ปฐมกาล 49 – TNCV & NASV

Thai New Contemporary Bible

ปฐมกาล 49:1-33

ยาโคบอวยพรบรรดาบุตรชาย

(ฉธบ.33:1-29)

1ยาโคบจึงเรียกบุตรชายทั้งหมดมากล่าวว่า “ล้อมวงกันเข้ามาเถิด เราจะบอกถึงสิ่งที่จะเกิดขึ้นกับพวกเจ้าในภายภาคหน้า

2“จงล้อมวงกันเข้ามาฟังเรา ลูกๆ ของยาโคบเอ๋ย

มาฟังอิสราเอลพ่อของเจ้าเถิด

3“รูเบน เจ้าเป็นลูกหัวปีของเรา

เจ้าเป็นอำนาจและเป็นผลแรกแห่งพละกำลังของเรา

เจ้าเป็นยอดแห่งเกียรติยศและพลังอำนาจ

4แต่เจ้าบ้าระห่ำเหมือนน้ำเชี่ยว เจ้าจะไม่ได้เป็นยอดอีกต่อไป

เพราะเจ้าล่วงล้ำเข้าไปถึงเตียงของพ่อ

เข้าไปถึงที่นอนของเรา และทำให้ที่นั่นแปดเปื้อนมลทิน

5“สิเมโอนกับเลวีเป็นพี่น้องกัน

ดาบ49:5 ในภาษาฮีบรูคำนี้มีความหมายไม่ชัดเจนของพวกเขาเป็นอาวุธเพื่อทำการอำมหิต

6อย่าให้เราเป็นพวกเดียวกันกับเขา

อย่าให้เราเข้าร่วมในที่ชุมนุมของพวกเขา

เพราะพวกเขาฆ่าคนเมื่อพวกเขาโกรธ

และตัดเอ็นขาวัวผู้เล่นตามความพอใจของเขา

7คำสาปแช่งจะตกอยู่แก่ความโกรธกริ้วอันเหี้ยมเกรียมของเขา

และตกอยู่แก่ความเดือดดาลอันโหดร้ายของเขา!

เราจะทำให้พวกเขาปะปนไปทั่วดินแดนของยาโคบ

และให้พวกเขากระจัดกระจายไปทั่วอิสราเอล

8“ยูดาห์49:8 คำว่ายูดาห์มีเสียงคล้ายและอาจมาจากคำภาษาฮีบรูที่มีความหมายว่าสรรเสริญเอ๋ย พี่น้องของเจ้าจะสรรเสริญเจ้า

มือของเจ้าจะขย้ำที่คอของศัตรู

พี่น้องร่วมสายโลหิตจะก้มกราบเจ้า

9ยูดาห์เอ๋ย เจ้าคือลูกสิงโต

ลูกของเราเอ๋ย เจ้ากลับมาจากกินเหยื่อ

เขาหมอบลงเหมือนราชสีห์

เขาเอนลงอย่างนางสิงห์ ใครจะกล้าไปแหย่เขาได้?

10คทาจะไม่พ้นจากมือของยูดาห์

อำนาจปกครองจะไม่ขาดไปจากเชื้อสายของเขา

จนกว่าบุคคลผู้เป็นเจ้าของอำนาจที่แท้จริงจะมาถึง49:10 หรือจนกว่าชิโลห์จะมาหรือจนกว่าคนที่เป็นเจ้าของบรรณาการจะมาถึง

บรรดาชนชาติจะเชื่อฟังผู้นั้น

11เขาจะผูกลาไว้ที่เถาองุ่น

ผูกลูกลาไว้ที่กิ่งที่ดีที่สุด

เขาจะซักล้างอาภรณ์ของตนในเหล้าองุ่น

ซักเสื้อผ้าในน้ำองุ่นสีเลือด

12ตาของเขาแวววาวกว่าเหล้าองุ่น

ฟันของเขาขาวยิ่งกว่าน้ำนม49:12 หรือตาของเขาจะเป็นสีหม่นจากเหล้าองุ่น / ฟันของเขาขาวจากน้ำนม

