撒迦利亞書 13 – CCBT & NASV

Chinese Contemporary Bible (Traditional)

撒迦利亞書 13:1-9

1「到那天,必為大衛家和耶路撒冷的居民開一個泉源,洗淨他們的罪惡和污穢。

2「到那天,我必剷除地上偶像的名號,使它們被人遺忘;我必除去地上的假先知和污穢的靈。這是萬軍之耶和華說的。 3若有人再說預言,他的親生父母必對他說,『你不得活命,因為你奉耶和華的名說謊。』他說預言的時候,他的親生父母必把他刺死。 4到那天,先知必因自己所講的異象而羞愧,不再穿著毛皮衣欺騙人。 5他必說,『我不是先知,我是農夫,我從小便以種田為生。』 6若有人問他,『你胸口上的傷是怎麼回事?13·6 異教的先知有用利器自割或自刺的習慣。』他必回答說,『是在我朋友家弄傷的。』」

牧人被殺

7萬軍之耶和華說:

「刀劍啊,醒來吧,

要攻擊我的牧人和同伴,

要擊打牧人,羊群將四散,

我必出手攻擊小羊。

8地上三分之二的人必遭剷除、毀滅,

只剩下三分之一的人存活。

這是耶和華說的。

9我必使這三分之一的人受到火一般的考驗;

我必像熬煉銀子一樣熬煉他們,

像試煉金子一樣試煉他們。

他們必呼求我的名,

我必回應他們。

我必說,『這是我的子民。』

他們必說,『耶和華是我們的上帝。』」

New Amharic Standard Version

ዘካርያስ 13:1-9

ከኀጢአት መንጻት

1“በዚያ ቀን የዳዊትን ቤትና የኢየሩሳሌምን ነዋሪዎች ከኀጢአትና ከርኩሰት የሚያነጻ ምንጭ ይከፈታል።

2“በዚያ ቀን የጣዖታትን ስም ከምድሪቱ አጠፋለሁ፤ ከእንግዲህም አይታሰቡም” ይላል እግዚአብሔር ጸባኦት። “ነቢያትንና ርኩስ መንፈስን ከምድሪቱ አስወግዳለሁ። 3ማንም ትንቢት ቢናገር ወላጅ አባትና እናቱ፣ ‘በእግዚአብሔር ስም ሐሰት ተናግረሃልና ሞት ይገባሃል’ ይሉታል። ትንቢት ሲናገርም የገዛ ወላጆቹ ይወጉታል።

4“በዚያን ቀን እያንዳንዱ ነቢይ ስለሚናገረው የትንቢት ራእይ ያፍራል፤ ለማታለልም የነቢያትን ጠጕራም ልብስ አይለብስም። 5እርሱም፣ ‘እኔ ገበሬ እንጂ ነቢይ አይደለሁም፤ ከልጅነቴ13፥5 ወይም ዐራሽ፤ በወጣትነቴ የተሸጥሁ ሰው ጀምሮ ኑሮዬ የተመሠረተውም በዕርሻ ላይ ነው’ ይላል። 6አንድ ሰው፣ ‘ይህ በሰውነትህ13፥6 በእጆችህ መኻል ያሉ ቍሰሎች የሚሉ አሉ። ላይ ያለው ቍስል ምንድን ነው?’ ብሎ ቢጠይቀው፣ ‘በባልንጀሮቼ ቤት ሳለሁ የቈሰልሁት ነው’ ይላል።”

እረኛው ተመታ፤ በጎቹ ተበተኑ

7እግዚአብሔር ጸባኦት እንዲህ ይላል፤

“ሰይፍ ሆይ፤ በእረኛዬ፣

በቅርብ ወዳጄ ላይ ንቃ!

እረኛውን ምታ፣

በጎቹ ይበተናሉ፤

እኔም ክንዴን ወደ ታናናሾቹ አዞራለሁ።”

8እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “የምድር ሁሉ፣

ሁለት ሦስተኛው ተመትቶ ይጠፋል፤

አንድ ሦስተኛው ግን በውስጡ ይቀራል፤

9ይህን አንድ ሦስተኛውን ክፍል ወደ እሳት አመጣለሁ፤

እንደ ብር አነጥራቸዋለሁ፤

እንደ ወርቅም እፈትናቸዋለሁ፤

እነርሱ ስሜን ይጠራሉ፤

እኔም እመልስላቸዋለሁ፤

እኔም፣ ‘ሕዝቤ ናቸው’ እላለሁ፤

እነርሱም፣ ‘እግዚአብሔር አምላካችን ነው’ ይላሉ።”