ดาเนียล 12 – TNCV & NASV

Thai New Contemporary Bible

ดาเนียล 12:1-13

วาระสุดท้าย

1“ครั้งนั้นเทพบดีมีคาเอลผู้พิทักษ์ประชากรของท่านจะมา จะเกิดช่วงทุกข์ลำเค็ญอย่างที่ไม่เคยมีมาก่อนตั้งแต่มีประชาชาติขึ้น แต่ในครั้งนั้นประชากรของท่านคือทุกคนที่มีชื่ออยู่ในหนังสือนั้นจะได้รับการช่วยกู้ 2คนเป็นอันมากที่ตายไปแล้วจะฟื้นขึ้น บางคนก็เข้าสู่ชีวิตนิรันดร์ บางคนก็เข้าสู่ความอับอายและถูกดูหมิ่นเหยียดหยามตลอดกาล 3บรรดาผู้มีปัญญา12:3 หรือผู้ให้ปัญญาจะส่องแสงเหมือนความสว่างแห่งฟ้าสวรรค์ และบรรดาผู้ที่นำคนเป็นอันมากมาสู่ความชอบธรรมจะส่องสว่างดั่งดวงดาวชั่วนิรันดร์ 4ส่วนท่าน ดาเนียลเอ๋ย จงม้วนและประทับตราถ้อยคำแห่งหนังสือม้วนนี้ไว้จนถึงวาระสุดท้าย คนเป็นอันมากจะไปที่นี่ที่นั่นเพื่อเพิ่มพูนความรู้”

5แล้วข้าพเจ้าดาเนียลมองไปเห็นชายสองคนยืนอยู่คนละฟากแม่น้ำ 6คนหนึ่งกล่าวกับผู้สวมเสื้อผ้าลินินซึ่งอยู่เหนือแม่น้ำว่า “อีกนานเท่าใดเหตุการณ์น่าประหลาดทั้งปวงนี้จึงจะสำเร็จครบถ้วน?”

7ชายผู้สวมเสื้อผ้าลินินซึ่งอยู่เหนือแม่น้ำก็ชูมือทั้งสองข้างขึ้นสู่ฟ้าสวรรค์และข้าพเจ้าได้ยินเขาปฏิญาณอ้างพระองค์ผู้ทรงพระชนม์อยู่เป็นนิตย์ว่า “จะเป็นหนึ่งวาระ หลายวาระ และครึ่งวาระ12:7 หรือหนึ่งปี สองปี และครึ่งปีเมื่ออำนาจของประชากรของพระเจ้าหมดสิ้นลง ในที่สุดสิ่งทั้งปวงนี้ก็จะสำเร็จสมบูรณ์”

8ข้าพเจ้าได้ยินแต่ไม่เข้าใจจึงถามว่า “ท่านเจ้าข้า ทั้งหมดนี้จะลงเอยอย่างไร?”

9เขาผู้นั้นตอบว่า “ดาเนียลเอ๋ย จงไปตามทางของท่านเถิด เพราะถ้อยคำเหล่านี้ถูกเก็บงำและประทับตราไว้จวบจนวาระสุดท้าย 10คนเป็นอันมากจะถูกถลุงและได้รับการชำระให้บริสุทธิ์ปราศจากตำหนิ ส่วนคนชั่วยังคงทำชั่วต่อไป ไม่มีคนชั่วคนใดจะเข้าใจแต่ผู้มีปัญญาจะเข้าใจ

11“ตั้งแต่ยกเลิกการถวายเครื่องบูชาประจำวันจนถึงวาระที่สิ่งที่น่าสะอิดสะเอียนอันเป็นต้นเหตุของวิบัติถูกตั้งขึ้นเป็นเวลา 1,290 วัน 12ผู้ที่รอคอยและอยู่จนครบ 1,335 วันก็เป็นสุข

13“ส่วนท่านจงไปตามทางของท่านจวบจนวาระสุดท้าย ท่านจะพักสงบและเมื่อสิ้นยุคท่านจะเป็นขึ้นมาเพื่อรับมรดกส่วนของท่าน”

