ሉቃስ 6 – NASV & CCBT

New Amharic Standard Version

ሉቃስ 6:1-49

የሰንበት ጌታ

6፥1-11 ተጓ ምብ – ማቴ 12፥1-14ማር 2፥23–3፥6

1በአንድ የሰንበት ቀን ኢየሱስ በዕርሻ መካከል ያልፍ ነበር፤ ደቀ መዛሙርቱም እሸት ቀጥፈው በእጃቸው እያሹ ይበሉ ነበር። 2ከፈሪሳውያን መካከል አንዳንዶቹ ግን፣ “በሰንበት ቀን ሊደረግ ያልተፈቀደውን ለምን ታደርጋላችሁ?” አሏቸው።

3ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰላቸው፤ “ዳዊት በተራበ ጊዜ ከባልንጀሮቹ ጋር ያደረገውን ከቶ አላነበባችሁምን? 4ወደ እግዚአብሔር ቤት ገብቶ ለካህናት ብቻ የተፈቀደውን ኅብስተ ገጽ ወስዶ በላ፤ አብረውት ለነበሩትም ሰጣቸው።” 5ደግሞም፣ “የሰው ልጅ ለሰንበት ጌታዋ ነው” አላቸው።

6በሌላ ሰንበት ቀንም ወደ ምኵራብ ገብቶ ያስተምር ነበር፤ በዚያም ቀኝ እጁ የሰለለ አንድ ሰው ነበረ። 7ጸሐፍትና ፈሪሳውያንም ሊከስሱት ምክንያት በመፈለግ፣ ይፈውሰው እንደ ሆነ ለማየት ይጠባበቁት ነበር። 8ኢየሱስም ሐሳባቸውን ዐውቆ እጁ የሰለለውን ሰው፣ “ተነሥተህ በመካከል ቁም” አለው፤ ሰውየውም ተነሥቶ ቆመ።

9ኢየሱስም፣ “እስቲ አንድ ነገር ልጠይቃችሁ፤ በሰንበት ቀን የተፈቀደው በጎ ማድረግ ነው ወይስ ክፉ ማድረግ? ነፍስ ማዳን ነው ወይስ ማጥፋት?” አላቸው።

10ደግሞም ኢየሱስ በዙሪያው ያሉትን ሁሉ ከተመለከተ በኋላ ሰውየውን፣ “እጅህን ዘርጋ” አለው። ሰውየውም እንደ ተባለው አደረገ፤ እጁም ፈጽሞ ዳነለት። 11ሰዎቹ ግን በቍጣ ተሞሉ፤ በኢየሱስ ላይ ምን ማድረግ እንዳለባቸውም እርስ በርስ ተወያዩ።

የዐሥራ ሁለቱ ሐዋርያት መመረጥ

6፥13-16 ተጓ ምብ – ማቴ 10፥2-4ማር 3፥16-19ሐሥ 1፥13

12ከእነዚያም ቀናት በአንዱ ኢየሱስ ሊጸልይ ወደ ተራራ ወጣ፤ ሌሊቱንም ሁሉ ወደ እግዚአብሔር ሲጸልይ ዐደረ። 13ሲነጋም ደቀ መዛሙርቱን ጠርቶ ከእነርሱ ዐሥራ ሁለቱን መረጠ፤ እነዚህንም ሐዋርያት ብሎ ሰየማቸው፤ 14እነርሱም፣ ጴጥሮስ ብሎ የጠራው ስምዖንና ወንድሙ እንድርያስ፣ ያዕቆብ፣ ዮሐንስ፣ ፊልጶስ፣ በርተሎሜዎስ፣ 15ማቴዎስ፣ ቶማስ፣ የእልፍዮስ ልጅ ያዕቆብ፣ ቀናተኛ የተባለው ስምዖን፣ 16የያዕቆብ ልጅ ይሁዳና ኋላ አሳልፎ የሰጠው የአስቆሮቱ ይሁዳ ነበሩ።

የቡራኬና የወዮታ ስብከት

6፥20-23 ተጓ ምብ – ማቴ 5፥3-12

17ኢየሱስም አብሯቸው ከተራራው ወርዶ ደልዳላ ቦታ ላይ ቆመ፤ ከደቀ መዛሙርቱም እጅግ ብዙ ሰዎች በዚያ ነበሩ፤ ከይሁዳ ሁሉና ከኢየሩሳሌም እንዲሁም ከጢሮስና ከሲዶና ባሕር ጠረፍ የመጣ ብዙ ሕዝብም በዚያ ነበረ፤ 18እነዚህም የመጡት ሊሰሙትና ካለባቸው ደዌ ሊፈወሱ ነበር። በርኩሳን6፥18 ወይም ክፉ መናፍስት ይሠቃዩ የነበሩትም ተፈወሱ፤ 19ኀይል ከእርሱ እየወጣ ሁሉንም ይፈውስ ስለ ነበር፣ ሰዎቹ ሁሉ እርሱን ለመንካት ይፈልጉ ነበር።

