申命记 26 – CCB & NASV

Chinese Contemporary Bible (Simplified)

申命记 26:1-19

奉献初熟的物产

1“你们进入你们的上帝耶和华将要赐给你们作产业的土地,征服那里,安居下来以后, 2要把在那里收获的各种初熟的物产放在篮子里,带到你们的上帝耶和华选定的敬拜场所。 3你们要对当值的祭司说,‘今天我们要向我们的上帝耶和华宣告,我们已经进入祂向我们祖先起誓要赐给我们的土地。’ 4祭司要从你们手中接过篮子,放在你们的上帝耶和华的祭坛前。 5你们要在你们的上帝耶和华面前宣告,‘我们的祖先原是到处流浪的亚兰人。他到埃及寄居时,家中人丁稀少,后来成为人口众多的强大民族。 6埃及人苦待我们,压迫我们,强迫我们做奴隶。 7于是,我们呼求我们祖先的上帝耶和华。祂听见我们的呼求,看见我们的艰难、困苦和所受的压迫, 8就伸出臂膀,用大能的手行神迹奇事,以伟大而可畏的作为带领我们离开埃及9祂带领我们来到这个地方,把这奶蜜之乡赐给我们。 10耶和华啊,现在我们从你赐给我们的土地上带来初熟的物产。’你们要把篮子放在你们的上帝耶和华面前,敬拜祂。 11你们和利未人以及住在你们中间的外族人,都要因你们的上帝耶和华赐给你们和你们家人的美物而欢喜快乐。

十一奉献年

12“每逢第三年是十一奉献年。你们应当把自己的十一奉献拿出来分给利未人、寄居者和孤儿寡妇,使他们在你们居住的城邑吃饱喝足。 13然后,你们要在你们的上帝耶和华面前宣告,‘我们已经按照你的诫命,从我们家里拿出圣物分给利未人、寄居者和孤儿寡妇。我们没有触犯也没有忘记你的任何诫命。 14这些圣物,我们守丧期间没有吃过,不洁净时没有拿过,也没有献给死人。我们听从你——我们的上帝耶和华,遵行你的一切吩咐。 15求你从天上圣洁的居所垂看,赐福给你的以色列子民和你赐给我们的土地——你向我们祖先起誓应许的奶蜜之乡。’

16“你们的上帝耶和华今天吩咐你们遵守这些律例和典章,你们要全心全意地谨慎遵守。 17你们今天已经宣称耶和华是你们的上帝,答应要听从祂,行祂的道,遵守祂的一切律例、诫命和典章。 18耶和华今天已经照祂的应许宣称你们是祂的子民,是祂宝贵的产业。因此,你们要遵守祂的一切诫命, 19这样祂必使你们备受赞誉和尊崇,超越祂所造的万国,并照着祂的应许使你们做属于祂的圣洁子民。”

New Amharic Standard Version

ዘዳግም 26:1-19

ዐሥራትና በኵራት

1አምላክህ እግዚአብሔር (ኤሎሂም ያህዌ) ርስት አድርጎ ወደሚሰጥህ ምድር ስትገባ፣ ስትወርሳትና ስትኖርባት፣ 2አምላክህ እግዚአብሔር (ኤሎሂም ያህዌ) ከሚሰጥህ ምድር ከምትሰበስበው ሰብል ሁሉ፣ በኵራት ወስደህ በቅርጫት ውስጥ አድርገው፤ ከዚያም አምላክህ እግዚአብሔር (ኤሎሂም ያህዌ) ለስሙ ማደሪያ እንዲሆን ወደሚመርጠው ስፍራ ሂድ፤ 3በዚያም ወቅት ለሚያገለግለው ካህን፣ “እግዚአብሔር (ያህዌ) ለእኛ ሊሰጠን ለአባቶቻችን ወደ ማለላቸው ምድር እንደ ገባሁ ዛሬ በአምላክህ በእግዚአብሔር (ኤሎሂም ያህዌ) ፊት እናገራለሁ” በለው። 4ካህኑም ቅርጫቱን ከእጅህ ተቀብሎ፣ በአምላክህ በእግዚአብሔር (ኤሎሂም ያህዌ) መሠዊያ ፊት ለፊት ያስቀምጠዋል። 5አንተም በአምላክህ በእግዚአብሔር (ያህዌ ኤሎሂም) ፊት እንዲህ ብለህ ትናገራለህ፤ “አባቴ ዘላን ሶርያዊ ነበር፤ ከጥቂት ሰዎችም ጋር ወደ ግብፅ ወረደ፤ በዚያም ተቀመጠ፤ ታላቅ፣ ኀያልና ቍጥሩ የበዛ ሕዝብ ሆነ። 6ግብፃውያን ግን ከባድ ሥራ በማሠራት አንገላቱን፤ አሠቃዩንም። 7ከዚያ በኋላ የአባቶቻችን አምላክ (ያህዌ) ወደ ሆነው ወደ እግዚአብሔር (ኤሎሂም) ጮኽን፤ እግዚአብሔርም ጩኸታችንን ሰማ፤ ጕስቍልናችንን፣ ድካማችንንና የተፈጸመብንን ግፍ ተመለከተ። 8ከዚህ የተነሣ እግዚአብሔር (ያህዌ) በብርቱ እጅና በተዘረጋች ክንድ፣ በታላቅ ድንጋጤ፣ በታምራዊ ምልክትና በድንቅ ከግብፅ አወጣን። 9ወደዚህ ስፍራ አመጣን፤ ማርና ወተት የምታፈስሰውን ይህችን ምድር ሰጠን፤ 10አሁንም እግዚአብሔር (ያህዌ) ሆይ፤ እነሆ፤ አንተ የሰጠኸኝን የምድሪቱን በኵራት አምጥቻለሁ።” ቅርጫቱንም በአምላክህ በእግዚአብሔር (ኤሎሂም ያህዌ) ፊት አስቀምጠው፤ በአምላክህ በእግዚአብሔር (ኤሎሂም ያህዌ) ፊት ስገድ። 11ከዚያም አንተ፣ ሌዋዊውና በመካከልህ የሚኖረው መጻተኛ፣ አምላክህ እግዚአብሔር (ኤሎሂም ያህዌ) ለአንተና ለቤትህ በሰጠው በጎ ነገር ሁሉ ደስ ይበላችሁ።

