መዝሙር 62 – NASV & CCBT

New Amharic Standard Version

መዝሙር 62:1-12

መዝሙር 62

ተስፋ በእግዚአብሔር ላይ ብቻ

ለመዘምራን አለቃ፤ ለኤዶታም፤ የዳዊት መዝሙር።

1ነፍሴ ዕረፍት የምታገኘው በእግዚአብሔር ብቻ ነው፤

ድነቴም የሚመጣልኝ ከእርሱ ዘንድ ነው።

2ዐለቴና መድኀኒቴ እርሱ ብቻ ነው፤

መጠጊያዬም እርሱ ነው፤ ከቶም አልናወጥም።

3ሰውን የምታጠቁት እስከ መቼ ነው?

ይህን የዘመመ ግድግዳ፣ የተንጋደደ ዐጥር፣

ሁላችሁ ገፍታችሁ ልትጥሉት ትሻላችሁ?

4ከታላቅ ክብሩ ሊያዋርዱት፣

ይህን አንድ ነገር ወጠኑ፤

ሐሰት ባለበት ነገር ደስ ይሰኛሉ፤

በአፋቸው ይመርቃሉ፤

በልባቸው ግን ይራገማሉ። ሴላ

5ነፍሴ ሆይ፤ ዐርፈሽ እግዚአብሔርን ብቻ ጠብቂ፤

ተስፋዬ ከእርሱ ዘንድ ነውና።

6ዐለቴና መድኀኒቴ እርሱ ብቻ ነው፤

መጠጊያዬም እርሱ ነው፤ እኔም አልናወጥም።

7መዳኔና ክብሬ በእግዚአብሔር ነው፤62፥7 ወይም ልዑል እግዚአብሔር ድነቴና ክብሬ ነው ተብሎ መተርጐም ይችላል።

ብርቱ ዐለቴና መሸሸጊያዬ በእግዚአብሔር ነው።

8ሰዎች ሆይ፤ ሁልጊዜ በእርሱ ታመኑ፤

ልባችሁን በፊቱ አፍስሱ፤

እግዚአብሔር መጠጊያችን ነውና። ሴላ

9ከተናቀ ወገን መወለድ ከንቱ፣

ከከበረውም መወለድ ሐሰት ነው።

በሚዛን ላይ ከፍ ብለው ቢታዩም፣

ሁሉም በአንድነት ከነፋስ የቀለሉ ናቸው።

10በዝርፊያ አትታመኑ፤

በቅሚያም ተስፋ አታድርጉ፤

በዚህ ብትበለጽጉም፣

ልባችሁ ይህን አለኝታ አያድርግ።

11እግዚአብሔር አንድ ነገር ተናገረ፤

እኔም ይህን ሁለት ጊዜ ሰማሁ፤

ኀይል የእግዚአብሔር ነው።

12ጌታ ሆይ፤ ምሕረትም የአንተ ነው፤

አንተ ለእያንዳንዱ፣

እንደ ሥራው ትከፍለዋለህ።

Chinese Contemporary Bible (Traditional)

詩篇 62:1-12

第 62 篇

唯上帝是拯救

大衛作的訓誨詩,交給樂長,照耶杜頓的做法。

1我的心默默等候上帝,

祂是我的拯救者。

2唯有祂才是我的磐石,

我的拯救,我的堡壘,

我必不致動搖。

3我就像一面搖搖欲墜的牆壁、行將倒塌的籬笆,

你們要攻擊我、置我於死地到何時呢?

4你們千方百計把我從高位拉下。

你們善於說謊,嘴上祝福,

心卻咒詛。(細拉)

5我的心啊!要默默等候上帝,

因為我的盼望從祂而來。

6唯有祂才是我的磐石,

我的拯救,我的堡壘,

我必不致動搖。

7上帝是我的拯救者,

是我的榮耀,

祂是我的堅固磐石,

是我的避難所。

8眾百姓啊,

要時刻信靠上帝,

向祂傾心吐意,

因為祂是我們的避難所。(細拉)

9卑賤人不過是一絲氣息,

尊貴人不過是一場幻影,

把他們放在天平上一秤,

比空氣還輕,毫無分量。

10不要敲詐勒索,

不要妄想靠偷盜發財,

即使財富增多,也不要倚靠它。

11上帝再三告訴我:

祂擁有權能,

12充滿慈愛。

主啊,你必照各人的行為來施行賞罰。