กันดารวิถี 26 – TNCV & NASV

Thai New Contemporary Bible

กันดารวิถี 26:1-65

สำมะโนประชากรครั้งที่สอง

1หลังจากภัยพิบัติยุติลงแล้ว องค์พระผู้เป็นเจ้าตรัสกับโมเสสและเอเลอาซาร์บุตรปุโรหิตอาโรนว่า 2“จงทำสำมะโนประชากรชายทุกคนในอิสราเอลที่มีอายุยี่สิบปีขึ้นไป เพื่อสำรวจว่าในแต่ละครอบครัวมีใครบ้างที่สามารถออกรบได้” 3ดังนั้นโมเสสและปุโรหิตเอเลอาซาร์จึงแจ้งพวกเขาขณะตั้งค่ายอยู่ในที่ราบโมอับริมแม่น้ำจอร์แดนตรงข้ามเมืองเยรีโค26:3 ภาษาฮีบรูว่าจอร์แดนแห่งเยรีโคอาจจะเป็นชื่อโบราณของแม่น้ำจอร์แดน เช่นเดียวกับข้อ 63ว่า 4“จงทำสำมะโนประชากรชายอายุยี่สิบปีขึ้นไปตามที่องค์พระผู้เป็นเจ้าตรัสสั่งโมเสส”

ชนอิสราเอลที่ออกมาจากอียิปต์ ได้แก่

5วงศ์วานของรูเบนบุตรหัวปีของอิสราเอลได้แก่

ตระกูลฮาโนคจากฮาโนค

ตระกูลปัลลูจากปัลลู

6ตระกูลเฮสโรนจากเฮสโรน

ตระกูลคารมีจากคารมี

7ทั้งหมดนี้คือตระกูลต่างๆ ของรูเบน นับได้ 43,730 คน

8บุตรชายของปัลลูคือเอลีอับ 9และบุตรชายของเอลีอับคือ เนมูเอล ดาธาน และอาบีรัม ดาธานและอาบีรัมนี้เป็นเจ้าหน้าที่ของชุมชนซึ่งได้กบฏต่อโมเสสและต่ออาโรน และเป็นพรรคพวกของโคราห์เมื่อเขากบฏต่อองค์พระผู้เป็นเจ้า 10พื้นธรณีแยกออกและสูบพวกเขาลงไปพร้อมกับโคราห์ และพรรคพวกของเขา 250 คนถูกไฟคลอกตาย และนั่นเป็นเครื่องเตือนเหล่าประชากร 11แต่เชื้อสายโคราห์ไม่ได้สูญสิ้นไป

