历代志上 6 – CCB & NASV

Chinese Contemporary Bible (Simplified)

历代志上 6:1-81

利未的后裔

1利未的儿子是革顺哥辖米拉利2哥辖的儿子是暗兰以斯哈希伯仑乌薛3暗兰的儿子是亚伦摩西,女儿是米利暗亚伦的儿子是拿答亚比户以利亚撒以他玛4以利亚撒非尼哈非尼哈亚比书5亚比书布基布基乌西6乌西西拉希雅西拉希雅米拉约7米拉约亚玛利雅亚玛利雅亚希突8亚希突撒督撒督亚希玛斯9亚希玛斯亚撒利雅亚撒利雅约哈难10约哈难亚撒利雅——这亚撒利雅耶路撒冷所罗门建的圣殿里任祭司, 11亚撒利雅亚玛利雅亚玛利雅亚希突12亚希突撒督撒督沙龙13沙龙希勒迦希勒迦亚撒利雅14亚撒利雅西莱雅西莱雅约萨答15在耶和华借尼布甲尼撒掳掠犹大耶路撒冷人的时候,约萨答也一起被掳去了。

16利未的儿子是革顺哥辖米拉利17革顺的儿子一个叫立尼,一个叫示每18哥辖的儿子是暗兰以斯哈希伯仑乌薛19米拉利的儿子是抹利姆示。以上是利未人按宗族分的各家族。

20革顺的儿子是立尼立尼的儿子是雅哈雅哈的儿子是薪玛21薪玛的儿子是约亚约亚的儿子是易多易多的儿子是谢拉谢拉的儿子是耶特赖

22哥辖的儿子是亚米拿达亚米拿达的儿子是可拉可拉的儿子是亚惜23亚惜的儿子是以利加拿以利加拿的儿子是以比雅撒以比雅撒的儿子是亚惜24亚惜的儿子是他哈他哈的儿子是乌列乌列的儿子是乌西雅乌西雅的儿子是少罗25以利加拿的儿子是亚玛赛亚希摩26亚希摩的儿子是以利加拿以利加拿的儿子是琐菲琐菲的儿子是拿哈27拿哈的儿子是以利押以利押的儿子是耶罗罕耶罗罕的儿子是以利加拿以利加拿的儿子是撒母耳28撒母耳的长子是约珥,次子是亚比亚29米拉利的儿子是抹利抹利的儿子是立尼立尼的儿子是示每示每的儿子是乌撒30乌撒的儿子是示米亚示米亚的儿子是哈基雅哈基雅的儿子是亚帅雅

圣殿的歌乐手

31约柜安放在耶和华的殿中之后,大卫便派人在那里负责歌乐。 32他们按班次在会幕供职,一直到所罗门耶路撒冷建造了耶和华的殿。 33以下是负责歌乐的人及其后代:

哥辖的后代有希幔希幔约珥的儿子,约珥撒母耳的儿子, 34撒母耳以利加拿的儿子,以利加拿耶罗罕的儿子,耶罗罕以列的儿子,以列陀亚的儿子, 35陀亚苏弗的儿子,苏弗以利加拿的儿子,以利加拿玛哈的儿子,玛哈亚玛赛的儿子, 36亚玛赛以利加拿的儿子,以利加拿约珥的儿子,约珥亚撒利雅的儿子,亚撒利雅西番雅的儿子, 37西番雅他哈的儿子,他哈亚惜的儿子,亚惜以比雅撒的儿子,以比雅撒可拉的儿子, 38可拉以斯哈的儿子,以斯哈哥辖的儿子,哥辖利未的儿子,利未以色列的儿子。 39希幔的族兄和助手亚萨比利迦的儿子,比利迦示米亚的儿子, 40示米亚米迦勒的儿子,米迦勒巴西雅的儿子,巴西雅玛基雅的儿子, 41玛基雅伊特尼的儿子,伊特尼谢拉的儿子,谢拉亚大雅的儿子, 42亚大雅以探的儿子,以探薪玛的儿子,薪玛示每的儿子, 43示每雅哈的儿子,雅哈革顺的儿子,革顺利未的儿子。 44希幔亚萨的族兄和助手有米拉利的后代以探以探基示的儿子,基示亚伯底的儿子,亚伯底玛鹿的儿子, 45玛鹿哈沙比雅的儿子,哈沙比雅亚玛谢的儿子,亚玛谢希勒迦的儿子, 46希勒迦暗西的儿子,暗西巴尼的儿子,巴尼沙麦的儿子, 47沙麦末力的儿子,末力姆示的儿子,姆示米拉利的儿子,米拉利利未的儿子。 48希幔亚萨的同族弟兄利未人都奉派到会幕——上帝的殿中担任各种职务。

