詩篇 2 – CCBT & NASV

Chinese Contemporary Bible (Traditional)

詩篇 2:1-12

第 2 篇

上帝膏立的君王

1列國為何咆哮?

萬民為何枉費心機?

2世上的君王一同行動,

官長聚集商議,

要抵擋耶和華和祂所膏立的王。

3他們說:

「讓我們掙斷他們的鎖鏈,

脫去他們的捆索!」

4坐在天上寶座上的主必笑他們,

祂必嘲笑他們。

5那時,祂必怒斥他們,

使他們充滿恐懼。

6祂說:

「在我的錫安聖山上,

我已立了我的君王。」

7那位君王說:

「我要宣告耶和華的旨意,

祂對我說,『你是我的兒子,

我今日成為你父親。

8你向我祈求,我必把列國賜給你作產業,

讓天下都歸你所有。

9你要用鐵杖統治他們,

把他們像陶器一般打碎。』」

10君王啊,要慎思明辨!

世上的統治者啊,要接受勸誡!

11要以敬畏的心事奉耶和華,

要喜樂也要戰戰兢兢。

12要降服在祂兒子面前,

免得祂發怒,

你們便在罪惡中滅亡,

因為祂的怒氣將臨。

投靠祂的人有福了!

New Amharic Standard Version

መዝሙር 2:1-12

መዝሙር 2

መሲሓዊ ትዕይንት

1ሕዝቦች ለምን ያሤራሉ?2፥1 ዕብራይስጡ እንዲሁ ሲሆን፣ ሰብዓ ሊቃናት ግን ይቈጣሉ ይላል።

ሰዎችስ ለምን ከንቱ ነገር ያውጠነጥናሉ?

2የምድር ነገሥታት ተነሡ፤

ገዦችም በእግዚአብሔርና በመሲሑ2፥2 ወይም የተቀባው ላይ

ሊመክሩ ተሰበሰቡ፤

3“ሰንሰለታቸውን እንበጥስ፣

የእግር ብረታቸውንም አውልቀን እንጣል” አሉ።

4በሰማይ ዙፋን ላይ የተቀመጠው ይሥቃል፤

ጌታም ይሣለቅባቸዋል።

5ከዚያም በቍጣው ይናገራቸዋል፤

በመዓቱም ያስደነግጣቸዋል፤

6ደግሞም፣ “እኔ ግን በተቀደሰው ተራራዬ፣

በጽዮን ላይ የራሴን ንጉሥ ሾምሁ” ይላል።

7የእግዚአብሔርን ሕግ ዐውጃለሁ፤

እርሱም እንዲህ አለኝ፤ “አንተ ልጄ ነህ፤

እኔ ዛሬ ወለድሁህ፤2፥7 ወይም …አባትህ ሆንሁ

8ለምነኝ፤

መንግሥታትን ርስት አድርጌ፣

የምድርንም ዳርቻ ግዛት እንዲሆንህ እሰጥሃለሁ።

9አንተም በብረት በትር ትቀጠቅጣቸዋለህ፤2፥9 ወይም በብረት ዘንግ ትሰባብራቸዋለህ

እንደ ሸክላ ዕቃ ታደቅቃቸዋለህ።”

10ስለዚህ እናንት ነገሥታት ልብ በሉ፤

እናንት የምድር ገዦችም፣ ተጠንቀቁ።

11እግዚአብሔርን በፍርሀት አገልግሉት፤

ለእርሱ መራድም ደስ ያሰኛችሁ።

12እንዳይቈጣና በመንገድ እንዳትጠፉ፣

ዝቅ ብላችሁ ልጁን ሳሙት፤

ቍጣው ፈጥኖ ይነድዳልና።

እርሱን መጠጊያ የሚያደርጉ ሁሉ የተባረኩ ናቸው።