13“เศบูลุนจะอาศัยอยู่ริมฝั่งทะเล

และกลายเป็นท่าเทียบเรือ

ชายแดนของเขาจะขยายไปจนจดไซดอน

14“อิสสาคาร์เป็นเหมือนลาที่แข็งแรง

นอนลงทั้งที่แบกถุงสัมภาระทั้งสองอยู่49:14 หรือหมอบลงท่ามกลางฝูงแกะ

15เมื่อเขาเห็นว่าที่พักพิงดี

และแผ่นดินน่าอภิรมย์เพียงไร

เขาก็จะย่อบ่าของตนลงแบกภาระ

และยอมเป็นทาสรับใช้

16“ดาน49:16 ในที่นี้แปลว่าเขาให้ความเป็นธรรมจะให้ความเป็นธรรมแก่พลเมืองของตน

เหมือนให้แก่เผ่าอื่นๆ ในอิสราเอล

17เขาจะเป็นเหมือนงูตามริมทาง

เหมือนงูพิษที่อยู่ตามถนน

มันจะฉกส้นเท้าม้า

ให้คนขี่ตกจากหลังม้า

18“ข้าแต่องค์พระผู้เป็นเจ้าข้าพระองค์รอคอยการช่วยกู้ของพระองค์

19“กองโจรจะเข้าโจมตีกาด49:19 แปลว่าโจมตีและกองโจรก็ได้

แต่กาดจะโต้ตอบและดักตีส้นเท้าคนเหล่านั้น

20“อาหารของอาเชอร์อุดมสมบูรณ์

เขาจะเป็นแหล่งอาหารชั้นเลิศที่คู่ควรกับกษัตริย์

21“นัฟทาลีเป็นกวางตัวเมียที่ถูกปล่อยเป็นอิสระ

ตกลูกอ่อนน่ารักมากมาย49:21 หรือเขาเปล่งถ้อยคำไพเราะ

22“โยเซฟเป็นเถาองุ่นที่ผลิดอกออกผล

เป็นเถาองุ่นที่ผลิดอกออกผลอยู่ใกล้น้ำพุ

กิ่งเถาของมันเลื้อยข้ามกำแพง49:22 หรือโยเซฟเป็นลูกลาป่า / เป็นลูกลาป่าใกล้น้ำพุ / ลาป่าที่อยู่บนเนินเขาขั้นบันได

23พลธนูโจมตีเขาด้วยความเคียดแค้น

ยิงเข้าใส่เขาด้วยใจเกลียดชัง

24แต่ธนูของเขานิ่งไม่สั่นไหว

แขนของเขาแข็งแรงไม่อ่อนล้า49:23,24 หรือพลธนูจะโจมตี… / จะยิงเข้าใส่… / แต่ธนูของเขาจะนิ่งไม่สั่นไหว / แขนของเขาจะแข็งแรงไม่อ่อนล้า

เนื่องด้วยพระหัตถ์ขององค์ผู้ทรงฤทธิ์ของยาโคบ

เนื่องด้วยพระผู้เลี้ยง พระศิลาของอิสราเอล

25เนื่องด้วยพระเจ้าของบิดาเจ้าผู้ทรงช่วยเจ้า

เนื่องด้วยองค์ทรงฤทธิ์ผู้ทรงอวยพรเจ้า

ด้วยพรแห่งสวรรค์เบื้องบน

พรแห่งที่ลึกเบื้องล่าง

พรแห่งอ้อมอกและครรภ์

26พรจากบิดาของเจ้ายิ่งใหญ่

กว่าพรแห่งภูเขาดึกดำบรรพ์

กว่า49:26 หรือแห่งบรรพบุรุษของข้า / ยิ่งใหญ่เท่ากับความอุดมแห่งเนินเขาเก่าแก่

ขอพระพรเหล่านี้จงอยู่บนศีรษะของโยเซฟ

อยู่บนกระหม่อมของเจ้าผู้ยิ่งใหญ่ท่ามกลาง49:26 หรือผู้ที่แยกจากพี่น้องของเจ้า

27“เบนยามินเป็นสุนัขป่าที่หิวโซ

ในตอนเช้าเขาขย้ำเหยื่อ

ในตอนเย็นเขาแบ่งของที่ยึดมาได้”