20ወደ ደቀ መዛሙርቱም በመመልከት እንዲህ አለ፤

“እናንት ድኾች ብፁዓን ናችሁ፤

የእግዚአብሔር መንግሥት የእናንተ ናትና፤

21እናንት አሁን የምትራቡ ብፁዓን ናችሁ፤

ኋላ ትጠግባላችሁና፤

እናንት አሁን የምታለቅሱ ብፁዓን ናችሁ፤

ኋላ ትሥቃላችሁና፤

22ሰዎች ስለ ሰው ልጅ ሲጠሏችሁ፣

ከመካከላቸው ሲለዩአችሁና ሲነቅፏችሁ፣

ክፉ ስምም ሲሰጧችሁ ብፁዓን ናችሁ።

23“እነሆ፤ ወሮታችሁ በሰማይ ታላቅ ነውና፣ በዚያን ቀን ደስ ይበላችሁ፤ ፈንድቁም፤ የቀድሞ አባቶቻቸውም በነቢያት ላይ ያደረጉት ይህንኑ ነበርና።

24“ነገር ግን እናንት ሀብታሞች ወዮላችሁ፤

መጽናናታችሁን አሁኑኑ ተቀብላችኋልና።

25እናንት አሁን የጠገባችሁ ወዮላችሁ፤

ኋላ ትራባላችሁና።

እናንት አሁን የምትሥቁ ወዮላችሁ፤

ኋላ ታዝናላችሁ፤ ታለቅሳላችሁም።

26ሰዎች ሁሉ ስለ እናንተ መልካም

ሲናገሩላችሁ ወዮላችሁ፤

የቀድሞ አባቶቻቸው ለሐሰተኞች

ነቢያት ያደረጉላቸው ይህንኑ ነበርና።

ጠላትን መውደድ

6፥2930 ተጓ ምብ – ማቴ 5፥39-42

27“ነገር ግን ለእናንተ ለምትሰሙ እላችኋለሁ፤ ጠላቶቻችሁን ውደዱ፤ ለሚጠሏችሁም መልካም አድርጉ፤ 28የሚረግሟችሁን መርቁ፤ ለሚበድሏችሁም ጸልዩ። 29አንዱን ጕንጭህን ለሚመታህ ሌላውን ጕንጭህን ደግሞ ስጠው፤ መጐናጸፊያህን ለሚወስድብህ እጀ ጠባብህን አትከልክለው። 30ለሚለምንህ ሁሉ ስጥ፤ ንብረትህን የሚወስድ እንዲመልስልህ አትጠይቀው። 31ሰዎች እንዲያደርጉላችሁ የምትፈልጉትን እናንተም እንዲሁ አድርጉላቸው።

32“የሚወድዷችሁን ብትወድዱ ምን የተለየ ዋጋ ታገኛላችሁ? ኀጢአተኞችም እንኳ የሚወድዷቸውን ይወድዳሉና። 33መልካም ላደረጉላችሁ መልካም ብታደርጉ ምን የተለየ ዋጋ ታገኛላችሁ? ኀጢአተኞችም እንኳ እንደዚያ ያደርጋሉና። 34ብድር ይመልሳል ለምትሉት ብታበድሩ ምን የተለየ ዋጋ ታገኛላችሁ? ኀጢአተኞችም እንኳ ያበደሩትን ያህል መልሰው ለመቀበል ለኀጢአተኞች ያበድራሉ። 35ነገር ግን ጠላቶቻችሁን ውደዱ፤ መልካም አድርጉ፤ መልሳችሁ ለመቀበል ተስፋ ሳታደርጉም አበድሩ፤ በዚህም ወሮታችሁ ታላቅ ይሆናል፤ የልዑልም ልጆች ትሆናላችሁ፤ እርሱ ለማያመሰግኑና ለክፉዎች ቸር ነውና። 36አባታችሁ ርኅሩኅ እንደ ሆነ እናንተም ርኅሩኆች ሁኑ።

በሌሎች አለመፍረድ

6፥37-42 ተጓ ምብ – ማቴ 7፥1-5

37“አትፍረዱ፤ አይፈረድባችሁም፤ አትኰንኑ፤ አትኰነኑም። ይቅር በሉ፤ ይቅር ትባላላችሁ። 38ስጡ፤ ይሰጣችኋል፤ በምትሰፍሩበት መስፈሪያ ተመልሶ ስለሚሰፈርላችሁ፣ ጫን በተደረገ፣ በተነቀነቀና በተትረፈረፈ መልካም መስፈሪያ ተሰፍሮ በዕቅፋችሁ ይሰጣችኋል።”

