፥1516ሉቃ 6፥17-19

7ኢየሱስ ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ወደ ባሕሩ ሄደ፤ ከገሊላ የመጣ እጅግ ብዙ ሕዝብም ተከተለው፤ 8የሚሠራውን ነገር የሰሙ ሰዎችም ከይሁዳ፣ ከኢየሩሳሌም፣ ከኤዶምያስ፣ በዮርዳኖስ ማዶ ካለው አገር እንዲሁም ከጢሮስና ከሲዶና አካባቢ ወደ እርሱ መጡ። 9የተሰበሰበውም ሕዝብ እንዳያጨናንቀው አነስተኛ የሆነ ጀልባ እንዲያዘጋጁለት ደቀ መዛሙርቱን አዘዛቸው። 10ብዙዎችን ፈውሶ ስለ ነበር፣ በሕመም የሚሠቃዩ ሁሉ ሊዳስሱት ይሽቀዳደሙ ነበር። 11ርኩሳን3፥11 ወይም ክፉ፤ እንዲሁም 30 ይመ መናፍስትም ባዩት ቍጥር ከፊቱ እየወደቁ፣ “አንተ የእግዚአብሔር ልጅ ነህ!” በማለት ይጮኹ ነበር። 12እርሱ ግን ማንነቱን እንዳይገልጹ አጥብቆ ይገሥጻቸው ነበር።

የዐሥራ ሁለቱ ሐዋርያት መሾም

3፥16-19 ተጓ ምብ – ማቴ 10፥2-4ሉቃ 6፥14-16ሐሥ 1፥13

13ኢየሱስ ወደ ተራራ ወጥቶ የሚፈልጋቸውን ወደ እርሱ እንዲመጡ ጠራቸው፤ እነርሱም ወደ እርሱ መጡ። 14ከእርሱ ጋር እንዲሆኑ፣ ለስብከትም ይልካቸው ዘንድ ዐሥራ ሁለቱን ሾማቸው፤ ሐዋርያትም ብሎ ጠራቸው3፥14 አንዳንድ ቅጆች ሐዋርያትም ብሎ ጠራቸው የሚለው ሐረግ የላቸውም።15አጋንንትን እንዲያስወጡም ሥልጣን ሰጣቸው። 16የሾማቸውም ዐሥራ ሁለቱ እነዚህ ናቸው፤ ጴጥሮስ ብሎ የጠራው ስምዖን፣ 17ቦአኔርጌስ ይኸውም፣ “የነጐድጓድ ልጆች” ብሎ የጠራቸው የዘብዴዎስ ልጆች ያዕቆብና ወንድሙ ዮሐንስ፤ 18እንድርያስ፣ ፊልጶስ፣ በርተሎሜዎስ፣ ማቴዎስ፣ ቶማስ፣ የእልፍዮስ ልጅ ያዕቆብ፣ ታዴዎስ፣ ተቀናቃኙ ስምዖን፣ 19እንዲሁም አሳልፎ የሰጠው የአስቆሮቱ ይሁዳ።

ኢየሱስና ብዔልዜቡል

3፥23-27 ተጓ ምብ – ማቴ 12፥25-29ሉቃ 11፥17-22

20ከዚያም ኢየሱስ ወደ አንድ ቤት ገባ፤ እርሱና ደቀ መዛሙርቱ ምግብ መብላት እንኳ እስኪሳናቸው ድረስ ሕዝቡ እንደ ገና በብዛት ተሰበሰበ። 21ሁኔታውን የሰሙ ዘመዶቹም፣ “አእምሮውን ስቷል” በማለት ይዘውት ለመሄድ ወዳለበት መጡ።

22ከኢየሩሳሌም የመጡ ጸሐፍትም፣ “ብዔልዜቡል3፥22 ግሪኩ ብዔዜቡል ወይም ብዔልዜቡል ይላል። ዐድሮበታል፤ አጋንንትን የሚያወጣው በአጋንንት አለቃ ነው” አሉ።

23እርሱም ጠራቸውና በምሳሌ እንዲህ አላቸው፤ “ሰይጣን ሰይጣንን እንዴት ሊያስወጣ ይችላል? 24እርስ በርሱ የሚከፋፈል መንግሥት ሊጸና አይችልም፤ 25ቤትም እርስ በርሱ ከተለያየ ሊቆም አይችልም። 26እንደዚሁም ሰይጣን እርስ በርሱ የሚፃረርና የሚከፋፈል ከሆነ ሊቆም አይችልም፤ ያበቃለታል። 27ከዚህም የተነሣ አንድ ሰው አስቀድሞ ኀይለኛውን ሰው ሳያስር ወደ ኀይለኛው ሰው ቤት ሊገባና ንብረቱን ሊዘርፍ አይችልም፤ ቤቱን መዝረፍ የሚቻለው ኀይለኛውን ሰው ሲያስር ብቻ ነው። 28እውነት እላችኋለሁ፤ የሰው ልጆች ኀጢአትና የሚሳደቡት ስድብ ሁሉ ይሰረይላቸዋል፤ 29ነገር ግን በመንፈስ ቅዱስ ላይ የስድብ ቃል የሚናገር ሁሉ የዘላለም ኀጢአት ዕዳ ይሆንበታል እንጂ ለዘላለም አይሰረይለትም።”