28ทั้งหมดนี้คืออิสราเอลสิบสองเผ่า และนี่เป็นคำพูดของยาโคบบิดาของพวกเขาเมื่ออวยพรลูกๆ โดยให้พรแต่ละคนตามที่เขาเห็นควร

ยาโคบสิ้นชีวิต

29แล้วยาโคบก็สั่งพวกเขาว่า “เรากำลังจะถูกรวบไปอยู่กับคนของเรา จงฝังเราไว้ร่วมกับบรรพบุรุษในถ้ำซึ่งอยู่ในทุ่งของเอโฟรนชาวฮิตไทต์ 30ถ้ำนี้อยู่ในทุ่งมัคเปลาห์ใกล้มัมเรในคานาอัน ที่อับราฮัมได้ซื้อพร้อมกับทุ่งนาจากเอโฟรนชาวฮิตไทต์เพื่อเป็นสุสาน 31ที่นั่นเป็นที่ฝังอับราฮัมกับซาราห์ภรรยาของเขา เป็นที่ฝังอิสอัคกับเรเบคาห์ภรรยาของเขา และเป็นที่ซึ่งเราได้ฝังเลอาห์ไว้ 32ทุ่งนาและถ้ำนั้นซื้อมาจากคนฮิตไทต์49:32 หรือลูกหลานทั้งหลายของเฮท

33เมื่อยาโคบสั่งเสียลูกชายทั้งหลายของเขาจบแล้วก็ยกเท้าขึ้นนอนลงบนที่นอน แล้วเขาก็สิ้นใจ ถูกรวมไปอยู่กับบรรพบุรุษของเขา

New Amharic Standard Version

ዘፍጥረት 49:1-33

ያዕቆብ ልጆቹን ባረከ

49፥1-28 ተጓ ምብ – ዘዳ 33፥1-29

1ከዚህ በኋላ ያዕቆብ ልጆቹን ሁሉ አስጠርቶ እንዲህ አላቸው፤ “በኋለኛው ዘመን ምን እንደሚደርስባችሁ እነግራችሁ ዘንድ ተሰብሰቡ፤

2“እናንተ የያዕቆብ ልጆች ሆይ፤

ተሰብሰቡና ስሙ፤

አባታችሁ እስራኤልንም አድምጡ፤

3“ሮቤል፣ አንተ የበኵር ልጄ ነህ፤

ኀይሌና የጕብዝናዬም መጀመሪያ፤

በክብር ትልቃለህ፤ በኀይልም

ትበልጣለህ።

4እንደ ውሃ የዋለልህ ነህና እልቅና

አይኖርህም፤

የአባትህን መኝታ ደፍረሃል፤

ምንጣፌንም አርክሰሃል።

5“ስምዖንና ሌዊ ወንድማማቾች፣

ሰይፎቻቸው49፥5 በዕብራይስጥ የዚህ ቃል ትርጕም አይታወቅም። የዐመፅ መሣሪያዎች ናቸው።

6ወደ ሸንጓቸው አልግባ፤

ጉባኤያቸው ውስጥ አልገኝ፤

በቍጣ ተነሣሥተው ሰዎችን ገድለዋል፤

የበሬዎችንም ቋንጃ እንዳሻቸው ቈራርጠዋል።

7እጅግ አስፈሪ የሆነ ቍጣቸው፣

ጭከና የተሞላ ንዴታቸው የተረገመ ይሁን፤

በያዕቆብ እበትናቸዋለሁ፤

በመላው እስራኤልም አሠራጫቸዋለሁ።

8“ይሁዳ፣49፥8 ይሁዳ የሚለው ቃል ውዳሴ የሚል ትርጕም ካለው የዕብራይስጥ ቃል የመጣ ሲሆን፣ ከዚሁ ቃል ጋር አንድ ዐይነት ድምፅ አለው። ወንድሞችህ ይወድሱሃል፤