12วงศ์วานของสิเมโอนแยกตามตระกูล ได้แก่

ตระกูลเนมูเอลจากเนมูเอล

ตระกูลยามีนจากยามีน

ตระกูลยาคีนจากยาคีน

13ตระกูลเศราห์จากเศราห์

และตระกูลชาอูลจากชาอูล

14ทั้งหมดนี้คือตระกูลต่างๆ ของสิเมโอน นับได้ 22,200 คน

15วงศ์วานของกาดแยกตามตระกูล ได้แก่

ตระกูลเศโฟนจากเศโฟน

ตระกูลฮักกีจากฮักกี

ตระกูลชูนีจากชูนี

16ตระกูลโอสนีจากโอสนี

ตระกูลเอรีจากเอรี

17ตระกูลอาโรดี26:17 ฉบับ MT. ว่าอาโรดจากอาโรดี

และตระกูลอาเรลีจากอาเรลี

18ทั้งหมดนี้คือตระกูลต่างๆ ของกาด นับได้ 40,500 คน

19เอร์และโอนันบุตรชายของยูดาห์เสียชีวิตที่คานาอัน

20วงศ์วานของยูดาห์แยกตามตระกูล ได้แก่

ตระกูลเชลาห์จากเชลาห์

ตระกูลเปเรศจากเปเรศ

ตระกูลเศราห์จากเศราห์

21วงศ์วานของเปเรศ ได้แก่

ตระกูลเฮสโรนจากเฮสโรน

และตระกูลฮามูลจากฮามูล

22ทั้งหมดนี้คือตระกูลต่างๆ ของยูดาห์ นับได้ 76,500 คน

23วงศ์วานของอิสสาคาร์แยกตามตระกูล ได้แก่

ตระกูลโทลาจากโทลา

ตระกูลปูวาห์จากปูวาห์

24ตระกูลยาชูบจากยาชูบ

และตระกูลชิมโรนจากชิมโรน

25ทั้งหมดนี้คือตระกูลต่างๆ ของอิสสาคาร์ นับได้ 64,300 คน

26วงศ์วานของเศบูลุน แยกตามตระกูลได้แก่

ตระกูลเสเรดจากเสเรด

ตระกูลเอโลนจากเอโลน

และตระกูลยาเลเอลจากยาเลเอล

27ทั้งหมดนี้คือตระกูลต่างๆ ของเศบูลุน นับได้ 60,500 คน

28วงศ์วานของโยเซฟแยกตามตระกูลนับตามมนัสเสห์และเอฟราอิมคือ

29วงศ์วานของมนัสเสห์ ได้แก่

ตระกูลมาคีร์จากมาคีร์

(มาคีร์เป็นบิดาของกิเลอาด)

ตระกูลกิเลอาดจากกิเลอาด

30วงศ์วานของกิเลอาด ได้แก่

ตระกูลอีเยเซอร์จากอีเยเซอร์

ตระกูลเฮเลคจากเฮเลค

31ตระกูลอัสรีเอลจากอัสรีเอล

ตระกูลเชเคมจากเชเคม

32ตระกูลเชมิดาจากเชมิดา

และตระกูลเฮเฟอร์จากเฮเฟอร์

33(เศโลเฟหัดบุตรเฮเฟอร์ไม่มีบุตรชาย

มีแต่บุตรสาวได้แก่ มาห์ลาห์ โนอาห์ โฮกลาห์ มิลคาห์และทีรซาห์)

34ทั้งหมดนี้คือตระกูลต่างๆ ของมนัสเสห์ นับได้ 52,700 คน

35วงศ์วานของเอฟราอิมแยกตามตระกูล ได้แก่

ตระกูลชูเธลาห์จากชูเธลาห์

ตระกูลเบเคอร์จากเบเคอร์

ตระกูลทาหานจากทาหาน

36วงศ์วานของชูเธลาห์คือ

ตระกูลเอรานจากเอราน

37ทั้งหมดนี้คือตระกูลต่างๆ ของเอฟราอิมนับได้ 32,500 คน

ทั้งหมดนี้คือวงศ์วานของโยเซฟแยกตามตระกูล

38วงศ์วานของเบนยามินแยกตามตระกูล ได้แก่

ตระกูลเบลาจากเบลา

ตระกูลอัชเบลจากอัชเบล

ตระกูลอาหิรัมจากอาหิรัม

39ตระกูลชูฟาม26:39 สำเนาฉบับ MT.ส่วนมากว่าเชฟูฟามจากชูฟาม

และตระกูลหุฟามจากหุฟาม

40วงศ์วานของเบลาทางอาร์ดและนาอามาน ได้แก่

ตระกูลอาร์ดจากอาร์ด26:40 ฉบับ MT. ไม่มีวลีว่าจากอาร์ด

และตระกูลนาอามานจากนาอามาน

41ทั้งหมดนี้คือตระกูลต่างๆ ของเบนยามิน นับได้ 45,600 คน

42วงศ์วานของดานแยกตามตระกูลคือ

ตระกูลชูฮัมจากชูฮัม

นี่คือตระกูลของดาน 43ทั้งหมดล้วนอยู่ในตระกูลชูฮัม รวม 64,400 คน

44วงศ์วานของอาเชอร์แยกตามตระกูล ได้แก่

ตระกูลอิมนาห์จากอิมนาห์

ตระกูลอิชวีจากอิชวี

ตระกูลเบรียาห์จากเบรียาห์

45และวงศ์วานของตระกูลเบรียาห์ ได้แก่

ตระกูลเฮเบอร์จากเฮเบอร์

ตระกูลมัลคีเอลจากมัลคีเอล

46(อาเชอร์มีบุตรสาวคนหนึ่งชื่อเสราห์)

