帖撒罗尼迦后书 2 – CCB & NASV

Chinese Contemporary Bible (Simplified)

帖撒罗尼迦后书 2:1-17

主再来的先兆

1弟兄姊妹,关于主耶稣基督再来和我们到祂那里相聚的事情, 2我们现在奉劝你们:无论是什么灵,或是传闻,或是冒充我们写的信,说主的日子已经到了,你们都不要轻易动摇,也不要惊慌。 3不管别人用什么诡计,你们都不要上当。因为那日子来临之前,必有离经叛道的事发生,而那不法之徒,就是那注定灭亡的人也要出现。 4他会抵挡主,高抬自己超过一切所谓的神明和人们崇拜的对象,甚至坐在上帝的殿中以上帝自居!

5我还在你们那里的时候,曾告诉过你们这些事,你们忘记了吗? 6现在,你们知道是什么拦阻他,使他等到特定的时间才出现。 7其实那不法之徒的阴谋已经在酝酿中,然而现在有一位在拦阻他。等到拦阻他的那位一离开, 8他就会出现,但主耶稣会用自己口中的气毁灭他,用从天降临的荣光废掉他。

9他来要按照撒旦的伎俩行各样虚假的异能、神迹和奇事, 10用尽各样诡计欺骗那些将要灭亡的人,因为他们不喜欢接受那能拯救他们的真理。 11上帝就让他们是非不辨,去相信那些虚假的谎言, 12使一切不相信真理、反喜爱不义的人都被定罪。

要坚定不移

13主所爱的弟兄姊妹,我们应该时常为你们感谢上帝,因为上帝一开始就拣选了你们,为了使你们借着圣灵得以圣洁,并且相信真理,从而得救。 14上帝借着我们所传的福音呼召了你们,使你们可以得到我们主耶稣基督的荣耀。 15所以,各位弟兄姊妹,务要坚定不移,无论是我们信上的教导还是口头的教导,你们都要坚守。

16愿主耶稣基督和爱我们、开恩将永远的安慰和美好的盼望赐给我们的父上帝, 17安慰你们的心,使你们在一切善行善言上刚强。

New Amharic Standard Version

2 ተሰሎንቄ 2:1-17

የዐመፅ ሰው

1ወንድሞች ሆይ፤ ስለ ጌታችን ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ መምጣትና ወደ እርሱም ስለ መሰብሰባችን ይህን እንለምናችኋለን፤ 2በመንፈስ ወይም በቃል ወይም ከእኛ እንደ ተላከ መልእክት የጌታ ቀን ደርሷል ብላችሁ ፈጥናችሁ ከአእምሯችሁ አትናወጡ፤ አትደንግጡም። 3ማንም ሰው በምንም መንገድ አያታልላችሁ፤ አስቀድሞ ዐመፅ ሳይነሣ፣ ለጥፋት የተመደበውም የዐመፅ2፥3 አንዳንድ ቅጆች የኀጢአት ይላሉ። ሰው ሳይገለጥ ያ ቀን አይመጣምና። 4እርሱም አምላክ ከተባለና ከሚመለከው ነገር ሁሉ በላይ ራሱን ከፍ ከፍ የሚያደርግ ተቃዋሚ ነው፤ እርሱም በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ተቀምጦ፣ “እኔ አምላክ ነኝ” እያለ ዐዋጅ ያስነግራል።

5ከእናንተ ጋር በነበርሁበት ጊዜ፣ እነዚህን ነገሮች ነግሬአችሁ እንደ ነበር ትዝ አይላችሁምን? 6በራሱ ጊዜ ይገለጥ ዘንድ አሁን ምን እንደሚከለክለው ታውቃላችሁ። 7የዐመፅ ምስጢር አሁንም እንኳ እየሠራ ነውና፤ ነገር ግን ይህ የሚሆነው የሚከለክለው ከመንገድ እስኪወገድ ድረስ ብቻ ነው 8ከዚያም በኋላ ጌታ ኢየሱስ በአፉ እስትንፋስ የሚያስወግደውና በምጽአቱም ክብር ፈጽሞ የሚያጠፋው ዐመፀኛ ይገለጣል። 9የዐመፀኛው አመጣጥ በሰይጣን አሠራር ላይ የተመሠረተ ሲሆን፣ ይህም በሐሰተኛ ታምራት በምልክቶችና በድንቅ ነገሮች ሁሉ ይሆናል፤ 10እንዲሁም ይድኑ ዘንድ እውነትን ባለመውደድ የሚጠፉትን ሰዎች በሚያታልል በተለያየ የክፋት ሥራ ይመጣል። 11በዚህም ምክንያት እግዚአብሔር በሐሰት እንዲያምኑ የስሕተትን አሠራር ይልክባቸዋል፤ 12ይህም የሚሆነው እውነትን ያላመኑት ነገር ግን በክፋት ደስ ይላቸው የነበሩ ሁሉ እንዲፈረድባቸው ነው።

ጸንታችሁ ቁሙ

13በጌታ የተወደዳችሁ ወንድሞች ሆይ፤ እኛ ግን ሁልጊዜ ስለ እናንተ እግዚአብሔርን ልናመሰግን ይገባናል። ምክንያቱም እግዚአብሔር እናንተን ከመጀመሪያ አንሥቶ በመንፈስ ተቀድሳችሁና በእውነትም አምናችሁ እንድትድኑ መርጧችኋል2፥13 አንዳንድ ቅጆች እግዚአብሔር በኵራቱ እንድትሆኑ መርጧችኋል ይላሉ።14የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ክብር ተካፋዮች እንድትሆኑም በወንጌላችን አማካይነት ጠርቷችኋል። 15እንግዲህ ወንድሞች ሆይ፤ ጸንታችሁ ቁሙ፤ በአንደበታችንም ሆነ በመልእክታችን ያስተላለፍንላችሁን ትምህርት2፥15 ወይም ወግ አጥብቃችሁ ያዙ።

16ራሱ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ደግሞም እኛን የወደደንና በጸጋው የዘላለም መጽናናትና መልካም ተስፋን የሰጠን እግዚአብሔር አባታችን፣ 17ልባችሁን ያጽናኑት፤ በበጎ ሥራና በቃል ሁሉ ያበርቷችሁ።