መዝሙር 83 – NASV & JCB

New Amharic Standard Version

መዝሙር 83:1-18

መዝሙር 83

በእስራኤል ጠላቶች ላይ የቀረበ ጸሎት

የአሳፍ መዝሙር፤ ማሕሌት።

1አምላክ ሆይ፤ ዝም አትበል፤

አምላክ ሆይ፤ ጸጥ አትበል፤ ቸል አትበል።

2ጠላቶችህ እንዴት እንደ ተነሣሡ፣

ባላንጣዎችህም እንዴት ራሳቸውን ቀና ቀና እንዳደረጉ ተመልከት።

3በሕዝብህ ላይ በተንኰል አሤሩ፤

በውድ ልጆችህ ላይ በአንድነት ተመካከሩ።

4“የእስራኤል ስም ከእንግዲህ እንዳይታወስ፣

ኑና ሕዝብ እንዳይሆኑ እንደምስሳቸው” አሉ።

5በአንድ ሐሳብ ተስማምተው ተማከሩ፤

በአንተም ላይ ተማማሉ፤

6የኤዶምና የእስማኤላውያን ድንኳኖች፣

የሞዓብና የአጋራውያን ድንኳኖች፣

7ጌባል፣83፥7 ቢብሎስ ለማለት ነው። አሞንና አማሌቅ፣

ፍልስጥኤምም ከጢሮስ ሕዝብ ጋር ሆነው ዶለቱ፤

8አሦርም ከእነርሱ ጋር ተባበረ፤

የሎጥ ልጆችም ረዳት ሆነ። ሴላ

9በምድያም ላይ እንዳደረግኸው አድርግባቸው፤

በቂሶንም ወንዝ በሲሣራና በኢያቢስ ላይ ያደረስኸው ይድረስባቸው።

10እነርሱም በዐይንዶር ጠፉ፤

እንደ ምድርም ጕድፍ ሆኑ።

11መኳንንታቸውን እንደ ሔሬብና እንደ ዜብ፣

መሳፍንታቸውንም ሁሉ እንደ ዛብሄልና እንደ ስልማና አድርጋቸው፤

12እነዚህም፣ “የእግዚአብሔርን የግጦሽ ቦታ፣

ወስደን የግላችን እናድርግ” የሚሉ ናቸው።

13አምላኬ ሆይ፤ በዐውሎ ነፋስ እንደሚነዳ ትቢያ፣

በነፋስም ፊት እንዳለ ገለባ አድርጋቸው።

14እሳት ደንን እንደሚያጋይ፣

ነበልባልም ተራራን እንደሚያቃጥል፣

15እንዲሁ በሞገድህ አሳድዳቸው፤

በማዕበልህም አስደንግጣቸው።

16እግዚአብሔር ሆይ፤ ስምህን ይሹ ዘንድ፣

ፊታቸውን በዕፍረት ሙላው፤

17ለዘላለም ይፈሩ፤ ይታወኩም፤

በውርደትም ይጥፉ።

18ስምህ እግዚአብሔር የሆነው አንተ ብቻ፣

በምድር ሁሉ ላይ ልዑል እንደ ሆንህ ይወቁ።

Japanese Contemporary Bible

詩篇 83:1-18

83

1ああ神よ、私たちが祈っているのに、じっと黙って、

何もしないでいることがありませんように。

祈りに答え、救い出してください。

2あの、敵の興奮して騒ぎ立てる声が、

御耳に入らないのですか。

主を憎む者どもの目に余る行為が、

御目に留まらないのですか。

3彼らは悪知恵を働かせて策略を練り、

あなたにとってかけがえのない人たちを

殺そうとしています。

4「さあ、イスラエルを抹殺しよう。

そんな国があったという

痕跡さえ残らないようにするのだ。」

5これが、彼らの首領たちの

一致した意見でした。

全能の神を敵に回して、彼らは同盟を結んだのです。

6こうして、イシュマエル人、エドム人、

モアブ人、ハガル人、

7ゲバル、アモン、アマレク、

ペリシテ、ツロの住民たち、

8それにアッシリヤも加わって、

このロトの子孫たちとの連合軍ができました。

9どうか彼らを、あのミデヤンと

同じような目に会わせてください。

もしくは、キション川でのシセラやヤビンと

同じ敗北を、なめさせてください。

10また、朽ちた死体が土地の肥やしとなった

エン・ドルでの敵のようにしてください。

11権力者の貴族たちには、

オレブとゼエブのような死に方をさせてください

(士師7・25参照)。

また高官たちも、

ゼバフとツァルムナのように葬り去ってください

(士師8・21参照)。

12この二人は、「神の牧場をそっくり頂いて、

われわれのものにしよう」と企んだ連中です。

13ああ神よ、砂ぼこりやもみがらのように、

彼らを吹き飛ばしてください。

14森林をなめ尽くす山火事のように襲ってください。

15猛烈な嵐や竜巻で、追い払ってください。

16ああ主よ、彼らがあなたの力と御名を

認めるようになるまで、

徹底的に恥をかかせてください。

17彼らがしようとすることを、

すべて失敗に終わらせてください。

そうして深く恥じ入り、おじけづき、

18ついには、全地を支配する神が

あなたおひとりであることを、

思い知るようにしてください。