47ทั้งหมดนี้คือตระกูลต่างๆ ของอาเชอร์นับได้ 53,400 คน

48วงศ์วานของนัฟทาลีแยกตามตระกูล ได้แก่

ตระกูลยาเซเอลจากยาเซเอล

ตระกูลกูนีจากกูนี

49ตระกูลเยเซอร์จากเยเซอร์

ตระกูลชิลเลมจากชิลเลม

50ทั้งหมดนี้คือตระกูลต่างๆ ของนัฟทาลีนับได้ 45,400 คน

51รวมพลอิสราเอลทั้งหมดได้ 601,730 คน

52องค์พระผู้เป็นเจ้าตรัสสั่งโมเสสว่า 53“จงแบ่งดินแดนแก่เผ่าต่างๆ ตามสัดส่วนจำนวนคนที่นับได้ 54เผ่าใหญ่ได้รับที่ดินมาก และเผ่าที่เล็กกว่าได้รับที่ดินน้อยลงตามส่วน และแต่ละกลุ่มจะได้รับมรดกตามจำนวนรายชื่อที่ขึ้นทะเบียนไว้ 55ให้จับฉลากแบ่งดินแดน แต่ละกลุ่มได้ครองกรรมสิทธิ์ตามจำนวนรายชื่อเผ่าบรรพบุรุษ 56แบ่งสรรกรรมสิทธิ์โดยจับฉลากตามส่วนเผ่าใหญ่และเผ่าเล็ก”

57ต่อไปนี้คือเผ่าเลวีนับตามตระกูล ได้แก่

ตระกูลเกอร์โชนจากเกอร์โชน

ตระกูลโคฮาทจากโคฮาท

ตระกูลเมรารีจากเมรารี

58ต่อไปนี้ก็คือตระกูลของเลวีด้วย ได้แก่

ตระกูลลิบนี

ตระกูลเฮโบรน

ตระกูลมาห์ลี

ตระกูลมูชี

ตระกูลโคราห์

(โคฮาทเป็นบรรพบุรุษของอัมราม 59ภรรยาของอัมรามชื่อโยเคเบดผู้เป็นเชื้อสายของเลวี ซึ่งเป็นบุตรสาวของชาวเลวี26:59 หรือโยเคเบดเป็นบุตรสาวของเลวี ที่เกิดในอียิปต์ อัมรามมีบุตรชายคืออาโรนกับโมเสส และบุตรสาวชื่อมิเรียม 60อาโรนมีบุตรชื่อ นาดับ อาบีฮู เอเลอาซาร์ และอิธามาร์ 61แต่นาดับและอาบีฮูสิ้นชีวิตไปเมื่อครั้งจุดไฟที่ไม่ได้รับอนุญาตต่อหน้าองค์พระผู้เป็นเจ้า)

62จำนวนผู้ชายทั้งหมดในตระกูลเลวีอายุหนึ่งเดือนขึ้นไปนับได้ 23,000 คน แต่ไม่ได้นับรวมเข้าในสำมะโนประชากรของอิสราเอล เพราะชาวเลวีไม่ได้รับส่วนแบ่งที่ดินเหมือนตระกูลอื่นๆ

63ทั้งหมดนี้คือสำมะโนประชากรซึ่งโมเสสและปุโรหิตเอเลอาซาร์จัดทำขึ้นในที่ราบโมอับริมแม่น้ำจอร์แดนตรงข้ามเมืองเยรีโค 64ไม่มีสักคนเดียวในสำมะโนประชากรนี้ที่มีชื่ออยู่ในสำมะโนประชากรคราวก่อนซึ่งโมเสสและปุโรหิตอาโรนทำขึ้นในถิ่นกันดารซีนาย 65ตามที่องค์พระผู้เป็นเจ้าได้ตรัสแก่ชาวอิสราเอลเหล่านั้นว่าพวกเขาจะตายในถิ่นกันดารแน่นอน ยกเว้นคาเลบบุตรเยฟุนเนห์และโยชูวาบุตรนูน