39ደግሞም ይህን ምሳሌ እንዲህ ሲል ነገራቸው፤ “ዕውር ዕውርን ሊመራ ይችላልን? ሁለቱ ተያይዘው ጕድጓድ አይገቡምን? 40ደቀ መዝሙር ከመምህሩ አይበልጥም፤ ነገር ግን በሚገባ የተማረ ሰው ሁሉ እንደ መምህሩ ይሆናል።

41“በወንድምህ ዐይን ውስጥ ያለውን ጕድፍ ለምን ታያለህ? በራስህ ዐይን ውስጥ የተጋደመውን ግንድ አትመለከትምን? 42በራስህ ዐይን ውስጥ ያለውን ግንድ ሳታይ ወንድምህን፣ ‘ወንድሜ ሆይ፤ በዐይንህ ውስጥ ያለውን ጕድፍ ላውጣልህ’ እንዴት ልትለው ትችላለህ? አንተ ግብዝ፤ በመጀመሪያ በዐይንህ ውስጥ የተጋደመውን ግንድ አውጣ፤ ከዚያ በኋላ በወንድምህ ዐይን ውስጥ ያለውን ጕድፍ ለማውጣት አጥርተህ ታያለህ።

ዛፍና ፍሬው

6፥4344 ተጓ ምብ – ማቴ 7፥161820

43“መልካም ዛፍ ሆኖ ሳለ መጥፎ ፍሬ የሚያፈራ የለም፤ እንዲሁም መጥፎ ዛፍ ሆኖ መልካም ፍሬ የሚያፈራ የለም። 44ዛፍ ሁሉ በፍሬው ይታወቃል፤ ከእሾኽ የበለስ ፍሬ አይለቀምም፤ ከቀጋ ቍጥቋጦ የወይን ፍሬ አይቈረጥም። 45መልካም ሰው በልቡ ከሞላው መልካም ነገር መልካሙን ያወጣል፤ ክፉ ሰውም በልቡ ከሞላው ክፉ ነገር ክፉውን ያወጣል፤ ሰው በልቡ ሞልቶ የተረፈውን በአፉ ይናገራልና።

ልባምና ሰነፍ ቤተ ሠሪዎች

6፥47-49 ተጓ ምብ – ማቴ 7፥24-27

46“እኔ የምለውን አታደርጉም፤ ታዲያ ለምን፣ ‘ጌታ ሆይ፤ ጌታ ሆይ’ ትሉኛላችሁ? 47ወደ እኔ የሚመጣ፣ ቃሌንም ሰምቶ የሚፈጽም ሁሉ ማንን እንደሚመስል ላሳያችሁ፤ 48ቤት ለመሥራት አጥልቆ የቈፈረና በዐለት ላይ መሠረቱን የመሠረተ ሰው ይመስላል፤ ጐርፍ በመጣ ጊዜ የውሃው ሙላት ያን ቤት ገፋው፤ በሚገባ ስለ ታነጸም ሊያነቃንቀው አልቻለም። 49ቃሌን ሰምቶ የማይፈጽም ግን ቤቱን ያለ መሠረት በዐፈር ላይ የሠራን ሰው ይመስላል፤ የወንዝ ሙላትም ቤቱን በመታው ጊዜ ወዲያው ወደቀ፤ ክፉኛም ፈራረሰ።”

Chinese Contemporary Bible (Traditional)

路加福音 6:1-49

安息日的主

1有一個安息日,耶穌和門徒走過一片麥田,門徒隨手摘下一些麥穗搓了吃。 2有些法利賽人說:「你們為什麼做在安息日不准做的事?」

3耶穌答道:「你們沒有讀過大衛的事嗎?有一天,大衛和他的部下餓了, 4他進入上帝的殿,拿了獻給上帝的供餅。這餅只有祭司才可以吃,大衛不但自己吃了,還分給他的部下吃。」 5耶穌又對他們說:「人子是安息日的主。」

6又有一個安息日,耶穌進入會堂教導人,座中有一個右手萎縮的人。 7律法教師和法利賽人密切地監視耶穌,看祂會不會在安息日醫治病人,好找個藉口控告祂。 8耶穌知道他們的心思,就對那個右手萎縮的人說:「起來,站在大家面前!」那人就起來站在那裡。