49亚伦和他的后代在祭坛和香坛上献祭烧香,负责至圣所里的各种工作,为以色列人赎罪,正如上帝的仆人摩西的吩咐。 50以下是亚伦的后代:以利亚撒非尼哈亚比书51布基乌西西拉希雅52米拉约亚玛利雅亚希突53撒督亚希玛斯

利未人住的地方

54以下是哥辖族人亚伦的后代分到的地方:

他们抽中第一签, 55得到了犹大境内的希伯仑城及其周围的草场, 56但城外的田地和村庄分给了耶孚尼的儿子迦勒57亚伦的子孙得到避难城希伯仑立拿及其周围的草场、雅提珥以实提莫及其周围的草场、 58希仑底璧59亚珊伯·示麦及这些城邑周围的草场。 60他们还得到了便雅悯支派的迦巴阿勒篾亚拿突及这些城邑周围的草场。他们各宗族所得的城邑共十三座。

61哥辖族其余的人从玛拿西半个支派中抽签分到了十座城。 62革顺各宗族的人从以萨迦亚设拿弗他利支派以及玛拿西支派的巴珊地区分到了十三座城。 63米拉利各宗族的人从吕便迦得西布伦支派抽签分到十二座城。 64以色列人把这些城邑及其周围的草场分给了利未人。 65以上提到的犹大西缅便雅悯支派的城邑也是用抽签的方式分给他们的。 66哥辖的一些宗族从以法莲支派分到城邑, 67其中有以法莲山区的避难城示剑及其周围的草场,还有基色68约缅伯·和仑69亚雅仑迦特·临门及这些城邑周围的草场。 70哥辖族其余的人从玛拿西半个支派中得到了亚乃比连城及其周围的草场。 71革顺族从玛拿西半个支派中得到了巴珊哥兰及其周围的草场,亚斯她录及其周围的草场。 72他们从以萨迦支派得到了基低斯大比拉73拉末亚念及这些城邑周围的草场。 74他们从亚设支派得到了玛沙押顿75户割利合及这些城邑周围的草场。 76他们从拿弗他利支派得到了加利利基低斯哈们基列亭及这些城邑周围的草场。 77米拉利族的人从西布伦支派得到了临摩挪他泊城及其周围的草场; 78约旦河东岸、耶利哥对面的吕便支派得到了旷野中的比悉雅哈撒79基底莫米法押及这些城邑的草场; 80迦得支派得到了基列拉末及其周围的草场、玛哈念81希实本雅谢及这些城邑周围的草场。