New Amharic Standard Version

ዘኍል 26:1-65

ሁለተኛው የሕዝብ ቈጠራ

1ከመቅሠፍቱ በኋላ እግዚአብሔር (ያህዌ) ሙሴንና የካህኑን የአሮንን ልጅ አልዓዛርን እንዲህ አላቸው፤ 2“ዕድሜያቸው ሃያ ዓመትና ከዚያ በላይ የሆናቸውን፣ በእስራኤልም ጦር ሰራዊት ውስጥ ለማገልገል ብቃት ያላቸውን ሁሉ ከመላው የእስራኤል ማኅበረ ሰብ ከየቤተ ሰቡ ቍጠሩ።” 3ስለዚህ ሙሴና ካህኑ አልዓዛር ከኢያሪኮ26፥3 በዕብራይስጥ የኢያሪኮ ዮርዳኖስ የሚባል ሲሆን፤ ይህም የዮርዳኖስ ወንዝ የጥንት ስም ሳይሆን አይቀርም። ማዶ በዮርዳኖስ አጠገብ ባለው በሞዓብ ሜዳ ለሕዝቡ እንዲህ ሲሉ ተናገሩ፤ 4እግዚአብሔር (ያህዌ) ሙሴን ባዘዘው መሠረት ዕድሜያቸው ሃያና ከዚያ በላይ የሆነውን ቍጠሩ።”

ከግብፅ የወጡት እስራኤላውያንም እነዚህ ነበሩ፤

5የእስራኤል የበኵር ልጅ የሆነው የሮቤል ዘሮች እነዚህ ነበሩ፤

በሄኖኀ በኩል፣ የሄኖኀውያን ጐሣ፤

በፈሉስ በኩል፣ የፈሉሳውያን ጐሣ፤

6በአስሮን በኩል፣ የአስሮናውያን ጐሣ፤

በከርሚ በኩል፣ የከርማውያን ጐሣ፤

7እነዚህ የሮቤል ጐሣዎች ሲሆኑ፤ ከእነዚህም የተቈጠሩት አርባ ሦስት ሺሕ ሰባት መቶ ሠላሳ ነበሩ።

8የፈሉስ ልጅ ኤልያብ ሲሆን፣ 9የኤልያብ ልጆች ደግሞ፣ ነሙኤል ዳታንና አቤሮን ነበሩ። እነዚሁ ዳታንና አቤሮን በሙሴና በአሮን ላይ ያመፁ የማኅበሩ ሹማምት ሲሆኑ፣ ቆሬና ተከታዮቹ በእግዚአብሔር (ያህዌ) ላይ ባመፁ ጊዜ እነርሱም በነገሩ ነበሩበት። 10ሁለት መቶ አምሳዎቹን ሰዎች እሳት በበላቻቸው ጊዜ የቆሬ ተከታዮች ሲሞቱ እነዚህን ደግሞ ምድር ተከፍታ ከእርሱ ጋር ዋጠቻቸው፤ መቀጣጫም ሆኑ፤ 11የቆሬ የዘር ሐረግ ግን አልጠፋም።