30ይህንም ያለው፣ “ርኩስ መንፈስ አለበት” ስላሉት ነበር።

የኢየሱስ እናትና ወንድሞቹ

3፥31-35 ተጓ ምብ – ማቴ 12፥46-50ሉቃ 8፥19-21

31ከዚህ በኋላ እናቱና ወንድሞቹ መጡ፤ በውጭ ቆመውም ሰው ልከውበት አስጠሩት። 32በዙሪያው የተቀመጡ ብዙ ሰዎችም፣ “እነሆ፤ እናትህና ወንድሞችህ ውጭ ይፈልጉሃል” አሉት።

33እርሱም መልሶ፣ “እናቴ ማን ናት፣ ወንድሞቼስ እነማን ናቸው?” አላቸው።

34በዙሪያው ወደ ተቀመጡትም በመመልከት፣ እንዲህ አለ፤ “እናቴና ወንድሞቼ እነዚህ ናቸው! 35የእግዚአብሔርን ፈቃድ የሚያደርግ ሁሉ እርሱ ወንድሜ፣ እኅቴ፣ እናቴም ነውና።”

Chinese Contemporary Bible (Traditional)

馬可福音 3:1-35

治好手枯的人

1耶穌又進了會堂,那裡有個人一隻手是萎縮的。 2當時有好些人密切地監視耶穌,看祂是否會在安息日醫治這個人,好找藉口控告祂。

3耶穌對那一隻手萎縮的人說:「起來,站在中間。」 4然後問眾人:「在安息日應該行善還是作惡?救人還是害人?」他們都不吭聲。

5耶穌生氣地看著四周這些人,為他們的心剛硬而感到極其難過。祂對那人說:「把手伸出來!」那人一伸手,手就立刻復原了。 6法利賽人離開後,立刻和希律黨的人策劃怎樣除掉耶穌。

群眾跟隨耶穌

7耶穌和門徒退到湖邊,有一大群人從加利利來跟隨祂。 8還有很多人聽見耶穌所做的一切,就從猶太耶路撒冷以土買約旦河東,甚至泰爾西頓一帶來找祂。 9耶穌見人多,就吩咐門徒為祂預備一條小船,以免人群擁擠祂。 10因為祂醫好了很多人,凡有疾病的人都想擠過來摸祂。 11每當污鬼看見祂,就俯伏在祂面前,大喊:「你是上帝的兒子!」 12耶穌卻嚴厲地吩咐牠們不要洩露祂的身分。

選立十二使徒

13耶穌上了山,把合自己心意的人召集到跟前, 14從中選出十二個人,設立他們為使徒,讓他們跟隨自己,並且差遣他們出去傳道, 15賜他們趕鬼的權柄。

16這十二位使徒是:西門——耶穌給他取名叫彼得17西庇太的兒子雅各雅各的兄弟約翰——耶穌給他們取名叫「半尼其」,就是「雷霆之子」的意思、 18安得烈腓力巴多羅買馬太多馬亞勒腓的兒子雅各達太、激進黨人西門19及後來出賣耶穌的加略猶大

耶穌和別西卜

20耶穌剛進家門,人群又聚集起來,以致祂和門徒連吃飯的時間也沒有。 21祂的親屬聽見這個消息,就出來要拉住祂,因為人們說祂瘋了。

22耶路撒冷下來的律法教師說:「祂被別西卜附體。」又說:「祂是靠鬼王趕鬼。」

23耶穌叫他們來,用比喻對他們說:「撒旦怎能驅逐撒旦呢? 24一個國內部自相紛爭,必然崩潰。 25一個家內部自相紛爭,必然破裂。 26同樣,撒旦如果與自己為敵,自相紛爭,就站立不住,必然滅亡。 27沒有人能進入壯漢家裡搶奪他的財物,除非先把那壯漢捆綁起來,才有可能搶劫他的家。

28「我實在告訴你們,世人一切的罪和褻瀆的話都可以得到赦免, 29唯有褻瀆聖靈的人永遠得不到赦免,他們要永遠擔罪。」 30耶穌這樣說是因為他們誣衊祂被污鬼附身。

誰是耶穌的親人

31這時候,耶穌的母親和兄弟來了,他們站在外面,託人叫耶穌。 32有許多人圍坐在耶穌身邊,他們告訴祂說:「看啊!你的母親和兄弟在外面找你。」

33耶穌說:「誰是我的母親?誰是我的弟兄?」 34然後祂望著周圍坐著的人說:「看啊!我的母親、我的弟兄在這裡。 35凡遵行上帝旨意的人就是我的弟兄、姊妹和母親。」