New Amharic Standard Version

1 ዜና መዋዕል 6:1-81

ሌዊ

1የሌዊ ወንዶች ልጆች፤

ጌድሶን፣ ቀዓት፣ ሜራሪ።

2የቀዓት ወንዶች ልጆች፤

እንበረም፣ ይስዓር፣ ኬብሮን፣ ዑዝኤል።

3የእንበረም ልጆች፤

አሮን፣ ሙሴ፣ ማርያም።

የአሮን ወንዶች ልጆች፤

ናዳብ፣ አብዩድ፣ አልዓዛር፣ ኢታምር።

4አልዓዛር ፊንሐስን ወለደ፤

ፊንሐስ አቢሱን ወለደ፤

5አቢሱ ቡቂን ወለደ፤

ቡቂ ኦዚን ወለደ፤

6ኦዚ ዘራእያን ወለደ፤

ዘራእያ መራዮትን ወለደ፤

7መራዮት አማርያን ወለደ፤

አማርያ አኪጦብን ወለደ፤

8አኪጦብ ሳዶቅን ወለደ፤

9ሳዶቅ አኪማአስን ወለደ፤

አኪማአስ ዓዛርያስን ወለደ፤

ዓዛርያስ ዮሐናንን ወለደ፤

10ዮሐናን ዓዛርያስን ወለደ፤ እርሱም ሰሎሞን በኢየሩሳሌም ባሠራው ቤተ መቅደስ በክህነት ያገለገለ ነበር፤

11ዓዛርያስ አማርያን ወለደ፤

አማርያም አኪጦብን ወለደ፤

12አኪጦብ ሳዶቅን ወለደ፤

ሳዶቅ ሰሎምን ወለደ፤

13ሰሎም ኬልቅያስን ወለደ፤

ኬልቅያስ ዓዛርያስን ወለደ፤

14ዓዛርያስ ሠራያን ወለደ፤

ሠራያ ኢዮሴዴቅን ወለደ።

15እግዚአብሔር የይሁዳና የኢየሩሳሌም ሕዝብ በናቡከደነፆር እጅ ተማርከው እንዲወሰዱ ባደረገ ጊዜ ኢዮሴዴቅም አብሮ ተማርኮ ሄደ።

16የሌዊ ወንዶች ልጆች፤

ጌድሶን፣ ቀዓት፣ ሜራሪ።

17የጌድሶን ወንዶች ልጆች፤

ሎቤኒ፣ ሰሜኢ።

18የቀሃት ወንዶች ልጆች፤

እንበረም፣ ይስዓር፣ ኬብሮን፣ ዑዝኤል።

19የሜራሪ ወንዶች ልጆች፤

ሞሖሊ፣ ሙሲ።

በየአባቶቻቸው ቤተ ሰብ የተቈጠሩት የሌዊ ጐሣዎች የሚከተሉት ናቸው፤

20ከጌርሶን፤

ልጁ ሎቤኒ፣ ልጁ ኢኤት፣

ልጁ ዛማት፣ 21ልጁ ዮአክ፣

ልጁ አዶ፣ ልጁ ዛራ፣ ልጁ ያትራይ።

22የቀዓት ዘሮች፤

ልጁ አሚናዳብ፣ ልጁ ቆሬ፣

ልጁ አሴር፣ 23ልጁ ሕልቃና፣

ልጁ አቢሳፍ፣ ልጁ አሴር፣

24ልጁ ኢኢት፣ ልጁ ኡርኤል፣

ልጁ ዖዝያ፣ ልጁ ሳውል።

25የሕልቃና ዘሮች፤

አማሢ፣ አኪሞት።

26ልጁ ሕልቃና፣6፥26 አንዳንድ የዕብራይስጥ ቅጆች፣ የሰብዓ ሊቃናት ትርጕምና የሱርስቱ ቅጅ ከዚህ ጋር ይስማማሉ፤ አብዛኞቹ የዕብራይስጥ ቅጆች ግን፣ ኪሞትና 26 ሕልቃና፤ የሕልቃና ወንዶች ልጆች፤ ልጁ ሱፊ፣

ልጁ ናሐት፣ 27ልጁ ኤልያብ፣

ልጁ ይሮሐም፣ ልጁ ሕልቃና፣

ልጁ ሳሙኤል6፥27 አንዳንድ የሰብዓ ሊቃናት ትርጕሞች (እንዲሁም 1ሳሙ 1፥1920 እና 1ዜና 6፥3334 ይመ) ከዚህ ጋር ይስማማሉ፤ ዕብራይስጡ ግን፣ ልጁ ሳሙኤል የሚለውን ሐረግ አይጨምርም

28የሳሙኤል ወንዶች ልጆች፤

የበኵር ልጁ ኢዮኤል6፥28 አንዳንድ የሰብዓ ሊቃናት ትርጕሞችና ሱርስቱ (እንዲሁም 1ሳሙ 8፥2 እና 1ዜና 6፥33 ይመ) ከዚህ ጋር ይስማማሉ፤ ዕብራይስጡ ግን፣ ኢዩኤል የሚለውን ስም አይጨምርም።

ሁለተኛው ልጁ አብያ።

29የሜራሪ ዘሮች፤

ሞሖሊ፣ ልጁ ሎቤኒ፣

ልጁ ሰሜኢ፣ ልጁ ዖዛ፣

30ልጁ ሳምዓ፣ ልጁ ሐግያ፣

ልጁ ዓሣያ።

የቤተ መቅደሱ መዘምራን

6፥54-80 ተጓ ምብ – ኢያ 21፥4-39

31ታቦቱ ከገባ በኋላ፣ ዳዊት የመዘምራን አለቃ አድርጎ በእግዚአብሔር ቤት የሾማቸው ሰዎች እነዚህ ናቸው፤ 32እነርሱም ሰሎሞን የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ በኢየሩሳሌም እስኪሠራ ድረስ፣ በማደሪያው፣ ይኸውም በመገናኛው ድንኳን ፊት ሆነው እየዘመሩ ያገለግሉ ነበር፤ አገልግሎታቸውንም የሚያከናውኑት በወጣላቸው ደንብ መሠረት ነው።