እጅህም የጠላቶችህን ዐንገት ዐንቆ ይይዛል፤

የአባትህ ልጆች በፊትህ ተደፍተው ይሰግዱልሃል።

9አንተ የአንበሳ ደቦል ይሁዳ፤

ከዐደንህ የምትመለስ ልጄ፣

እንደ አንበሳ ያደፍጣል፤ በምድርም ላይ ይተኛል፤

እንደ እንስት አንበሳም ያደባል፤

ታዲያ ማን ሊቀሰቅሰው ይደፍራል?

10በትረ መንግሥት ከይሁዳ እጅ አይወጣም፤

የገዥነት ምርኵዝም ከእግሮቹ መካከል።

ገዥነት የሚገባው እስኪመጣ ድረስ፣49፥10 ወይም ሴሎ እስኪመጣ ድረስ ወይም ክብር የሚገባው እስኪመጣ ድረስ

ሕዝቦች ሁሉ ይታዘዙታል።

11አህያውን በወይን ግንድ፣

ውርንጫውንም በምርጡ የወይን ሐረግ

ቅርንጫፍ ላይ ያስራል፤

ልብሱን በወይን ጠጅ፣

መጐናጸፊያውንም በወይን ጭማቂ ያጥባል።

12ዐይኖቹ ከወይን ጠጅ የቀሉ፣

ጥርሶቹም ከወተት ይልቅ የነጡ ይሆናሉ።

13“ዛብሎን፣ በባሕር ዳር ይኖራል፤

የመርከቦች መጠጊያም ይሆናል፤

ወሰኑም እስከ ሲዶና ይደርሳል።

14“ይሳኮር፣ በጭነት49፥14 የመስክ ላይ እሳት መካከል የሚተኛ

ዐጥንተ ብርቱ አህያ ነው።

15ማረፊያ ቦታው መልካም፣

ምድሪቱም አስደሳች መሆኗን ሲያይ፣

ትከሻውን ለሸክም ያመቻቻል፤

ተገድዶም ያገለግላል።

16“ዳን፣49፥16 ዳን ማለት ፍትሕ ይሰጣል ማለት ነው። ከእስራኤል ነገዶች እንደ አንዱ ሆኖ፣

በራሱ ሕዝብ ላይ ይፈርዳል።

17ዳን የመንገድ ዳር እባብ፣

የመተላለፊያም መንገድ እፉኝት ነው፤

ጋላቢው የኋሊት እንዲወድቅ፣

የፈረሱን ሰኰና ይነክሳል።

18እግዚአብሔር ሆይ (ያህዌ)፤ ማዳንህን እጠባበቃለሁ።

19“ጋድን49፥19 ጋድ ማለት ማጥቃት እንዲሁም ወራሪ ሰራዊት ማለት ነው። ወራሪዎች አደጋ ይጥሉበታል፤

እርሱ ግን ዱካቸውን ተከታትሎ ብድሩን ይመልሳል።

20“አሴር ማእደ ሰፊ ይሆናል፤

ለነገሥታትም የሚስማማ ምግብ ያቀርባል።

21“ንፍታሌም ነጻ እንደ ተለቀቀች፣

የሚያማምሩም ግልገሎች49፥21 ወይም ነጻ፤ ውብ ቃሎችን የሚናገር

እንደምትወልድ ሚዳቋ ነው።

22“ዮሴፍ፤ ፍሬያማ የወይን ተክል፣

በምንጭ ዳር የተተከለ ወይን ነው።

ሐረጎቹ ቅጥርን ያለብሳሉ።49፥22 ወይም ዮሴፍ የዱር የፈረስ ግልገል፣ በምንጭ ዳር ያለ የፈረስ ግልገል፣ በባለ ዕርከን ኰረብታ ላይ የዱር አህያ ነው

