Daily Manna for Friday, May 7, 2021

Daily Manna is a daily Bible devotional service provided by Biblica. The Scripture is provided in many forms and is new every day. It is a great way to receive the encouragement and hope found in the Word of God.

Verse of the Day

መዝሙር 145:1-7

መዝሙር 145

አምላኬና ንጉሤ ሆይ፤ ከፍ ከፍ አደርግሃለሁ፤

ስምህን ከዘላለም እስከ ዘላለም እባርካለሁ።

በየቀኑ እባርክሃለሁ፤

ስምህንም ከዘላለም እስከ ዘላለም አመሰግናለሁ።

እግዚአብሔር ታላቅ ነው፤ እጅግ ሊመሰገንም ይገባዋል፤

ታላቅነቱም አይመረመርም።

ሥራህን አንዱ ትውልድ ለሌላው ትውልድ ያስተጋባል፤

ብርቱ ሥራህን ያውጃል።

ስለ ግርማህ ውበትና ክብር ይናገራሉ፤

ስለ ድንቅ ሥራህም ያወራሉ።

ስለ ድንቅ ሥራህ ብርታት ይነጋገራሉ፤

እኔም ስለ ታላቅነትህ ዐውጃለሁ።

የበጎነትህን ብዛት በደስታ ያወሳሉ፤

ስለ ጽድቅህም በእልልታ ይዘምራሉ።