12የዐሥራት ዓመት የሆነውን የሦስተኛውን ዓመት ምርት አንድ ዐሥረኛ ለይተህ ካወጣህ በኋላ በየከተሞችህ ውስጥ በልተው እንዲጠግቡ፣ ለሌዋዊው፣ ለመጻተኛው፣ አባት ለሌለውና ለመበለቲቱ ስጣቸው፤ 13ከዚያ በኋላ ለአምላክህ ለእግዚአብሔር (ኤሎሂም ያህዌ) እንዲህ በል፤ “በሰጠኸኝ ትእዛዝ መሠረት የተቀደሰውን ክፍል ከቤቴ አውጥቼ ለሌዋዊው፣ ለመጻተኛው፣ አባት ለሌለውና ለመበለቲቱ ሰጥቻለሁ። ከትእዛዝህ አልወጣሁም፤ አንዱንም አልረሳሁም። 14በሐዘን ላይ ሳለሁ፣ ከተቀደሰው ክፍል ላይ ምንም አልበላሁም፤ ባልነጻሁበትም ጊዜ ከዚሁ ላይ ያነሣሁትም ሆነ ለሙታን ያቀረብሁት ምንም ነገር የለም፤ አምላኬን እግዚአብሔርን (ኤሎሂም ያህዌ) ታዝዣለሁ፤ ያዘዝኸኝንም ሁሉ ፈጽሜአለሁ። 15ከቅዱስ ማደሪያህ ከሰማይ ተመልከት፤ ሕዝብህን እስራኤልንና ለአባቶቻችን በመሐላ ቃል በገባኸው መሠረት፣ ለእኛ የሰጠኸንን ይህችን ማርና ወተት የምታፈስሰውን ምድር ባርክ።”

የእግዚአብሔርን ትእዛዞች ስለ መጠበቅ

16አምላክህ እግዚአብሔር (ኤሎሂም ያህዌ) ይህን ሥርዐትና ሕግ ትጠብቅ ዘንድ ዛሬ ያዝዝሃል፤ አንተም በፍጹም ልብህ፣ በፍጹምም ነፍስህ ትፈጽመው ዘንድ ተጠንቀቅ። 17እግዚአብሔር አምላክህ (ያህዌ ኤሎሂም) እንደ ሆነ በመንገዱም እንደምትሄድ፣ ሥርዐቱን፣ ትእዛዙንና ሕጉን እንደምትጠብቅና እንደምትታዘዝለት በዛሬዪቱ ዕለት ተናግረሃል። 18እግዚአብሔር (ያህዌ) በሰጠህ ተስፋ መሠረት አንተ፣ ሕዝቡና ርስቱ መሆንህን፣ ትእዛዙንም ሁሉ እንደምትጠብቅ በዛሬው ዕለት ተናግሯል። 19ከፈጠራቸው ሕዝቦች ሁሉ በላይ በምስጋና፣ በስም፣ በክብርም ከፍ እንደሚያደርግህና በሰጠውም ተስፋ መሠረት ለአምላክህ ለእግዚአብሔር (ኤሎሂም ያህዌ) ቅዱስ ሕዝብ እንደምትሆን ተናግሯል።