12የስምዖን ዘሮች በየጐሣቸው እነዚህ ነበሩ፤

በነሙኤል በኩል፣ የነሙኤላውያን ጐሣ፤

በያሚን በኩል፣ የያሚናውያን ጐሣ፤

በያኪን በኩል፣ የያኪናውያን ጐሣ፤

13በዛራ በኩል፣ የዛራውያን ጐሣ፤

በሳኡል በኩል፣ የሳኡላውያን ጐሣ፤

14እነዚህ የስምዖን ጐሣዎች ሲሆኑ፣ ከእነዚህ የተቈጠሩትም ሃያ ሁለት ሺሕ ሁለት መቶ ነበሩ።

15የጋድ ዘሮች በየጐሣዎቻቸው እነዚህ ነበሩ፤

በጽፎን በኩል፣ የጽፎናውያን ጐሣ፤

በሐጊ በኩል፣ የሐጋውያን ጐሣ፤

በሹኒ በኩል፣ የሹናውያን ጐሣ፤

16በኤስና በኩል፣ የኤስናናውያን ጐሣ፤

በዔሪ በኩል፣ የዔራውያን ጐሣ፤

17በአሮዲ26፥17 በኦሪተ ሳምራውያኑ ቅጅ አሮዲ፣ በማሶሬቲክ ቅጅ አሮድ ተብሏል። በኩል፣ የአሮዳውያን ጐሣ፤

በአርኤሊ በኩል፣ የአርኤላውያን ጐሣ፤

18እነዚህ የጋድ ጐሣዎች ሲሆኑ፣ ከእነዚህ የተቈጠሩት አርባ ሺሕ አምስት መቶ ነበሩ።

19ዔርና አውናን የይሁዳ ልጆች ነበሩ፤ ነገር ግን በከነዓን ምድር ሞተዋል።

20የይሁዳ ዘሮች በየጐሣቸው እነዚህ ነበሩ፤

በሴሎም በኩል፣ የሴሎማውያን ጐሣ፤

በፋሬስ በኩል፣ የፋሬሳውያን ጐሣ፤

በዛራ በኩል፣ የዛራውያን ጐሣ፤

21የፋሬስ ዘሮች በየጐሣቸው እነዚህ ነበሩ፤

በኤስሮም በኩል፣ የኤስሮማውያን ጐሣ፤

በሐሙል በኩል፣ የሐሙላውያን ጐሣ፤

22እነዚህ የይሁዳ ጐሣዎች ሲሆኑ፣ ከእነዚህ የተቈጠሩት ሰባ ስድስት ሺሕ አምስት መቶ ነበሩ።

23የይሳኮር ዘሮች በየጐሣቸው እነዚህ ነበሩ፤

በቶላ በኩል፣ የቶላውያን ጐሣ፣

በፋዋ በኩል፣ የፋዋውያን ጐሣ፣

24በያሱብ በኩል፣ የያሱባውያን ጐሣ፣

በሺምሮን በኩል፣ የሺምሮናውያን ጐሣ፤

25እነዚህ የይሳኮር ጐሣዎች ሲሆኑ፣ ከእነዚህ የተቈጠሩት ስድሳ አራት ሺሕ ሦስት መቶ ነበሩ።

26የዛብሎን ዘሮች በየጐሣቸው እነዚህ ነበሩ፤

በሴሬድ በኩል፣ የሴሬዳውያን ጐሣ፤

በኤሎን በኩል፣ የኤሎናውያን ጐሣ፣

በያሕልኤል በኩል፣ የያሕልኤላውያን ጐሣ፤

27እነዚህ የዛብሎን ጐሣዎች ሲሆኑ፣ ከእነዚህ የተቈጠሩት ስድሳ ሺሕ አምስት መቶ ነበሩ።

28የዮሴፍ ዘሮች በምናሴና በኤፍሬም በኩል ያሉት በየጐሣቸው እነዚህ ነበሩ፤

29የምናሴ ዘሮች፤

በማኪር በኩል፣ የማኪራውያን ጐሣ፤ ማኪርም የገለዓድ አባት ነው፤

በገለዓድ በኩል፣ የገለዓዳውያን ጐሣ፤

30የገለዓድ ዘሮች እነዚህ ነበሩ፤

በኢዔዝር በኩል፣ የኢዓዝራውያን ጐሣ፣

በኬሌግ በኩል፣ የኬሌጋውያን ጐሣ፣

31በአሥሪኤል በኩል፣ የአሥሪኤላውያን ጐሣ፣

በሴኬም በኩል፣ የሴኬማውያን ጐሣ፣

32በሸሚዳ በኩል፣ የሸሚዳውያን ጐሣ፣

በኦፌር በኩል፣ የኦፌራውያን ጐሣ፣

33የኦፌር ልጅ ሰለጰዓድ ወንዶች ልጆች አልነበሩትም፤ ልጆቹ ሴቶች ብቻ ነበሩ፤ እነርሱም ማህለህ፣ ኑዓ፣ ዔግላ፣ ሚልካና ቲርጻ ይባላሉ።