23ቀስተኞች በጭካኔ አጠቁት፤

በጥላቻም ነደፉት።

24ነገር ግን በያዕቆብ ኀያል አምላክ ክንድ፣49፥23-24 ወይም ቀስተኞች ያጠቃሉ… ያስፈነጥራሉ… ይኖራሉ… ይቈያሉ

እረኛው በሆነው በእስራኤል ዐለት፣ ቀስቱ ጸና፤

ጠንካራ ክንዱም ቀለጠፈ።

25አንተን በሚረዳህ በአባትህ አምላክ፣

በሚባርክህ፣ ሁሉን ማድረግ በሚችል አምላክ፣49፥25 ዕብራይስጡ ሻዳይ ይለዋል

ከላይ ከሰማይ በሚገኝ ረድኤት፣

ከምድር ጥልቅ በሚገኝ በረከት፣

ከማሕፀንና ከጡት በሚገኝ ምርቃት ይባርክሃል።

26ከጥንት ተራሮች በረከት፣

ከዘላለም ኰረብቶች ምርቃት ይልቅ፣

የአባትህ በረከት ይበልጣል።49፥26 …ከአያት ቅድማያቶቼ… ታላቅ ነው

ይህ ሁሉ በዮሴፍ ራስ ላይ ይውረድ፤

በወንድሞቹ መካከል አለቃ በሆነውም ግንባር ላይ ይረፍ።49፥26 ወይም ከ… የተለየ

27“ብንያም፣ ነጣቂ ተኵላ ነው፤

ያደነውን ማለዳ ይበላል፤

የማረከውን ማታ ይከፋፈላል።”

28እነዚህ ሁሉ ዐሥራ ሁለቱ የእስራኤል ነገዶች ናቸው። ይህም እያንዳንዳቸውን ተገቢ በሆነው በረከት አባታቸው ሲባርካቸው የተናገረው ቃል ነው።

የያዕቆብ መሞት

29ከዚህ በኋላ ያዕቆብ እንዲህ ሲል አዘዛቸው፤ “እነሆ፤ ወደ ወገኖቼ የምሰበሰብበት ጊዜ ደርሷል፤ በኬጢያዊው በኤፍሮን ዕርሻ ውስጥ ባለችው ዋሻ ከአባቶቼ ዘንድ ቅበሩኝ፤ 30ይህ በከነዓን ምድር፣ በመምሬ አጠገብ፣ በማክፌላ ዕርሻ ውስጥ ያለው ዋሻ፣ የመቃብር ቦታ እንዲሆን አብርሃም ከኬጢያዊው ኤፍሮን ላይ ከነዕርሻ ቦታው የገዛው ነው። 31በዚያ አብርሃምና ሚስቱ ሣራ ተቀብረዋል፤ በዚያ ይስሐቅና ሚስቱ ርብቃ ተቀብረዋል፤ 32እኔም ልያን የቀበርኋት እዚያው ነው። ዕርሻውና ዋሻው የተገዙት ከኬጢያውያን49፥32 ወይም ከኬጢ ልጆች ላይ ነው።”

33ያዕቆብ እነዚህን ቃላት ለልጆቹ ተናግሮ እንዳበቃ፣ እግሮቹን በዐልጋው ላይ ሰብስቦ፣ የመጨረሻ ትንፋሹን ተነፈሰ፤ ወደ ወገኖቹም ተሰበሰበ።