申命记 25 – CCB & NASV

Chinese Contemporary Bible (Simplified)

申命记 25:1-19

1“如果发生纠纷,双方告上法庭,审判官要判明是非。 2如果有罪的一方被判受鞭打,审判官要命令他当场伏在地上,按罪行轻重受刑。 3最多可以鞭打他四十下。如果超过四十下,你们就是在公开羞辱自己的同胞。

4“牛在踩谷时,不可笼住它的嘴。

为死亡的兄弟传宗接代

5“如果兄弟们住在一起,其中一个没有儿子便死了,死者的妻子不可改嫁给外人。死者的兄弟要尽兄弟的责任娶她为妻。 6她生的第一个儿子要算为死者的儿子,免得死者在以色列绝后。 7如果死者的兄弟不愿娶那寡妇,她要到城门口见长老们,告诉他们,‘我丈夫的兄弟不肯尽兄弟的责任娶我,不肯为我丈夫留后。’ 8长老们要把死者的兄弟召来,与他商谈。如果他执意不肯, 9那寡妇要当着众长老的面,上前脱下他的鞋,吐唾沫在他脸上,说,‘这就是不肯为兄弟留后之人的下场。’ 10从此以后,他的家在以色列要被称为‘被脱鞋者之家’。

其他条例

11“如果两个男人打架,其中一人的妻子为帮助丈夫而伸手抓住另外一人的下体, 12就要砍掉她的手,不可怜悯她。

13“你们做买卖时,口袋里不可有一大一小两种砝码, 14家里也不可用一大一小两种量器。 15你们必须诚实无欺,使用同样的砝码和量器,以便在你们的上帝耶和华要赐给你们的土地上得享长寿。 16因为你们的上帝耶和华憎恶行事诡诈的人。

灭绝亚玛力人的命令

17“你们要记住,你们从埃及出来的路上,亚玛力人是怎样对待你们的。 18他们趁你们疲惫不堪时,袭击你们当中掉队的人,毫不敬畏上帝。 19所以,当你们的上帝耶和华赐给你们那片土地作产业、使你们四境安宁时,要灭绝亚玛力人,抹去世人对他们的记忆。你们要切记!

New Amharic Standard Version

ዘዳግም 25:1-19

1በሰዎች መካከል ጠብ ቢነሣና ወደ ፍርድ አደባባይ ቢሄዱ፣ ዳኞች ተበዳይን ነጻ፣ በዳይን ግን ጥፋተኛ በማድረግ የፍርድ ውሳኔ ይስጡ። 2በደለኛው ሰው መገረፍ የሚገባው ሆኖ ከተገኘ፣ ዳኛው መሬት ላይ ያጋድመው፤ ለጥፋቱ ተመጣጣኝ የሆነ ግርፋት እርሱ ባለበት ይገረፍ። 3ሆኖም ግርፋቱ ከአርባ የሚበልጥ አይሁን፤ ከዚህ ካለፈ ግን፣ ወንድምህ በፊትህ የተዋረደ ይሆናል።

4እህል እያበራየ ያለውን በሬ አፉን አትሰር።

5ወንድማማቾች በአንድነት ቢኖሩና ከእነርሱ አንዱ ወንድ ልጅ ሳይወልድ ቢሞት፣ የሟቹ ሚስት ከቤተ ሰቡ ውጭ ባል ማግባት የለባትም። የባሏ ወንድም ይውሰዳትና ያግባት፤ የዋርሳነት ግዴታውንም ይፈጽምላት። 6በመጀመሪያ የምትወልደውም ልጅ ስሙ ከእስራኤል ፈጽሞ እንዳይጠፋ በሟች ወንድሙ ስም ይጠራ።

7ሆኖም ግን አንድ ሰው የወንድሙን ሚስት ለማግባት ባይፈልግ፣ ሴትየዋ በከተማዋ በር ወዳሉት ሽማግሌዎች ሄዳ፣ “የባለቤቴ ወንድም የወንድሙን ስም በእስራኤል ለማስጠራት አልፈለገም፤ የዋርሳነት ግዴታውንም አልፈጸመልኝም” ትበላቸው። 8ከዚያም የከተማው ሽማግሌዎች ያን ሰው ጠርተው ያነጋግሩት፤ እርሱም፣ “እርሷን ላገባት አልፈልግም” ብሎ በዐሳቡ ቢጸና፣ 9የወንድሙም ሚስት በሽማግሌዎች ፊት ወደ እርሱ ቀርባ፣ የአንድ እግሩን ጫማ በማውለቅ በፊቱ ላይ ትትፋበትና “የወንድሙን ቤት በማይሠራ ሰው ላይ እንዲህ ያለው ድርጊት ይፈጸምበታል” ትበል። 10የዚያም ሰው የዘር ሐረግ በእስራኤል ዘንድ፣ “ጫማው የወለቀበት ቤት” ተብሎ ይታወቃል።

11ሁለት ሰዎች ቢደባደቡ፣ የአንደኛው ሚስት ባሏን ከደብዳቢው እጅ ለማስጣል መጥታ፣ እጇን ዘርግታ ብልቱን ብትይዘው፣ 12እጇን ቍረጠው፤ አትራራላት።

13በከረጢትህ ውስጥ ከባድና ቀላል የሆኑ ሁለት የተለያዩ ሚዛኖች አይኑሩህ። 14በቤትህም ውስጥ ትልቅና ትንሽ የሆኑ ሁለት የተለያዩ መስፈሪያዎች አይኑሩህ። 15አምላክህ እግዚአብሔር (ኤሎሂም ያህዌ) በሚሰጥህ ምድር ዕድሜህ እንዲረዝም፣ ትክክለኛና የታመነ ሚዛንና መስፈሪያ ይኑርህ። 16አምላክህ እግዚአብሔር (ኤሎሂም ያህዌ) እንዲህ ያሉትን ነገሮች የሚፈጽመውንና የሚያምታታውን ሁሉ ይጸየፈዋልና።

17ከግብፅ በወጣህ ጊዜ፣ አማሌቅ በመንገድ በአንተ ላይ ያደረገብህን አስታውስ፤ 18ደክመህና ዝለህ በነበርህበት ጊዜ፣ በጕዞ ላይ አግኝተውህ፣ ከኋላ ያዘግሙ የነበሩትን ሁሉ ገደሉ፤ እግዚአብሔርንም (ኤሎሂም) አልፈሩም። 19አምላክህ እግዚአብሔር (ኤሎሂም ያህዌ) ርስት አድርጎ በሚሰጥህ ምድር ዙሪያ ካሉት ጠላቶችህ ሁሉ ባሳረፈህ ጊዜ፣ ከሰማይ በታች ያለውን የአማሌቅን መታሰቢያ ደምስስ፤ ከቶ እንዳትረሳ!