34እነዚህ የምናሴ ጐሣዎች ሲሆኑ፣ ከእነዚህ የተቈጠሩት አምሳ ሁለት ሺሕ ሰባት መቶ ነበሩ።

35የኤፍሬም ዘሮች በየጐሣቸው እነዚህ ነበሩ፤

በሱቱላ በኩል፣ የሱቱላውያን ጐሣ፣

በቤኬር በኩል፣ የቤኬራውያን ጐሣ፣

በታሐን በኩል፣ የታሐናውያን ጐሣ፤

36የሱቱላ ዘሮች እነዚህ ነበሩ፤

በዔዴን በኩል፣ የዔዴናውያን ጐሣ፤

37እነዚህ የኤፍሬም ጐሣዎች ሲሆኑ፣ ከእነዚህ የተቈጠሩት ሠላሳ ሁለት ሺሕ አምስት መቶ ነበሩ።

እነዚህም በየጐሣቸው የተቈጠሩ የዮሴፍ ዘሮች ነበሩ።

38የብንያም ዘሮች በየጐሣቸው እነዚህ ነበሩ፤

በቤላ በኩል፣ የቤላውያን ጐሣ፣

በአስቤል በኩል፣ የአስቤላውያን ጐሣ፣

በአኪራን በኩል፣ የአኪራናውያን ጐሣ፣

39በሶፋን26፥39 ጥቂት የማሶሬቲክ፣ የኦሪተ ሳምራውያን፣ የቩልጌትና የሱርስት ቅጆች ሶፋን የሚሉ ሲሆን፣ አያሌ የማሶሬቲክ ቅጆች ግን ሼፉፋም ይላሉ። በኩል፣ የሶፋናውያን ጐሣ፣

በሑፋም በኩል፣ የሑፋማውያን ጐሣ፤

40የቤላ ዘሮች በአርድና በናዕማን በኩል፤

በአርድ በኩል፣ የአርዳውያን ጐሣ፣

በናዕማን በኩል፣ የናዕማናውያን ጐሣ፤

41እነዚህ የብንያም ጐሣዎች ሲሆኑ፣ ከእነዚህም የተቈጠሩት አርባ አምስት ሺሕ ስድስት መቶ ነበሩ።

42የዳን ዘሮች በየጐሣቸው እነዚህ ነበሩ፤

በስምዔ በኩል፣ የሰምዔያውያን ጐሣዎች።

እነዚህ እንግዲህ የዳን ጐሣዎች ሲሆኑ፣ 43ሁሉም የሰምዔያውያን ጐሣዎች ነበሩ፤ ከእነዚህ የተቈጠሩት ደግሞ ስድሳ አራት ሺሕ አራት መቶ ነበሩ።