33ከወንዶች ልጆቻቸው ጋር ሆነው ያገለገሉ ሰዎች እነዚህ ናቸው፤

ከቀዓታውያን ልጆች፤ ዘማሪው ኤማን፣ የኢዮኤል ልጅ፣ የሳሙኤል ልጅ፣

34የሕልቃና ልጅ፣ የይሮሐም ልጅ፣

የኤሊኤል ልጅ፣ የቶዋ ልጅ፣

35የሱፍ ልጅ፣ የሕልቃና ልጅ፣

የመሐት ልጅ፣ የአማሢ ልጅ፣

36የሕልቃና ልጅ፣ የኢዮኤል ልጅ፣

የዓዛርያስ ልጅ፣ የሶፎንያስ ልጅ፣

37የታሐት ልጅ፣ የአሴር ልጅ፣

የአብያሳፍ ልጅ፣ የቆሬ ልጅ፣

38የይስዓር ልጅ፣ የቀዓት ልጅ፣

የሌዊ ልጅ፣ የእስራኤል ልጅ።

39እንዲሁም የሔማን ወንድም አሳፍ በስተ ቀኙ ሆኖ ያገለግል ነበር፤

አሳፍ የበራክያ ልጅ፣ የሳምዓ ልጅ፣

40የሚካኤል ልጅ፣ የበዓሤያ ልጅ፣

የመልክያ ልጅ፣ 41የኤትኒ ልጅ፣

የዛራ ልጅ፣ የዓዳያ ልጅ፣

42የኤታን ልጅ፣ የዛማት ልጅ፣

የሰሜኢ ልጅ፣ 43የኢኤት ልጅ፣

የጌድሶን ልጅ፣ የሌዊ ልጅ፤

44በስተ ግራቸው በኩል አብረዋቸው ያሉት የሜራሪ ልጆች፤

የቂሳ ልጅ ኤታን፣ የአብዲ ልጅ፣

የማሎክ ልጅ፣ 45የሐሸብያ ልጅ፣

የአሜስያስ ልጅ፣ የኬልቅያስ ልጅ፣

46የአማሲ ልጅ፣ የባኒ ልጅ፣

የሴሜር ልጅ፣ 47የሞሖሊ ልጅ፣

የሙሲ ልጅ የሜራሪ ልጅ፣

የሌዊ ልጅ።

48ሌዋውያን ወንድሞቻቸው ግን የእግዚአብሔርን ቤት የማደሪያ ድንኳን ተግባር እንዲያከናውኑ ተመድበው ነበር። 49የእግዚአብሔር ባሪያ ሙሴ ባዘዘው መሠረት፣ ስለ እስራኤል ማስተስረያ በቅድስተ ቅዱሳኑ ውስጥ የሚከናወነውን ተግባር ሁሉ፣ በመሠዊያው ላይ የሚቃጠል መሥዋዕትና በዕጣኑ መሠዊያ ላይ የሚቀርበውን መሥዋዕት የሚያቀርቡት ግን አሮንና ዘሮቹ ብቻ ነበሩ።

50የአሮን ዘሮች እነዚህ ነበሩ፤

ልጁ አልዓዛር፣ ልጁ ፊንሐስ፣

ልጁ አቢሱ 51ልጁ ቡቂ፣

ልጁ ኦዚ፣ ልጁ ዘራእያ፣

52ልጁ መራዮት፣ ልጁ አማርያ፣

ልጁ አኪጦብ፣ 53ልጁ ሳዶቅ፣

ልጁ አኪማአስ።

54መኖሪያዎቻቸው እንዲሆኑ የተመደቡላቸው ቦታዎች እነዚህ ናቸው፦ የመጀመሪያው ዕጣ የእነርሱ ስለሆነ፣ ከቀዓት ጐሣ ለሆኑት ለአሮን ዘሮች የተመደቡላቸው መኖሪያዎች እነዚህ ነበሩ።

55ለእነርሱም በይሁዳ ምድር የምትገኘው ኬብሮንና በዙሪያዋ ያለው የግጦሽ ቦታ ተሰጠ፤ 56በኬብሮን ዙሪያ የሚገኙት የዕርሻ ቦታዎችና መንደሮች ግን ለዮፎኒ ልጅ ለካሌብ ተሰጡ። 57ለአሮን ዘሮች የመማፀኛ ከተሞች የሆኑትን ኬብሮንን፣ ልብናን፣ የቲርን፣ ኤሽትሞዓን፣ 58ሖሎንን፣ ዳቤርን፣ 59ዓሳንን፣ ዮታን6፥59 የሱርስቱ ቅጅ (እንዲሁም የሰብዓ ሊቃናትና ኢያ 21፥16) ከዚህ ጋር ይስማማሉ፤ ዕብራይስጡ ግን፣ ዮታን የሚለውን ስም አይጨምርም።፣ ቤትሳሚስን ከነመሰማሪያዎቻቸው ሰጡ።