9耶穌問眾人:「我問你們,在安息日應該行善呢,還是作惡呢?救人呢,還是害人呢?」 10祂環視眾人,然後對那人說:「把手伸出來!」那人的手一伸就復原了。

11但法利賽人和律法教師卻怒火中燒,開始商議對付耶穌的辦法。

揀選十二使徒

12一天,耶穌到山上整夜向上帝禱告。 13天明時分,祂召集門徒,從中選出十二人立為使徒。 14他們是:西門——耶穌給他取名叫彼得西門的兄弟安得烈雅各約翰腓力巴多羅買15馬太多馬亞勒腓的兒子雅各、激進黨人6·15 當時激進的民族主義者,常以行動反抗統治他們的羅馬政府。西門16雅各的兒子猶大和出賣耶穌的加略猶大

17耶穌和他們下了山,站在一處平地上,身邊有一大群門徒,還有大批從猶太耶路撒冷以及泰爾西頓沿海地區來的人,要聽祂講道,盼望祂醫治他們的疾病。 18那些被污鬼纏身的人也得到了祂的醫治。 19大家都想去摸祂,因為有能力從祂身上發出來,可以治好人們的疾病。

論四福

20耶穌抬頭望著門徒,對他們說:

「貧窮的人有福了,

因為上帝的國屬於你們!

21現在饑餓的人有福了,

因為你們將得飽足!

現在哀哭的人有福了,

因為你們將要歡笑!

22你們為人子的緣故而遭人憎恨、棄絕、侮辱、毀謗,就有福了! 23那時你們要歡喜雀躍,因為你們在天上有大賞賜!他們的祖先也曾這樣惡待以前的先知。

論四禍

24「富有的人有禍了,

因為你們已經享盡了人世間的安逸!

25現在飽足的人有禍了,

因為你們將要挨餓!

現在歡笑的人有禍了,

因為你們將要哀哭!

26人人都誇讚你們的時候,

你們就有禍了,

因為他們的祖先也是這樣誇讚假先知!

論愛仇敵

27「但是,我告訴你們這些聽道的人,要愛你們的仇敵,要善待恨你們的人, 28要為咒詛你們的人祝福,要替惡待你們的人禱告。 29如果有人打你一邊的臉,連另一邊也轉過來讓他打。如果有人奪你的外衣,連內衣也由他拿去。 30有人向你求什麼,就給他;有人拿了你的東西,不要追討。 31你們想要別人怎樣對待你們,你們就要怎樣對待別人。 32如果你們只愛那些愛你們的人,有什麼功勞呢?就是罪人也會這樣做。 33如果你們只善待那些善待你們的人,有什麼功勞呢?就是罪人也會這樣做。 34如果你們借錢給人,指望收回,有什麼功勞呢?即使罪人也會借貸給罪人,日後再如數收回。

35「然而,要愛你們的仇敵,善待他們;無論借出什麼,都不要指望歸還。這樣,你們將有大賞賜,並且將成為至高者的兒子,因為祂以恩慈待那些忘恩負義和作惡的人。 36你們要憐憫人,像你們的天父憐憫人一樣。

責人先責己

37「不要論斷人,免得你們被人論斷;不要定人的罪,免得自己也被定罪。要饒恕人,這樣你們也必蒙饒恕。 38你們要給他人,這樣上帝必給你們,並且會用大號升斗搖勻壓實,滿滿地倒給你們,因為你們用什麼樣的量器量給別人,上帝也會用什麼樣的量器量給你們。」

39耶穌又給他們講了個比喻,說:「瞎子豈能給瞎子帶路?二人豈不是要雙雙掉進坑裡嗎? 40學生不會高過老師,學成之後不過像老師一樣。 41為什麼你只看見你弟兄眼中的小刺,卻看不見自己眼中的大樑呢? 42你既看不見自己眼中的大樑,又怎能對弟兄說『讓我除去你眼中的小刺』呢?你這偽君子啊!要先除掉自己眼中的大樑,才能看得清楚,以便清除弟兄眼中的小刺。

樹和果子

43「好樹不結壞果子,壞樹也結不出好果子。 44樹的好壞從果子就可以分辨出來。人不會從荊棘中採集無花果,也不會在蒺藜上摘取葡萄。 45善人心存良善,就從他裡面發出良善;惡人心存邪惡,就從他裡面發出邪惡。因為心裡充滿的,口裡自然會說出來。

兩種蓋房子的人

46「你們為什麼『主啊,主啊』地稱呼我,卻不遵行我的話呢? 47我要告訴你們那到我這裡來,聽了我的話又去遵行的人是什麼樣。 48他好比一個人蓋房子,把地挖深,根基立在磐石上。當河流氾濫,洪水沖擊房子時,房子卻屹立不搖,因為它的根基穩固。 49但聽了我的話卻不遵行的人,好比一個人沒有打根基,便將房子蓋在地面上,洪水一沖,房子立刻倒塌,完全毀壞了。」