44የአሴር ዘሮች በየጐሣቸው እነዚህ ነበሩ፤

በዩምና በኩል፣ የዩምናውያን ጐሣ፣

በየሱዋ በኩል፣ የየሱዋውያን ጐሣ፣

በበሪዓ በኩል፣ የበሪዓውያን ጐሣ፤

45እንዲሁም በበሪዓ ዘሮች በኩል፣

በሔቤር በኩል፣ የሔቤራውያን ጐሣ፣

በመልኪኤል በኩል፣ የመልኪኤላውያን ጐሣ።

46አሴር ሤራሕ የምትባል ልጅ ነበረችው።

47እነዚህ የአሴር ጐሣዎች ሲሆኑ፣ ከእነዚህ የተቈጠሩት አምሳ ሦስት ሺሕ አራት መቶ ነበሩ።

48የንፍታሌም ዘሮች በየጐሣቸው እነዚህ ነበሩ፤

በያሕጽኤል በኩል፣ የያሕጽኤላውያን ጐሣ፣

በጉኒ በኩል፣ የጉናውያን ጐሣ፣

49በዬጽር የዬጽራውያን ጐሣ፤ በሺሌም በኩል፣ የሺሌማውያን ጐሣ፤

50እነዚህ የንፍታሌም ጐሣዎች ሲሆኑ፣ ከእነዚህ የተቈጠሩት አርባ አምስት ሺሕ አራት መቶ ነበሩ።

51በአጠቃላይ የእስራኤል ወንዶች ቍጥር ስድስት መቶ አንድ ሺሕ ሰባት መቶ ሠላሳ ነበር።

52እግዚአብሔር (ያህዌ) ሙሴን እንዲህ አለው፤ 53“ምድሪቱ በስማቸው ቍጥር ልክ ተደልድላ በርስትነት ለእነርሱ ትሰጥ። 54በርከት ያለ ቍጥር ላለው ጐሣ ሰፋ ያለውን ርስት፣ አነስ ያለ ቍጥር ላለው ጐሣ ደግሞ አነስ ያለውን ስጥ፤ ርስቱንም እያንዳንዱ በዝርዝሩ ላይ በተመለከተው ቍጥር መሠረት ይረከባል። 55የመሬት ድልድሉም በዕጣ ይሁን፤ እያንዳንዱ የሚወርሰውም በየነገድ አባቶቹ ስም ይሆናል። 56እያንዳንዱም ርስት በትልልቆቹና በትንንሾቹ ነገዶች መካከል በዕጣ ይደለደላል።”

57በየጐሣቸው የተቈጠሩት ሌዋውያን እነዚህ ነበሩ፤

በጌድሶን በኩል፣ የጌድሶናውያን ጐሣ፣

በቀዓት በኩል፣ የቀዓታውያን ጐሣ፣

በሜራሪ በኩል፣ የሜራራውያን ጐሣ፤

58እነዚህም ደግሞ የሌዊ ጐሣዎች ነበሩ፤

የሊብናውያን ጐሣ፣

የኬብሮናውያን ጐሣ፣

የሞሖላውያን ጐሣ፣

የሙሳውያን ጐሣ፣

የቆሬያውያን ጐሣ።

ቀዓት የእንበረም ቅድመ አያት ነበር፤ 59ሚስቱ ዮካብድ ትባል ነበር፤ እርሷም በግብፅ አገር ከሌዋውያን የተወለደች የሌዊ ዘር ነበረች። ከእንበረምም አሮንን፣ ሙሴንና እኅታቸውን ማርያምን ወለደች። 60አሮንም የናዳብና የአብዮድ፣ የአልዓዛርና የኢታምር አባት ነበር። 61ነገር ግን ናዳብና አብዩድ ባልተፈቀደ እሳት ለእግዚአብሔር (ያህዌ) መሥዋዕት ስላቀረቡ ሞቱ።

62አንድ ወርና ከዚያ በላይ የሆናቸው ሌዋውያን ወንዶች ሁሉ ተቈጥረው ሃያ ሦስት ሺሕ ሆኑ፤ እነርሱም ከሌሎቹ እስራኤላውያን ጋር ርስት ተካፋዮች ስላልነበሩ አብረዋቸው አልተቈጠሩም።

63ሙሴና ካህኑ አልዓዛር ከኢያሪኮ ማዶ በዮርዳኖስ ወንዝ አጠገብ ካለው ከሞዓብ ሜዳ ላይ የእስራኤልን ሕዝብ በቈጠሩበት ወቅት የተቈጠሩት እነዚህ ናቸው። 64ሙሴና ካህኑ አሮን በሲና ምድረ በዳ እስራኤላውያንን በቈጠሩ ጊዜ ከእነዚህ ከተቈጠሩት መካከል አንዳቸውም አልነበሩም፤ 65ምክንያቱም በርግጥ በምድረ በዳ እንደሚሞቱ ያን ጊዜ እግዚአብሔር (ያህዌ) ነግሯቸው ነበር፤ ከዮፎኒ ልጅ ከካሌብና ከነዌ ልጅ ከኢያሱ በስተቀር ከእነርሱ የተረፈ ማንም ሰው አልነበረም።