60ከብንያም ነገድ ድርሻ ላይ ገባዖንን፣6፥60 ኢያ 21፥17 ከዚህ ጋር ይስማማል፤ ዕብራይስጡ ግን ገባዖን የሚለውን ስም አይጨምርም። ጌባን፣ ጋሌማን፣ ዓናቶትን ከነመሰማሪያዎቻቸው ሰጡ።

ለቀዓት ዘሮች የተከፋፈሉት እነዚህ ከተሞች በአጠቃላይ ዐሥራ ሦስት ናቸው።

61ለቀሩት የቀዓት ዘሮች ደግሞ ከምናሴ ነገድ እኩሌታ ድርሻ ዐሥር ከተሞች ተሰጧቸው።

62ለጌድሶን ነገድ በየጐሣቸው ከይሳኮር፣ ከአሴር፣ ከንፍታሌምና በባሳን ከሚገኘው ከምናሴ ነገድ ድርሻ ላይ ዐሥራ ሦስት ከተሞች ተመደቡላቸው።

63ለሜራሪ ዘሮች በየጐሣቸው ከሮቤል፣ ከጋድና ከዛብሎን ድርሻ ላይ ዐሥራ ሁለት ከተሞች ተመደቡላቸው።

64እስራኤላውያንም ከተሞቹን በዚሁ ሁኔታ መድበው ከነመሰማሪያዎቻቸው ለሌዋውያኑ ሰጧቸው።

65ቀደም ብለው የተጠቀሱትንም ከተሞች ከይሁዳ፣ ከስምዖንና ከብንያም ነገድ ላይ ወስደው መደቡላቸው።

66ለአንዳንድ የቀዓት ጐሣዎችም ከኤፍሬም ነገድ ድርሻ ላይ የሚኖሩበት ቦታ ተሰጣቸው።

67በኰረብታማው በኤፍሬም ምድር የሚገኙትን የመማፀኛ ከተሞች ሴኬምን፣ ጌዝርን፣ 68ዮቅምዓምን፣ ቤትሖሮን፣ 69ኤሎንንና ጋትሪሞን ከነመሰማሪያዎቻቸው ሰጧቸው።

70እንዲሁም እስራኤላውያን ከምናሴ ነገድ እኩሌታ ድርሻ ላይ ዓኔርና ቢልዓም የተባሉትን ከተሞች ከነመሰማሪያዎቻቸው ወስደው ለቀሩት የቀዓት ጐሣዎች ሰጧቸው።

71ጌድሶናውያን ከዚህ የሚከተሉትን ከተሞች ወሰዱ፤

ከምናሴ ነገድ እኩሌታ፣ በባሳን የሚገኘውን ጎላንና አስታሮትን ከነመሰማሪያዎቻቸው ወሰዱ፤

72ከይሳኮርም ነገድ፣ ቃዴስን፣ ዳብራትን 73ራሞትንና ዓኔምናን ከነመሰማሪያዎቻቸው ወሰዱ፤

74ከአሴር ነገድ መዓሳልን፣ ዓብዶን፣ 75ሑቆቅንና፣ ረአብን ከነመሰማሪያዎቻቸው ወሰዱ፤

76ከንፍታሌም ነገድ በገሊላ የሚገኘውን ቃዴስን፣ ሐሞንንና፣ ቂርያታይምን ከነመሰማሪያዎቻቸው ወሰዱ።

77ከሌዋውያን የቀሩት የሜራሪ ጐሣዎች ደግሞ ከዚህ የሚከተለውን ወሰዱ፤

ከዛብሎን ነገድ ዮቅኒዓምን፣ ቀርታህን፣6፥77 የሰብዓ ሊቃናት ትርጕምንና ኢያ 21፥34 ይመ፤ ዕብራይስጡ ግን፣ ዮቅኒዓምን፣ ቀርታህን የሚለውን አይጨምርም። ሬሞንና፣ ታቦርን ከነመሰማሪያዎቻቸው ወሰዱ።

78ከዮርዳኖስ ወንዝ ማዶ ከኢያሪኮ በስተ ምሥራቅ ከሚገኘው ከሮቤል ነገድ፣

በምድረ በዳ የሚገኘውን ቦሶርን፣ ያሳን፣ 79ቅዴሞትንና ሜፍዓትን ከነመሰማሪያዎቻቸው ወሰዱ፤

80ከጋድ ነገድ በገለዓድ የምትገኘውን ሬማትን፣ መሃናይምን፣ 81ሐሴቦንና ኢያዜርን ከነመሰማሪያዎቻቸው ወሰዱ።