New Amharic Standard Version

ዳንኤል 12:1-13

የመጨረሻ ዘመን

1“በዚያን ዘመን ስለ ሕዝብህ የሚቆመው ታላቁ አለቃ ሚካኤል ይነሣል። መንግሥታት ከተመሠረቱበት ጊዜ ጀምሮ እስከዚያ ዘመን ድረስ ታይቶ የማይታወቅ ታላቅ የመከራ ጊዜ ይሆናል። ነገር ግን በዚያን ጊዜ ስማቸው በመጽሐፉ ተጽፎ የተገኘው ሕዝብህ ሁሉ ይድናሉ። 2በምድር ዐፈር ውስጥ ካንቀላፉት ብዙዎች ይነቃሉ፤ አንዳንዶቹ ለዘላለም ሕይወት፣ ሌሎቹም ለውርደትና ለዘላለም ጕስቍልና ይነሣሉ። 3ጥበበኞች12፥3 ወይም ጥበብን የሚገልጡ እንደ ሰማይ ጸዳል፣ ብዙዎችንም ወደ ጽድቅ የሚመልሱ እንደ ከዋክብት ለዘላለም ይደምቃሉ። 4ዳንኤል ሆይ፤ አንተ ግን፣ እስከ ፍጻሜው ዘመን ድረስ የመጽሐፉን ቃል ዝጋ፤ ዐትመውም። ብዙዎች ወዲያ ወዲህ ይራወጣሉ፤ ዕውቀትም ይበዛል።”

5እኔም ዳንኤል ተመለከትሁ፤ እነሆ ከፊት ለፊቴ ሌሎች ሁለት ቆመው ነበር፤ አንዱ ከወንዙ በዚህኛው ዳር፣ ሌላው ደግሞ ከወንዙ በዚያኛው ዳር። 6ከእነርሱም አንዱ፣ ከወንዙ ውሃ በላይ የነበረውንና በፍታ የለበሰውን ሰው፣ “እነዚህ አስደናቂ ነገሮች ሊፈጸሙ ምን ያህል ጊዜ ይቀራል?” አለው።

7ከወንዙ ውሃ በላይ የነበረው በፍታ የለበሰው ሰው፣ ቀኝ እጁንና ግራ እጁን ወደ ሰማይ አንሥቶ፣ “ለዘመን፣ ለዘመናት፣ ለዘመንም እኩሌታ12፥7 ወይም ለዓመት፣ ለሁለት ዓመታት፣ ለዓመትም እኩሌታ ይሆናል፤ የተቀደሰው ሕዝብ ኀይል መሰበር ሲያከትም፣ እነዚህ ሁሉ ነገሮች ይፈጸማሉ” ብሎ ለዘላለም በሚኖረው በእርሱ ሲምል ሰማሁ።

8እኔም ሰማሁ፤ ነገር ግን አላስተዋልሁትም፤ ስለዚህ፣ “ጌታዬ ሆይ፤ የዚህ ሁሉ ፍጻሜ ምንድን ነው?” ብዬ ጠየቅሁ።

9እርሱም እንዲህ አለኝ፤ “ዳንኤል ሆይ፤ ቃሉ እስከ ፍጻሜው ዘመን ድረስ የተዘጋና የታተመ ስለሆነ ሂድ። 10ብዙዎች ይነጻሉ፤ ይጠራሉ፤ እንከን አልባም ይሆናሉ፤ ክፉዎች ግን በክፋታቸው ይጸናሉ፤ ከክፉዎች አንዳቸውም አያስተውሉም፤ ጠቢባን ግን ያስተውላሉ።

11“የዘወትሩ መሥዋዕት ከተቋረጠበትና ጥፋትን የሚያመጣው የጥፋት ርኩሰት ከተተከለበት ጊዜ ጀምሮ አንድ ሺሕ ሁለት መቶ ዘጠና ቀን ይሆናል። 12የሚታገሥና እስከ አንድ ሺሕ ሦስት መቶ ሠላሳ አምስት ቀን ፍጻሜ የሚደርስ የተባረከ ነው።

13“አንተ ግን እስከ ፍጻሜው ድረስ ሂድ፤ ታርፋለህ፤ በቀኖቹ መጨረሻም ተነሥተህ የተመደበልህን ርስት ትቀበላለህ።”